id
stringlengths
8
13
url
stringlengths
36
41
title
stringlengths
14
73
summary
stringlengths
6
277
text
stringlengths
318
10.6k
news-48885486
https://www.bbc.com/amharic/news-48885486
የኢትዮ ቴሌኮም 49 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ይቀርባል ተባለ
ኢትዮ ቴሌኮም ከጠቅላላ የድርጅቱ አክሲዮን ድርሻ እስከ 49 በመቶውን ለሽያጭ በማቅረብ አብላጫ ድርሻውንና የቦርዱን አስተዳደር ይዞ እንዲቀጥል ተወሰነ።
ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ. ም የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ፤ ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዘዋወሩን ሂደት ለማስፈጸም ነጻና ገለልተኛ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እንዲቋቋም የሚፈቅድ አዋጅ መውጣቱም ተገልጿል። ባለሥልጣኑ ሁለት ተጨማሪ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ወደ ገበያ እንዲገቡ እንደሚያደርግና ሂደቱ በ2012 ዓ. ም ሦስተኛ ሩብ ዓመት እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል። • ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? አሁን መንግሥት የቅድመ ፕራይቬታይዜሽን (በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ ተቋሞችን ወደ ግል የማዘዋወር) ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት መስመር ዝርጋታና የአገልግሎት አቅርቦት በተባሉ ሁለት ዘርፎች ይደራጃልም ተብሏል። የመስመር ዝርጋታው ዘርፍ ዓለም አቀፍ መገናኛዎችን፣ አገር አቀፍ ፋይበር ኦፕቲክ፣ ለኔትወርክ ጠቃሚ የሆኑ እንደ የሞባይል ኔትወርክ ማማ (ሴሉላር ታወርስ) ያሉትን ሥራዎች የመገንባት ድርሻ ሲኖረው፤ የአገልግሎት ዘርፉ የሞባይል፣ የኢንተርኔት እና የመደበኛ ስልክ የችርቻሮ ሽያጭ ኃላፊነትን ተረክቦ እንደሚሠራ ተመልክቷል። • አየር መንገድንና ቴሌን ለሽያጭ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው? ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ፤ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ከመሳብ ባሻገር፤ የአገልግሎት ክፍያ እንደሚቀንስ እንዲሁም የአገልግሎት ጥራትና ፍጥነት እንደሚጨምርም ተገልጿል። የስኳር ኮርፖሬሽንን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወደ ግል የማዘዋወር ሂደትን በተመለከተ የገንዘብ ሚንስቴር የድርጅቶቹን ንብረቶች ዋጋ፣ የፋብሪካውን አቅም እንዲሆም እያንዳንዱ ፋብሪካ በተቋቋመበት አካባቢ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን አስመልክቶ ጥናት እየተካሄደ እንደሚገኝ በመግለጫው ተመልክቷል። • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? የስኳር ፋብሪካዎች አዋጅ እየተረቀቀ ሲሆን፤ ስኳር የማምረት፣ የመሸጥ፣ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡና ወደ ውጪ የሚላኩ የስኳር ምርቶችን ለመቆጣጠርም ይረዳል ተብሏል። ከስኳር ፋብሪካዎች አምስቱ ወይም ስድስቱን ወደ ግል የማዘዋወር ሥራ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚወስም ተገልጿል።
news-55156385
https://www.bbc.com/amharic/news-55156385
ቻይና ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተከለች
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተከለች። ይህ የሆነው ተቀናቃኟ አሜሪካ ሰንደቅ አላማዋን ጨረቃ ላይ ካስቀመጠች ከ50 ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው።
የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ ከቻይና ብሔራዊ የህዋ አስተዳደር ተቋም ይፋ የተደረጉት ምስሎች ባለአምስት ኮከቡ ቀዩ የቻይና ሰንደቅ ዓላማ ነፋስ በሌለበት የጨረቃ ገጽ ላይ ተተክሎ ያሳያሉ። ምስሎቹ የተነሱት ቻንጌ-5 የተባለው የህዋ አሳሽ መንኮራኩር ሐሙስ ዕለት ከጨረቃ ላይ የአለት ናሙናዎችን ሰብስቦ ከመመለሱ በፊት እንደሆነ ተነግሯል። በቻይና መንግሥት የሚዘጋጀው 'ግሎባል ታይምስ' ጋዜጣ እንዳለው፤ የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ መተከሉ የአሜሪካው አፖሎ 11 ጉዞ ወቅት የተፈጠረው አይነት "ደስታንና መነቃቃትን" ፈጥሯል። በጨረቃ ገጽ ላይ የተተከለው የቻይና ሰንደቅ ዓላማ 2 ሜትር ስፋትና 90 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ክብደቱም አንድ ኪሎ ያህል እንደሆነ ተነግሯል። "በምድር ላይ የምንጠቀመው አይነት ማንኛውም የሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ በጨረቃ ላይ ያለውን ሁኔታ መቋቋም አይችሉም" ያሉት የጨረቃው ጉዞ ፕሮጀክት መሪ ሊ ዮንፌንግ ለግሎባል ታይምስ ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሰንደቅ ዓላማው የተለያዩ የአየር ሁኔታዎችን እንዲቋቋም ተደርጎ ነው የተሰራው። የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ቀደም ሲል ወደ ጨረቃ በተጓዙት ቻንጌ-3 እና ቻንጌ-4 የተባሉት የአሰሳ መንኮራኩሮች ላይ በተሳሉት ባንዲራዎች አማካይነት ሲሆን፤ ከጨርቅ ተሰርቶ የጨረቃ ገጽ በሰንደቅ ላይ የተተከለው ግን የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የቻይናን ሰንደቅ ዓላማ በመትከል የመጀመሪያው የሆነው ቻንጌ-5 የተባለው የህዋ ተልዕኮ ባለፉት ሰባት ዓመታት ቻይናን በተሳካ ሁኔታ ጨረቃ ላይ እንድታርፍ ካደረጉት ሦስተኛው ነው። ከዚህ በፊት በተደረጉት የቻይና ሁለት የጨረቃ ጉዞዎች ወቅት መንኮራኩሮቹ ላይ በቀለም ከተሳለው የቻይና ባንዲራ ውጪ በጨረቃ ገጽ ላይ የአገሪቱ ሰንደቅ አልተተከለም ነበር። አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረቃ ገጽ ላይ ሰንደቅ ዓላማዋን የተከለችው ከ50 ዓመታት በፊት እአአ በ1969 አፖሎ 11 የተባለችው መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ባደረገችው ጉዞ ነበር። ከዚያ በኋላም እስከ 1972 (እአአ) በተደረጉ ጉዞዎች አምስት ጊዜ ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተክላለች። ከስምንት ዓመት በፊት በናሳ ሳተላይቶች የተነሱ ፎቶዎች እንዳሳዩት በጨረቃ ላይ ተተክለው ለዓመታት የቆዩት አምስቱም የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማዎች በቦታቸው ላይ የሚታዩ ቢሆንም በፀሐይ ብርሃን ምክንያት ደብዝዘው ወደ ነጭነት መቀየራቸውን ባለሙያዎች ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። የመጀመሪያውን የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ጨረቃ ላይ የተከለው ጠፈረተኛ በዝ አልድሪን ሲሆን፤ ከመንኮራኩሯ ግርጌ ተክሎት ነበረ። ምናልባትም መንኮራኩሯ ወደ ምድር ለመመለስ ስትነሳ በሚፈጠረው ከባድ ግፊት ከተተከለበት ቦታ ተነቅሎ ሳይወድቅ አይቀርም ብሎ ነበር። ጠፈርተኛው በዝ አልድሪን በጨረቃ ላይ ከተከለው የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ጎን (1969 እአአ)
news-51798143
https://www.bbc.com/amharic/news-51798143
ኮሮኖቫይረስ፡ እውን ነጭ ሽንኩርት የኮሮናቫይረስ ጠር ነው?
የኮሮናቫይረስ ከአገር አገር እየተስፋፋ ነው። በየቀኑ አዳዲስ አገራት 'ኧረ እኛም አገር ገባ እኮ' እያሉ ነው። እስካሁን ኮሮናን ውልቅ አድርጎ የሚያስወጣ ሐኪሞች ያጨበጨቡለት መድኃኒት አልተገኘም።
'እነ ነጭ ሽንኩርትና ባሕር ዛፍ ምን ሠርተው ይበላሉና' የሚል ምክር ሰምተው ይሆናል። ዓለም በአንድ ስጋት ስትናጥ ተከትሎ የሚመጣ አንድ ፅንሰ-ሐሳብ አለ፤ በእንግሊዝ አፍ 'ኮንስፓይረሲ ቲየሪ' ይሰኛል፤ የሴራ ፅንሰ-ሐሳብ ብለን እንተርጉመው። ወደ ኢንተርኔት ዓለም ብቅ ቢሉ ወሬው ሁሉ ስለኮሮናቫይረስ ነው፤ የወቅቱ የዓለም ስጋት ነውና። ኮሮናን ይከላከላሉ ተብሎ የሚወራላቸው ደግሞ ብዙዎች ናቸው። ነጭ ሽንኩርት ደግሞ የአጥቂ መስመር ላይ ተሰልፋለች። ነጭ ካባ ከደረበ ዶክተር. . . ነጭ ሽንኩርት ዝናዋ በዓለም የናኘ ነው። የፌስቡክ ገፅ ቢኖራት ኖሮ 6 ቢሊዮን ሕዝብ የሚከተላት ነጭ የደረበች ሽንኩርት. . . ። ነጭ ሽንኩርት ፌስቡክ ለመቆጣጠር ገፅ አላሻትም። የኮሮናቫይረስን መፈወሻ ተበለው ፌስቡክ ላይ ዝናቸው ከናኘ ነገሮች መካከል ነጭ ሽንኩርት አንደኛ ነች። ግን ኮሮናን መከላከልም ሆነ ማዳን ትችል ይሆን? ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ግን እንዲህ ይላል - ነጭ ሽንኩርት ብሉ በውስጡ መልካም ነገር አዝሏልና፤ ነገር ግን ከአዲሱ ቫይረስ ሊከላከል እንደሚችል በሳይንስ አልተረጋገጠም። እርግጥ የዶ/ር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት እንዳለው ነጭ ሽንኩርት በልኩ መብላት ይመከራል። ከኮሮናቫይረስ ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር የለም። ደቡብ ቻይና ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ይታደገኛል ብለው 1.5 ኪሎ ግራም ነጭ ሽንኩርት 'ዱቄት' ያደረጉ አንዲት ሴት ጉሮሯቸው ተቃጥሎ በሕክምና ነው የዳኑት። የዓለም ጤና ድርጅት፤ ፍራፍሬና ጥራጥሬ እንዲሁም አትክልት በልኩ ተመገቡ፤ ውሃም ጠጡ ይላል። ነገር ግን ይላል ድርጅቱ. . . ነገር ግን ኮሮናን ይታደጋል ተበሎ ፈቃድ የወጣለት ምንም ዓይነት ምግብ እስካሁን አልተገኘም። ተዓምረኛ ንጥረ-ነገሮች ዩቲዩበኛው ጆርዳን ሳዘር በተለያዩ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ብዙ ሺህ ተከታዮች አሉት። ይህ ግለሰብ አንድ 'ኤምኤም የተሰኘ ተዓምራዊ ንጥረ-ነገር የኮሮናቫይረስን ድራሽ ማጥፋት ይችላል' እያለ ይሰብካል። ንጥረ ነገሩ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ የተሰኘ አንጭ ኬሚካል አዝሏል። ጆርዳንና መሰሎቹ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ ያለበት ኤምኤም የካንሰር ሴልን ያጠፋል እያሉ ይሰብኩ ነበር። አሁን ደግሞ ለኮሮናቫይረስ ፍቱን መድኃኒት ነው ብለው ብቅ ብለዋል። ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ይህንን ኬሚካል መጠጣት ለጤና እጅግ አስጊ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር። መሥሪያ ቤቱ ይህንን ኬሚካል የምትጠጡ ወዮላችሁ፤ ኬሚካሉ በሽታ እንደሚከላከል የሚጠቁም ጥናት የለም ሲል ነው ያስጠነቀቀው። አልፎም ኬሚካሉ ሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽን አሟጦ በመጨረስ ለከፍተኛ የውሃ ጥም ሊያጋልጥ ይችላል። 'ሳኒታይዘር' ጨርሰናል የሚሉ ማስታወቂያዎች ማየት እየተለመደ መጥቷል ጓዳ ሠራሽ 'ሳኒታይዘር' «ባለሱቅ፤ ሳኒታይዘር አለ?» «ውይ! አንድ ቀርታ ነበር። እሷን ደግሞ ለእኔ . . .» ከመዳፎቻችን ላይ ባክቴሪያ ነሽ ቫይረስ እንዲሁም ቆሻሻ ያስወግዳሉ የሚባልላቸው 'ሳኒታይዘሮች' [ተህዋሲያን ማጽጃ ፈሳሽ] ከገበያ እየጠፉ ነው። ጣልያን ውስጥ ነው አሉ። የሳኒታይዘር እጦት የወሬ ሟሟሻ ሆነ። ኮሮናቫይረስ ሰቅዞ የያዛት የጣልያን ነዋሪዎች ታድያ ወደ ኩሽና ገቡ። የተገኘውን ነገር መቀላቀል ጀመሩ። በአገሬው ዘንድ ታዋቂ የሆነ አንድ ኬሚካል ግን ቆዳ እንዲያፀዳ ሳይሆን እምነ-በረድ እንዲያፀዳ የተሰናዳ ነው። በተለይ ደግሞ ውስጣቸው በመቶኛ ከፍ ያለ የአልኮል መጠንን ያዘሉ ፈሳሾች ለመቀየጫነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ደግሞ የምንጠቀማቸው ሳኒታይዘሮች ቢያንስ ከ60-70 በመቶ የአልኮልነት መጠን ቢኖራቸው ሲል ይመክራል። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ኩሽና ውስጥ ቫይረስና ባክቴሪያ የሚገድል 'ሳኒታይዘር' ማምረት ከባድ ነው ይላሉ። ቮድካ እንኳ 40 በመቶ ብቻ የአልኮል ይዘት ነው ያለው። እና ሌሎች. . . ከላይ ከተጠሱት አልፎ የቀለጠ ሲልቨር መጠጣት፣ ውሃ በ15 ደቂቃ ልዩነት መጠጣ [የሞቀ ውሃማ ፍቱን ያሉም አልጠፉም]፣ ሙቀት ማግኘት እና አይስ ክሬም አለመላስ የኮሮናቫይረስን ለመፈወስ ፍቱን ናቸው ተብለው በማኅበራዊ ድር-አምባዎች ማስታወቂያ የተሠራላቸው ናቸው። ሳይንሱ ግን እስካሁን የተረጋገጠ ፈውስ አልተገኘም ይላል። ነገር ግን በሽታውን ለመከላከል ዋናውና ቀላሉ መፍትሔ እጅን በሳሙን በደንብ ፈትጎ መታጠብ፣ የእርስ በርስ ንክኪን መቀነስ፣ ፊትን በእጅ አለመነካካት፣ በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ አለማድረግ. . . ነው። አደራዎትን 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ስልቅጥ አድርገው በጠላ ካወራረዱ በኋላ እንደ ዉሃኗ ነዋሪ ርዕሰ-አንቀፅ እንዳይሆኑ። ሐኪም ያላዘዘውን መጠቀም ጠንቅ ነውና!
news-45657239
https://www.bbc.com/amharic/news-45657239
ጉባኤው ብአዴንን የት ያደርሰዋል?
በገዢው ግንባር ኢህአዴግ ጥምረት ውስጥ በተካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና አላቸው ተብለው ከሚጠቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤውን ያካሂዳል።
የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ ሆኖ በቆየባቸው ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ በውስጡ አንዳንድ ለውጦችን እያደረገ በገዢው ግንባር አባልነት ዘልቋል። • የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር • አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ የብአዴን መስራች አባላት ዋነኛ መሠረታቸው ከሆነው ኢህአፓ በመለየት መንቀሳቀስ በጀመሩበት ጊዜ መጠሪያቸውን ኢህዴን (የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የሚል አድርገው ነበር። ነገር ግን በገዢው ግንባር ውስጥ ያሉት ሦስት ድርጅቶች የተወሰነ ሕዝብና አካባቢን የሚወክል መጠሪያ በመያዛቸው ኢህዴን በተለይ የአማራ ህዝብን ወካይ የኢህአዴግ አባል መሆኑን ለማጉላት ስያሜውን ወደ ብአዴን ቀይረ። ከዚህ ውጪ ግን እንደቀሪዎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በግንባሩ ስር በመሆን ተመሳሳይ ለውጦችንና ውሳኔዎችን በክልሉ ውስጥ ሲወስንና ሲያስፈፅም ቆይቷል። በዚህም በርካቶች ብአዴን የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ አቋም የሌለው እንዲሁም መጠሪያው ያደረገውን ህዝብ ጥቅምና መብት ማስከበር የማይችል ድርጅት ነው በማለት ሲተቹት ቆይቷል። • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ በተለይ ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖሩ አማሮች የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሟቸው ብአዴን አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን የሚጠበቅበትን አልተወጣም የሚሉ በርካቶች ናቸው። ለረዥም ጊዜ የተለያዩ አካላት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጡ ባለመሆናቸው በአግባቡ ሊወክሉት አይችሉም በማለት ከንቅናቄው እንዲወጡ በተለያየ መንገድ ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል። ግለሰቦቹ የወከሉትን ህዝብ በአግባቡ አላገለገሉም ከመባላቸው ባሻገር የድርጅቱንና የህዝብን ንብረት አባክነዋል፤ እንዲሁም እንደቤተሰብ ንብረት ተገልግለውባቸዋል የሚሉ ወቀሳዎችም ሲቀርቡባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ ስፍራዎች ወቀሳና ተቃውሞዎች ሲቀርቡበት የቆየው ብአዴን ንቁ ሆኖ በኢህአዴግ ውስጥ በመንቀሳቀስ የህዝቡንና የክልሉን ጥቅም የሚያስከብሩ ሥራዎችን እንዲሰራ ከውስጥም ከውጪም ግፊቶች ሲደረጉበት ቆይቷል። በተለይ ከ2008 ወዲህ በተለያዩ የሃገሪቱና የክልሉ አካባቢዎች እየተጠናከረ የመጣው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ንቅናቄውን ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግን ጭምር ስጋት ውስጥ በማስገባቱ በግንባሩ ውስጥ ለውጦችን ለማድረግ ሰፊና ተከታታይ ስብሰባዎች ተካሂደው ነበር። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? በግንባሩና በመንግሥት አመራር ላይ ለውጦችን ይዞ የመጣው ተከታታይ ስብሰባና ግምገማ በኢህአዴግና አባል ድርጅቶቹ ውስጥም ከፍተኛ የሚባል፣ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥና መነቃቃትን በመፍጠሩ በርካቶች ብአዴንም ይህንን ለውጥ በማጠናከር በኩል አስተዋጽኦ እንደነበረው ይናገራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞም የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በነሐሴ ወር አጋማሽ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን በጥረት ኮርፖሬት ላይ በፈጠሩት ችግር ምክንያት እስከ ድርጅቱ ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ የታገዱት አባላት ከንቅናቄው አመራሮች ጋር በመገናኛ ብዙሃን እሰጥ አገባ ገጥመው ነበር። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" የአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤም በአቶ በረከትና በአቶ ታደሰ ላይ የመጨረሻ ውሳኔውን ከማሳለፍ ባሻገር ሌሎች መስራችና ነባር አባላቱን እንደሚያሰናብት እየተነገረ ነው። ግልጽ ያልሆነው ነገር እነዚህ የሚሰናበቱት አመራሮች ኦዴፓ (ኦህዴድ) እንዳደረገው በክብር ይሰናበቱ ይሆን የሚለው ነው። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ሲተቹበት የቆየው አዳዲስና ወጣት አመራሮችን አለማብቃታቸው ዋነኛው ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ያልተጠበቁ ለውጦችን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ እንዳመጡ የሚነገርላቸው ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ወጣቶችን ወደ አመራር የማምጣቱ ጥያቄ በየአባል ድርጅቶቹ ውስጥ ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል። በዚህም ኦዴፓ እንዳደረገው ብአዴንም በርካታ ቀደምት የድርጅቱን አመራሮች በማሰናበት አዳዲስ ወጣቶችን ወደፊት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ቀልብ እየሳበ ያለውን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተግዳሮት ለመቋቋም ሊጠቀምበት ይችላል። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ብአዴን "የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲያዊ አንድነት " በሚል መሪ ሀሳብ የሚያካሂደው 12ኛ ደርጅታዊ ጉባኤ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም በተለያዩ መስኮች የለውጥ እርምጃዎችን በመውሰድ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ተመራጭ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መገኘት የሚያስችሉትን ውሳኔዎች እንደሚሰጥበት ንቅናቄው በተለያዩ አጋጣሚዎች አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪም የብአዴን አቻ ኦህዴድ እንዳደረገውና የንቅናቄው አባላት ጥያቄ እንደሆነ የተነገረው የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ማሻሻያ እንደሚያደረግ ይጠበቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ባለፉት ዓመታት የአማራ ክልልን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለህዝቦች መፈናቀልና መሰደድ፣ ለህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ለመፍታት የሚረዱ መንገዶች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም ተጠቅሷል። በተጨማሪም በድርጅቱ ስር ያሉ የልማት ድርጅቶች፣ ማለትም ጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ የተባሉት ድርጅቶች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግሥት እንዲሆን ተወስኗል።
news-46402439
https://www.bbc.com/amharic/news-46402439
በአፍጋኒስታን የአየር ጥቃት 23 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ
በአፍጋኒስታን ደቡባዊ ግዛት ሄልማንድ አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ድብዳባ ቢያንስ 23 ንፁሃን ዜጎች ተገደሉ። የተባበሩት መንግስታት እንዳስታወቀው አብዛኞቹ ተጎጂዎች ሴቶችና ህፃናት ናቸው።
10 የሚሆኑ ህፃናት ሲገደሉ 3 ቱ ለጉዳት ተዳርገዋል የአየር ድብደባው የደረሰው የአፍጋን ወታደሮችና የአሜሪካ ኃይሎች ባካሄዱት ውጊያ ወቅት ነው። • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው • በዌስት ባንክ ዘጠኝ ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ጭምብል ተገኘ ቢያንስ 10 ህፃናት እና 8 ሴቶች በጥቃቱ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ገልፀዋል። የአሜሪካ ኃይሎች ግን የተጎጂዎችን ቁጥር በማጣራት ላይ እንደሚገኙ መርማሪዎች አስታውቀዋል። አሜሪካ ባለፈው ዓመት በአፍጋን ላይ ጥቃት ለማድረስ አዲስ ስልት ካወጀች ወዲህ በንፁሃን የሚደርሰው ጉዳት እየተባባሰ መጥቷል። ስልቱ ፈንጂዎችንና በርካታ ቦምቦችን መጠቀምን የሚፈቅድ ነው። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የታሊባንና እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖችን ለማጥቃት የወታደሮችን ቁጥር ለማሳዳግ ባለፈው ዓመት ነበር ውሳኔውን ያሳለፉት። በአፍጋኒስታን በአሜሪካ የሚመራው የኔቶ ጦር እንዳስታወቀው በጋርምሰር አካባቢ የሄሊኮፍተር ድብደባው የተፈፀመው በአሜሪካ የሚደገፈው የአፍጋን ልዩ ኃይልና ታሊባን ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ ወቅት ነው። ኔቶ በበኩሉ ታሊባኖች በርካታ ንፁሃን ዜጎች የሚጠለሉበትን ህንፃ እንደ ምሽግ መጠቀሙ ለበርካታ ንፁሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ሆኗል ብሏል። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው የአካባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአየር ድብደባው ሲፈፀም የታሊባን ተዋጊዎች በህንፃው አቅራቢያ ነበሩ። እማኙ ጨምረው እንደተናገሩት በጥቃቱ ከተጎዱት በዕድሜ ትንሹ የ 6 ዓመት ህፃን እንደሆነ ተናግረዋል። • የሰከረው ጃፓናዊ አብራሪ የ10 ወራት እስር ተበየነበት በአፍጋኒስታን የተባበሩት መንግስታት እንዳስተወቀው ባለፉት 9 ወራት ብቻ በተፈፀመ የአየር ድብዳባ 649 ንፁሃን ዜጎች ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል። ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ የተጎጂዎች ቁጥርም እየጨመረ እንደመጣ ተናግረዋል። ባለፈው ሚያዚያ ወር ብቻ በሰሜን ምስራቋ ኩንዱዙ ግዛት በአንድ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ በአሜሪካ የሚመራው የአፍጋን የአየር ጥቃት 30 ህፃናት መገደላቸውን አስታውሰዋል። የአሜሪካ አየር ኃይል በዚህ ዓመት ብቻ ባለፉት 10 ወራት ቀደም ካሉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር ያለው 6 ሺህ የሚጠጉ የጦር መሳሪያዎችን አስገብቷል። በአፍጋኒስታን የሚደርሰው እልቂት በይበልጥ የመንግስት ተቀናቃኝ በሆኑት የታሊባን ታጣቂዎችና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች የሚፈፀም ነው።
45962289
https://www.bbc.com/amharic/45962289
በፈረንሳይ ልማደኛው ሌባ የአንበሳ ደቦል ሰርቆ ተያዘ
የ30 ዓመቱ ፈረንሳዊ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአንበሳ ደቦል ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ባለሥልጣናቱ የዱር እንሰሳትን እንደለማዳ እንሰሳ ቤት ውስጥ ማቆየት ወንጀል ስለመሆኑ ሲናገሩ ነበር እንደ ፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ፖሊስ መረጃው የደረሰው ግለሰቡ የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያላትን ደቦል በ 10 ሺህ ዮሮ ለመሸጥ ሲያስማማ ነው። ማክሰኞ ዕለት ጎረቤቶቹ ቤት ቁምሳጥን ውስጥ የደበቃት ሲሆን ደቦሏ ግን የሕፃን አልጋ ላይ ተገኝታለች። • በአሜሪካ አንበሳዋ የልጆቿን አባት ገደለች • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። • ለህገወጥ አዳኞች ፈተና የሆኑት ውሾች ደቦሏ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የተነገረ ሲሆን ለዱር አራዊት ባለሥልጣናትም ተላልፋ ተሰጥታለች። እንደ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ወንጀለኛው ልማደኛ ሌባ ነበር ተብሏል። ፖሊስ በሕገወጥ መልኩ በሰዎች መኖሪያ ውስጥ የዱር እንስሳትን ሲያገኝ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። በ2017 አንድ ግለሰብ በምግብ እጥረት የተጎዳ የአንበሳ ደቦል ሰው በማይኖርበት ሕንፃ ውስጥ ደብቆ መገኘቱ ይታወቃል። ወንጀለኛው የተደረሰበትም ከደቦሏ ጋር ምሥለ-ራስ ፎቶ (ሰልፊ) ተነስቶ ፎቶውን ከተሠራጨ በኋላ ነው። የኋላ ኋላ ደቦሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የእንስሳት ማቆያ ተወስዷል። በዚህ ወርም ኔዘርላንዳዊ መንገደኛ አንድ ደቦል በመንገድ ላይ ተጥሎ አግኝቷል።
news-49232316
https://www.bbc.com/amharic/news-49232316
ደቡብ አፍሪካዊያን ታዳጊ አብራሪዎችን ሲረዱ የነበሩት ፓይለቶች በአውሮፕላን አደጋ ሞቱ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት አየር ላይ ከበረሩት ደቡብ አፍሪካዊያን ታዳጊ አብራሪዎች ጀርባ ሆነው ፕሮጀክቱን ሲያስተባብሩ የነበሩ ሁለቱ ደቡብ አፍሪካዊያን ፓይለቶች ቅዳሜ ዕለት ታንዛንያ ውስጥ ባጋጠማቸው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ መዲና ግብፅ መግባታቸው የሚታወስ ነው፤ ከታዳጊዎቹ ጀርባ ደግሞ ሁለት ፓይለቶች ፕሮጀክቱ እንዲሳካ ጥረዋል። •ታዳጊዎቹ በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ ገቡ •ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ ዴስ ዌርነርና ዌርነት ፍሮንማን የተባሉት ፓይለቶች ታዳጊዎቹ የሚያበሯትን አውሮፕላን ከኋላ አጅበው በመቆጣጠር በጉዟቸው ይከተሏቸው ነበር። ደቡብ አፍሪካ በዛሬው ዕለት እንደሚደርሱ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ከታንዛንያ ታቦራ አየር ማረፊያ የተነሱት አብራሪዎቹ ቅዳሜ ዕለት መከስከሳቸውን የታንዛንያ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ፓይለቶቹ ከእይታ ከመጥፋታቸው በፊት የሞተር ችግር እንዳጋጠማቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን የታንዛንያ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል። አውሮፕላኗ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የሆነች ሲሆን ማግኘት የተቻለውም ጥቂት አካሏን መሆኑንም ባለስልጣናቱ አክለው ተናግራዋል። አውሮፕላኗ ባለቤትነቷ ዩ ድሪም ግሎባል የሚባል ድርጅት ሲሆን ይህም ከታዳጊዎቹ ፓይለቶች አንዷ ሜጋን ዌርነርና አሁን ህይወቱ ያለፈው አባቷ ዴስ ዌርነር ነው። "ከኬፕታውን ካይሮ ታዳጊዎቹን አጅባ ስትበር የነበረችው አውሮፕላን መከስከሷን መስማት ያሳዝናል፤ የፕሮጀክቱ ጠንሳሾች ዴስ ዌርነርና ዌርነር ፍሮምናንም ህይወታቸውን አጥተዋል። ሌላ አደጋ የደረሰበት ሰው የለም" ሲል ድሪም ግሎባል በፌስቡክ ገፁ ይህንን መልዕክት አስፍሯል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ሁለቱ ፓይለቶች የታዳጊዎቹን አብራሪዎች አውሮፕላን ፕሮጀክት ከጅምሩ የጠነሰሱት ሲሆን በዳይሬክተርነትም እየመሩት ነበር ተብሏል። ታዳጊዎቹ የሚያበሯት አራት መቀመጫ ያላት አውሮፕላን ከተለያየ ስፍራ በተውጣጡ 20 ተማሪዎች ነው የተገጣጠመችው። ይህንን ፕሮጀክት የጀመረችው የ17 ዓመቷ ሜጋን ስትሆን አንድ ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም ባደረጉት ማጣራት20 ተማሪዎች ተመርጠዋል። ስድስቱም ታዳጊዎች የአብራሪነት ፍቃድ ያገኙ ሲሆን 12 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት በረራም በስድስቱ ትከሻ ላይ ወድቆ ነበር። በሦስት ሳምንት ጉዟቸውም ናሚቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ዛንዚባር፣ ዩጋንዳ የመሳሰሉ አገራትን አካልለዋል። ታዳጊዎቹ አውሮፕላኗን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ሳምንታት የፈጀባቸው ሲሆን፤ የውስጥ አካሏን ከደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በመግዛት እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ የውስጥ አካሏን መገጣጠም ችለዋል። አንዳንድ የአውሮፕላኑ ክፍሎችና ሞተሩ በሰለጠኑ ሰዎች የተገጠሙ ሲሆን አጠቃላይ አውሮፕላኑ የተገጣጠመው በታዳጊዎቹ ነው።
news-45470153
https://www.bbc.com/amharic/news-45470153
"ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ ከመታሰቡ በፊት ሰላምና መረጋጋት ሊሰፍን እንደሚገባ ትናንት የንቅናቄያቸውን አመራሮችና አባላትን በመምራት አዲስ አበባ የገቡት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ምርጫና ውድድር ሳይሆን በሰከነ ሁኔታ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት የሚያጠናክር ሰላምና መረጋጋት በሃገሪቱ እንዲኖር ማድረግ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ምርጫ የሚካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ከማስቀመጥ በፊት ምርጫውን በተገቢው ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችሉና ሕብረተሰቡ የሚተማመንባቸው ተቋማትን በቀዳሚነት በተገቢው ቦታ ላይ መኖራቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። • ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? • ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? "ትኩረታችን መሆን ያለበት የተቀመጠን የምርጫ ጊዜን ማሳካት ላይ ሳይሆን፤ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስፈልጉት ተቋማትን እውን በማድረግ ላይ መሆን አለበት" ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ። አሁን ኢትዮጵያ እያስተዳደረ ያለው መንግሥት ሃገሪቱን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት እያደረገ መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ አሁን በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሀገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ከመሆን ውጭ ሌላ መደራሻ የለውም ሲሉም ብለዋል። አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ሰላማዊና ህጋዊ ፓርቲነት የመጣው በሀገሪቱ የተጀመረውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከርና የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት መሆኑን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል። በበርካታ ወጣቶች ባካሄዱት ትግልና መስዋፅትነት እንዲሁም በኢህአዴግ ውስጥ ባሉ ለውጥ ፈላጊዎች አሁን የተገኘው ለውጥ ያለው መዳረሻ አንድ መሆኑን ያመለከቱት ፐሮፌስር ብርሃኑ እሱም "ኢትዮጵያን እውነተኛ ዲሞክራሲያዊት ሃገር ማድረግ ነው" ብለዋል። ለዚህም ሃገሪቱን ማረጋጋት ቀዳሚው ተግባር መሆን እንዳለበት አመልከተው፤ በማስከተልም ለዴሞክራሲያው ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ተቋማት የሚገነቡበት ጊዜ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። • "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 • በኢሳትና ኦ ኤም ኤን ላይ የተከፈቱ ክሶች ተቋረጡ ጨምረውም ለውጡ እውን እንዲሆን መስዋዕትነት ለከፈሉ መላው የሃገሪቱ ሕዝቦች ፤ እንዲሁም መብታችን ይከበር ብለው ባዶ እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ታግለው ለተሰዉ ወጣቶችም ምስጋና አቅርበዋል። በተመሳሳይም የሕዝቡን ትግል በመረዳት ከፍ ያላ ሃላፊነት በመውሰድ በኢህአዴግ ውስጥ የለውጥ ኃይል ለሆኑት እንዲሁም የእርቅና የአንድነት መንፈስን ላጠናከሩት የመንግሥት ባለስልጣናት አድናቆታቸውን ገልፀዋል። በቁጥር በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይዞ በተናጠል መንቀሳቀስ ለሕዝቡም ሆነ ለሃገሪቱ የሚኖረው ፋይዳ ጠቃሚ ስለማይሆን ፓርቲዎች በአመለካከት ከሚቀራረቧቸው ጋር እየተዋሃዱ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ መፍጠር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሚመራው መንግሥት እንዲሁም ለለውጥ ከሚታገሉ ከየትኛው ወገኖች ጋር በትብብር ለመስራት ንቅናቄያቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። መንቀሳቀሻውን ኤርትራ ውስጥ በማድረግ የትጥቅ ሲኣደርግ የቆየው የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አዲስ አበባ በገቡበት ጊዜ በደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
news-45166880
https://www.bbc.com/amharic/news-45166880
ታይዋናዊ ቱሪስት ኬንያ ውስጥ ፎቶ ሊያነሳው በነበረው ጉማሬ ተነክሶ ሞተ
ታይዋናዊ ቱሪስት ኬንያ ውስጥ ጉማሬ ፎቶ ለማንሳት ሲሞክር ጉማሬው ደረቱ ላይ ነክሶ ገድሎታል። የ 66 ዓመቱ ቻንግ ሚንግ ቻውንግ 'ሌክ ናይቫሻ' በተሰኘው የዱር እንስሳት ማቆያና መዝናኛ ውስጥ ነበር ጉማሬውን ፎቶ ለማንሳት የሞከረው።
ስል ጥርስ ያለው ጉማሬ አደገኛ እንስሳ ነው ጉማሬው ሌላ ታይዋናዊም ነክሷል። የአይን እማኞች እንደተናገሩት ሁለቱ ቱሪስቶች ጉማሬውን ፎቶ ለማንሳት በጣም ተጠግተውት ነበር። ህይወቱ ያለፈው ጎብኚ በጉማሬው ከተነከሰ በኃላ ወደ ህክምና መስጫ ቢወሰድም ብዙ ደም ስለፈሰሰው ሊተርፍ አልቻለም። • ካልጠፋ ዘመድ ከአዞ ጋር ፎቶ የተነሳችው አሜሪካዊት ው ፔንግ ቴ የተባለው ሌላው ታይላንዳዊ የደረሰበት ጉዳት ለክፉ የሚሰጥ አልነበረም። የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ቱሪስቶቹ ቻይናውያን ናቸው ብለው ቢገምቱም የኃላ ኃላ የታይዋይን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ታይዋናውያን መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የሌክ ናይቫሻ ባለ መርከቦች ማህበር አስተዳዳሪ ዴቪድ ኪሎ ለኬንያው ስታር ጋዜጣ እንደተናገሩት የአካባቢው ሐይቅ የውሀ መጠኑ ከፍ ስላለ ጉማሬዎች ከሐይቅ እንዲወጡ ግድ ብሏቸዋል። ከሐይቁ ወጥተው በሆቴል አቅራቢያ ስለሚዘዋወሩም በቀላሉ ከሰዎች ጋር ይገናኛሉ። ከአጥቢ እንስሳት መካከል እጅግ አደገኛው ጉማሬ ነው። በአካባቢው በዚህ ዓመት ብቻ ስድስት ሰዎች በጉማሬ ተገድለዋል። ጉማሬዎች እስከ 2,750 ኪሎ ግራም ድረስ ሊመዝኑ ይችላሉ። አፍሪካ ውስጥ በየዓመቱ 500 ሰዎች በጉማሬ ተበልተው ይሞታሉ። ታይዋናዊው ጎብኚ የሞተባት ኬንያ አምና 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ጎብኝተዋት ከቱሪዝም 1.2 ቢልየን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
news-55541613
https://www.bbc.com/amharic/news-55541613
በኢትዮጵያ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ቀረጥ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ተደረገ
ኢትዮጵያ በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በዚህ ውሳኔ መሰረት የሴቶች ወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) እንዲሁም የህፃናት ንጽህና መጠበቂያ (ዳይፐር) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ለምርታቸው በሚያስፈልጉና ከውጭ በሚያስገቧቸው የጥሬ እቃ ግብዓቶች ላይ የነበረው ታክስ እንዲነሳ መወሰኑን አመልክቷል። በተጨማሪም እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ደግሞ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ይህ የመንግሥት ውሳኔ እነዚህ መሠረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በተለይም በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማስቻልና የአገር ውስጥ አምራቾች እንዲበረታቱ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ መደረጉ ታውቋል። ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ይህ የቀረጥና ታክስ ማሻሻያ፣ ሴቶች የንጽህና መጠበቂያን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ በማድረግ ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከወር አበባ ጋር በተዛመዱ ምክንያቶች እንዳያቋርጡና በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ላይ የሥነ ልቦና ጫና እንዳይገጥማቸው ለማገዝ ነው ብሏል። በተጨማሪም እርምጃው የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና ዋጋ እንዲቀንስ በማድረግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ችግር ዘላቂ በመሆነ መንገድ መፍታት እንዲሁም ጥራት ያላቸው ምርቶች እንዲቀርቡ ለማስቻል እንደሚያግዝ ተገልጿል። በሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች አቅርቦት ዙሪያ በኢትዮጵያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በእነዚህ ምርቶች ላይ ባለው የዋጋ ውድነትና የአቅርቦት ችግር የተነሳ አብዛኞቹ ሴቶች የሚጠቀሙት በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ የወር አበባ መጠበቂያ ዘዴዎችን ነው። ይህም በተለይ አብዛኛው ሕዝብ በሚኖርባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶች ትምህርትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖን እንደሚያሳድር ይነገራል። ለሴቶች መብት የሚሰሩ ማኅበራት፣ ተቋማትና ግለሰቦች የሴቶችን ጤናና ሁለገብ ተሳትፎ ለማበረታታት መንግሥት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ በእጅጉ የሚቀንሱ እርምጃዎችን እንዲወስድ ለዓመታት ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ተጥሎ የቆየውን የቀረጥ ታክስ ለማንሳት እንዲሁም ለመቀነስ የወሰደችው እርምጃ በምርቶቹ ዋጋ ላይና አቅርቦት ላይ ጉልህ ውጤት እንደሚኖረው ይጠበቃል። የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳለው በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ስምንት የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) የሚያመርቱ ፋብሪካዎች አሉ።
news-51058879
https://www.bbc.com/amharic/news-51058879
ካናዳ፣ አሜሪካ እና ዩኬ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አለን አሉ
ምዕራባውያን መሪዎች የዩክሬኑ አውሮፕላን ቴህራን አቅራቢያ የመከስከሱ ምክንያት ኢራን በስህተት በሚሳኤል መትታ ስለጣለችው ነው አሉ።
የአሜሪካ፣ ካናዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም መሪዎች አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ ማስረጃ መኖሩን ጠቁመዋል። ከምዕራባውያን ሃገራት በተጨማሪ የኢራቅ እና የዩክሬን መንግሥታትም አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አድሮባቸዋል። ለ176 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የአውሮፕላን መከስከስ ዙሪያ ዝርዝር ምርመራዎች እንዲደረጉ የዩናይድ ኪንግደም እና ካናዳ መንግሥታት ጠይቀዋል። ትናንት አመሻሽ ላይ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ኃላፊ ለሲቢኤስ የዜና ወኪል ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በኢራን ሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ ጥቆማ ከሰጡ በኋላ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ዩክሬን ቀደም ብላ አውሮፕላኑን እንዲከሰከስ ያደረገው ከኢራን የተተኮሰ ሚሳኤል ሊሆን እንደሚችል ግምት አስቀምጣ የነበረ ሲሆን፤ ኢራን ግን የዩክሬንን ምልከታ አጣጥላው ነበር። ኢራን ሩሲያ ሰራሽ ቶር የመከላከያ ሚሳኤል ሥርዓት ባለቤት መሆኗ ይታወቃል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ኢራን አውሮፕላኑን መትታ የጣለችው የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጋር አሳስታ ስለመሆኑ በስፋት እየዘገቡ ነው። አንድ አውሮፕላን በሚሳኤል ተመትቶ ከወደቀ ለጥቃቱ ጥቅም ላይ የዋለው ሚሳኤል በራዳር፣ ኢንፍራሬድ ወይም ሳተላይት ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ሲግናሉን ማግኘት እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሲቢኤስ የዜና ወኪል አንድ የአሜሪካ የደህንነት ባለሙያን ጠቅሶ እንደዘገበው ሁለት ሚሳኤሎች ሲወነጨፉ እና ሚሳኤሎች ያስከተሉት ፍንዳታ በሳተላይት ተመዝግቦ ተገኘቷል። በሌላ በኩል ኒውስዊክ የተሰኘው ሌላው የአሜሪካ የዜና ተቋም የፔንታጎን፣ የአሜሪካ እና የኢራቅ መንግሥታት የደህንነት ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፤ አውሮፕላኑ ተመትቶ የወደቀው በሩሲያ ሰራሽ ቶር ሚሳኤል ነው። የዩክሬን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ አውሮፕላን ቴህራን ከሚገኘው ኢማም ኮሜይኒ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው የተከሰከሰው። አውሮፕላኑ ጉዞውን ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ አድርጎ ነበር የተነሳው። ኢራን የአውሮፕላኑን የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ጥቁር ሳጥን (ብላክ ቦክስ) ለአሜሪካም ሆነ ለቦይንግ አልሰጥም ማለቷ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ኢራን የዩክሬን እና ቦይንግ መርማሪዎች በምርመራው ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢራን እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥታለች። እንደ ዓለም አቀፍ አቪዬሽን ሕግ ከሆነ ኢራን ምርመራውን የመምራት መብት ያላት ሲሆን፤ በተለምዶ ግን የአውሮፕላኑ አምራቾች በምርመራው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ይኖራቸዋል። ምዕራባውያን መሪዎች ምን አሉ? የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ አውሮፕላኑ ከምድር ወደ ሰማይ ተወንጫፊ በሆነ ሚሳኤል ተመትቶ ስለመጣሉ ብዙ የደህንነት መረጃዎች ደርሰውኛል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ትሩዶ፤ ባገኙት መረጃ መሠረት ኢራን አውሮፕላኑን ሆነ ብላ አልመታችም። "ካናዳውያን ጥያቄዎች አሏቸው። ለጥያቄዎቻቸውም ምላሽ ማግኘት ይገባቸዋል" በማለት በአደጋው ዙሪያ ዝርዝር ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ለአደጋው የትኛውንም አካል ተጠያቂ ለማድረግም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜው ገና መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት 178 ሰዎች መካከል 63 ካናዳውያን ሲሆን፤ ከዩክሬኗ ኪዬቨ ወደ ቶሮንቶ ካናዳ የሚያቀኑ ነበሩ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ትናንት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ''ከዚህ አውሮፕላን ጋር በተገናኘ ጥርጣሬ አለኝ። የሆነ አካል ስህተት ሳይሰራ አይቀርም'' ከማለት ውጪ ዝርዝር ነገር መናገርን አልፈቀዱም። የዩናይት ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንም፤ ሃገራቸው ከካናዳ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አገራት ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል። ቀደም ሲል የዩክሬን የደህንነት ኃላፊ ለአውሮፕላኑ መከስከስ ሦስት ምክንያቶችን አስቀምጠው ነበር። እነዚህም፦ ኢራን ምን እያለች ነው? የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኃላፊ አሊ አቤደዛዱህ "አውሮፕላኑ በምዕራብ አቅጣጫ ከአየር ማረፊያ ተነስቶ መብረር ከጀመረ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ቀኝ ዞሮ ተመልሶ ለማረፍ እየመጣ ሳለ ነው የተከሰከሰው" ብለዋል። ኃላፊው ጨምረውም የዓይን እማኞች አውሮፕላኑ አየር ላይ ሳለ በእሳት ተያይዞ ማየታቸውን ገልጸዋል። "በሳይንሳዊ መንገድ ከተመለከትነው፤ ይህ አውሮፕላን በሚሳኤል ተመትቶ ነው የወደቀው የሚለው የሚያስኬድ አይደለም" ብለዋል። የአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ ለበርካታ ንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው ይህ ሁሉ እሰጣ ገባ የጀመረው አሜሪካ በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒን ከገደለች በኋላ ነው። ዶናልድ ትራምፕ፤ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒን 'አሸባሪ' ይበሉት እንጂ በኢራናውያን ዘንድ እንደ 'ጀግና' ነበር የሚቆጠረው። የጦር ጀነራሉ፤ ከፕሬዝደንቱ በላይ እና ከኃይማኖት መሪው በታች የሚገኙ ሁለተኛው የኢራን ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ ነበሩ። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ፤ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኩድስ ኃይል አዛዥ ነበሩ። ኢራን ለጀነራሉ ግድያ በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ምላሽ ለመውሰድ ብዙ ከዛተች በኋላ፤ በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር መንደሮች ላይ የሚሳኤል ድብደባ አድርጋ ነበር።
44150425
https://www.bbc.com/amharic/44150425
ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?
ከአንድ ሳምንት በፊት ኢትዮ ቴሌኮም ለመኖሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰጥ ለሃገር በቀል የግል ድርጅት ፍቃድ ሰጥቻለሁ ብሎ ካሳወቀ በኋላ ዜናው የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
በርካቶች የኢትዮ ቴሌኮም እርምጃ የተሻለ የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማግኘት መልካም አጋጣሚ ነው በማለት ተስፋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ መንግሥት የግል ኩባንያዎች የቴሌኮም ዘርፉን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ አስቧል ይህም የመጀመሪያው እርምጃ ነው በማለት የሚከራከሩ የዘርፉ ባለሙያዎች አሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ ፍቃድ የተሰጠው ድርጅት ሃገር በቀል አይደለም፣ ባለቤቶቹም ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሉ ክሶችን ጭምሮ በርካታ አስተያየቶች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ሲንሸራሸር ቆይቷል። ከኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ ፍቃድ ከወሰዱት ድርጅቶች መካከል አንዱ አቶ ብሩክ ሞገስ የሚያስተዳድሩት ጂቱጂ (G2G) ግሩፕ ይገኝበታል። አቶ ብሩክ ጂቱጂ ግሩፕ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሴክተሩን በአራት ከፍሎ እየሰራ የሚገኘ ኩባንያ ነው ሲሉ ስለሚመሩት ድርጅት ያስረዳሉ። ከአራቱ ምድቦች መካከል አንዱ ጂቱጂ አይቲ ክላሪቲ አንዱ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮም አጋር እና በቅርቡ ለመኖሪያ ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀ ድርጅት መሆኑንን ያስረዳሉ። ጂቱጂ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የአጭር የጽሁፍ መልዕክትን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ እንደቆየ አቶ ብሩክ ያስታውሳሉ። የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል የማዘዋወር የመጀመሪያ እርምጃ? የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ኢትዮ ቴሌኮም የተወሰኑ አገልግሎቶቹን የግል ኩባንያዎች በማሳተፍ እያስፋፋ ይገኛል ይላሉ። እንደምሳሌም ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮ ቴሌኮም የሲም ካርድ ሽያጩን የግል አከፋፋዮችን በመጠቀም ወደ ገበያ ማቅረቡን የሚያስታውሱት አቶ ዘመዴነህ፤ ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ተሞክሮ የሲም ካርድ ሽያጩን በከፍተኛ ደረጃ ከፍ እንዳደረገለት ይናገራሉ። "አሁንም የግል ኩባንያዎችን በማሳተፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋፋት ይህን ፕሮግራም እንዳስጀመረ እንጂ በእኔ ግምት የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል የማዘዋወር እርምጃ ሆኖ አይታየኝም" ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህር የሆኑት አቶ ጉታ ለገስ በበኩላቸው የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል ለማዘዋወር ይህ የመጀመሪያው ትንሹ እርምጃ ነው ይላሉ። እንደ አቶ ጉታ ከሆነ የተለያዩ ዘርፎችን ወደ ግል ለማዘዋወር ብዙ ደረጃዎች መታለፍ አለባቸው። ከዚህ አንጻርም የግል ኩባንያዎች የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንዲሰጡ ማስቻል የመጀመሪያዋ ትንሿ እርምጃ ነች ሲሉ ያስረዳሉ። የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱራሂም አህመድ በበኩላቸው የቴሌኮም ዘርፉን ወደግል የማዘዋወር እርምጃ ነው የሚለው ''የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። የሞባይል ካርድ እንዲሸጡ ፍቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች፤ የሞባይል ካርዶችን ከቴሌ በብዛት ገዝተው እንደሚቸረችሩት ሁሉ ይህም ድርጅት ከእኛ ይገዛና ለደንበኞቹ ያስተላልፋል እንጂ የፖሊሲ ለውጥ የለም'' ሲሉ ተናግረዋል። የአገልግሎት ጥራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ተክሊት ሃይላይ የኢንተርኔት አገልግሎት በግል ኩባንያዎች አማካኝነት ለደንበኞች እንዲደርስ ማድረጉ ተደራሽነቱን ከፍ ያደርጋል እንዲሁም የተጠቃሚውን ቁጥር ይጨምራል ባይ ናቸው። እንደ አይሲቲ ባለሙያው ከሆነ የኢትዮ ቴሌኮም /ኮር ኔትዎርክስ/ ዋና ኔትዎርኮች ብዙ ወጪ የፈሰሰባቸው እና ጥራታቸው አስተማማኝ ነው። አቶ ተክሊት ''የኢትዮ ቴሌኮም የኔትዎርክ ችግር የሚከሰተው ከአክሰስ ኔትወርክ ነው። በየሰፈሩ የሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ማከፋፈያ ሳጥኖች እስከ ደንበኛው ድረስ ያለው መስመር በተደጋጋሚ ችግር ያጋጥመዋል ይህም በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ ችግር ያስከትላል'' በማለት ያስረዳሉ። የጂቱጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ በበኩላቸው በየሰፈሩ ከሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ማከፋፈያ ሳጥኖች እሰከ ደንበኛው ድረስ ያለው የመስመር ችግርን በመቅረፍ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችለናል ይላሉ። እንደ አቶ ብሩክ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ቴሌኮም ከሚሰጠው የኢንተርኔት ዋጋ ለመኖሪያ ቤቶች ከ10 እሰከ 50 በመቶ እንዲሁም ለንግድ ድርጅቶች ከ5-20 በመቶ ቅናሽ እናደርጋለን ብለዋል። የድርጅቱ ባለቤትነት ከዓመታት በፊት ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በስድስት ዓይነት የኢትዮ ቴሌኮም ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍቃድ እንደተሰጣቸው፤ ከእነዚህም መካከል አንዱ አሁን የተጀመረው የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሆነ አቶ ብሩክ ይናገራሉ። የድርጅቱ ባለቤት የማን እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ብሩክ ሲመልሱ ''ድርጅቱ የአክሲዮን ማህበር ነው። የማህበሩን አባላትን ይፋ ማድረግ አልሻም፤ ይሁን እንጂ ከድርጅቱ ባለቤቶች መካከል መግለጫ የሰጠነው እኔ እና ባልደረባዬ ቴዎድሮስ መሃሪ እንገኝበታለን'' ብለዋል። ''ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቴ በፊት ኤ ኤንደ ዲ አይቲ ሶሉሽንስ የሚባል ድርጅት በአትላንታ አሜሪካ አቋቁሜ ነበር። ይህን ድርጅት በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ስሞክር ተጨማሪ አጋሮች በማግኘቴ ጂቱጂ የሚባል በኢትዮጵያ የተመዘገበ ሃገር በቀል ድርጅት መሰረትን'' ሲሉ ይናገራሉ። የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊው አቶ አብዱራሂም ስለ ጂቱጂ ግሩፕ ሲናገሩ ''ይህ ድርጅት ጎልቶ ወጣ እንጂ አጠቃላይ ይህን አገልግሎት እንዲሰጡ ለ8 ድርጅቶች ፍቃድ ሰጥተናል። ዋናው ነገር ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የሚሰጠውን ፍቃድ የሚያገኝ ድርጅት አገልግሎቱን ለመስጠት በዘርፉ ሊሰማራ ይችላል'' ብለዋል።
news-55241933
https://www.bbc.com/amharic/news-55241933
የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንኖች ሴት ወታደሮች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ ተባረሩ
የአሜሪካ ጦር አስራ አራት ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራር ያሉ ወታደራዊ መኮንኖች በሴት ወታደሮች ላይ ግድያን ጨምሮ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳን ፈፅመዋል በሚል አባሯቸዋል።
በቴክሳስ በሚገኘው የፎርት ሁድ የጦር ሰፈርም ነው እነዚህ ተደጋጋሚ ጥቃቶች የተፈፀሙት። ቫኔሳ ጉሊየን የተባለች ወታደር በባለፈው አመት መገደሏንም ተከትሎ ነው በጦር ሰፈሩ ላይ ምርመራ የተጀመረው። የ20 አመቷ ቫኔሳ ለሁለት ወር ያህል ጠፍታ የነበረ ሲሆን የአስከሬኗም የተወሰነ ክፍል የተገኘው በሰኔ ወር ነበር። በጦር ሰፈሩ ውስጥ በድብደባ እንደተገደለችም መርማሪዎች ገልፀዋል። በሞቷ ዋነኛው ተጠርጣሪ የጦር መኮንኑ አሮን ሮቢንሰን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲል ሃምሌ ወር ላይ ራሱን አጥፍቷል። የቫኔሳ ቤተሰቦች በአሮን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባታል ቢሉም ባለስልጣናቱ በበኩላቸው ወሲባዊ ጥቃትና ትንኮሳ ሪፖርት አልደረሰንም በማለት ተናግረዋል። የቫኔሳ ግድያ የምርመራ ጉዳይ ገና አልተቋጨም። የጦሩ ዋና ፀሃፊ ራያን ማካርቲ እንዳሉት " በፎርት ሁድ ጦር ሰፈር የተፈፀሙት ጉዳዮች ቀጥታ አመራሩ ጉድለት ጋር የተያያዙ ናቸው" ከዚህም በተጨማሪ በጦር ሰፈሩ ጠፉ የተባሉ ወታደሮችንም በተመለከተ አዲስ ፖሊሲ እንዲወጣ ጦሩ ትእዛዝ አስተላልፏል። የተባረሩትና የታገዱት ወታደራዊ መኮንኖች ጉዳይ የተገለፀው በትናንትናው ዕለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሜጀር ጄኔራሎቹ ስኮት ኤፍላንድትና ጄፈሪ ብሮድዋተር ይገኙበታል። በተለይም የቫኔሳ ግድያ "ሁላችንም አስደንግጦናል። በአሜሪካ ጦርም ውስጥም ሆነ በፎርት ሁድ ጦር ውስጥ ስር የሰደደውን ችግር እንድንመለከተው አድርጎናል" ብለዋል ዋናው ፀሃፊው። አክለውም "በስርዓታችን፣ በፖሊሲዎቻችንና ራሳችንንም በጥልቀት እንድንመለከትና እንድንፈትሽም አስገድዶናልም" በማለት ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። በፎርት ሁድ በሚገኘው የጦር ሰፈር በአንድ አመት ብቻ 25 ወታደሮች በተለያዩ ምክንያቶች ሞተዋል። አንዳንዶቹ ራሳቸውን አጥፍተዋል፣ ተገድለዋል ወይም አደጋ ደርሶባቸው ነው የሞቱት በማለት አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
news-53511871
https://www.bbc.com/amharic/news-53511871
ማይክ ታይሰን ወደ ቦክስ መድረክ ሊመለስ ነው
የቀድሞው የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን ወደ ቡጢው ዓለም ሊመለስ ነው።
ዝነኛው የቦክስ ተፋላሚ ማይክ ታይሰን ዕድሜው 54 ደርሷል። ወደ ቦክስ መፋለሚያ መድረክ የመመለሱ ዜና እያነጋገረ ነው። ማይክ ታይሰን ለአጭር ደቂቃ በሚቆየው ፍልሚያ የሚገጥመው የአራት ጊዜ የቀድሞው የዓለም ሻምፒዮን የነበረውን ሮይ ጆንስ ጁኒየርን ይሆናል። ሁለቱ ዝነኞች ለዚሁ ግጥሚያ የሚገናኙት መስከረም 12 ላይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው። ማይክ ታይሰን ለመጨረሻ ጊዜ ደንበኛ የቦክስ ግጥሚያ አደረገ የሚባለው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2005 ነበር። በዚያ ውድድር ላይ በአየርላንዳዊው ተወዳዳሪ ኬቪን ማክብራይድ ክፉኛ ተደብድቦ ነበር። ይህም ታይሰን ካደረጋቸው 58 የቡጢ ፍልሚያዎች 6ኛው ሽንፈቱ ነበር። በመጪው መስከረም ወር ታይሰንን የሚገጥመው ጆንስ ዕድሜው 51 ሲሆን በየካቲት 2018 ቡጢኛ ስኮት ሲግመንን ካሸነፈ ወዲህ ውድድር አድርጎ አያውቅም። የካሊፎርኒያ ግዛት የአትሌቲክስ ኮሚሽን ይህ የቡጢ ፍልሚያ ሰዎች በተገኙበት እንዳይካሄድ ያዘዘ ሲሆን፤ ውድድሩ በክፍያ ብቻ በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል። ፍልሚያው 8 ዙሮች ይኖሩታል። ማይክ ታይሰን የዓለም የከባድ ሚዛንን ሻምፒዮና የሆነው ገና በ20 ዓመቱ ነበር። ይህም የሆነው በፈረንጆቹ በ1986 ትሪቨር በርቢክን ማሸነፉን ተከትሎ ነው። በቅርቡ ታይሰን በማኅበራዊ ሚዲያ የቦክስ ልምምድ ሲያደርግ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መውጣታቸውን ተከትሎ ወደ ቦክስ ስፖርት ሊመለስ ነው የሚሉ ጉምጉምታዎች እዚያም እዚህም መሰማት ጀምረው ነበር። በ2006 ታይሰን ተመሳሳይ አራት ዙር የቦክስ ግጥሚያ ከኮሪ ሳንደርስ ጋር ማድረጉ ይታወሳል። ያም የሆነው ማይክ ታይሰን በ2003 የገንዘብ ኪሳራ ገጥሞት ስለነበረና ገንዘብ ስላስፈለገው ነበር። በቅርብ ጊዜ ደግሞ ማይክ ታይሰን ከኢቫንደር ሆሊፊልምድ ጋር ዳግም ሊገጥም ይችላል የሚሉ ወሬዎች መውጣት ጀምረው ነበር። የ57 ዓመቱ ሆሊፊልድ ከቡጢ ራሱን ያገለለው በ2016 ነበር። ከታይሰን ጋር በ1990ዎቹ ሁለት ጊዜ በቦክስ መድረከረ ላይ ተገናኝተው ሁለቱንም ጊዜ ሆሊፊልድ ድል ቀንቶት ነበር። ከዚህ ውስጥ በብዙዎች አእምሮ የቀረው በ1997 ታይሰን የሆሊፊልመድን ጆሮ መንከሱ ነበር። የታይሰን የአሁኑ ተጋጣሚ ጆንስ ጁኒየር ስለ ውድድሩ በለቀቀው የቪዲዮ ማስታወቂያ "የታይሰንና የእኔ ወድድር የዳዊትና የጎሊያድ ፍልሚያ ነው የሚሆነው" ሲል ቀልዷል።
news-54143953
https://www.bbc.com/amharic/news-54143953
የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ቀን ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ህሙማን መዘገበ
የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ቀን ቫይረሱ የተገኘባው ሰዎች ከፍተኛውን ቁጥር መመዝገቡን ገለጸ። በ24 ሰዓት ውስጥ 307 ሺህ 930 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በአንድ ቀን 5 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሲሆን፤ ይህም የሟቾችን ቁጥር 917 ሺህ 417 አድርሶታል። በበሽታው በተያዙ ሰዎች ቁጥር ሕንድ፣ አሜሪካ እና ብራዚል ቀዳሚ ናቸው። በመላው ዓለም 28 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ከነዚህ ገሚሱ የአሜሪካ ነዋሪዎች ናቸው። ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር የተመዘገበው ከስምንት ቀን በፊት ሲሆን፤ ቁጥሩም 306,857 እንደነበር ተገልጿል። በዓለም ጤና ድርጅት አሐዝ መሠረት፤ ትላንት በሕንድ 94,372፣ በአሜሪካ 45,523 እና በብራዚል 43,718 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሕንድ እና በአሜሪካ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ሲሞቱ፤ በብራዚል 847 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሕንድ ነሐሴ ላይ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖረት አድርጋለች። ይህም ቫይረሱ መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ወር የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ነው። በአገሪቱ በአማካይ በአንድ ቀን 64,000 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ይህም በሐምሌ ከነበረው 84 በመቶ ጨምሯል። መስከረም ከገባ ወዲህ በየቀኑ የሚሞቱ ሰዎች 1,000 ይጠጋሉ። በብራዚል ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከላቲን አሜሪካ አገሮች ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የታየውም በብራዚል ነው። እስካሁን 131,000 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዓለም በበሽታው ከተያዙ ሰዎች አንድ አራተኛው የሚገኙት በአሜሪካ ነው። እስካሁን ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል። ከሐምሌ ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየናረ መጥቷል። እስካሁን 194,000 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ከዓለም ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበውም በአሜሪካ ነው። ሌሎች አገራትስ? አውሮፓ ውስጥ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ቫይረሱ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋትም አለ። በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲያደርጉና አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁም ማሳሰቢያ እየተሰጠ ይገኛል። ቫይረሱ ዳግመኛ ካገረሸባቸው አገሮች መካከል ፔሩ፣ እስራኤል፣ ደቡብ ኮርያ እና አውስትራሊያ ይጠቀሳሉ። እሁድ በአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ ከተማ ፖሊስ 70 ተቃዋሚዎችን አስሯል። ግለሰቦቹ ከቤት ያለመውጣት ሕግን በመተላለፋቸው ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። በሜልቦርን በተካሄደው ተቃውሞ ላይ ቢያንስ ወደ 250 ሰዎች ተሳትፈዋል። ስለ ወረርሽኙ የሴራ ትንታኔዎች ሲስተጋቡም ነበር። በሌላ በኩል እስራኤል እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ልታደርግ መሆኑ ተገልጿል። የአይሁዳውያን አዲስ ዓመት አርብ ሲከበር፤ እስከ ሦስት ሳምንት የሚቆዩ ጠንካራ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይተላለፋሉ ተብሎም ይጠበቃል። በእስራኤል153,000 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፤ 1,108 መሞታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አሐዝ ይጠቁማል።
news-53080079
https://www.bbc.com/amharic/news-53080079
ከአስተናጋጅነት ምርጡን የአፍሪካ ባንድ የመሰረተው ሙዚቀኛ
በኬንያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስመጥር ከሆኑት አንዱ የሆነው ጆን ንዜንዜ ከሰሞኑ ህይወቱ አልፏል።
በግራ በኩል ያለው ጆን ንዜንዜና ሲሆን በቀኝ በኩል ደግሞ የመጀመሪያ ሙዚቃውን አብሮ የቀረፀው ዳውዲ ካባካ ኬንያ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችበት ወቅት፤ ግድያ፣ ስቃይና መቆርቆዝ የጥቁሮች እውነታ በነበረበት በዚያ ዘመን በሚያቀነቅናቸው ዘፈኖቹ ተስፋን መፈንጠቅ የቻለ ነው። ድምጻዊ፣ ጊታር ተጫዋች፣ እንዲሁም ዳንሰኛው ጆን ንዜንዜ የኬንያን ትዊስት የተባለውንም የሙዚቃ አይነትም ከፍ ወዳለ ስፍራ በማድረስ አሻራውን ያኖረ ሙዚቀኛ ነው። በጎርጎሳውያኑ 1960ና 1970ዎቹም በምሥራቅ አፍሪካ በፈንክ የሙዚቃ አይነት ምርጥ ሥራዎችን ካበረከቱት ባንዶች መካከልም አንዱ የእሱ ነበር። "ታዋቂ ስትሆን በተወሰነ መልኩ እብሪተኛ ወይም ትዕቢተኛ መሆንህ አይቀርም። እኔም በእብሪተኛነቴ ነው የእራሴን ኤይር ፊየስታ ማታታ ባንድ የመሰረትኩት" በማለት ከመሞቱ በፊት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጿል። ባንዱ ከኮንጎ የመጡ ስደተኞችንም ያካተተ ሲሆን በዓለም ላይ እውቅና ለማግኘትም የወሰደበት ጊዜ ጥቂት ዓመታትን ነው። በጎርጎሳውያኑ 1968ም በአልጀሪያ ተካሂዶ በነበረው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ፌስቲቫልም በተደረገው ውድድር ባንዱ ሦስተኛ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላም በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ለብዙ ወራት ቆይታ በማድረግ በርካታ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። ቢቢሲ አፍሪካ ምርጡ የአፍሪካ ባንድ በሚል በ1971 ሽልማትን የሰጣቸው ሲሆን በወቅቱም ስመ ጥር ከነበሩት ከአሜሪካዊው ጄምስ ብራውንና ኦሲቢሳ ቡድንም ጋር አብረው ለንደን ውስጥ አቀንቅነዋል። በጎርጎሳውያኑ 1972 በዩናይትድ ኪንግደም የሙዚቃ ስራቸውን ሲያቀርቡ በዚህ በለንደን በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ ሙገሳና ውደሳን ቢጎናጸፉም የባንዱ መጨረሻም ሆነ። የባንዱ በርካታ አባላት ኬንያውያኑም ሆነ የኮንጎ ዜግነት ያላቸው በእንግሊዝ ለመቆየት በመወሰናቸው የባንዱም ፍጻሜ ሆነ። "ወደ ኬንያ ልንመለስ ስንል ኮንጎዎቹ የባንዳችን አባላት ኬንያ ውስጥ በስደተኝነት ከምንኖር እዚሁ ብንቆይ ይሻላል አሉ። በርካቶችም ለንደን ለመቆየት በመወሰናቸው ባንዱ ፈረሰ በማለት" ጆን ይናገራል። ባንዱ ቢፈርስም ጆንን ብቻውን የሚወደውን ሙዚቃ ከመቀጠል አላገደውም። ሌሎች ባንዶችንም ተቀላቅሎ ተጫውቷል። በመዲናዋ ናይሮቢም ፊልኮ ለሚባል ስቱዲዮም ለተለያዩ ሙዚቀኞችም ፕሮዲውስ አድርጓል። የሙዚቃውን ዓለም እንዴት ተቀላቀለ? በወቅቱ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው የኬንያዋ መዲና በጎርጎሳውያኑ 1940 ነው የተወለደው። ትምህርቱን የተከታተለው በናይሮቢ እንዲሁም የቤተሰቦቹ የትውልድ ቦታ በሆነችው ምዕራብ ኬንያ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አቁሞ በሆቴል ውስጥ በአስተናጋጅነት ተቀጠረ። የሙዚቃ ጉዞው ግን የተጠነሰሰው ከዚያ በፊት ነው፤ በአስራዎቹ እድሜ ላይ እያለ የአባቱን ጊታር አንስቶ የሙዚቃ ህይወቱን 'ሀ' ብሎ ጀመረ። የኬንያ መዲና ናይሮቢ በጎርጎሳውያኑ 1940ዎቹ በጊዜው ስመ-ጥር በነበረው ኖርፎክ ሆቴል ነው በአስተናጋጅነት የተቀጠረው። የሆቴሉ ሠራተኞችም ያድሩ የነበረው በዚያው በሆቴሉ ውስጥ ነበር። ክፍሉን ይጋራው ከነበረው ዳውዲ ካባካም ጋር ሙዚቃዎችን ማቀናበር እንዲሁም መቅረፅ ጀመሩ። ወደ በኋላ ግን ዳውዲ ብቻውን ሙዚቃዎቹን እንዳቀናበረ በተደጋጋሚ በመናገሩ ጆን ደስተኛ አልነበረም። ለሙዚቃዎቹ ዳውዲ በብቸኝነት ስሙ በሬድዮ መነገሩ ያናደደው ጆን ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን ለሕዝብ ጆሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የደረሰውን 'አንጀሊክ' የተሰኘ ነጠላ ዜማውን ቀረፀ። ከሁሉ በላይ ሙዚቃው በሬድዮ በመጫወቱ በወቅቱ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረለት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር "ገንዘቡ አይደለም፤ ዋናው ለእኔ ሙዚቃዬ ነው" ብሏል። በኬንያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታዋቂ ከሆኑ ዘፈኖች ውስጥ አንዱ የሆነው 'አንጀሊክ' የሴት ፍቅረኛው ወደ ቤት እንድትመለስ የሚማፀን ሙዚቃ ነው። ከአንጀሊክ በፊት ከዳውዲ ጋር አግኔታ ስለምትባለው ፍቅረኛውም ዘፍኖ ነበር። በወቅቱ ጆን ያላወቀው አግኔታ የዳውዲም ፍቅረኛ መሆኗን ነው። ግጥሙም ላይ አግኔታን እንዴት ናይሮቢ እንደተዋወቃት፤ ይዋደዱ እንደነበርና በወቅቱ ባል ወይም ጓደኛ እንዳላት ሲጠይቃት እንደሌላት መንገሯን እናም አንድ ቀን እሷ ቤት ሄደው አብረው በተኙበት ወቅት በር ተንኳኳ። ማነው ሲልም "የቤቱ ባለቤት ነኝ" አለው። ግጥሙም ላይ አግኔታ ይህ ሥራ ኣሳፋሪ ነው ይላታል። ሁለት ፍቅረኛ መያዝ ይላል። ከሰውየው ጋርስ ተጣልቼ ቢሆን? ተጎዳድተንስ ቢሆን? ምን ታደርጊ ነበር በማለት በግጥሙም ይጠይቃል። ጆን ሙዚቃው በራሱ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የሴቶቹን እውነተኛ ስም ግን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። በሚስረቀርቅ ዜማ የብዙዎች ልብ ውስጥ መግባት የቻለው ሙዚቀኛ ዝናንም ማትረፍ የቻለው ፍቅርን በውብ ቃላት መግለፅ በመቻሉ ነው። በወቅቱ በተለያየ ጊዜ ይወዳቸው ለነበሩ ሴቶች የነበረውን ፍቅር ገልጿል፤ ልብ ስብራቱንም እንዲሁ። "ሴቶችን በሙዚቃህ ማስደሰት ካልቻልክ ሙዚቃህ ብዙ ትርጉም አይኖረውም። ሴቶች ሙዚቃህን ሲወዱ ነው ወንዶችም የሚከተሉት" በማለትም በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። "ወጣቶች ነበርን፤ ፍቅርም ውስጥ ነበርን" በማለት አክሏል። ጆን በመድረክ አዘፋፈኑ እንዲሁም ታዳሚዎቹን በዘፈኖቹ በመማረክ ከፍተኛ ሙገሳና ውደሳን አትርፏል። ከዚህ የመድረክ ስጦታውም ጋር ተያይዞ በርካታ የዘመኑ ዘፋኞች ሙዚቃቸው ከጥበቡ ይልቅ ለቴክኖሎጂ ከፍተኛ ስፍራ በመስጠታቸው ሥራቸውንም ሆነ ሙዚቃውን አያውቁትም በማለትም ተችቷቸዋል። "አንዳንድ ሙዚቀኞች የትኛው የሙዚቃ መሳርያ ቁልፎች ላይ ዘፈኖቹ እንደሚያርፍ እንኳን አያውቁም፤ አቀናባሪው ብቻ ነው የሚያውቀው" ብሏል። የእሱ ሙዚቃዎች ከግጥም ይዘታቸውም ጋር ተያይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ መሸጋገር እንደቻሉም በኩራትም ይናገራል። "የእኔ ሙዚቃ የግጥም ጥልቀት ነበረው፤ ሙዚቃውም ጊዜ ተወስዶበት በደንብ ተደርጎ ነው የተሰራው። የዘመኑ ግን ዛሬ ተሰርተው ለነገ ይቀርባሉ። ወዲያውም ይሰለቻሉ" በማለት ከአምስት ዓመት በፊት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። ከአንጀሊክ በተጨማሪ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻሉት በስዋሂሊ ከተቀነቀኑት መካከል 'ኒናሙይሊላ ሱዛና' (ለሱዛን እያለቀስኩ ነው)፣ 'ኒ ቪዙሪ ኩዋ ና ቢቢ' (ሚስት ሲኖርህ መልካም ነው)፣ 'ማርሻይ ያ ዋሬምቦ' (የሴቶች ሽቶ) የመሳሰሉ ሙዚቃዎቹ ይገኙበታል። ነገር ግን ለቢቢሲ እንደተናገረው የአንጀሊክን ያህል ድንበሮችን የተሻገረ እንዲሁም በሌላው ዓለምም መግነን የቻለ ሙዚቃ እንደሌለው ተናግሮ ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2004 ወራትን ባስቆጠረው የመርከብ ጉዞ ላይ ጃፓንን ጨምሮ በሲንጋፖርና በሌሎች አገራትም ለወራት ያህል ተጫውቷል። "የሆነ ደረጃ ላይ ከደረስክ በሙዚቃህ ገንዘብ ታገኝበታለህ። አንጀሊክ በርካታ አገራት ወስዶኛል" ብሎም ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2014ም ከሌላ ኬንያዊ ሙዚቀኛ ፒተር አክዋቢ ጋር በመሆን በአሜሪካ የሙዚቃ ጉዞ ያደረገ ሲሆን በስሚዝሶኒያን ፌስቲቫልም ላይ ተጫውቷል። ከተወዳጅ ሙዚቀኛነቱም በተጨማሪ ለሌሎች ሙዚቀኞች ያለውን ድጋፍም በተለያየ መንገድ ያሳይ የነበረ አርቲስት ነው። እንደ ሌሎች አገራት በኬንያ የሚገኙ ሙዚቀኞች ሥራዎችም በሕገወጥ መንገድ ተባዝተው ጎዳናዎች ላይ ይቸረቸራሉ። የተለያዩ የምሽት ክበቦችም ሆኑ የመዝናኛ ቦታዎች ያለ ሙዚቀኞቹ ፈቃድ ያጫውታሉ። ይህንንም ለመታገል ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ጋር የሚሰራ የኬንያ የሙዚቃ ቅጅ መብቶች ማኅበርን ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን መስርቷል። የቦርድ አባልም ሆኖ ለብዙ ዓመታት አገልግሏል። የኬንያ መንግሥት ሙዚቀኛው በአስርት ዓመታት ውስጥ ላበረከተውም ጉልህ ሚና በጎርጎሳውያኑ 2009 ሽልማት አበርክቶለታል። ከሌሎች አራት ስመ ጥር ሙዚቀኞችም ጋር በመሆን የአገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት በወቅቱ ከነበሩት ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ እጅ ተቀብሏል። በጎርጎሳውያኑ 2016 ጡረታ የወጣ ሲሆን፤ ኑሮውንም በምዕራብ ኬንያ በምትገኘው ካይሞሲ በምትባል ግዛት አድርጎ ነበር። የ80 ዓመቱ ሙዚቀኛ በካንሰር ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ህይወቱ ያለፈው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር። የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለሙዚቀኛው የነበራቸውን አድናቆት እንዲሁም የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል "ለሙዚቃ የተሰጠች ነፍስ ነበረው። ድምፁ የሚገርም ነበር። በሙዚቃዎቹ ላይ ያሳየው ፈጠራና ችሎታ የዘመኑ ወርቃማ ሙዚቀኛ ብለው አያንሰውም" ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም "ጥሎልን ባለፈው ድንቅ ሙዚቃዎቹ ሁልጊዜም እናስታውሰዋለን። ስሙ ከመቃብር በላይ ነው። አንረሳህም" ብለዋል።
news-53749528
https://www.bbc.com/amharic/news-53749528
ፊልም ፡ በዚህ ዓመት በሆሊውድ ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የተከፈላቸው ተዋናዩች ታወቁ
በዚህ ዓመት የትኞቹ ተዋናዮች ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች ተከፈሏቸው? ብሎ ለሚጠይቅ ዘንድሮ ድዋይን "ዘ ሮክ" ጆሐንሰንን በክፍያ የሚያህለው አልተገኘም አጭሩ መልስ ነው።
ድዋይን ጆሐንሰንን የሐብታም የገንዘብ መጠን አደባባይ በማስጣት የሚታወቀው ፎርብስ የአዱኛ ዝርዝር መጽሔት ትናንት እንዳስነበበው ከሆነ ድዋይን ጆሐንሰን በዚህ ዓመት ብቻ 87 ሚሊዮን ተኩል ዶላር አጋብሷል። ይህም ካለፈው ዓመት ሰኔ እስከ ዘንድሮ ሰኔ መሆኑ ነው፤ በፈረንጆች አቆጣጠር። ደግሞም የድዋይን ከፍተኛ ተከፋይነት ዘንድሮ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት መሆኑ አስገራሚ ሆኗል። የቀድሞው የነጻ ትግል ተወዳዳሪና የአነቃቂ ዲስኩርተኛ ጆሐንሰን ዘ ሮክ በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የምድራችን ትልቅ ገንዘብ ተከፋይ ተዋናይ ተብሎ መሰየሙ ይታወሳል። ድዋይን ዘ ሮክ ጆሐንሰን ይህ ክፍያው ኔትፍሊክስ ላይ በቅርብ መታየት ለሚጀምረው "ሬድ ኖቲስ" (Red Notice) ለተሰኘው ፊልም ማስታወቂያና ትወና የተከፈለውን 23 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ይጨምራል። በፊልሙ ላይ ድዋይን ራሱ መሪ ሆኖ ይተውንበታል። ሬድ ኖቲስ በቅርብ በኔትፍሊክስ የሚቀርብ አንድ ኢንተርፖል በጥብቅ በሚፈልገው የዓለማችን የሥዕል ቀበኛ ላይ የሚያጠነጥን 'አክሽን ኮሜዲ' ዘውግ ያለው ፊልም ነው። ከዚህ ባሻገር የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አልባሳት ማምረቻ የሆነውና "ፕሮጀክት ሮክ" የሚል ስም ያለው ድርጅቱ ለድዋይን ዘ-ሮክ ጠቀም ያለ ገንዘብ ያስገኝለታል። ከድዋይን 'ዘ-ሮክ' ጆሐንሰን ጋር 'በሬድ ኖቲስ' ፊልም ላይ አብሮት የሚሰራው ሌላኛው ተዋናይ ራየን ሬይኖልድ 2ኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው፤ በፎርብስ መጽሔት መረጃ መሰረት። ራየን ሬይኖርልድ 71 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ወደ ኪሱ አስገብቷል በዚህ ዓመት። ይህ ገንዘብ 'ሬድ ኖቲስ' ላይ ለሚተውንበት የተከፈለውን 20 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሲክስ አንደርግራው (Six Underground) ለተሰኘው ፊልም ደግሞ ሌላ 20 ሚሊዮን የተከፈለውን ይጨምራል። ፎርብስ የዓለማችን ሦስተኛው ከባድ ተከፋይ ተዋናይና ፕሮዲዩሰሩ ማርክ ዋልበርግ እንደሆነ አስታውቋል። 58 ሚሊዮን ዶላር በዓመት ገቢ አግኝቷል ማርክ። በአራተኛና በአምስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ቤን አፍሌክ እና ቪን ዲዝል ናቸው። ከዚህ ሌላ የቦሊውዱ ኩማር እስከ 10 ከገቡ ከፍተኛ ተከፋዮች ብቸኛው ሆኗል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሚራንዳ፣ ዊል ስሚዝ እና አዳም ሳንድለር ይገኙበታል። ጃኪ ቻንም እስከ 10 ባለው ዝርዝር ቦታ አላጣም። ፎርብስ የወንድ ተዋናይንን ዝርዝ ነው ለጊዜው ይፋ ያደረገው። በቀጣይ ሴት ተዋንያንን እንዲሁ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በዚህ የከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ከሴት ተዋንያን ሁሉ ልቃ የተገኘችው ስካርሌት ጆሐንሰን ነበረች፤ 56 ሚሊዮን ዶላር በማፈስ። ይህ ገንዘብ መጠን ባለፈው ዓመት ከወንዶች ዝርዝር ሰባተኛ ደረጃን የሚያስቀምጥ ነበር።
news-54725930
https://www.bbc.com/amharic/news-54725930
የአሜሪካ ምርጫ የሕዳሴ ግድብ ፖለቲካን እንዴት ሊቀይር ይችላል?
የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እና ዲሞክራቱ ጆ ባይደን የሚያደርጉትን የምረጡኝ ዘመቻቸውም እያጠናቀቁ ይገኛሉ። ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጉ አሜሪካውያንም ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ይህን የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሜሪካውያን ብቻ ሳይሆኑ መላው ዓለም በአትኩሮት የሚመለከተው ጉዳይ ነው። የዚህ የምርጫ ውጤትም መጠን እና ስፋቱ ይለያይ እንጂ በሕዳሴ ግድብ ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ሊያመጣ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው። አሜሪካ "በሽብር" ላይ ከፍታ በነበረው ጦርነት በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ አንዷ ትልቋ አጋር ኢትዮጵያ ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጂ በቅርቡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ካለችው የኃይል ማመንጫ ግድብ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምታደርገው ድጋፍ 130 ሚሊዮን ዶላር መከልከሏ ይታወሳል። በግድቡ ጉዳይም አሜሪካ ለግብጽ ወግና ቆማለች። ይህንንም ፕሬዚደንት ትራምፕ በአደባባይ አንጸባርቀዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግብጽ የሕዳሴ ግድቡን "ልታፈነዳው ትችላለች" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ የምርጫው ውጤት በሕዳሴ ግድብ ፖለቲካ ላይ የሚኖረው ለውጥ ምንድነው? 'አሜሪካ ግብጽን ትታ ለኢትዮጵያ አትወግንም' በዩናትድ ኪንግደም በሚገኘው ኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አወል አሎ (ዶ/ር) ሪፐብሊካኖቹም ይሁኑ ዲሞክራቶች ምርጫውን ቢያሸንፉ የነበረውን የአሜሪካ የውጪ ፖሊስ የሚያስቀጥሉት ይላሉ። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊስ ሁልጊዜም ቢሆን በአገሪቱ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በማስታወስ የምርጫው ውጤት በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል የቆየውን ግነኙነት ያን ያህል ሊቀይር እንደማይችል ይናገራሉ። የተለየ የሚያደርገው "ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም አቀፍ ሕግ እና ስምምነቶች ተገዢ የሚሆኑ ሰው አይደሉም የሕዝቡን ትኩረት ለማግኘት ከእርሳቸው የማይጠበቅ ንግግር ይናገራሉ" ይላሉ። ትራምፕ አንዳንድ ጊዜ እንደ ፕሬዚዳንት ሳይሆን "ልክ እንደ ሰባት ዓመት ልጅ ይናገራሉ" ይላሉ። ስለ ሕዳሴ ግድብ በቅርቡ የተናገሩትም ለዚሁ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን አወል አሎ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ቀድሞውንም ቢሆን በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ አሜሪካ ግብጽን ገሸሽ አድርጋ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ታዞራለች ብሎ ማሰቡ ስህተት መሆኑንም ጠቆም ያደርጋሉ። አሜሪካ በመካለኛው ምስራቅ አገራት ልዩ ፍላጎቶች እንዳላት የሚያስረዱት አዎል (ዶ/ር) ከእነዚህም መካከል ዋነኛው የእስራኤልን ፍላጎት ማስጠበቅ ነው ይላሉ። ለአሜሪካ ሁነኛ ወዳጅ ለሆነችው እስራኤል ደግሞ እውቅና እና ድጋፍ ስታደርግ የቆየችው ተጽእኖ ፈጣሪ የአረብ አገር ግብጽ መሆኗንም ያወሳሉ። ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ከደረሱ እና ለእስራኤል እውቅና ከሰጡ ጥቂት የአረብ አገራት መካከል አንዷ ግብጽ መሆኗ ይታወቃል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ፤ "ትራምፕ ፒስ ፕላን" በተባለው እቅዳቸው ለእስራኤል እና ፍልስጥኤም ግጭት መፍትሄ ያሉትን አማራጭ እየተገበሩ ይገኛሉ። በቅርቡም የተባበበሩት ዩናይትድ አረብ ኤምሬት እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ደርሰዋል። ጎረቤት አገር ሱዳንም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ለመፈረም በዝግጅት ላይ ትገኛለች። አዎል አሎ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈው ለሁለተኛ ዙር የሰልጣን ዘመን በዋይት ሃውስ የሚቆዩ ከሆነ በዚሁ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲያቸው የሚቀጥሉ ይሆናል ይላሉ። ዲሞክራቶችም ቢሆኑ ይህን ምርጫ ቢያሸንፉ በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ቁልፍ ነገር ስለሆነ ለኢትዮጵያ ለውጥ ይዞ እንደማይመጣም ይገልፃሉ። ይሁን እንጂ ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ጉዳዩን ትራምፕ እየሄዱበት ባለው መንገድ ሳይሆን የሚያስቀጥሉት ዓለም አቀፍ ሕግ እና ስምምነቶችን ተከትሎ እንደሚሆንም ያስረዳሉ። የትራምፕ አስተዳደር ያቋረጠውን የገንዘብ እርዳታም ጆ ባይደን ሊያስቀጥሉ እንደሚችሉ በመጠቆም ይሁን እንጂ የጆ ባይደን አስተዳደርም ግብጽን ትቶ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ያዞራል ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም ይላሉ። በሌሎች አገራት ላይ ግን የምርጫ ውጤት ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ ዲሞክራቶች ወይስ ሪፐብሊካን . . . ? ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ብርሃኔ ቤካ የዋሺንግተን ዲሲ ነዋሪ ሰትሆን ከዲሞክራት ፓርቲ ጋር አብራ እንደምትሰራ ትናገራለች። ብርሃኔ፤ "ሰልጣን መልሰን ለመያዝ ትልቅ ቅስቀሳ እያደረግን ነው" ትላለች። ብርሃኔ የመምረጥ መብት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራት እጩዎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ ቅስቀሳ እያደረጉ መሁኑን በመጥቀስ አብዛኛው የመምረጥ መብት ያለው ስደተኛ ድጋፉን እየገለጸ ያለው ለጆ ባይደን ፓርቲ ነው ትላለች። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዲሞክራቱ ባራክ ኦባማ ለሥራ ጉብኝነት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሳ ዲሞክራቶች ምርጫውን ቢያሸንፉ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የተሻለ ግንኙነት እንደሚኖራቸው ትናገራለች። ሌላኛው ትውልድ ኢትዮጵያዊት እና ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር አብራ የምትሰራው ሴና ጂምጂሞ ይህ የአሜሪካ ምርጫ ለአሜሪካውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ወሳኝነት አለው ትላለች። ሴና ዲሞክራቶች በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ አሜሪካ ከአፍሪካ ጋርም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር የተሻለ ግነኙነት ነበራት ትላለች። የትራምፕ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር በስልጣን እንዲቆይ እድሉን የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግድብ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ታስረዳለች። የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 24 ይካሄዳል።
news-49457671
https://www.bbc.com/amharic/news-49457671
ናሳ ህዋ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል ተፈጸመ አለ
አን ማክሌን ጠፈርተኛ ናት። ከምድር ብዙ ርቀት ተጉዛ ህዋ ላይ የምትገኘው አን፤ በጠፈር ምርምር ታሪክ ህዋ ላይ ሳለች ወንጀል የሠራች የመጀመሪያዋ ግለሰብ መሆኗን ናሳ ይፋ አድርጓል።
ጠፈርተኛዋ ከፍቅር ጓደኛዋ ጋር ከተቃቃረች ቆየት ብሏል። ህዋ ላይ መሆኗ ታዲያ የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት ከመፈተሽ አላገዳትም። አን የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት መፈተሿን ብታምንም፤ "ምንም አላጠፋሁም" ማለቷን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። አን እና ስመር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 ትዳር መስርተው፤ 2018 ላይ ተለያይተዋል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? የቀድሞ ወዳጇ ስምር ዎርደን ጉዳዩን ለንግድ ኮሚሽን ሪፖርት ካደረገ በኋላ፤ ጠፈርተኛዋ ወደ መሬት ተመልሳለች። አን በጠበቃዋ በኩል ለኒዮርክ ታይምስ እንደተናገረችው፤ የስመርን የባንክ አካውንት የፈተሸችው አብረው ሳሉ በጋራ ያሳድጉት የነበረውን የስምር ልጅ የሚያስተዳድርበት በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ ነበር። ጠበቃዋ ረስቲ ሀርዲን "አንዳችም ጥፋት የለባትም" ሲሉ ተደምጠዋል። • በ2024 እቃና ሰው ጫኝ መንኮራኩር ወደጨረቃ ይላካል ተባለ ናሳ ጉዳዩን ከሁለቱም ግለሰቦች እያጣራ እንደሚገኝ ለኒውዮርክ ታይምስ ገልጿል። አን 2013 ላይ ናሳን ከመቀላቀሏ በፊት ለ800 ሰዓታት የጦር አውሮፕላን ወደ ኢራቅ አብርራለች። ናሳ ሙሉ በሙሉ ሴቶች ያሳተፈ የህዋ ጉዞ ለማድረግ ባቀደበት ወቅት ከተካተቱ ጠፈርተኞች አንዷ ናት። ሆኖም ናሳ "ለጠፈርተኞቹ የሚሆን ልብስ አላዘጋጀሁም" ብሎ ጉዞው መሰረዙ ይታወሳል። ለመሆኑ ህዋ ላይ ሕግ የሚተገበረው እንዴት ነው? የህዋ ማዕከሉ ባለቤቶች አሜሪካ፣ ሩስያ፣ አውሮፓ፣ ጃፓን እና ካናዳ ናቸው። አንድ ሰው ወንጀል ቢፈጽም የሚጠየቀው በአገሩ ሕግ ነው። • ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች አንድ አገር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውን ግለሰብ በሌላ አገር ሕግ ለመዳኘት ከወሰነች፤ ግለሰቡ ወደ ምድር እንዲመለስ ከተደረገ በኋላ ለፍርድ ይቀርባል። ከዚህ ቀደም ህዋ ላይ ወንጀል ተሠርቶ ስለማያውቅ የህዋ ሕግ ተግባራዊ የሚሆንበት እድል አልነበረም። ምናልባትም ቱሪስቶች ህዋን መጎብኘት ሲጀምሩ ሕጉን መተግበር ይጀመር ይሆናል።
41979679
https://www.bbc.com/amharic/41979679
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
የዚምባብዌ የጦር ኃላፊ የሃገሪቱ ገዢ ፓርቲን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ ካልሆነ ደግሞ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ አስጠነቀቁ።
የዚምባብዌ ጦር ኃላፊ ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90 ስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለጋዜጣዊ መግለጫ የቀረቡት ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የማንንም ስም አልጠቀሱም። የሙጋቤን ቦታ ሊተኩ ይችላሉ ሲባል የነበሩት ምናንጋግዋ ሸሽተው ሃገሪቱን ጥለው ወጥተዋል። አሁን የፕሬዝዳንት ሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን ለመተካት ቅድሚያውን አግኝተዋል። ምናንጋግዋንም "ጭንቅላቱ ሊደበደብ የሚገባ እባብ" ሲሉ ገልጸዋቸዋል። ባላቸው ብልህ አስተሳሳብ "አዞው" በሚል ስም የሚታወቁት ምናንጋግዋ "ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ያንተና የሚስትህ እንደፈለጋችሁ የምታደርጉት የግል ንብረታችሁ አይደለም" ሲሉ ሙጋቤን ተችተዋል። በጦሩ ዋና መስሪያ ቤት መግለጫ የሰጡት ጄነራል ቺዌንጋ፤ በነጻነት ትግሉ ውስጥ የነበሩ እና እንደምናንጋግዋን ያሉ ሰዎችን ማባረር በትዕግስት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። ግሬስ ሙጋቤና ምክትል ፕሬዝዳንት ኤመርሰን መናንጋግዋ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ሊሆኑ ይችላሉ ሲባል ነበር "በነጻነት ትግሉ ውስጥ ያለፉና እና የፓርቲው አባላት የሆኑት ሰዎች ላይ ያነጣጠረው የማባረር ስራ መቆም አለበት" ብለዋል። "ከአሁኑ ስራ ጀርባ ያሉ ሰዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ አብዮታችንን በተመለከተ ጦሩ ጣልቃ ከመግባት ወደኋላ አይልም" ብለዋል። ምናንጋግዋ ቀደም ሲል የመከላከያ እና የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ሙጋቤ በበኩላቸው "ጀነሬሽን 40" (የአርባዎቹ ትውልድ) የሚባለው የዚምባብዌ ወጣት ፖለቲከኞች ድጋፍ አላቸው። በፖለቲከኞች መካከል ያለው እሰጣ አገባ "ሃገሪቱ ላላፉት አምስት ዓመታት የተጨበጠ ዕድገት እንዳታስመዘግብ አድርጓታል" ሲሉ ጄነራል ቺዌንጋ ተናግረዋል። በችግሩ ምክንያት ዚምባብዌ "በገንዘብ እጥረት፣ ግሽበትና በሸቀጦች ዋጋ መጨመር" እንድትሰቃይ አድርጓታል።
54159838
https://www.bbc.com/amharic/54159838
ጎርፍ፡ በኢትዮጵያ በመቶ ዓመታት ይከሰታል በተባለ ጎርፍ ግማሽ ሚሊዮን ሰው ተጎዳ
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች መጎዳታቸውን መንግሥት ገለፀ።
የሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል እና የውሃ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለጋዜጠኞች በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ የዘንድሮ ክረምት ዝናብ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በቤቶችና መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈርያት ካሚል በሶስት ክልሎች እና 23 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ መከሰቱን ገልፀው፣ 580 ሺህ ዜጎች መጎዳታቸውንና ከእነዚህም ውስጥ 217 ሺህ የሚሆኑት ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። በ100 ዓመታት መካከል አንዴ የሚከሰት እንደ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለፃ ከሆነ ሰሞኑን የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከአዋሽ ወንዝ መነሻ እስከ መድረሻው ፣ በኦሞ ወንዝ፣ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሚገኙ እንደ ባቱ (ዝዋይ) እና መቂ ባሉ ከተሞች፣ በአባይ ተፋሰስ አካባቢ እና ጣና ሐይቅን ጀምሮ እስከ ሱዳን እንደዚሁም ደግሞ በባሮ ወንዝ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በመቶ አመታት ውስጥ አንዴ የሚከሰት መሆኑን ዶ/ር ስለሺ ጨምረው አስረድተዋል። በአዋሽ ወንዝ የተከሰተው ደግሞ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መሆኑን አክለዋል። ዘንድሮ ከባድ ዝናብ መተንበዩን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም አብራርተዋል። እንደምሳሌም በኦሮሚያና በአፋር ክልል ውስጥ 134 ኪሜትር ርዝመት ያለው የውሃ መውረጃ መስመር ጥገና መሰራቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም የተፋሰሱ ምክር ቤት ከክልሎች ፕሬዝዳንቶች እና ጉዳይ የሚመለከታቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ጋር መወያየታቸውንና ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ይናገራሉ። አደጋው የደረሰበት ስፍራ "በሄሊኮፕተር በመታገዝ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ሳይደርስ የተሳካ ስራ መስራት ተችሏል፤ ጎርፉ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በተወሰኑ ከብቶች ላይ አደጋ ደርሷል፤ የተወሰኑ ቤቶችም በጎርፍ ተውጠዋል" ብለዋል። ከነፍስ ማዳን ስራ ባሻገር ሰዎች ለችግር እንዳይጋለጡ ማድረግ እና የምግብና ሌሎች ቁሳቁስ አቅርቦቶች እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት የሰላም ሚኒስትሯ፣ ጎርፉ ካለፈ በኋላ የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አስከ ጳጉሜ 1/2012 ድረስ የተሰበሰበ መረጃን መሰረት ያደረገ
news-53756124
https://www.bbc.com/amharic/news-53756124
ኮሮናቫይረስ፡ "ከመንግሥት በላይ ለጤናዬ የሚጨነቅ አምላክ ስላለ ጭምብል አላጠልቅም" አሜሪካዊቷ ከመቶ ዓመታት በፊት
ከመንግሥት በላይ ለጤናዋ የሚጨነቅ አምላክ ስላለ ወረርሽኙን ለመከላከል ጭምብል እንደማታጠልቅ አንዲት አሜሪካዊት ሴት ተናገረች።
ይህ አባባል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የወጣውን ጭምብል ማጥለቅ እምቢተኝነት በማሳየት አሜሪካውያን ለተቃውሞ ከመውጣታቸው አንፃር በቅርቡ የተነሳ ይመስላል። ግን አይደለም ይሄንን የተናገረችው የዴንቨር ነዋሪ ከመቶ ዓመታት በፊት የታላቁ ኢንፍሉዌንዛ፣ ስፓኒሽ ፍሉ ወይም በኢትዮጵያ የኅዳር በሽታ ተብሎ የሚጠራውን ወረርሽኝ ለመከላከል የወጣን መመሪያ በመቃወም ነው። መቶ ዓመታት ወደፊት እንምጣና በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ከአርባ ግዛቶች በላይ ተጠቅተዋል። በየቀኑም አዳዲስ ሞቶችና በወረርሽኙ የሚጠቁ ሰዎችን ታሪክም መስማት የተለመደ ሆኗል። በወረርሽኙ ቀዳሚ በሆነችው አሜሪካ ከአምስት ሚሊዮኖች በላይ ሰዎች ተጠቅተዋል፤ ከ160 ሺዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። የጤና ባለሙያዎችም በተደጋጋሚ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እርምጃዎችን ተግባራዊ ልታደርግ ይገባል ካለበለዚያ ግን ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ ኋላ መመለስ ይከብዳልም ይላሉ። የቫይረሱን ስርጭትም ለመቆጣጠር አካላዊ ርቀትን መጠበቅና በሕዝባዊ ቦታዎች ላይ የፊት ጭምብል ማድረግ በአሁኑ ወቅት ዋነኛ መከላከያ መንገዶች ናቸው በሚልም በርካታዎች እየተገበሩት ይገኛሉ። ምንም እንኳን በርካታ አሜሪካውያን ጭምብል ማድረግን በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ቢቀበሉትም፤ በሕዝባዊ ቦታዎች ላይ ጭምብል አናደርግም የሚል እምቢተኝነት ተንፀባርቋል። የተለያዩ ግዛቶችም እነዚህን መመሪያዎች ማስከበር አዳግቷቸዋል። በርካታ ሰልፈኞች በስኮትስዴል፣ አሪዞና፣ ኦስቲን፣ ቴክሳስና ሌሎች ከተሞች ግዛቶች ያወጧቸውን ጭምብል የማጥለቅ መመሪያዎችን በመቃወም በከተሞቹ ከንቲባ ፅህፈት ቤቶች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ተቃዋሚዎች መብታችን እየተገፋ ነው የሚሉ ድምፆች በመበርታታቸውም ዋሽንግተንና ሰሜን ካሮላይና የመሳሰሉ ግዛቶች መመሪያዎቹን ተግባራዊ አናደርግም የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። እስቲ በታሪክን ወደኋላ እንጓዝና በጎርጎሳውያኑ 1918 የነበረውን ስፓኒሽ ፍሉ (የኅዳር በሽታ) ወረርሽኝን እንይ። ከመቶ ዓመታት በፊት ክትባትም ሆነ መድኃኒትም በሌለበት ሁኔታ የታላቁ ኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ እንዳይዛመት የተለያዩ መመሪያዎች መውጣት ነበረባቸው። ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት ተዘጉ፤ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ታገዱ፤ በጉንፋኑም የተጠቁት ሰዎች እንዲለዩና ተገልለውም ለብቻቸው እንዲቆዩ ተደረጉ። የዚህን ወረርሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር ዜጎች ጭምብል እንዲያጠልቁ ታዘዙ። ቁጣዎችን የቀሰቀው ለይቶ ማቆያው ሳይሆን ጭምብል አጥልቁ መባሉ ነበር። ስፓኒሽ ፍሉን አስመልክቶ የወጡ የቺካጎ ጋዜጦች ለአገራችሁ ስትሉ እድርጉት ወቅቱ ጥቅምት አጋማሽ 1918 ነበር፤ በሰሜን ምሥራቅ የአሜሪካ ግዛቶች አሰቃቂ የሚባል ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሆኑ የመንግሥት የጤና ኃላፊዎች ሁሉም ዜጎች አፍና አፍንጫቸውን በጭምብል እንዲሸፍኑ ጠየቁ። ቀይ መስቀልም እንዲሁ ዜጎች ጭምብል እንዲያጠልቁና በቀላሉም በቤታቸው ውስጥ ካሉ ጨርቆች፣ ክሮችም ሆነ ፋሻዎች ጭምብል አስራርንም ለማበረታት በጋዜጦች ላይ ማስታወቂያዎችን ያወጣ ነበር። ካሊፎርኒያ፣ ኡታህና ዋሽንግተንን የመሳሰሉ ግዛት ጤና ማዕከላት ደግሞ የራሳቸው ጅምሮች ነበራቸው። በመላው አገሪቷም ጭምብል ማጥለቅ የዜግነት ግዴታ መሆኑን የሚያትቱ ፖስተሮች መለጠፍ ጀመሩ። በተለይም የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በጦርነቱ ወቅት ይለፈፉ የነበሩ ፕሮፓጋንዳዎችም በዚህም ወቅት ማኅበራዊ ኃላፊነትና አርበኝነት ጋር በማያያዝም ቀጠሉ። የሳንፍራንሲስኮ ከንቲባ ጄምስ ሮልፍም "ለአገር ማሰብ፣ አርበኝነት፣ ራስንና ሌሎችን ለመጠበቅ" ጭምብል ማድረግ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው አሉ። የኦክላንድ ከንቲባ ጆን ዴቪም እንዲሁ "ምንም እንኳን የተለያዩ እምነቶች ቢኖሩንም አርበኝነትና ሌሎችን ማስቀደም ማለት ዜጎችን መጠበቅ የሚቻለው ጭምብልን ስናደርግ ነው" በማለት መንፈስን የሚያነቃቃ መልዕክታቸውን አስተላለፉ። መንገድ ጠራጊ በኒውዮርክ ጎዳና ላይ ጭምብል አጥልቀው መመሪያዎችን ማፅደቅ ፈታኝ ሲሆን የጤና ኃላፊዎች የሕዝቡ ባህርይ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ፈታኝ እንደሆነ ተረድተውታል፤ በተለይም ጭምብል ማጥለቅ ምቾት ይነሳናልም በመባሉ ማሳመን ፈታኝ ሆኖ አግኝተውታል። አርበኝነት፣ አገር፣ ብሔራዊ ኃላፊነት የሚሉ አገራዊ ስሜቶችን ለማነቃቃት የሚተላለፉ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ብዙ የሚያስኬዱ አልሆኑም። ለዚያም ነው የካሊፎርኒያው ባለስልጣን "ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲባል መገደድ አለባቸው" ያሉት። ቀይ መስቀልም እንዲሁ "ወንድ፣ ሴት፣ ልጅ፣ ማንኛውም ጭምብል የማያጠልቅ አደገኛና ለሰዎች የማያስቡ ናቸው" በማለት ጭምብል የማያጠልቁ ሰዎችን በግልፅ በማውገዝ አስተላለፈ። በርካታ ግዛቶች በተለይም በአሜሪካ በምዕራብ የሚገኙ ግዛቶች ጭምብል ማጥለቅን አስገዳጅ አድርገውትም ነበር። አንዳንዶች አጠር ላለ ጊዜ እንዲታሰሩ እንዲሁም ከ5 እስከ 200 ዶላርም የገንዘብ ቅጣትም የተቀጡ በርካቶች ናቸው። ሆኖም መመሪያዎቹ በአወዛጋቢነታቸው ቀጠሉ። ለምሳሌ የሳክራሜንቶ የጤና ዳይሬክተር የከተማዋ ኃላፊዎች መመሪያውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ መጠየቅን ጨምሮ፣ መለማመጥና መማፀን ነበረባቸው። በሎስ አንጀለስ መመሪያው ሊፀድቅ አልቻለም። በፖርትላንድም ረቂቁ ከፍተኛ ክርክርና ውዝግብም አስነስቷል፤ አንደኛው የከተማዋ ምክር ቤት አባልም "ጨቋኝና ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው" ሲሉ ወርፈውታል። "በምንም ተአምር እንደ ውሻ አያስገድዱኘም" አሉ። እንዳሉትም መመሪያው ሳይሳካ ቀረ። የኡታህ የጤና ኃላፊዎችም በጭምብል አስፈላጊነት ከተወያዩ በኋላ አላስፈላጊ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል። ለዚህም ምክንያታቸው ዜጎች ሐሰተኛ ደኅንነት ስለሚሰማቸውና ባዶ ተስፋም ስለሚሰጣቸው ከመጠንቀቅ ችላ ይላሉ ብለው ነው። ወረርሽኙ ሁለተኛ ዙር እንደገና ሲያገረሽም ኦክላንድ ጭምብል ማጥለቅ ላይ ሌላ ክርክር ጀመረች። ከንቲባዋ በሌላ ግዛት ውስጥ ጭምብል ሳያደርጉ ተገኝተው መታሰራቸው በጣም አበሳጭቷቸው የነበረ ሲሆን በኦክላንድም ይህ እንዳይደገም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራከሩ። ይሄንን ክርክር ሲታዘቡ የቆዩ አንድ ታዋቂ ዶክተር በወቅቱም "በዋሻ ይኖር የነበረ ግለሰብ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎችን ቢያይ እብድ ናቸው ይለናል" ብለዋል። መመሪያዎችን ተግባራዊ የማድግ ፈተና ጭምብል የማጥለቅ መመሪያዎች ከላይ ቢታዘዙም ነዋሪዎች ግን ሕጎቹን አናከብርም በማለት መጣሳቸው አልቀረም። የገበያ መደብሮች ጭምብል ያላጠለቁ ደንበኞችን መልሱ ቢባሉም ከመግባት አላገዷቸውም። ሠራተኞችም ጭምብል አጥልቆ መስራት አይመችም በማለት ቅሬታዎችን ያሰሙ ነበር። የዴንቨር ነዋሪ የሆነች የሽያጭ ሠራተኛም "አፍንጫዋ እየደነዘዘ" በመሆኑ ጭምብል አላጠልቅም ብላ እምቢተኝነቷን አሳየች። ሌላኛዋ ደግሞ "ከዴንቨር የጤና ቢሮ በላይ ስለ ደኅንነቷ የሚጨነቅ አምላክ" ስላለ አፏንም ሆነ አፍንጫዋን እንደማትሸፍን ተናገረች። የወቅቱ ጋዜጦች እንደዘገቡት ምንም እንኳን መመሪያው ቢፀድቅም "ሕዝቡ እምቢተኝነቱን በማሳየት ችላ ብሎታል፤ እንዲያውም ትዕዛዙ ማፌዣና መቀለጃ ሆኗል" ብሏል። እናም ሕጉ ተሻሽሎ ለባቡርና ለአውቶብስ አሽከርካሪዎች ብቻ ጭምብል እንዲያደርጉ ቢታዘዝም እነሱም የሥራ ማቆም አድማ እናካሂዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ከተማዋ ጭምብል የማድረግ መመሪያዋን ልታላላ ተገዳለች። ዴንቨር የሕዝቡን ደኅንነትና ጤንነት የሚያስጠብቅ መመሪያዎች ሳይኖሯትም ወረርሽኙን ተጋፈጠችው። በሲያትል ግን የአውቶብስ አሽከርካሪዎች ጭምብል ያላጠለቁ ተጓዦችን አናሳፍርም አሉ። በተለያዩ ግዛቶች መመሪያውን የሚጥሱ ከመብዛታቸው የተነሳ በኦክላንድ የሚገኙ ባለስልጣናት 300 የቀድሞ ወታደሮችን በበጎ ፈቃደኝነት አሰማርተው ነበር። እነዚህ ወታደሮች ሕግ የሚጥሱ ሰዎችን ስምና አድራሻ በመመዝገብ እንዲቀጡ ለባለስልጣናት ይሰጡ ነበር። በሳክራሜንቶ ጭምብል የማጥለቅ መመሪያው ሲፀድቅ የፖሊስ ኃላፊው "ወደየጎዳናዎቹ ውጡና ጭምብል ያላደረጉ ሰዎችን ስታዩ ይዛችኋቸው ኑ" ብለው ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ። በሃያ ደቂቃ ውስጥም ፖሊስ ጣቢያው ጥፋተኛ በተባሉት ሰዎች ከአፍ አስከ ገደፉ ተሞላ። በሳንፍራንሲስኮም መመሪያውን በመተላለፍ የታሰሩ ዜጎች በዝተው የፖሊስ ኃላፊው እስር ቤቶቹ ሞልተዋል በማለት ለከተማው አስተዳዳሪዎች ማሳሰቢያ ለመስጠት ተገደው ነበር። ዳኞችና ኃላፊዎችም ከሰዓት እላፊ ውጪ አምሽተው መስራት፣ ቅዳሜና እሁድንም ያለ እረፍት በመስራት መመሪያ የተላለፉ ሰዎች ላይ ብይን ይሰጡ ነበር። ተቃውሞ ጭምብል ሳያጠልቁ የተያዙት በርካቶቹ ሳይነቃብን የእለት ሥራችንን እናከናውናለን ያሉ ናቸው። ሆኖም በሳንፍራንሲስኮ ጭምብል ሳያጠልቁ የሚወጡ ሰዎች ከመበርከታቸው ብዛት የተነሳ ሌላ ዙር ወረርሽኘ ለመከሰቱ መንስኤ ሆነ። የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በጎርጎሳውያኑ ጥር 1919 ጭምብል እንዲደረግ ሌላ ትዕዛዝ ለማውጣት ተገደዱ። ሕዝቡም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ፣ ነፃነትን የሚጋፋና መብትን የሚጥስ ነው በማለት አወገዘው። በጥር 25/1919 ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የፀረ-ጭምብል ከፍተኛ ተቃውሞን አካሄዱ። በዚህ ተቃውሞ ላይ ከተሳተፉት መካከል ታዋቂ የህክምና ዶክተሮች እንዲሁም የሳንፍራንሲስኮ የጤና ቁጥጥር ቦርድ አባላት ይገኙበታል። ትናንትናና ዛሬ ዋሽንግተን በ1918 በ1918 የነበረውን ጭምብል ውጤታማነት በአሁኑ ወቅት ማወቅ አዳጋች ነው። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ጭምብሎች ተሻሽለው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መግታት እንደሚችሉም ማረጋገጥ ተችሏል። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ በቀጠለበት ወቅት አሜሪካውያን የፊት ጭምብል ማድረጋቸው አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው። ለዚህም ስር የሰደደ የግለሰብ ነፃነት፣ በጭምብሎች አደራረግ ላይ ግልፅ ያለ መልዕክት አለመኖር፣ የአመራር ችግር እንዲሁም ስለ ጭምብሎች የሚወሩ መሰረት የሌላቸው መረጃዎች ምክንያት ናቸው ተብሏል። በአሁኑ ወቅትም እየተከሰተ ባለው ቀውስ ጭምብል ማድረግ አስገዳጅ ሊሆን በተገባ ነበር። በ1918ቱም 675 ሺህ አሜሪካውያን ህይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁንም ህይወታቸውን እያጡ ነው። ታሪክ ራሱን እየደገመ ይሆን?
news-45937014
https://www.bbc.com/amharic/news-45937014
ስለ ሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቀው
የሳዑዲ ዜግነት ያለው ዝነኛው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ ቱርክ ኢስታንቡል ወደ ሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ገብቶ ደብዛው ከጠፋ ሁለት ሳምንታት አልፈው ነበር።
በወቅቱ የቱርክ ባለስልጣናት በሳዑዲ ሰዎች ስለመገደሉ የድምጽ ማስረጃ አለን ብለዋል ። ሳዑዲ ግን በተደጋጋሚ ጀማል ወደ ቆንስላው ከገባ ከደቂቃዎች በኋላ ቆንስላውን ለቅቆ ወጥቷል ብትልም አሁን ግን መገደሉን አምናለች። • የሳዑዲ እገዳ ለየመን ጥፋት ነው • የአውሮፓ አገራት የተገደለው የሳዑዲ ጋዜጠኛ ምርመራ እንዲቀጥል አሳሰቡ ሳዑዲ ጀማል መገደሉን ከማመኗ በፊት የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በቆንስላው ውስጥ በነበሩ ሰዎች እና ጀማል መካከል በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ሊሞት ችሏል ብለው ነበር። ስለ ጀማል ኻሾጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው። ጀማል ኻሾጂ ማን ነበር? ጀማል በሳዑዲ ዝነኛ ጋዜጠኛ ነበር፤ የሶቪየት ሕብረት የአፍጋኒስታን ወረራን በዝርዝር ዘግቧል። እንደ ኦሳማ ቢን ላድን ከመሳሰሉ ግለሰቦች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ለሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ የቅርብ ሰው ነበር፤ የሳዑዲ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ሆኖም ሰርቷል። ባለፈው ዓመት ግን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሃገር ጥሎ ወደ አሜሪካ ተሰደደ። አሜሪካም ሆኖ የዋሽንግተን ፖስት አምደኛ ሆነ። በጽሑፎቹ የሳዑዲ አረቢያውን ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማንን ይተች ነበር። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ • "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው ዲፕሎማሲ ቀለም አልባ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ እንዳስገባው በርካቶች ይናገራሉ። ወደ ሳዑዲ ቆንስላ ለምን አቀና? ጀማል ወደ ቆንስላው የሄደው ከቀድሞ ሚስቱ ጋር መፋታቱ የሚያረጋገጥ ዶሴ ለማግኘት፣ ከዚያም ቱርካዊት እጮኛውን ለማግባት በእለተ አርብ ሴብቴምበር 28 በቆንስላው ተገኘ። በቆንስላው ያሉ ሰዎች ግን ለማክሰኞ ኦክቶበር 2 ቀጠሩት። ''ቱርክ ውስጥ በሚገኝ የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ ምንም ሊያደርጉኝ አይችሉም ብሎ ገምቶ ነበር'' ስትል እጮኛው ለዋሽንግተን ፖስት ጽፋለች። ''ጀማል ምንም እንደማይገጥመው እርግጠኛ ነበር'' ማክሰኞ ሴብቴምበር 2 ከቀጠሮ ሰዓት 15 ደቂቃ ቀደም ብሎ ወደ ቆንስላው ሲገባ በተንቀሳቃሽ ምስል ይታያል። ጀማል ወደ ቆንስላው ከመግባቱ በፊት ለእጮኛው ሁለት ስልክ ቁጥሮች ሰጥቷት ካልተመለስኩ ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይር ኤርዶጋን አማካሪዎች ደውለሽ ንገሪያቸው ብሏት ነበር። እጮኛው ሳትታክት ለ10 ስዓታት በቆንስላው በር ላይ ጠበቀችው። በነጋታውም ወደ ቆንስላው ሄዳ ጠበቀችው ጀማል ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። የጀማል እጮኛ ሳትታክት ለ10 ስዓታት በቆንስላው በር ላይ ጠብቃው ነበር። በጉዳዩ ላይ የሳዑዲ አረቢያ ምላሽ ምን ነበር? ለሁለት ሳምንታት ያክል ሳዑዲ በጀማል እጣ ፈንታ ላይ የማውቀው ነገር የለም ስትል ቆይታ ነበር። ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ለብሉምበርግ ሲናገሩ ''ጀማል ላይ ስለሆነው ነገር ለማወቅ ጓጉችያለሁ። ከደቂቃዎች በኋላ ወይም ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ ጉዳዩን ጨርሶ ወጥቷል'' ብለው ነበር። ''ምንም የምንደብቀው ነገር የለም'' ሲሉም ተደምጠዋል። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የሳዑዲ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛው በቆንስላው ውስጥ በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ለሞት ተዳርጓል ሲል ዘገበ። ብሔራዊ የቴሌቪዝን ጣቢያው ጨምሮ እንደዘገበው ከጀማል ግድያ ጋር በተያያዘ 18 የሳዑዲ ዜጎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በኢስታንቡል የሚገኘው የሳዑዲ ቀንጽላ ቱርክ ጀማል ላይ ምን ደረሰ አለች? የቱርክ ባለስልጣናት ጀማል በሳዑዲ የጸጥታ ኃይሎች በቆንጽላ ውስጥ እንዲሰቃይ ተደርጎ ተገድሏል፤ ከዚያም አስክሬኑ በሰዋራ ስፍራ ተጥሏል ይላሉ። ቱርኮች ይህን የሚያረጋግጥ የቪዲዮ እና የድምጽ ማስረጃ አለን ይላሉ። ይሁን እንጂ የቪዲዮ እና የድምጽ መረጃዎቹ ለህዝብ ይፋ አልሆኑም። ሳብሃ የተሰኘ የቱርክ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ በቆንጽላው ውስጥ የሚሰሩ የቱርክ ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች በጀማል ቀጠሮ ዕለት በፍጥነት ቆንጽላውን ጥለው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። በጀማል ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉት የሳዑዲ የጸጥታ ኃይል አባላት እነማን ናቸው? የቱርክ መገናኛ ብዙሃን 15 አባላት ያሉት የሳዑዲ ቡድን የጀማል ደብዛ የጠፋ ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢስታንቡል ቱርክ በግል አውሮፕላን መጥተዋል። ከ15 ሰዎች መካከል ማህር ሙትሬብ የተባለው ግለሰብ ሎንዶን በሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ የጸጥታ እና ደህንነት አባል መሆኑን ቢቢሲ አረጋግጧል። አራት ግለሰቦች ደግሞ ከልዑል አልጋ ወራሹ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጋር ቅርርብ አላቸው። የቱርክ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት ከሆነ 15ቱ ግለሰቦች አጥንት መቁረጫ መጋዝ ይዘው ነው የመጡት። ከግለሰቦቹም መካከል አንዱ የሬሳ ምርመራ ባለሙያ ነው። የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ይዘውት የወጡት ቪዲዮ እንደሚያሳየው ከጀማል የቀጠሮ ሰዓት አንድ ሰዓት ቀድም ብሎ የቡድኑ አባላት መኪና እያሽከረከሩ ወደ ቆንስላው ሲያመሩ ያሳያል። ከዚያም የቡድን አባላቱ ለሁለት ተከፍለው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተመልሰው ሄደዋል። ምረመራው እንዴት እየሄደ ነው? ጀማል ከተሰወረ ከ13 ቀናት በኋላ የቱርክ መርማሪዎች ወደ ቆንስላው እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። የመርማሪ ቡድን አባላቱ ወደ ቆንስላው ከመግባታቸው በፊት የሳዑዲ ባለስልጣናት እና የጽዳት ሰራተኞች ቀድመው ገብተው ነበር። በቆንጽላው አቅራቢያ በሚገኙ ወንዞችና ጫካዎች አቅራቢያ ምረመራዎች ተደርገዋል። ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ ወደነዚህ ስፍራዎች ከቆንጽላው የተነሱ መኪኖች ሲያቀኑ ታይተዋል። ''ጀማል ተገድሏል'' ዛሬ ጠዋት ሳዑዲ ጀማል ስለመገደሉ አምናለች። የሳዑዲ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አደል አል-ጁቤር ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ ''ከፍተኛ ስህተት ተፈጽሟል'' ካሉ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ የልዑል አልጋ ወራሹ እጅ እንደሌለበት ተናግረዋል። የተፈጸመውን ሁሉ ለማጣራት ቁርጠኛ ነን። በጉደዩ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ እንቀጣለን'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሳዑዲ የሚተቹ ሁሉ እምጥ ይግቡ እስምጥ የማይታወቀው ለምንድን ነው?
news-56206404
https://www.bbc.com/amharic/news-56206404
ጉቱ አበራ-"እወድሻለሁ ብሎ መንገር ሳይሆን ልክ እንደ ዓመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለኩት"
ሀዋነዋ (Hawanawa) ለወራት መልካም ዜና ለራቀው የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ የተወሰነም ቢሆን እስትፋስ የሰጠ ሙዚቃ ነበር። የሙዚቃው ቪዲዮ በተለቀቀ በሰአታት ውስጥ ነበር የብዙዎችን ቀልብ የገዛው። እንዲህ ያሉ አስተያየቶችን መቀበሉን ሙዚቀኛውም ይናገራል።
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ነገር ጥሩ እንዳልሆነ እናውቃለን። አንዳንዴ ግን እረፍት ያስፈልጋል። አንዳንዶቹ በዚህ ሙዚቃ እረፍት እናደርጋለን፤ ከዛ ተመልሰን ወደ ጭንቀታችን እንመለሳለን ይሉኛል (ሳቅ)›› ይላል ጉቱ። ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በአዲስ ስራው ብቅ ያለው ጉቱ አበራ በኦሮምኛ ያቀነቀነው ሙዚቃ ቋንቋውን በማይናገሩ አድማጮች ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነትን አትርፎለታል። ሀዋነዋ (Hawanawa) ለህይወት ዘመኔ እፈለግሻለሁ እንደማለት ነው። ግጥሙም ዜማውንም ራሱ ጉቱ ጽፎታል። ነገር ግን ሙዚቃውን ያቀናበረችው ሚራ ቲሩቼልቫም (Mira Thiruchelvam) ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራት። ጉቱ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ለሚራ እውቅናውን ሰጥቷል። ጉቱ ማነው? የተወለደው በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ውስጥ ነው። የ16 አመት ታዳጊ ሆኖ ነበር ቤተሰቦቹ በስደት ወደ ሚኖሩባት ኖርዌይ ከ 12 አመት በፊት የሄደው። ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍተኛ የሙዚቃ ፍላጎት እንደነበረው የሚናገረው ጉቱ ኖርዌይ ከሄደ በኋላ ወደ ጥሩ ሙዚቀኞች እየሄደ ሙዚቃን በመማር አዲስ ነገር ለመፍጠር እና በተለይም የፊውዥን ሙዚቃዎች ላይ አተኩሮ መስራት ጀመረ። በሶሻል ወርክ እና አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘው ጉቱ በሞያው ሶሻል ወርከር ነው። የትምርት ዝግጅቱም ለሙዚቃ ስራው እገዛ እንዳደረገለት ይናገራል፡፡ ‹‹ስራዬ እኮ እሱ ነው፤ ወደ ሙዚቃ ግን ጠቅልዬ መግባቴ ነው መሰለኝ አሁንስ (ሳቅ)። ከሆነልኝማ ሙዚቃውን እመርጣለሁ። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፤ እስከመጨረሻው ሙዚቃን እሰራለሁ›. ሲል ይናገራል። "በኖርዌይ የኦሮሞን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ለማምጣት ጥረት ማድረግ ጀመርኩኝ፤ በዚህም ምክንያት የተለያዩ አገር ሙዚቃዎችን በመጨማመር የሚሰራ ፋርገስ ፒል (Fargespill) የተሰኘ የሙዚቃ ባንድ አባል ሆንኩኝ።" የሚለው ጉቱ ከዚህ በኋላ የኦሮምኛ እና የምዕራብውያን ሙዚቃ በመቀላቀል መድረክ ላይ ማቅረብ መጀመሩን ይናገራል። ኦሮሚያ በሎ (ሰፊዋ ኦሮሚያ) የሚለው ሙዚቃ ከበርካታ ሰዎች ጋር እንዳስተዋወቀውም ለቢቢሲ ገልጿል። ከዚህም የተነሳ በኖርዌይ ንጉስና ንግሥቱቷ ፊት ለፊት ተጋብዞ መጫወቱንም ይናገራል። ኦሮሚያ በሎ የሚለው ሙዚቃ ቅድሚያ የተጫወተው ሌላ ድምጻዊ ሲሆን፣ ኦሮምኛ የማይችሉ የባንዱ አባላትን በማሰልጠን በተለያዩ መድረኮች ላይ በጋራ ስራውን አቅርቧል። ጉቱ አበራ የተሰኘ የሙዚቃ ባንድንም ማቋቋሙን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል። ጉቱ ስለ አዲሱ ሙዚቃው አጠር ያለ ቆይታ ከበቢሲ ጋር አድርጎ ነበር፡፡ ቢቢሲ- ሀዋነዋ የተሰኘው ነጠላ ቪዲዮህ ከወጣ ገና አንድ ሳምንት አለሞላውም፣ ነግር ግን በኢትዮጵያ ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እጅግ ተወዶልሃል። ጠብቀህው ነበር? ጉቱ አበራ- ይህ ስራዬ ለየት ብሎ የተሰራ ነው። ሀዋናዋም ለመያዝ የሚቀል እና ሳቢ መጠሪያ ነው። ሙዚቃው አዲስ ስለሆነ ነው መሰለኝ ብዙ ሰዎች መልዕክቶችን እየላኩልኝ ነው። በርታ ጥሩ ነው እያሉኝ ነው። ይህ ሙዚቃ የተወሰነ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ ስለመጣ ሰዎች ዝግጁ አይሆኑም በሚል ምናልባት ተደማጭነቱ ላይ ጫና ያመጣ ይሆን ብዬ ሰግቼ ነበር። ግን ደግሞ ሙዚቃው በጥሩ ጥራት መሰራቱን ደግሞ አውቃለሁ። በቀጥታ መሳሪያዎች ነው የተቀረፀው። ስኬሉም ትንሽ ይለያል። የእኛ አገር ሙዚቃ ፔንታ ቶኒክ ነው፣ ይሄ ደግሞ በተለይ ኳየሮቹ በሌላ ስኬል ነው የገቡት። ስለዚህ በተለይ ከወጣቱ ትውልድ አድማጭ አገኛለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን እንደዚህ ቶሎ ብዙ ተቀባይ አገኛለሁ ብዬ ግን አልጠበኩም። ስለዚህ ይሄንን ያህል ባልጠብቅም የተወሰነ ግምት ግን ነበረኝ። በዚህ ሙዚቃ ደስ ያለኝ ነገር ቢኖር እስከዛሬ መልክት ከሚልኩልኝ አድናቂዎች ውጪ አዳዲስ አድናቂዎች አፍርቻለሁ። ይህ ሙዚቃ በኦሮምኛም ሆነ በአማርኛ ከሚዘፈኑ ዘፈኖች ለየት ያለ መልክ በመያዙ ምክንያት ይመስለኛል። ከመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ መልክቶች እየደረሱኝ ነው። ጥሩ ነው ብለውኛል። ቢቢሲ- በኦሮምኛ ሙዚቃዎች ውስጥ የፍቅር ዘፈኖች ብዙ ግዜ በውስጣቸው ሰም እና ወርቅ አላቸው፤ አንዳንዴ ስለ አገር ወይም ፖለቲካዊ መልክት ይይዛሉ። ሃዋነዋ ሰምና ወርቅ ይኖረው ይሆን? ጉቱ አበራ-ይህ ሙዚቃ በውስጡ የተለየ መልክት አልያዘም፣ በግልፅ ከሚገልፀው የፍቅር መልክት ውጪ። እኔ ተወልጄ ያደኩት ወለጋ ውስጥ ነው። ይሄን ዘፈን ደግሞ ለሸዋ ልጅ ነው የዘፈንኩት። የጥበብ ስራው ላይ ትኩረት አድርጌአለሁ። ሁሉም ሰው የኦሮምኛ ሙዚቃን እንዲያዳምጥ እና ጥበባችን ከፍ እንዲል የፈለኩት እንጂ ምንም ፖለቲካዊ መልዕክት የለውም። ቢቢሲ- የሙዚቃ ቪዲዮውም ሆነ ሙዚቃው ከኦሮሞ እና ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በተጨማሪ የአፍሪካ መልክ የሚሰጡ ነገሮች አሉት። በተጨማሪም ወደ ኋላ አስርተ አመታትን ሄደህ ከባህል ባሻገርም የዘመን ህብር ፈጥረሃል። እንዴት ይህንን ለመፍጠር አሰብክ? ጉቱ አበራ- ሙዚቃው እንደሰማሽው ተለዋዋጭ (ዳይናሚክ) ነው። መጀመሪያ ሲገባ በቤዝ ጌታር እና በፕርኪሽን እጀምራለሁ፤ መጨረሻ ላይ ደግሞ በጣም ሞቅ ብሎ ያልቃል። ቪዲዮውም እሱን ነው የሚመስለው። መጀመሪያ እኔ እና እሷ ቀስ ብለን ሳይክል እየነዳን እንሄዳለን ከዛ ጭፈራውም ከሙዚቃው ጋር ከፍ ይላል። ስለዚህ የሙዚቃ ቪዲዮው ታስቦበት ነው የተሰራው። ሌላው በቀጥታ የሙዚቃ መሳሪያ ስለተሰራ ድምጹ ተፈጥሮአዊ ነው። ስለዘመን ስናወራ ደግሞ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ 1970 እና 1980 ዎቹ በጣም ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ነበር። እኔ በተለይም የዚያን ግዜ የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች በበለጠ እወዳለሁ፤ አዳምጣለሁ። እናም ወደዚያ መመለስ እና ከዚያ መጀመር ነው የፈለኩት። አሁን ያለው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያኔ እንደነበረው ብቃት ላይ አይደለም። በአሊ ቢራ እና አለማየሁ እሸቴ ጊዜ ኢትዮ ጃዝ በጣም ያደገበት ወቅት ነበር። አሁንም እነርሱ ትልቅ ናቸው፤ አከብራቸዋለሁ። እኔ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ገና ያልተነካ ነው ብዬ ነው የማምነው። በተለይ ከጥሩ ባለሞያዎች ጋር ቢሰራበት አዲስ ነገር መስራት ይቻላል። ስለዚህ ነው በኔም ስራ በዚህ መልኩ አዲስ ነገር መስራት የፈለግነው፣ ደግሞም አድርገነዋል። በተጨማሪም አቀናባሪዋ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ታጠናለች እና ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ያላት እውቀት በጣም ጥልቅ ነው። ስለዚህ ለእርሷ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከሌሎች አይነት ሙዚቃዎች ጋር ማቀናበር አልከበዳትም። ሀዋነዋ ሙዚቃው ጃዝ፣ ብሉዝ፣ ራያ/ወሎ፣ አፍሮ፣ ኢቺሳ፣ ጌሎ፣ ሸጎዬ ምቶች የተቀላቀለበት ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን ችክችካ እና አፍሮ ቢትስም አሉበት። ስለዚህ አንዱን ሪትም የማይወድ ቢያንስ ሌላውን እንዲወድ አድርገን ነው የቀረጽነው። እርሷ እንደ ባለሞያ ስታቀናብር እኔ አብሬያት ስለበርኩ በምፈልገው መልኩ ለመቅረፅ ችያለሁ። ስለዚህ ያ ለሙዚቃው ጣዕም የራሱ አበርክቶ እንዲኖረው አድርጓል። ቢቢሲ- የሙዚቃ ቪዲዮህ የመብራት አጠቃቀሙ በጣም ፈካ ያለ ነው። ቅድም አንተም እንዳለከው የዘፈንህን ግጥም የማይሰሙ ሰዎችም ሙዚቃህን ወደውልሃል። የሃዋነዋ ግጥም ክሊፑ ላይ ከተጠቀምከው የመብራት ሴቲንግ ጋር ይገናኛል? ጉቱ አበራ- የኔ ፍላጎት ታሪኩን መንገር ብቻ አይደለም። ስሜቱን መፍጠር ላይ ነበር ትኩረት ያደረኩት። ሰዎች ሙዚቃውን ሲሰሙ ደስተኛ ይሆናሉ፣ ቀለማቱን እንዲሁም የተቀረፀበት ቦታ የሚፈጥረው ስሜት አለ። የሙዚቃ ቪዲዮ ሲሰራ ልክ እንደ ፊልም ታሪኩን መንገር አይደለም ዋና አላማው፣ ሰዎች ስሜቱ እንዲሰማቸው አድርጎ መፍጠር ነው። እኔም ልክ እንደ አመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለግኩት። በአጠቃላይ ግጥሙ የፍቅር ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው እወድሻለሁ ብሎ መንገር ሳይሆን ልክ እንደ አመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለኩት። አድማጮቼ ስሜቱን ወድደውታል ብዬ አስባለሁ። እንደ መሰናበቻ ጉቱ አድናቂዎቹን ‹‹በጣም አመሰግናለሁ። አዳዲስ ሙዚቃ በቅርቡ ሰርቼ ለመመለስ እሞክራለሁ። ያላችሁኝን መልካም ነግሮች በሙሉ አከብራለሁ። እናም ታትሬ እንደምሰራ ቃል እገባላችኋለሁ። በቅርቡ ደግሞ በመድረክ ላይ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ›› ሲል አመስግኗችኋል። አክሎም ‹‹አልበሜ በ ያዝነው የፈረንጆች አመት መጨረሻ፤ ካልሆነ ደግሞ 2022 መጀመሪያ ይወጣል ብዬ አስባለሁ። ከዛ በፊት አንድ ነጠላ ዜማ መስራቴ ግን አይቀርም›› ብሏል።
news-55329587
https://www.bbc.com/amharic/news-55329587
ኮሮናቫይረስ፡ በኬንያ የመጀመሪያው ዙር ክትባት በጥር ወር ይደርሳል ተባለ
ኬንያ የመጀመሪያው ዙር የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት በሚቀጥለው፣ ጥር ወር እንደሚደርሳት አስታውቃለች።
የጤና ሚኒስትሩ ሙታይ ካግዌም ይህንኑ ማሳወቃውን የኔሽን አፍሪካ ጋዜጣ ዘግቧል። ሚኒስትሩ የኦክስፎርዱ አስትራዜኔካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ለህዝቡ እናቀርባለን ብለዋል። አስትራዜኑካ የሚባለው ክትባት ከሞደርናና ፋይዘር ከተሰኙት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባቶች ጋር ሲነፃፀር ዋጋው ረከስ እንደሚልም ተናግረዋል። ነገር ግን የኦክስፎርዱ ክትባት በየትኛውም አገር እስካሁን እውቅና አላገኘም። ኬንያ በግሎባል ቫክሲን አሊያንስ ኢንሺዬትቭ በተባለው ድርጅት አማካኝነት 24 ሚሊዮን መጠን ብልቃጥ ክትባቶችን ያዘዘችው ባለፈው ሳምንት ነው። ይህም መጠን ከአገሪቷ ህዝብ መካከል 20 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል። የኬንያ መንግሥት 10 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ (89 ሚሊየን ዶላር) ገንዘብ ለክትባቱ እንዳወጣም ተገልጿል። ክትባቱ ሲደርስ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤና ባለሙያ ሰራተኞች፣ ፖሊሶች፣ አረጋውያንና መምህራን ይሆናሉ። ከዚህም በተጨማሪ ህዝብ በተጨናነቀበት አካባቢ የሚኖሩና እንዲሁም ከአንድ ወይም ሁለት በላይ ተደራራቢ ህመም ያለባቸውም እንዲሁ የመጀመሪያው ዙር ክትባት ተጠቃሚም ይሆናሉ ተብሏል። ኢትዮጵያም ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት ዓይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ አስረድተዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በአፍሪካ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ117 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 800 በላይም ህይወታቸውን አጥተዋል። ከ72 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪዎችም በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ሕይወታቸውን ማጣታቸው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል።
news-51396025
https://www.bbc.com/amharic/news-51396025
ኮሮናቫይረስ፡ "ጭንቀት ላይ ነን" ኢትዮጵያዊቷ ከቻይና ውሃን
በቻይናዋ የዉሃን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ዘርፍ ትምህርቷን አጠናቃ፣ ለአንድ ሴሚስተር ማንዳሪን ቋንቋ ለመማር በሚል ቆይታዋን ያስረዘመችው ሶልያና አረጋዊ፤ ወደ አገሯ የመመለሻ ቀኗን የቆረጠችው በዚሁ ወር ነበር።
ለአራት ዓመታት ያህል በታሪካዊዋ በጎርጎሳውያኑ 1893 የኪንግ ስርወ መንግሥትን ይመራ በነበረው ዛንግ ዚዶንግ የተመሰረተችው፣ ጥንታዊቷ የቻይና ዚኪያንግ ተቋም የአሁኗ ዉሃን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የማይረሳ ጊዜም ነበራት። የመጨረሻ ሳምንታቶቿን አንዳንድ የቀሯትን ነገሮች በማጠናቀቅ ላይ እያለች ነው አዲስ አይነት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃው፣ ከአራት መቶ ሰዎች በላይ ህይወትን በነጠቀው ኮሮናቫይረስ ምክንያት ካለችበት ከተማ መውጣት እንደማትችል ያወቀችው። •የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ •በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ ከሳምንታት በፊት ትኩሳት (ፊቨር) እንደተከሰተና ጥንቃቄ አድርጉ፣ ጭምብል አጥልቁ የሚባሉ መልዕክቶች መተላለፍ ጀምረው የነበረ ቢሆንም እንደዚህ የከፋ ደረጃ ደርሶ ከአገር መውጣትና መግባት ይከለከላል ብላ ሶልያና አላሰበችም። አስራ አንድ ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት፣ ስምንተኛዋ ትልቋ የቻይና ከተማና የንግድ መናኸሪያዋ ዉሃን ፀጥ ረጭ ብላለች። በያንግትዜና ሃን ወንዞች የተከፋፈለችው፣ የብዙ ሐይቆችና ፓርኮች የጥንታዊት ቻይና ስልጣኔ መገለጫ የሆነችው ዉሃን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተወረረች ከተማ መስላለች። በቱሪስቶች የሚሞሉት ሙዚየሞች፣ በቡድሂስት አማኞች ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ጉያን ቴምፕል (ምኩራብ)፣ በነዋሪዎቿ ዘንድ ልብን የሚሰርቀው የዉሃን ያንግትዜ ድልድይ፣ እነ ሰመር ሃውስ ፒዛ ባር፣ ዳሚያኖ የጣልያን ሬስቶራንት፣ አሎሃ፣ አቶሚየም ጭር ብለዋል። ከዉሃን ዩኒቨርስቲ በሃያ ደቂቃ የምትገኘውና በማንታቀላፋው በሶልያና 'ዳውን ታውን' ሰፈርም እንቅስቃሴ ከጠፋ ሰነባበተ፤ ሶልያናም እየለመደችው ይመስላል። "ድሮ ማታ ላይ ተኝቼ ራሱ መኪና ማለፍ አያቆምም፤ ውይ መተኛት ከባድ ነበር። ሁልጊዜም ሲያልፉ እንደቀሰቀሱኝ ነው። አሁን መኪናም የለም። ያስፈራል፤ የሞተች ከተማ መስላለች። እንዴ ዉሃን እንደዚህ ነበረች ወይ እንላለን?" ትላለች። የሶልያና ሰፈር ብቻ አይደለም። ከተለያዩ አገራት በመጡ ቢያንስ ሦስት ሺህ ተማሪዎች የምትጨናነቀው ዉሃን ዩኒቨርስቲ እንቅስቃሴ አይታይባትም፤ ተማሪዎች ዶርማቸውን ከርችመዋል። ኑሮ፤ መንቀሳቀስ በማይቻልባት ዉሃን ቤት ውስጥ ቁጭ ማለት የማትወደው ሶልያና ያሁኑን አያድርገውና ዉሃንን ከጫፍ ጫፍ አዳርሳታለች። ብዙ ጓደኞችንም አፍርታባታለች። የተለያዩ ዝግጅቶችም ሲኖሩም ሶልያና አትቀርም። በአሁኑ ሰዓት ግን ድንገተኛ ካልሆነ መኪናም ሆነ ሞተር መንዳት በከተማዋ ውስጥ ክልክል ነው። ከተማው ውስጥ የተመደቡት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት ጥቂት ናቸው። ከቤት መውጣትና መንቀሳቀስ ከተማዋ ውስጥ ባይመከርም ክልክል አይደለም፤ "ግን ወጥቼስ የት እሄዳለሁ ትላለች ሶልያና?" ሁሉ ነገር ዝግ ነው በሰዓት ወስነው ከሚከፍቱት እነ ዋልማርትን ከመሳሰሉ ትልልቅ መደብሮች በስተቀር፤ ሆነም ቀረም ጭምብል ሳያጠልቁ እንቅስቃሴ ብሎ ነገር የለም። ሶልያናም ሙሉ በሙሉ የሚያስፈልጓትን ግብይቶችን የምትፈፅመው የተለያዩ ድረገፆችን በመጠቀም ነው። •ኬንያ ተማሪዎቿን ከቻይና ዉሃን ከተማ ልታስወጣ ነው •ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ባለባት ዉሃን መንቀሳቀስ ከተከለከለ ሁለት ሳምንት ሊደፍኑ ነው፤ ቀኑስ ለሶልያና እንዴት ያልፋል፣ ይመሻል፣ ይነጋልስ? ከእንቅልፏ የምትነሳው አርፍዳ ነው፤ በሱም የተወሰነውን ቀን ትገፋዋለች። 'ዳያሪዋ' ላይ ትፅፋለች፣ ማንበብ የምትፈልጋቸውን መፃህፍትና ጊዜ በማጣት የተወቻቸውን እያነበበች እንደሆነም በሳቅ በተሞላ ንግግሯ ገልፃለች። ፊልም ማየት፣ ጓደኟቿ ጋር ማውራት፣ ቤተሰብ ጋር በመደወል መመለሻዋን በመናፈቅ ቀናቱን እያሳለፈች ነው። "ወይ ቁጭ ብለሽ ታነቢያለሽ፤ ስልክ ታወሪያለሽ፤ መውጣት ብትፈልጊም ስለማትችይ ያው ቢሰለችም ምን ማድረግ ይቻላል" ትላለች። ሶልያና ምንም እንኳን ከቤተሰቦቿ ጋር በቀን ሁለት ጊዜ የምታወራበት ጊዜ ቢኖርም ያለችበትን ሁኔታ አያምኑም። "ቀን በቀን ነው የሚደውሉት፤ እናም ምን አዲስ ነገር አለ ትባያለሽ? ያው ምንም የለም፤ አትጨነቁ ደህና ነኝ፤ ሁሉ ነገር አለኝ እላቸዋለሁ" የምትለው ሶልያና ከውጭ ሆኖ ለሚያየው ሁኔታው ቢያስፈራም "እኔ እዚህ ስላለሁ ሁሌም አልደነግጥም። ይለመዳል" ትላለች ቀለል አድርጋ። በመጀመሪያ ስለቫይረሱ ለቤተሰቦቿ አልነገረቻቸውም ነበር፤ ምክንያቱም በአንድ ሳምንት ውስጥ ተዘግቶ ሁሉ ነገር ይሻሻላል በሚል ግምት፤ ዜና ላይ ሲሰሙ ደወሉላት ብታስረዳቸውም ጭንቀቱ አልለቀቃቸውም። ለእናቷ በተለይ ልጃቸውን ማረጋጋትም ሆነ እሷ ጋር መደወል በቂ አልነበረም፤ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሄዳቸውን በፈገግታ ሶልያና ትገልፃለች። " እዚህ አስፈላጊ የሚባሉ መረጃዎች መምህሮቻችንም ሆነ ዩኒቨርስቲው ስለሚሰጡን፤ አትሂጂ እያልኳት ነው የሄደችው" እናቷም አሻፈረኝ ብለው ጥያቄዎቻቸውን ጠይቀው፤ ስልክም ተቀብለው መጥተዋል ። "ያው እንደ ወላጅ ያስጨንቃል፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ የማትችይበት ሁኔታ ሲሆን ትንሽ ያሳስባል" ትላለች። የተማሪዎች ስጋትና መልሱን ጥያቄ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ መሆን በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። ምንም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ኢትዮጵያውያን ባይኖሩም፤ ወደ አገራችን መልሱን በሚሉ በሺዎች በሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች ተሞልታለች። ድምፃቸውን በዩኒቨርስቲው ግቢ እየተንቀሳቀሱ አይደለም እያሰሙ ያሉት፤ ሰውን በመፍራት፣ ቫይረሱን በመፍራት ኢንተርኔትን መርጠዋል። ከሰው ጋር ንክኪ የሚያስፈራበት ዘመን፤ የኢትዮጵያውን ተማሪዎችም በዚሁ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው። በዉሃን ዩኒቨርስቲ ከሦስት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ያሉ ሲሆን፤ በሁቤይ ግዛት ውስጥ በሚገኙ ከተሞችም ያሉ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ400 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች አሉ። በዉሃንም ሆነ በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች እንቅስቃሴ የተገደበ ስለሆነ ብቸኛው የመገናኛ መንገዳቸውም በኢንተርኔት መልዕክት በመላላክ ነው። ሶልያና ከተማሪዎች ማደሪያ ውጭ ተከራይታ በራሷ ስለምትኖር ሁኔታዎችን ቀለል ቢያደርግላትም በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚያድሩ ተማሪዎች ምግብ፣ ውሃም ሆነ ሌሎች ቁሳቁሶች ቢቀርብላቸውም አንዳንዶች ቸልተኝነት እንዳለባቸው ከኢትዮጵያውያኑ ሰምታለች። ተማሪዎቹ የቡድን (ግሩፕ) ቻት ስላላቸው ያሉበትን ሁኔታ፣ ስጋታቸውን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ይቀያየራሉ። "አንዳንድ ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። ትምህርት ቤቱ ቸልተኝነት በማሳየቱ ወይም የሚገባቸውንና የሚያስፈልጋቸውን ባለመስጠቱ ይሆናል" ትላለች። የምግብ እጥረት፣ የህክምና ቁሳቁሶች ለምሳሌ የጭምብል እጥረት በተደጋጋሚ የሚነሱ ጉዳዮች ነበሩ። በሆዋጆንግ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ በሲቪል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት የዶክትሬት ተማሪ የሆነችውና በቻይና ዉሃን ውስጥ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ዘሃራ አብዱልሃጅ በበኩሏ እነዚህ እጥረቶች የአንድ ሰሞን ችግር እንደነበሩ ነው። አንድ ሰሞን የጭምብል እጥረት አጋጠመ በተባለበት ወቅት ህብረቱ ሪፖርት አድርጎ ፋርማሲ ሄደው መግዛት እንዲችሉ መመቻቸቱንና፤ የምግብ አቅርቦት ችግር አለ ከተባለም እንዲሁ ህብረቱ በሚያሳውቅበት ወቅት የቻይና መንግሥት ምላሽ ፈጣን መሆኑን ነው። •ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? •ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? ምንም እንኳን በሁቤይ ግዛት ሁሉም ሰው እንቅስቃሴውን እንዲያቋርጥና፣ በቤቱ እንዲገደብ ቢወሰንም የቻይና መንግሥትም ማንኛውንም እርዳታ ለመለገስ መዋቅር ተዘርግቷል። ቫይረሱን ለመግታት ከፍተኛ ዘመቻ ላይ እንደሆኑ ሶልያናም ሆነ ዘሃራ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ሲሆን በእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የውጭ አገር ተማሪዎችን የሚንከባከቡበትን ሁኔታም አድናቆቷን ዘሃራ ችራለች። የቻይና መንግሥት በእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ ነፃ ምግብ ከማቅረብ በተጨማሪ የተማሪዎቹን ጉዳይ ለመቆጣጠር ፕሮፌሰሮች ተመድበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ያሉበትን የጤና ሁኔታ እንዲሁም ያለባቸውን ችግር ሌሎችንም ጉዳዮችን ለመከታተል ዓለም አቀፍ ቢሮዎች አሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ደግሞ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት የሚወያዩበት እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን የሚያንሸራሽሩበት የቻት [የውይይት] ቡድን አላቸው። አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት ህብረቱ ለቆንስላው ሪፖርት ያደርጋሉ፣ ያ ፅህፈት ቤት ደግሞ ለዉሃን ባለስልጣናት ያሳውቃል፤ እነሱም የተዘረጋውን የራሳቸውን መዋቅር በመጠቀም ዩኒቨርስቲው ጋር ግንኙነት ይፈጥራሉ። የሚያስፈልጓቸውን የምግብ አቅርቦት የጤና ቁሳቁሶችን በሟማላት ላይ የነበሩ ቢሆንም ነገር ግን በየዕለቱ ከሚሰሙ ዜናዎች ሁኔታዎች እየከፉ በመሄዳቸው ተማሪውን እንዲረበሽ አድርጎታል። ተማሪዎቹ እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንቀጥላለን? ወደ አገራችን ብንሄድ? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መነሳቱን ተከትሎ ህብረቱ ተማሪዎቹን እንዲያስወጣ ጥያቄያቸውን ለኤምባሲ አስገብተዋል። "የተማሪው እንቅስቃሴው ስለተገደበ በራሱ የሚያስጨንቅ ነገር አለው። ግፊትም ስለበዛብን ኤምባሲው እንዲያስወጣን ጥያቄውን አቅርበናል" ትላለች ዘሃራ። በተለይም አሜሪካና ፈረንሳይን የመሳሰሉ አገራት ዜጎቻቸውን ማውጣታቸውን ተከትሎ ሌሎች የእስያ አገራት ተማሪዎቻቸውን ወስደዋል። ያ ሁኔታ በራሱ ግፊት እንደፈጠረ ዘሃራ ታምናለች። ሶልያናም ሆነ ዘህራ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር መጨመር እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ያሉበት ጭንቀት ተማሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ነው የሚጠቅሱት። "ተማሪው ከቤተሰቡ ጋር ሲያወራ፤ ቤተሰብ ይጨነቃል የሚሰማው ነገር በጣም ከባድ ነው፤ ስለዚህ እስከመቼ ነው እንደዚህ የምንቆየው 'ኳረንታይን' መደረግ ካለብን እንደረግ ከቤተሰቦቻችን መቀላቀል ይሻለናል" በማለት በተደጋጋሚ እንደሚናገሩ ዘሃራ ትናገራለች። ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ መልስ ይሰጠን እያሉ እየጠየቁ ሲሆን ማህበሩም "ታገሱን ዝግጀት ይፈልጋል። ኤምባሲውም የራሱ የሆነ ሂደት አለው፤ የውጭ ጉዳይም እንዲሁ፤ ይህንን ሂደት እየተጠባበቅን ነው ያለነው" የሚል ምላሽም በመስጠት ላይ ናቸው። ሆነም ቀረም "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በጣም አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን እያሰቡ እንዲጨነቁ አልፈልግም፤ ከራሳቸው ዜጋ ባልተናነሰ መልኩ ክትትል እየተደረገልን ነው" በማለት ቤተሰቦች መረጋጋት አለባቸው ትላለች። ሁሉም ሰው በጭንቀት ላይ እንደሆነ የምትናገረው ሶልያና "ምክንያቱም መልስ እየጠበቅን ነው፤ ለምንም ነገር መዘጋጀት አለብን፤ እሱ ላይ ትንሽ ግራ ስለተጋባን፤ አብዛኞቻችን መወዛገብ ሁኔታ ላይ ነን" ትላለች። በተለይም ህብረቱ ደብዳቤ ካቀረበ በኋላ ኤምባሲው ምላሽ አለመስጠቱ ለሶልያናም ሆነ ለተማሪዎቹ አሳሳቢ በመሆኑ ሶልያና ጉዳዩን ወደ ትዊተር በመውሰድ ለሚመለከታቸው አካላት "እባካችሁ መልስ ስጡን" በማለትም ጠይቃለች፤ ተማፀናለች። በትዊተርም ምላሽ ስጡን ብላ ትዊት ካደረገች በኋላም ብዙዎች በጎ ምላሽ ቢሰጧትም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፀጥታ አስጨንቋታል። ከአራት መቶ በላይ ተማሪ ማስተናገድ ቀላል እንዳልሆነና ጫናውንም ብትረዳም "ዝም ከማለት ምንም አይነት ምላሽ ይሻላል" ትላለች። በአብዛኛው እየቀረበ ያለው ጥያቄ ከዉሃን ታስወጡናላችሁ ወይ? ከሆነስ እንዴት ነው የሚሆነው የሚል ነው? ተማሪዎቹን ከዉሃን ማስወጣት ከተቻለ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል? ምክንያቱም ሙቀት መለካት ብቻ ሳይሆን በሽታው ሳይገለጥ 14 ቀናት ሊቆይ ስለሚችል፤ የክትትሉ ሁኔታ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። ሌሎች አገራት በለይቶ ማቆያ ለአስራ አራት ቀን እንደሚያስቀምጡ ኢትዮጵያስ ያንን ትከተላለች ወይ የሚሉት ጥያቄዎችም የተማሪዎቹ መወያያ ሆኗል። የምርመራ ሁኔታው ምን ይመስላል? ተመርምረው ቫይረሱ ከተገኘ ኢትዮጵያ በቂ ህክምና የማድረግ ዝግጅቱም ሆነ ብቃቱ አላት ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች በተማሪዎች ዘንድ እየተንሸራሸሩ ነው። ይህ የተማሪዎቹ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አፍሪካ የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በሽታ ቢያጋጥማት ያላት ዝግጅት ላይ ስጋት እንዳለው ገልጿል። "ተማሪዎችን ካወጣሽ እነዚህን ሁሉ ተሟልተው መሆን አለበት፤ ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ ማውጣት ችግር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ ይኑርብሽ አይኑርብሽ ላታውቂ ትችያለሽ፤ እዚህ ተጋላጭ ነን" የምትለው ሶልያና ነገር ግን ተማሪዎቹን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለማቆየት ዝግጅት ካለ መውጣቱን ትመርጣለች። "ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል የመቆየቱ ሁኔታ ተማሪዎቹን የበለጠ እያጋለጣቸው እንጂ የሚጨምረው ነገር የለም" በማለትም ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ታስረዳለች። ምላሽ ቢሰጣቸው ነገሮችን ያቀላል የምትለው ሶልያና "እናስወጣችኋለን ከተባለ ዝግጅት ታደርጊያለሽ፤ አይሆንም ከተባለም ምግብ እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ወደ ማከማቸት ትሄጃለሽ" ትላለች። ቀድሞም ለመዘጋጀት፣ ቲኬትም ለመግዛት፣ የቤት ኪራይ ልክፈል አልክፈል የሚሉ ጥያቄዎችም እንዲሁ መነጋገሪያ ጉዳዮቻቸው ከሆኑ ከራረሙ። የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ምክትል ሚሽን መሪ የሆኑት አቶ ገነት ተሾመ የተማሪዎቹ ጥያቄ በማህበሩ በኩል እንደቀረበና፤ አጠቃላይ ሁኔታውንም እየገመገሙት እንዳሉና የቻይና መንግሥትም ሁኔታውን ለመቆጣጠር አበክሮ እየሰራ ከመሆኑ አንፃር ተማሪዎቹ ከቤት እንዳይወጡ ምክር እየሰጧቸው ነው። "በእኛም አገር በኩል ይሄ ዝግጅትም፣ ውሳኔም ይጠይቃል፤ ዝም ብለን ከዚህ ማውጣት አይቻልም ፤ መጀመሪያ መውጣታቸው መታመን አለበት፤ በቂ ኳረንታይን ያስፈልጋል የሚያስፈልጋቸውን መሰረታዊ ፍጆታዎች ምግብና መገልገያዎች ለተማሪዎቹ በነፃ እየቀረበ ነው" ብለዋል። የተማሪዎቹን የመውጣት ፍላጎት ጉጉት ቢገባቸውም፤ ከተማው በኳረንታይን የሚቆየው እስከ ጥር ሰላሳ ከመሆኑ አንፃር መንቀሳቀስ ሲፈቀድ ነገሮች እንደሚስተካከሉ አቶ ገነት ተስፋ ያደርጋሉ። ሁሉንም ነገር አጠናቃ በዚህ ወር ወደ አገሯ ለመጓዝ ቲኬቷን ቆርጣ የነበረችው ሶልያና እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባታውቅም፤ ጉንፋንም ሆነ ሙቀት ሰው ሲሰማቸው ያለው ድንጋጤ ከፍተኛ ነው። ያለው የአየር ፀባይ ብርድ ከመሆኑም አንፃር ጉንፋን ሰው በሚታመምበት ወቅት እንዲሁም ምልክቶቹም ስለሚመሳሰሉ በድንጋጤ በተደጋጋሚ ድንገተኛ ቁጥሮችን ይደውላሉ ትላለች። "የሆነ ቀን ሳስነጥስ ደንግጨ ነበር፤ የሌለ ጥርጣሬ ነው የሚፈጥረው።" •አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ የጤና ተቋማት የኮሮናቫይረስን በማከም በከፍተኛ ሥራም ስለተጠመዱ እንዳው ማንኛውም ስሜት ሰው ስለተሰማው ተዘሎ አይኬድም፤ ድንገተኛ ተደውሎና ምልክቶቹን እርግጠኛ ካልሆኑ ዝም ብሎ መሄድም አይመከርም። ቻይና ኮሮናቫይረስን ለማከም ከአቅሟ በላይ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን በብቸኝነትም በሽታውን ማከም የሚችሉ ሆስፒታሎችን ገንብታለች። በተለይ ሶልያና ትምህርቷን ከማጠናቀቋ አንፃር እንዲሁም ለመመለስ በዝግጅትም ላይ ስለነበረች መቼ ነው ሊሻሻል የሚችለው? የሚለውን እርግጠኛ አለመሆን፣ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር እንዲሁም ሌሎች አገሮችም ላይ እየተከሰተ መሆኑ የሚያሳስቧት ጉዳዮች ናቸው። "ትጨነቂያለሽ ራስሽን ደግሞ ያንን ያህል አታስጨንቂውም፤ ያው ያለሽበት ሁኔታ ስለሆነ ችለሽ ትቀጥያለሽ። ያው መቆጣጠራቸው አይቀርም፤ ግን ጊዜ ይፈጅባቸዋል ብዬ አስባለሁ።"
news-46041930
https://www.bbc.com/amharic/news-46041930
ትራምፕ አሜሪካ ለተወለዱ ልጆች የምትሰጠውን ዜግነት ለማስቀረት እየጣሩ ነው
በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የገቡ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙ እንኳን አሜሪካ ውስጥ የተወለዱ ልጆቻቸው በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነትን ያገኛሉ።
ከዚህ አልፎም ለጉብኝትም ሆነ ለህክምና ወደ አሜሪካ የሄደች እናት በቆይታዋ ወቅት ልጇን ከወለደች ፍላጎቱ ካላት ልጇ የአሜሪካ ዜግነት እንድታገኝ/እንዲያገኝ ማድረግ ትችላለች። ለዚህም አቅሙ ያላቸው የእኛ ሃገር እናቶችን ጨምሮ በርካቶች መውለጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንደሚያቀኑ ይነገራል። አሁን ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ150 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14 ላይ የሰፈረው ማንኛውም በአሜሪካ ምድር ላይ የተወለደ ሰው ዜግነት ያገኛል የሚለውን ህግ ለማስቀረት እየሰሩ እንደሆነ አስታውቀዋል። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? "ህጉን ለመቀየር ሃሳቤን ሳቀርብ ሁሌም ህገ መንግሥቱ መሻሻል አለበት ይሉኛል፤ እኔ ደግሞ እንደውም ምንም ማሻሻል አያስፈልገውም ባይ ነኝ'' ብለዋል። "በተጨማሪ ምክር ቤቱ ካጸደቀው መቀየር እንደሚቻል ነግረውኝ ነበር፤ ነገር ግን በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝም መቀየር እንደሚቻል ተነግሮኛል።" ይህ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት ደግሞ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ሰዎችም እንዲህ አይነት አከራካሪ የህገ መንግሥቱን ክፍል ፕሬዝዳንቱ በቀጭን ትዕዛዝ መቀየር ይችላሉ ወይ? በማለት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። 1. በመወለድ የሚገኝ ዜግነት ምንድነው? የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14 የመጀመሪያ አረፍተ ነገር በመወለድ ስለሚገኝ ዜግነት ያትታል። ''ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው'' ይላል። የስደተኞች ወደ አሜሪካ መጉረፍ ያሳሰባቸው ሰዎች ህጉ የህገ ወጥ ስደተኞች 'ማግኔት' ነው በማለት ማንኛዋም ሴት አሜሪካ መጥታ መውለድን የሚያበረታታው ህግ እንዲቀር ይከራከራሉ። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች እንደውም አብዛኛዎቹ እናቶች በህገ ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ወደ አሜሪካ በመግባት ነው ልጆቻቸውን የሚወልዱት። የዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች ህጉን የወሊድ ቱሪዝም የሚል ስም ሰጥተውታል። "የሚወለዱት ህጻናት ቢያንስ ለ85 ዓመታት ከነሙሉ ጥቅማጥቅሞቹ የአሜሪካ ዜጋ ሆነው ይቆያሉ፤ ይህ የማይሆን ነገር ነው'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ፒው የተባለ የምርምር ማዕከል በአውሮፓውያኑ 2015 በሰራው አንድ ጥናት መሰረት 60 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን ህጉን የሚደግፉ ሲሆን፤ 37 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህጉ መቀየር አለበት ባይ ናቸው። 2. አሜሪካ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ ዜግነት መነሻው ምንድነው? ስለጉዳዩ የሚያወራው አንቀጽ 14 በአሜሪካ ህገ መንግሥት ውስጥ የተካተተው በአውሮፓውያኑ 1868 ልክ የእርስ በርስ ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ነበር። አንቀጽ 13 የባሪያ ንግድን በ1865 ሲከለክል አንቀጽ 14 ደግሞ በአሜሪካ የሚገኙ ነጻ የወጡ ባሪያዎችን የዜግነት መብት ጥያቄ የሚመልስ ሆነ። በአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ክርክሮች ጥቁሮች የአሜሪካ ዜጋ መሆን እንደማይችሉ ተወስኖ የነበረ ሲሆን፤ አንቀጽ 14 ለዚህ ክርክር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልስ የሰጠ ነው። • በኢትዮጵያ አደገኛ ከሆኑት መንገዶች አንዱ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው አሜሪካ ውስጥ የተወለዱ የስደተኛ ልጆች ዜግነት ማግኘት አለማግኘትን በተመለከተ የአሜሪካው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ውሳኔ ያስተላለፈው በ1898 ነበር። ሰውዬው ዎንግ ኪም የሚባል የ24 ዓመት ወጣት ነው። ቤተሰቦቹ በስደት ወደ አሜሪካ መጥተው ነው እሱ የተወለደው። የቤተሰቦቹን ሃገር ለመጎብኘት ወደ ቻይና ሄዶ ሲመለስ ግን የአሜሪካ ዜጋ አይደለህም ስለዚህ መግባት አትችልም ተብሎ ተከለከለ። ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ወስዶ በክርክሩ አሸነፈ። ከዚህ አጋጣሚ በኋላም ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ሰው ቤተሰቦቹ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ይምጡ፣ ምንም አይነት የኑሮ ደረጃ ይኑራቸው የአሜሪካ ዜግነት ማግኘት እንደሚችሉ ተወሰነ። ከዚህ ውሳኔም በኋላ የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን ጉዳይ በድጋሚ አይቶት አያውቅም። 3. በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን በትራምፕ ውሳኔ ብቻ መቀየር ይቻላል? ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚስማሙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጭን ትዕዛዝ የህገ መንግሥቱን አንድ ክፍል መቀየር አይችሉም። ሁሉም ነገር በህግና ደንብ መሰረት ስለሚሰራ በቀላሉ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው ብለዋል። በቨርጂንያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፕሮፌሰርና የህገ መንግሥት ኤክስፐርት የሆኑት ሳይክሪሽና ፕራካሽ እንደሚሉት፤ "ይህ ሃሳብ ብዙ ሰዎችን የማያስደስትና በፍርድ ቤት ብቻ መወሰን የሚችል ነገር ነው። ፕሬዝዳንቱ ለብቻው መወሰን የሚችለው ነገር አይደለም።" • የኢትዮጵያ እና የጂ-20 ወዳጅነት ባለሙያው ሲያብራሩ ፕሬዝዳንቱ ምናልባት የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ዜግነትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲያወጡ ሊያዙ ይችላሉ፤ ነገር ግን ህጉን የማስቀየር ስልጣን የላቸውም። ይሄ አካሄድ የማያባራ ክርክር የሚያስነሳ ሲሆን በመጨረሻ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለውሳኔ መቅረቡ አይቀርም። "ነገር ግን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ ዜግነት ከሌላቸው ወይም በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ ካልገቡ ሰዎች የሚወለዱ ልጆች ዜግነት ስለማግኘት አለማግኘታቸው ውሳኔ አላሳለፈም" ሲሉ 'በርዝራይት ሲቲዝንስ' መጽሃፍ ደራሲ ማርታ ጆንስ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረወዋል። 4. ከዚህ ውሳኔ ጀርባ ምን አለ? በመወለድ የሚገኝ የአሜሪካ ዜግነትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እየሰሩት ያለውን ነገር በቀጣይ ሳምንት ከሚካሄደው የአጋማሽ ወቅት ምርጫ ጋር አያይዞ መመለክት አስፈላጊ ነው። መንግሥት ከ5ሺህ በላይ ወታደሮችን ወደ ሜክሲኮ ድንበር ማሰማራቱና የፕሬዝዳንቱ ከዜግነት ጋር የተያያዘ አስተያየታቸው የአሜሪካዊያንን ትኩረት ወደ ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ለማዞር ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሲጀምሩም የኢሚግሬሽን ጉዳይ ዋናው ነጥባቸው የነበረ ሲሆን፤ ለማሸነፋቸውም እንደ ምክንያት ይጠቅሱታል። 5. ተመሳሳይ ህግ ያላቸው ሃገራት አሉ? ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተያየታቸውን ሲሰጡ አሜሪካ በመወለድ የዜግነት መብት የምትሰጥ የዓለማችን ብቸኛዋ ሀገር ናት ብለው ነበር። ነገር ግን ተሳስተዋል፤ የአሜሪካ ጎረቤት የሆኑት ካናዳና ሜክሲኮን ጨምሮ 33 የዓለማችን ሃገራት በሃገራቸው ለተወለዱ ህጻናት የዜግነት መብት ይሰጣሉ። • ታንዛኒያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን አድና ልታስር ነው አብዛኞቹ የአውሮፓ ሃገርም ሆነ የምሥራቅ እሲያ ሃገራት በመወለድ የዜግነት መብት የማይሰጡ ሲሆን፤ እንግሊዝ ግን ከቤተሰቦች መካከል አንዳቸው እንግሊዛዊ ከሆኑ አልያም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው የዜግነት መብት ትሰጣለች። 6. ከዚህ ዜግነት መብት የሚጠቀመው ማነው? ፒው የተባለው የምርምር ማዕከል በሰራው ጥናት መሰረት በአውሮፓውያኑ 2014 ዓ.ም ብቻ 275 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ከህገወጥ ስደተኞኛ ቤተሰቦች አሜሪካ ውስጥ ተወልደዋል። በአውሮፓውያኑ በ1990ዎቹ እና በ2000 አካባቢ በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ከገቡ ቤተሰቦች ወይም ህጋዊ ወረቀት ከሌላቸው ቤተሰቦች የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። በ2006 ከፍተኛ የሚባለውን ቁጥር አስመዘግቦ ከዚያ በኋላ ግን መቀነስ አሳይቷል። ምንም እንኳን የምርምር ተቋሙ ስደተኞቹ ከየትኞቹ ሃገራት በብዛት ወደ አሜሪካ እንደሚገቡ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይችልም፤ ሦስት አራተኛ የሚሆኑት ህገወጥ ስደተኞች ከላቲን አሜሪካ ሃገራት እንደሚመጡ ያስቀምታል።
news-53348436
https://www.bbc.com/amharic/news-53348436
ጃዋር መሐመድ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ
አሁን ላይ በእስር ከሚገኙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ “ወደ ሕገ ወጥ መሪነት” እያመሩ ነው ማለቱ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል ሽልማት ካገኙ ወዲህ ከታሰሩ እውቅ የተቃውሞ ፖለቲከኞች አንዱ ጃዋር፤ ፌስቡክ ላይ ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ተከታዮች አሉት። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተነሳው ግርግር በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንዱ ሲሆን፤ በግርግሩ ሳቢያ ከተገደለ ፖሊስ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበታል። ደጋፊዎቹ ክሱን በማጣጣል፤ የታሰረው በጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ለማክሸፍ ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይና ፖለቲከኛው ጃዋር የወደፊቷን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያላቸው ራዕይ የተለያየ ይመስላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ሲይዙ በብሔር መስመሮች የተከፋፈለችውን ኢትዮጵያ ለማዋሃድና ዴሞክራሲ ለማስፈን ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የመንግሥትን ሐሳብ የሚደግፉ አካላት፤ ጀዋር መታሰሩ ብሔርን ያማከለ ንቅናቄን ለማክሰም ያግዛል ይላሉ። ከጠቅላይ ሚንስትሩ የ “አንድነት” ራዕይ በተቃራኒው ብሔር ተኮር ግጭቶት ለመነሳታቸው ጀዋርን ተጠያቂ ስለሚያደርጉም መታሰሩን በበጎ ያዩታል። በተቃራኒው የጃዋር ደጋፊዎች እንደሚሉት መታሰሩ፤ ለ34 ዓመታት ሲቀነቀን የነበረው የኦሮሞ እንዲሁም የሌሎች ብሔሮች ራስን የአስተዳደር ሀሳብን ጠቅላይ ሚንስትሩ ማስተናገድ እንዳልቻሉ ያሳያል ይላሉ። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” ጃዋር የተወለደው እንደ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1986 ነው። አባቱ ሙስሊም እናቱ ደግሞ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው። ያኔ በስደት አሜሪካ የነበረው ጃዋር 2013 ላይ ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቆይታ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” ብሎ፤ ኢትዮጵያዊ የሚለው ማንነት “እንደተጫነበት” ገልጾ ነበር። በኬል ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት አወል አሎ የዚያን ጊዜውን የጃዋር አስተያየት “ፖለቲካዊ ሱናሚ” አስነስቷል ብለው ነበር። ንግግሩ በኢትዮጵያና በውጪ አገራትም ጃዋርን በእጅጉ በሚደግፉና አጥብቀው በሚተቹ ሰዎች መካከል የጋለና የተካረረ ክርክርንም አጭሮ ነበር። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” የኋላ ኋላ ወደ ፖለቲካዊ ንቅናቄ አድጓል። ጃዋር በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በመዘዋወር ዳያስፖራው የኢትዮጵያን አገዛዝ እንዲያወግዝ፣ ለነፃነቱ እንዲታገልም ቀስቅሷል። ንቅናቄው ይበልጥ የተቀጣጠለው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) 2013 ላይ የቴሌቭዥንን ጣቢያ በከፈተበት ወቅት ነው። ጣቢያው ሲመረቅ ጃዋር “አሁን የኦሮሚያን አየር ሞገድ ነፃ አውጥተናል” ማለቱ ይታወሳል። የኦኤምኤን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳለ፤ ጣቢያው የወጣቱን (ቄሮ) ድምጽ እንዲያስተጋባ አድርጓል። ቄሮ የሚለው መጠሪያ በስፋት የተዋወቀው በ1990ዎቹ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አማካይነት ነበር። ኦነግ ከሚንቀሳቀስባቸው ከተሞች በአንዱ ያደገው ጃዋር “የተወለድኩት በኦሮሞ ትግል ውስጥ ነው፤ በአምባገነኖች እና በአጼዎቹ ዘመን የኦሮሞ ሕዝብ መጨቆኑን አስተውያለሁ” ይላል። ጃዋር መሐመድ ከኢትዮጵያ የወጣው በወጣትነቱ ነው። 2003 ላይ ሲንጋፖር የነፃ ትምህርት እድል አግኝቶ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ አሜሪካ ሄዶ ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ 2013 ላይ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በሰብዓዊ መብት ይዟል። ጃዋርና ጠቅላይ ሚንስትሩ ጃዋር የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለ ራሱን ከኦነግ አርቆ ነበር። በአመራሩ መካከል ያለው መከፋፈል ግንባሩን “እንዳይጠገን አርጎ ሰብሮታል” ሲል በጦማሩ ላይ ጽፎ ነበር። ሆኖም ዳያስፖራ የኦሮሞ ተወላጆች የአገር ቤቱን ትግል እንዲደግፉ ከማነሳሳት ወደ ኋላ አላለም። በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመነሳቱ ምክንያት ከሆኑ እንቅስቃሴዎች አንዱም ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዶ/ር ዐብይ ሲተኩ፤ ጀዋር “ስትራቴጂያዊ ስህተት” ብሎ ሥልጣኑን መያዝ ያለባቸው የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ እንደሆኑ ተናግሮ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመሪነት መንበሩን እንደያዙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ ሲያደርጉና ጃዋርን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ውጪ የነበሩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ከ ‘ሽብርተኛ’ መዝገብ ከሰረዙ በኋላ፤ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትሩን መደገፍ ጀምሮ ነበር። ወደ አገር ቤት ተመልሶም የኦኤምን ቅርንጫፍን በአዲስ አበባ ከፍቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሩን በመደገፉ አልገፋበትም። የራስ አስተዳደር ለሁሉንም ብሔሮች የምጣኔ ሃብት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥና መረጋጋትን የሚፈጥር ነው ብሎ ስለሚያምን ከጠቅላይ ሚንስትሩ በተቃራኒው ቆሟል። የጃዋር መታሰር ደጋፊዎቹ በጠቅላይ ሚንስትሩ የነበራቸውን የተስፋ ጭላንጭል ያከሰመ ይመስላል። በተለይም በኮቪድ-19 ሳቢያ የተራዘመው ምርጫ ጉዳይ የሚነሱትን ጥያቄዎች አጉልቷቸዋል። ብልጽግና ፓርቲ እና ኦፌኮ ጠቅላይ ሚንስትሩ በብሔር ውክልና ላይ የተመሠረተውን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባርን (ኢሕአዴግ) አክስመው ብልጽግና ፓርቲን ፈጥረዋል። ጃዋር ደግሞ ከኦኤምኤን ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለቆ፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) ተቀላቅሏል። ኦፌኮ እና በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሊኖር በሚችልባቸው አካባቢዎች በተቀናቃኝነት ሳይሆን በመደጋገፍ ለመሥራት ተስማምተዋል። ይህም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በኦሮሚያ የምርጫ ቀጠናዎች ሊያገኙ የሚችሉትን ድምጽ ሊያሳጣ ይችላል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በወረርሽኙ ስጋት ሳቢያ ምርጫው እንደተራዘመ ማስታወቁን ተከትሎ፤ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከመስከረም 2013 ዓ. ም በኋላ “ሕገ ወጥ መሪ” ናቸው ብሏል። የኦፌኮ አመራሮች እንደሚሉት የጀዋር ጠበቃና ቤተሰቦቹን እስካሁን ሊያገኙት አልቻሉም። የረሃብ አድማ ላይ እንደሆነም የፓርቲው አመራሮች ገልጸዋል።
news-49224756
https://www.bbc.com/amharic/news-49224756
ቴክሳስ የሚገኝ መገበያያ ውስጥ በተከሰተ ጅምላ ጥቃት 20 ሰዎች ሞተዋል
በአሜሪካዋ ቴክሳስ ክፍለ-ግዛት ውስጥ በምትገኝ አል-ፓሶ በተባለች ሥፍራ በደረሰ ጅምላ ግድያ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ 26 ደግሞ በፅኑ መጎዳታቸው ታውቋል።
የቴክሳስ ሃገረ-ገዥ ግሬግ አቦት ግድያው በግዛቲቱ ታሪክ አሰቃቂው ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ዎልማርት የተባለ መገበያያ ሥፍራ ውስጥ ሃገር ሰላም ብለው ሲገበያዩ የነበሩ ሰዎች ናቸው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት። • በካሊፎርኒያ ከተገደሉት መካከል የስድስት ዓመት ታዳጊ ይገኝበታል ከግድያው ጋር በተያያዘ ፓትሪክ ክሩሲየስ የተባለ አንድ የ21 ዓመት ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አሳውቋል። ግለሰቡ ጥቃቱ ከደረሰበት አንድ ሺህ ኪሎሜትር ርቃ የምትገኘው የዳላስ ግዛት ነዋሪ ነው ተብሏል። የሲሲቲቪ ካሜራው እንደሚያሳየው ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ጥቁር ቲሸርት አድርገው፤ በድምፅ መከላከያ መሰል ነገር ጆሯቸው ጀቡነው ነው ወደ መገበያያው የገቡት። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱን 'የአረመኔነት መገለጫ' ሲሉ ገልፀውታል። በትዊተር ገፃቸው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዝደንቱ ጥቃት አድራሾቹን ያደረጉት ድርጊት ምንም ዓይነት ፍትሃዊ አመክንዮ የሌለው ነው ሲሉ ተደምጠዋል። • 'የተሳመው ከንፈር' ጥቃት ደረሰበት አሜሪካን ከሜክሲኮ ከሚያዋስነው ድንበር አካባቢ በደረሰው በዚህ ጥቃት የሞቱ ግለሰቦች ስም እስካሁን ይፋ አልሆነም። የሜክሲኮው ፕሬዝደንት ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር ግን ሶስት የሃገሬ ሰዎች ሞተዋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ጥቃቱ በሃገሪቱ አቆጣጠር ከረፋዱ 4 ሰዓት ሲሆን የደረሰው በርካቶች በድንጋጤ ሕንፃውን እየለቀቁ ሰወጡ ታይተዋል። ካሊፎርኒያ ውስጥ በነበረ የምግብ ፌስቲቫል ላይ አንድ በአሥራዎቹ የሚገኝ አፍላ ሶስት ሰዎች ከገደለ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው ይህኛው የጅምላ ጥቃት የደረሰው። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት
news-56110666
https://www.bbc.com/amharic/news-56110666
ኮሮናቫይረስ፡ ወረርሽኙን ተከትሎ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች የተበራከቱባት ጃፓን
ጃፓን ከየትኛውም ዓለም በፈጠነና ትክክለኛ በሆነ መልኩ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን መረጃ በአግባቡ ትመዘግባለች።
ከሌሎች አገራት በተለየ መልኩ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች መረጃ በየወሩ እየተጠናቀረ ይቀመጣል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ደግሞ ይህ መረጃ በጣም አስፈሪ ታሪኮችን ይፋ አድርጓል። 2020 ላይ ከ11 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር በጣም ከፍ ብሏል። በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ የወንድ ሟቾች ቁጥር በትንሹም ቢሆን የቀነሰ ሲሆን ራሳቸውን የሚያጠፉ ሴቶች ቁጥር ደግሞ 15 በመቶ ጨምሯል። ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከዛ በፊት በነበረው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ራሰቸውን የሚያጠፉ ሴቶች ቁጥር 70 ከመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቶ ነበር። በጃፓን ምን እየሆነ ነው? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከወንዶች በተለየ ሴቶችን ለምን ራሳቸውን እንዲያጠፉ አደረጋቸው? ማስጠንቀቂያ፡ አንዳንድ አንባቢያን ይህ ጽሁፍ ሊያስደነግጣቸው ይችላል? በተደጋጋሚ እራሷን ለማጥፋት የሞከረችን ሴት በአካል አግኝቶ ማውራት ከባድ ነገር ነው ይላል የቢቢሲው የቶክዮ ዘጋቢ ሩፐርት ዊንግፊልድ። ያየውን እንዲህ ይገልጻል. . . ሰዎች ራሰችውን እንዳያጠፉ መከላከል ላይ የሚሰሩ ሰዎችን በጣም እንዳደንቃቸው አድርጎኛል። በዮኮሀማ ሬድ ላይ ዞን ውስጥ በሚገኝ በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ውስጥ ነው የምገኘው። ከፊልት ለፊቴ አንድ የ19 ዓመት ወጣት ተቀምጣለች። ምንም አይነት ስሜት አይታይባትም። ቀስ ብላ የግል ታሪኳን ታጫውተኝ ጀመር። ነገሩ የጀመረው የ15 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር። በወቅቱ ታላቅ ወንድሟ ቀላል የማይባል አካላዊ ጥቃት ይፈጽምባት ነበር። በመጨረሻ ከቤት ጠፍታ ለማምለጥ ወሰነች። ነገር ግን ብቸኝነቱንና ህመሙን መቋቋም አልቻለችም። የታያት የመጨረሻ አማራጭም ራሷን ማጥፋት ነበር። ''ከባለፈው ዓመት ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት ሆስፒታል ስገባና ስወጣ ነበር የቆየሁት'' ትላለች። ''ብዙ ጊዜ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬያለው ነገር ግን ሊሳካልኝ አልቻለም። ምናልባት አሁን ተስፋ በመቁረጥ ራሴን ለማጥፋት መሞከር ትቻለሁ።'' ራሷን ለማጥፋት ከመሞከር እንድትቆጠብ ያደረጋት ደግሞ በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያለው 'ቦንድ' የተሰኘው ፕሮግራም ነው። ደህንነቱ የተጠበቀ መኖሪያ ቦታ አግኝተውላታል፤ በተጨማሪም ተገቢውን የአእምሮ ጤና ክትትል እንድታገኝ ረድተዋታል። ጁን ታቺባና የቦንድ ፕሮጀክት መስራች ነች። በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ጠንካራ ሴት ናት። ''ሴቶች በተለይ ታዳጊ ሴቶች ችግር ውስጥ ሲገቡና ስነ ልቦናዊ ህመም ሲሰማቸው በትክክል ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም። እኛ እዚህ ያለነው የእነሱን ችግር ለመስማት ነው። መፍትሄ ለመስጠትና ችግራቸውን ለመጋራት'' ትላለች። ጁን እንደምትለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መጀመሪያውኑ ችግር ያለባቸውንና ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በጣም ጎድቷል። በፕሪጀክቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች በወረርሽኙ ወቅት እጅግ አስፈሪና አሳዛኝ የስልክ ጥሪዎችን እንዳስተናገዱም ታስታውሳለች። ''ብዙ ጊዜ መሞት እፈልጋለሁ አልያም ምንም አይነት የምሄድበት ቦታ የለኝም የሚሉ ጥሪዎች ይደርሱናል። በጣም የሚያም ነገር እንደሆነ ይነግሩናል። አንዳንዶቹም ብቸኝነት እንደሚሰማቸውና መጥፋት እንደሚፈልጉ ነው የሚገልጹት።'' ከዚህ በፊት አካላዊና ጾታዊ ጥቃት ይደርስባቸው የነበሩ ሰዎች ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነገሮችን ይበልጥ አስከፊ አድርጎባቸዋል። ''በአንድ ወቅት አንዲት ታዳጊ ደውላ በአባቷ ጾታዊ ጥቃት እየደረሰባት እንገሆነ ገልጻ ነበር። በኮሮናቫይረስ ምክንያት አባትየው ለስራ ብሎ ከቤት ስለማይወጣ በየቀኑ ይህንን አሳዛኝ ጥቃት መጋፈጥ ነበረባት።'' በጃፓን ከዚህ በፊት የነበሩትን ቀውሶች ስንመለከት ለምሳሌ በአውሮፓውያኑ 2008 አጋጥሞ በነበረው የባንክ ዘርፋ ቀውስ ወይም በ1990ዎቹ አካባቢ በነበረው የአክስዮን ገበያ መውደቅ ምክንያት በርካታ ጃፓናውያን በተለይ አዋቂ ወንዶች በእጅጉ ተጎድተው ነበር። በነዚህ ጊዜያት ራሳቸውን የሚያጠፉ ወንዶች ቁጥር በጣም ከፍ ብሎ ነበር። ኮቪድ-19 ግን የተለየ ነገር ነው። የወረርሽኙ መዘዝ በዋነኛነት ወጣቶችን በተለይ ደግሞ ወጣት ሴቶችን እያጠቃ ይገኛል። ምክንያቶቹ ደግሞ የተወሳሰቡ ናቸው። ጃፓን ከዚህ በፊትም ቢሆን ካደጉት አገራት ጋር ስትወዳደር ከፍተኛውን ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ታስተናግድ ነበር። ባለፉት አስር ዓመታት ደግሞ አገሪቱ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ቁጥር በአንድ ሶስተኛ መቀነስ ችላለች። ፕሮፌሰር ሚቺኮ ኡዌዳ በጃፓን በዙዳዩ ላይ ቀዳሚ የሚባሉ ተመራማሪ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት በጃፓን ባለፉት ቅርብ ወራት ውስጥ ብቻ የታየው ራሰቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእጅጉ የሚያስደነግጥ ነው። ''በተለይ ደግሞ ሴቶች ራሳቸውን እያጠፉ ያሉበት አካሄድ ያልተለመደና አሳሳቢ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ጥናት ማካሄድ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ እንዲህ አይነት ቁጥር ተመልክቼ አላውቅም። ምናልባት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በእጅጉ ካዳከማቸው ዘርፎች መካከል እንደ ቱሪዝም፣ ችርቻሮ ንግድና ምግብን የመሳሰሉት ሴቶች በብዛት የሚሰማሩባቸው መሆናቸው እንደ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል'' ይላሉ ፕሮፌሰሯ። በጃፓን ሌላው ቀርቶ ብቻቸውን የሚኖሩ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፤ ዋነኛ ምክንያታቸው ደግሞ ትዳርን ሽሽት ነው። ብቻቸውን ሲኖሩ ደግሞ ከማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም በጣም ከባድ ነገር ነው። ''በርካታ ወጣት ጃፓናውያን ሴቶች አላገቡም። ቤተሰቦቻቸውንም የሚረዱት እነሱ ናቸው። በርካታዎቹ ደግሞ ቋሚ ስራ የሌላቸው ሲሆን በወረርሽኙ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጫና መገመት ቀላል ነው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ብቻ በጃፓን 879 ሴቶች ራሳቸውን አጥፍተዋል። ከዛ በፊት ከነበረው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ ቁጥሩ 70 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ጃፓን በአሁኑ ሰአት ሶስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ትገኛለች። መንግስትም ለሁለተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን አዟል። እስከሚቀጥለው ወር ድረስ ሊቀጥል እንደሚችልም ይገመታል። በርካታ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች በራቸውን እየዘጉ ሲሆን በዚሁ ምክንያትም በርካቶች ስራቸውን እንዳጡ ነው። ራስን ማጥፋት ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ እንዲሁ በቀላሉ መፍትሄ መዘርዘር የሚቻል አይደለም። ትልቁና ተመራጩ መፍትሄ ግን ተግባቦትን ማጠናከር ነው። ሰዎች ስለ ሕይወታቸው እንዲያወሩ ማድረግ፣ የሚደገፉበትን ትከሻ አለመንፈግ፣ ሙሉ ጆሮ እና ጥሞናን መስጠት። ሌላው ሊዘነጋ የማይገባው ነገር፤ ሰዎች ራስን የማጥፋት መዘዝ ለሌላውም እንደሚተርፍ ማወቅ አለባቸው። ራስን አለማጥፋት ምርጫ እንደሆነ ማሳየት ባለሙያዎች የሚመክሩት አንዱ የመፍትሄ ሃሳብ ነው። ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ላይ ትቶ የሚያልፈውን ጠባሳ ማስተዋል፤ ሃሳቡ ያላቸው ሰዎች ቆም ብለው እንዲያጤኑ ያደርጋል። በበርካታ ሃገራት እራስን ማጥፋት የመኪና አደጋ ከሚያደርሰው በላይ ጥፋት ያደርሳል። ነገር ግን ለመኪና አደጋ የሚሠራውን ያህል ግንዛቤ ስለ ለራስ ማጥፋት አይሠራም። አንዳንድ ቦታዎች ራስ ማጥፋትን በተመለከተ ምክር የሚሰጡና የሚሠሩ ተቋማት መመሥረታቸው እንደ በጎ ጅምር እየታየ ነው። ለምሳሌ እንግሊዝ የራስ ማጥፋት መከላከል ሚኒስቴር አላት። የችግሩ መጠንም በትንሹ መቀነስ አሳይቷል።
news-48381381
https://www.bbc.com/amharic/news-48381381
ኮንዶም መጠቀም እያቆምን ይሆን?
ሄይሊ የ24 ዓመት ወጣት ነች። ውጪ ከምታሳልፋቸው ምሽቶች በአንዱ ወደ መጠጥ ቤት ጎራ ብላ ነበር። ሌሊቱ ሊጋመስ ጥቂት ሲቀረው ከዚህ በፊት ትምህርት ቤት አብሯት የተማረ ሰው በድንገት አገኘች።
አብረው ሲጠጡ አምሽተው ተያይዘው ወደቤት ገቡ። ያለምንም መከላከያም ግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጸሙ። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ሰክሬ ባደረግኩት ነገር ባልደሰትም ይበልጥ ያሳሰበኝ ግን ያለኮንዶም ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸሜ ነው ትላለች። ሄይሊ እንደምትለው፤ በግብረ ስጋ ግንኙት ወቅት ኮንዶም ስለመጠቀም ለማውራት ምቾት አይሰጣትም። ''አንዳንዴም መከላከያ ስለመጠቀም ባወራ ጓደኛዬ ምን ይለኛል? ብዬ እተወዋለው።'' • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች • የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር የእንግሊዙ የማኅበረሰብ ጤና ቢሮ በቅርቡ በሠራው ጥናት መሰረት፤ እድሜያቸው ከ16 እስከ 24 የሆኑ ወጣቶች አብዛኛዎቹ ከፍቅር ጓደኛቸው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ከአስር ወጣቶች አንዱ ደግሞ እስከነጭራሹ ኮንዶም ተጠቅመው አያውቁም። በአውሮፓውያኑ 2003 በተደረገ ጥናት መሰረት ግን እድሜያቸው ከ16 እስከ 24 ከሆኑ ወጣቶች መካከል 43 በመቶ የሚሆኑት ኮንዶም እንደሚጠቀሙ ተናግረው ነበር። ከአስር ዓመት በኋላ ያሉትን ቁጥሮች ያመሳከሩት ባለሙያዎች እንግሊዝ ውስጥ ብቻ ኮንዶም የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር 36 በመቶ ቀንሷል ብለዋል። አሜሪካ ውስጥ ኮንዶም ይጠቀሙ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር 2007 ላይ ከነበረው 62 በመቶ፤ በ2017 ወደ 54 በመቶ ቀንሷል። በዚሁ ጥናት ላይ እንደተጠቆመው፤ በግብረ ስጋ ግንኙት የሚተላለፉ በሽታዎች በብዛት የሚታዩት እድሜያቸው ከ16 እስከ 24 ዓመት ክልል ውስጥ ባሉ ወጣቶች መሆኑ ነገሮችን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጓቸዋል። እንግሊዝ ውስጥ እንደ ጨብጥና ቂጥኝ ያሉ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች የተያዙ ወጣቶች ቁጥር 2017 ላይ 20 በመቶ ጨምሮ የነበረ ሲሆን፤ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገዱ ያለመከላከያ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ነው። የኮንዶም ተወዳጅነት የቀነሰበት ዋነኛ ምክንያት ተብሎ የሚገመተው እርግዝናን የሚከላከሉ የተለያዩ አይነት ዘመን አመጣሽ አማራጮች ቁጥር መጨመር ነው። እንግሊዝ ውስጥ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን የሚገዙ ወጣት ሴቶች ቁጥር ከምን ጊዜውም በላይ ጨምሯል። በ1950ዎቹ መተዋወቅ የጀመረው ኮንዶም ምንም አይነት ለውጥ ሳይደረግበት እስካሁን ድረስ አለ። ምናልባትም ከኮንዶም ጋር የተያያዙ ብዙ ለውጦች አለመኖራቸው ሰዎች በቀላሉ እንዲሰለቹትና ወደሌሎች አማራጮች እንዲሄዱ ሳያደርጋቸው እንዳልቀረ ይገመታል። ቤት ሠራሽ ኮንዶሞች ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ መዋል የጀመሩት በጥንት ዘመን ሲሆን፤ የዛኔ የነበሩ ሰዎች የበግ አልያም የፍየል አንጀትና የሽንት ፊኛ ይጠቀሙ ነበር። ከኤችአይቪ ጋር ተያይዘው የሚሠሩ ማስታወቂያዎችና መልእክቶች መቀነስ በራሱ ለኮንዶም ጥቅም ላይ አለመዋል የራሱን የሆነ አስተዋጽኦ አለው። በተለይ ደግሞ ባደጉት አገራት የኤችአይቪ ስርጭት እጅጉን የቀነሰና ጠፍቷል በሚባል ደረጃ መሆኑ በተለይ ወጣቶች ኮንዶም ለመጠቀም የሚያስገድዳቸው ነገር እንደሌለ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች • ኤምአርአይ ምንድነው? ከነዚህ ነገሮች ሁሉ ወጣ ስንል ደግሞ ያልተፈለገ እርግዝና መረሳት የለበትም። ብዙ ወጣት ሴቶች በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ይልቅ ያልተፈለገ እርግዝናን ይፈራሉ። ኮንዶም መጠቀም ካለባቸውም እርግዝናን ለመላከል እንደሆነ እያሰቡ ነው የሚያደርጉት። የሥነ ተዋልዶ ጤና ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ሲንቲያ ግራሃም እንደሚሉት፤ በተለይ ደግሞ ወጣቶች ኮንዶም መጠቀም ከግብረ ስጋ ግንኙነት የሚገኘውን ደስታ ይቀንስብናል ብለው ያስባሉ። አብዛኛዎቹ ወንዶች ደግሞ ኮንዶም ሲጠቀሙ ብልታቸው በተገቢው ሁኔታ እንደማይነቃቃላቸው ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ሲንቲያ ግን ወጣም ወረደም ኮንዶም መጠቀምን የመሰለ ቀላልና ጠቃሚ አማራጭ የለም ብለው ያምናሉ።
news-53666383
https://www.bbc.com/amharic/news-53666383
ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ፡ የአውቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ 75ኛ ዓመት ሲታወስ
ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 3 ዓለም በአሰቃቂነቱ የሚያወሳው የጃፓኖቹ ሂሮሺማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ የአሜሪካ የአውቶሚክ ቦምቦች የዘነቡበት፣ የሰው ልጅ እንደ ቅጠል የረገፈበት 75ኛ ዓመት ነው።
በሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ ሲዘከሩ በእነዚህ የቦምብ ጥቃቶች ምን ያህል ሰዎች እንዳለቁ ትክክለኛ ቁጥር ባይኖርም ከሂሮሺማ 350 ሺህ ሕዝብ ውስጥ 140 ሺህዎቹ ሞተዋል። በናጋሳኪም እንዲሁ 74 ሺህዎች ተፈጅተዋል። በአውቶሚክ ቦምቡ ጥቃቱ ምክንያት ጃፓን በ1937 እጅ ሰጥታለች። እንዲሁም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ክፍል የሆነውና በእስያ የነበረውን ጦርነት ማብቂያን ያበሰረ ነው ቢሉም አንዳንዶች በዚህ ሃሳብ አይስማሙም። ጃፓን እጅ ለመስጠት ዳር ዳር እያለች የነበረች ከመሆኑ አንፃር ሽንፈቷን ከአውቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ ጋር ማያያዝ ትርጉም አልባ ነው ይላሉ። ማን ያውራ የነበረ? ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ ከዚህ እልቂት የተረፉት ስለማይሽር ጠባሳቸውና ህመማቸው ይናገራሉ። የእልቂቱ ተራፊዎችም በጃፓናውያን ዘንድ ስም ተሰጥቷቸዋል፤ 'ሂባኩሻ' ይባላሉ። ተራፊዎቹም ከሞቱት በላይ ሆኑ እንጂ ያጋጠማቸው ችግርና ስቃይ እንዲሁ ዝም ብሎ በቃላት የሚነገር አይደለም። በጨረር በመመረዛቸው ለዘመናት የሚወልዷቸው ልጆች የአካል ጉዳት ያለባቸው እንዲሆኑ እንዲሁም ለሥነ ልቦና ጉዳት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል። የእንግሊዟ ፎቶ ጋዜጠኛ ሊ ካረን ስቶው የእልቂቱን የተረፈውን በፎቶ አስቀርታለች፤ እንዲሁም ትናንት የተፈጠረ በሚመስል ሁኔታ ከ75 ዓመታት በፊት የተፈጠረውንም ስቃይ ከሦስት ሴቶች አንደበት ሰምታለች። ቴሩኮ ኡኖ ነርስ ሆነው እያገለገሉ በነበረበት ወቅትና ከአራት አመት በፊት ቴሩኮ ኡኖ ዕለቱ ሐምሌ 30/1937 ዓ.ም ነበር፤ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በሂሮሺማ ላይ የአውቶሚክ ቦምብ የጣሉት። በህይወት የተረፉት ቴሩኮ የ15 አመት ታዳጊ ነበሩ። በጥቃቱ ወቅት ቴሩኮ የሁለተኛ ዓመት የነርስ ተማሪ ነበሩ። ትምህርታቸውንም ይከታተሉ የነበረው ሂሮሺማ ሬድ ክሮስ በሚባል ሆስፒታል ውስጥ ነበር። በጥቃቱም የተማሪዎቹ ማደሪያ በእሳት ጋየ፤ ቴሪኮ እሳቱን ለማጥፋት ቢታገሉም የበርካታ ተማሪዎች ህይወት በእሳት አደጋው ተቀጠፈ። አንዳንድ ነገሮች እንደ ሩቅ ህልም ትዝ ቢሏቸውም፤ በዚያ ሳምንት በእሳት የተቃጠሉ ሰዎችንና አሰቃቂ አደጋዎችን በህይወት እያሉ አይረረሷቸውም። በሞትም ቢሆን የሚከተላቸው ይመስላቸዋል። እሳቸውን ጨምሮ በርካታ ነርሶች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ህይወት ለማትረፍ ቀን ከሌት እየለፉ ነበር። ምግብም ውሃም ለሁሉም በቂም አልነበረም። ቴሩኮ ተመርቀውም በዚያው ሆስፒታል ሥራቸውን ቀጠሉ። በቃጠሎው ወቅት በሚደርስ አደጋ የሰውነት ቆዳቸው ለተለበለበ ግለሰቦች የሚደረገውን የቀዶ ህክምና ድጋፍም ማድረግ ጀመሩ። ቶሞኮ ከእናቷ ቴሩኮና ከአባቷ ታትሱዩኪ ጋር በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ህይወት ትቀጥላለችና ቴሩኮ ከአውቶሚክ ቦምም ፍንዳታ የተረፈውን ታትሱዩኪም ጋር በትዳር ተጣመሩ። የመጀመሪያ ልጃቸውንም ፀነሱ፤ አይናቸውን በአይናቸው ለማት ቢጓጉም ልጃቸው በጤና ትወለድ ይሆን? የሚለውም ሌላ ጭንቀት ነበር። በህይወትስ ትኖራለች? የሚለውም አሳሳቢ ሆነ። ልጃቸው ቶሞኮም ተወለደች፤ ለቴሩኮም ተስፋን ፈነጠቀችላቸው፤ ለቤተሰቡም የአዲስ ህይወት መመስረትን አበሰረች። "ሲዖልን ባላየውም በህይወታችን ያሳለፍነው ስቃይ ግን ሲዖል ተብሎ ሲነገር እንደሰማሁት ነው። መቼም ቢሆን ሊደገም የማይገባ ሰቆቃ ነው" ይላሉ ቴሩኮ። "የኒውክሊየር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አንዳንድ ሰዎች ጥረት ቢያደርጉም የመጀመሪያ ደረጃ ቁርጠኝነት የሚያስፈልገው ከመንግሥታት ነው። እነሱ ይህ ሊወገድ ይገባል ማለት አለባቸው" የሚሉት ቴሬኮ "የዓለም መንግሥታት ሁሉ በአንድነት የኒውክሊየር መሳሪያዎችን በመቃወም ትብብራቸውን ሊያሳዩ ይገባል" ይላሉ። ቴሩኮ ከልጃቸው ቶሞኮና ከልጅ ልጃቸው ኩኒኮ ጋር ከአራት አመታት በፊት "ለሰባ አምስት ዓመታት ያህልም ዛፍ፣ ሳርም አይበቅልም የተባለባት ሂሮሺማ በአሁኑ ጊዜ አረንጓዴ ሆናለች። የከተማዋ ወንዞች ከእጸዋቱ ጋር ውብ አድርገዋታል" ትላለች የቴሩኮ ልጅ ቶሞኮ። ምንም እንኳን ከተማዋ ተመልሳ ውበቷን ብትጎናፀፍም "ሂባኩሻ" [ከቦምቡ ጥቃት የተረፉት] በጨረሩ መርዛማነት እየተሰቃዩ ነው። ሰቆቃቸውም ለልጅ ልጅ ተርፏል። "የሂሮሺማና ናጋሳኪ ቦምብ ጥቃት ትዝታዎች ከአዕምሯችን ቢደበዝዝም አሁንም መስቀለኛ መንገድ ላይ ነን።" "የወደፊቱ ዕጣ ፈንታችን በእጃችን ነው። ሰላም እውን የሚሆነው እሳቤያችንን ሰፋ ስናደርገው ነው። ለሌሎች ማሰብ ስንጀምር፤ እሱንም እውን ለማድረግ የሚጠበቅብንን ስንተገብር ነው። ሰላምን ለመገንባት የማያሰልስ ጥረት ያስፈልጋል" በማለት የቴሩኮ የልጅ ልጅ ኩኒኮም ታስረዳለች። "የአውቶሚክ ቦምቡ ገፈት ቀማሽ አይደለሁም፤ ሂሮሺማን የማውቃት እንደገና ከተገነባች በኋላ ነው። ግን ምን አይነት ዘግናኝና አሰቃቂ እልቂት እንደነበር መገመት እችላለሁ" ትላለች። ከእልቂቱ የተረፉትን ታዳምጣለች። በዚያች ቀን ከተማዋ እንዴት እንደጋየች፣ ሰዎች፣ ወፎች፣ ዛፍ፣ ሳርና ቅጠሉ ሳይቀር እንደተቃጠለም ነግረዋታል። ሂሮሺማ ከአቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ በኋላ የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ አይደሉም፤ ለእርዳታ የመጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሞተዋል። ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ፍለጋ ከሌላ ከተሞች የመጡ እንዲሁ አልቀዋል። የተረፉትም ለማይድን ህመም ተጋልጠዋል። ኩኒኮ ከሂሮሺማና ናጋሳኪ የተረፉትን ብቻ ሳይሆን በዩራኒየም ማዕድን ቁፋሮ የሚሰሩ፣ በማዕድን ማበልፀጊያ አካባቢ የሚኖሩ፣ የኒውክሊየር መሳሪያዎችን የሚሞክሩና፣ በዚህም ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰቃዩ ሰዎችም ዕጣ ፈንታ ተመሳሳይ ከመሆኑ አንፃር ከእነሱም ጋር ያላት ግንኙነት ጠበቅ ያለ ነው። ኤሚኮ ኦካዳ ኤሚኮ ኦካዳ በአለም ላይ ያሉ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያዎችን ቁጥር የያዘ ግራፍ እያሳዩ በሂሮሺማ ላይ የአውቶሚክ ቦምብ ሲጣል ኤሚኮ የስምንት ዓመት ልጅ ነበሩ። በፍንዳታውም ታላቅ እህታቸው ሚየኮን ጨምሮ አራት የቤተሰባቸው አባላት ተገድለዋል። እህታቸው ኤሚኮንም ሆነ ሌሎች ቤተሰባቸውን ፎቶ ዘመድ ቤት ሲያዩ ያ ጨለማ ጊዜ ድቅን ይልባቸዋል። ኤሚኮ ከእናታቸው ፉኪ ናካሶና ከእህታቸው ሚዬኮ ጋር የዚያችን ዕለት እህታቸው በጠዋት ተነስታ "በኋላ እንገናኝ" ብላ እየፈነደቀች ወጣች። "ገና አስራ ሁለት ዓመቷ ነበር። ፈገግታ የማይለያት፤ ህይወትን በተስፋ የምታይ ልጅ ነበረች" ይላሉ ኤሚኮ። ነገር ግን ከወጣችበት አልተመለሰችም፤ የት እንደደረሰችም አልታወቀም። ቤተሰቦቿም ለዓመታትም ተስፋ ሳይቆርጡ እናገኛታልን ብለው ካሰቡበት ቦታ ሁሉ ፈለጓት። አስከሬኗንም አላገኙ። እናም በህይወት ትኖራለች በማለትም በተስፋ መኖር ጀመሩ። በወቅቱም የኤሚኮ እናት ነፍሰ ጡር ነበሩ፤ ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ በሚያሳዝን ሁኔታ ፅንሱ ጨነገፈ። "በቤታችን የሚላስ የሚቀመስ አልነበረም። ስለ ጨረሩ የምናውቀው ነገርም ስላልነበረ ተመረዘ አልተመረዘ ያገኘነውን ዕቃም ሆነ ምግብ መሰብሰብ ጀመርን" ይላሉ። በእነዚያ ተስፋ አስቆራጭ ቀናትም ሰዎች የሚበሉት ሲያጡ ምግብም ይሰርቁ ነበር፤ "ውሃማ ብርቅ ነበር" ይላሉ። ያ አስቸጋሪ ጊዜ አሁን ተረስቷል። የኤሚኮ እህት ሚዬኮ የጃፓን ባህላዊ ዳንስ ቡዮን እየደነሰች ከትንሽ ጊዜያት በኋላ አስደንጋጭ ነገር መከሰት ጀመረ። የኤሚኮ ፀጉራቸው ይረግፍ ጀመ፣ ድዳቸው ያለማቋረጥ ይደማል እንዲሁም ያለ ምክንያትም መድከም አመጡ። "በወቅቱ በጨረር መመረዝ ምን እንደሆነ አናውቅም ነበር። ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ነው የደም ህዋሳቶቼ በትክክል ማመንጨት እንደማይችሉ የተነገረኝ" ይላሉ። በሂሮሺማ በየዓመቱ ጥቂት ቀናት ፀሐይዋ ስትጠልቅ ደማቅ ቀይ ቀለም ሰማይ ላይ ይታያል። ከመድመቋ የተነሳ የሰዎችም ፊት ወደቀይነት ይቀየራል። ይህም ሁኔታ አስደሳች ቢመስልም ለእሳቸው ግን ወደኋላ ይወስዳቸውና፤ ከተማዋ የተቃጠለችበት ሁኔታ ድቅን ይልባቸዋል። "ለሦስት ቀናት ያህል ከተማዋ ስትቃጠል ነበር፤ ለዚያም ነው ያንን የሚያስታውሰኝን ሁሉ የምጠላው። ፀሐይዋ ስትጠልቅ ማየት አልፈልግም፤ በከፍተኛ ሁኔታ ነው የምጠላው" ይላሉ። ከቦምቡ ጥቃት የተረፉት በርካቶች ታሪካቸውንም ሳይነግሩ፤ እንደተማረሩ ህይወታቸው አልፏል። "እነሱ መናገር ባይችሉም እኔ የነበረውን እናገራለሁ" ይላሉ። "በርካቶች ዓለም ሰላም እንድትሆን ምኞታቸውን ይናገራሉ። ለእኔ ግን የሚቀድመው ድርጊት ነው። የዓለም ሕዝቦች ማድረግ የምንችለውን መፈፀም አለብን።" "እኔም ብሆን ለልጆቼና ለልጅ ልጆቼ የተሻለ ህይወት እንዲመሩ፤ በደስታ እንዲኖሩ የምችለውን ማድረግ አለብኝ።" ሬይኮ በአምስት አመታቸውና ከአራት አመታት በፊት ሬይኮ ሃዳ የትውልድ ቀያቸው ናጋሳኪን አውቶሚክ ቦምቡ እንዳልነበረ ሲያፈራርሳት ሬይኮ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ነበሩ። ዕለቱ ነሐሴ 3/1937 ከረፋዱ አምስት ሰዓት ገደማ ነበር። ያስታውሳሉ ዕለቱ ሐሙስ ነበር። በጠዋትም በአየር ጥቃት ዙሪያ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ይተላለፉ ስለነበር ሬይኮም ቤታቸው እድብ ብለው ተቀመጡ። ማስጠንቀቂያው ሲቆምም አካባቢያቸው ወደሚገኝ ምኩራብ አመሩ። የአየር ጥቃት ይደርሳል የሚሉ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ በመነገሩ ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ አቁመው ነበር። ጊዜያቸውንም በምኩራብ ውስጥ በማጥናት ያሳልፉ ነበር። ሬይኮ ወደ ምኩራቡ ከደረሱ ከአርባ ደቂቃ በኋላ መምህራቸው አሰናበቷቸው፤ ሬይኮም ወደቤታቸው አቀኑ። ቤት ሊገቡ ሲሉ "ደረጃውን ወጥቻለሁ መሰለኝ። ድንገት የሆነ ድብልቅልቅ ያለ ነገር ተፈጠረ። በቃላት መግለፅ የማይቻል የብርሃኑ ድምቀት አይንን የሚያጥበረብር ቀለማት ማየት ጀመርን። ቢጫ፣ ብርቱካናማ፣ . . . ሁሉም ተደባልቆ እንደ ህልም አየን።" "ምን እንደሆነ እንኳን ለማሰብ ጊዜ ሳላገኝ ሁሉ ነገር ነጭ ሆነ።" "ከዚያም ብቻዬን የቀረሁ መሰለኝ። ከዚያም ከፍተኛ ድምፅ አምባረቀ፤ ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ አለ። እኔም አቅሌን ስቼ ወደቅኩ።" በአቶሚክ ቦምቡ የፈራረሰችው የናጋሳኪ ከተማ ከዚያም ድንገት ሲነቁ መምህራቸው ያላቸው ነገር ትዝ አላቸው። በአየር ጥቃት ወቅት ወደተዘጋጁት ድንገተኛ መሸሸያ ቦታዎች ማምራት። እናታቸውን ቤት ውስጥ አገኟቸውና ተያይዘውም በአቅራቢያቸውም ወዳለ መጠለያ አመሩ። "ምንም መቧጨር እንኳን አልደረሰብኝም። የኮንፒራ ተራራ አድኖኛል። በተራራው ሌላ ክፍል የሚኖሩት ግን እንደኛ እድለኛ አልነበሩም በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል።" በርካቶችም ተሰደው ወደእነሱ አካባቢ መጡ። ሁኔታቸው የሚዘገንን ነበር። "አይናቸው የተጎለጎለ፣ ፀጉራቸው የተቃጠለ፤ እርቃናቸውንና ብዙዎቹም ሰውነታቸው ተቃጥሎ ቆዳቸው ተንጠልጥሎ ነበር" በማለት ያስታውሳሉ። እናታቸውን ጨምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እናቶች ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች አቅራቢያቸው ወደሚገኘው የንግድ ኮሌጅ አዳራሽ ወሰዷቸው። እዚያም አረፍ እንዲሉ አደረጓቸው። ሬይኮ ከአባታቸው ኬዚዮ ኡራና ታላቅ እህታቸው ሺዙዬ ኡራ "ውሃ ጠማን ይላሉ። ውሃም እንዳመጣም ታዘዝኩ። የተሰባበረ ባሊ አገኘሁና ቅርብ ወዳለ ወንዝ ሄጄ ቀድቼ መጣሁ።" "ውሃውን እንደጠጡትም ብዙዎቹ ሞቱ። . . . አንድ በአንድ ሞቱ።" "ወቅቱ ሞቃታማ ነበር ። አስከሬናቸው እተበላሸ ጠረን በማምጣቱ እንዲቃጠል ተደረገ። አስከሬናቸው በኮሌጁ መዋኛ ገንዳ ተከምሮ ነበር። እንጨትም ተሰብስቦ ነደደና ተቃጠ፤ አመድም ሆኑ።" "እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማወቅ ይከብዳል። እንደ ሰው ልጆች በክብር አልሞቱም።" "የወደፊቱ ትውልድ መቼም ቢሆን እኛ ባለፍንበት መንገድ ማለፍ የለበትም። መቼም ቢሆን፤ በጭራሽ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ መፍቀድ የለብንም።" "ሰላምን የሚፈጥሩት ሰዎች ናቸው። ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት ብንኖርም፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ብንናገርም ሰላም እንዲሰፍን ያለን ምኞት ተመሳሳይ ነው።" ሬይኮ ሃዳ
news-52367655
https://www.bbc.com/amharic/news-52367655
ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ የሰው ህይወት አለፈ
በከባድ ዝናብ ምክንያት በኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ጨምሮ በሌሎች ምሥራቅ አፍሪካ አገራት የጎረፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ተባለ።
የኬንያ ሜትዮሮሎጂ ክፍል ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ጎርፍ ሊያጋጥም እንደሚችል አሰጠንቅቋል። ተቋሙ እንዳስታወቀው በዋና መዲናዋ ናይሮቢና በምዕራብና ምሥራቅ የአገሪቷ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል። ከትናንት በስቲያ በጋሞ ዞን የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፋና መዘገቡ ይታወሳል። በምዕራብ ኬንያ እየጣለ ያለውን ከባድ ዝናብም ተከትሎ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ ከ10 ሰዎች በላይ ሕይወታቸው አልፏል። በተመሳሳይ በኡጋንዳም ከባድ ዝናብ እየጣለ መሆኑን ተከትሎ የቪክቶሪያ ሐይቅ መጠን በመጨመሩ በሐይቁ ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው እሁድ አሳስበዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍልም በጎርፍ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ከ10 በላይ ሰዎች ድግሞ ሞተዋል። ባለፈው ዓመት በህዳርና ታህሳስ ወር ባልተጠበቀ መልኩ የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ ማስከተሉ ይታወሳል። በመሆኑም አሁን እየጣለ ያለው ዝናብም ባልተጠበቀ መልኩ ከባድ እንደሚሆን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
51670264
https://www.bbc.com/amharic/51670264
በናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ
ናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያውን ሰው ሪፖርት አደረገች።
ታማሚው ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን ናይጄሪያ ውስጥ እንደሚሰራና ከሶስት ቀን በፊት( ፌብሪዋሪ 25) ከሚላን ወደ ሌጎስ መምጣቱ ተነግሯል። የናይጄሪያ ጤና ጥበቃ ባለሰልጣናት ግለሰቡ ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው፣ ሌጎስ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት የግል አውሮፕላን ተፈላጊነት ጨመረ • ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገሯ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉዞዎችን አገደች • "ቻይና፣ ዉሃን በመሆኔ ደህንነቴ የተጠበቀ ነው" ኢትዮጵያዊው ተማሪ የናይጄሪያ መንግሥት የብሄራዊ ድንገተኛ ጊዜ እቅድ አውጥቶ አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራው በመግባት የመከላከል ሥራውን መስራት መጀመሩን ተናግረዋል። ከታማሚው ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉት በአጠቃላይ መለየት መጀመራቸውን ባለሰልጣናቱ ፀጨምረው አስረድተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወሳኝ ነጥብ ላይ መድረሱን በመግለጽ አገራት አስፈላጊውን የመከላከል እርምጃ ሁሉ እንዲወስዱ አሳስቧል። ከቻይና ውጪ በአሁን ወቅት ኢራንና ጣሊያን የወረርሽኙ መገኛ ማዕከል ሆነዋል። በኢራን ከፍተኛ ባለሰልጣናት ሳይቀር በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰውም ሞቷል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በሚገኙ ከ50 በላይ ሀገራት 80 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ይታወቃል። እስካሁን ድረስ ከቻይና ውጪ 60 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በቻይና በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። በአፍሪካ ከናይጄሪያ ውጪ በአልጄሪያ እንዲሁም ግብጽ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መገኘቱ ይታወሳል።
news-55391881
https://www.bbc.com/amharic/news-55391881
ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው
በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች አገር አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው።
አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ባለው ብቻ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ቤልጂየም ሁሉም ወደ ታላቋ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል። ዛሬ ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል። ለፈረንጆች ገናና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል። የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑም ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም። ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮናቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል እንዲባል አድርጓል። የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ይፋ ባደረገች በሰዓታት ውስጥ ኔዘርላንድ ማንኛውም በረራ ከታላቋ ብሪታኒያ እንዳይመጣብኝ ብላለች። ፈረንሳይ በተመሳሳይ ከባድ መኪና ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ ጀልባዎች፣ እግረኛና በበራዎችን ከእንግሊዝ በኩል ወደ አገሯ እንዳይገቡብኝ ብላለች። አየርላንድና ጀርመንም ተመሳሳይ ውሳኔን አሳልፈዋል። ጣሊያን እስከ ጃንዋሪ 6 ማንም ከታላቋ ብሪታኒያ አይምጣብኝ ብላለች። በአዲሱ የቫይረስ ዝርያ የተጠቃ አንድ ሰው በጣሊያን መገኘቱም ድንጋጤን ፈጥሯል። ቱርክ፣ ቡልጋሪያና ኦስትሪያም ከታላቋ ብሪታኒያ ጉዞ እቀባ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩናይትድ ኪንግደም አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም እስካሁን በተዘጋጁት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር።
news-53041154
https://www.bbc.com/amharic/news-53041154
በዛፍ ላይ ተሰቅለው የተገኙት ጥቁር አሜሪካውያን አሟሟት ላይ ዳግም ምርመራ ሊጀመር ነው
የአሜሪካ ፌደራል ባለስልጣናት በቅርቡ በዛፍ ላይ ተንጠልጥለው የተገኙት ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን አሟሟት ላይ የተደረገውን ምርመራ ሊገመገም እንደሆነ አስታውቀዋል።
ግለሰቦቹ ሞተው የተገኙት በካሊፎርኒያ ሲሆን፤ ከአሟሟታቸውም ጋር በተያያዘ የተቀጣጠለውንም ተቃውሞ ተከትሎ ነው ምርመራው እንደገና እንዲጀመር የተወሰነው። የአካባቢው ፖሊስ ሮበርት ፉለርና ማልኮልም ሃርሽ የተባሉት ጥቁር አሜሪካውያን ግድያ አይደለም ብሏል። በካሊፎኒያ ግዛት በተለያየ ከተማ በዛፍ ላይ ተንጠልጥለው የተገኙት ጥቁር አሜሪካውያኑ በሁለት ሳምንታት ልዩነት ነው የሞቱት። ብዙዎች ራሳቸውን አጥፍተው ሳይሆን ተገድለው ነው በሚልም ምርመራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የ24 አመቱ ሮበርት ፉለር ፓልሜድ በምትባለው አካባቢ ከሚገኝ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ የተገኘው ሰኔ 3፣ 2012 ዓ.ም ነው። ምንም እንኳን የአካባቢው ባለስልጣናት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ራሱን አጥፍቶ ነው ቢሉም፤ ብዙዎች አልተቀበሉትም። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ምርመራ እንዲካሄድ ፊርማቸውን አሰባስበዋል። ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ራሱን ነው የገደለው የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ሊዋጥላቸው አልቻለም "የሚነግሩን ነገር በሙሉ ስህተት ነው፤ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ወንድሜ ራሱን ማጥፋት አይፈልግም ነበር" በማለት የሮበርት ፉለር እህት ዳይመንድ አሌክሳንደር ተናግራለች። ሌላኛው ሟች ማልኮልም ሃርሽም ግንቦት 23፣ 2012 ዓ.ም ቪክቶርቪል በምትባል አካባቢ በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ነው የተገኘው። ባለስልጣናቱም የ37 አመቱ ማልኮልም ራሱን አጥፍቷል የሚል ግምት ቢኖራቸውም አሟሟቱን በተመለከተ ይፋዊ መረጃ ገና አልወጣም። "አሟሟቱን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች አሉን፤ ምላሾችም እየጠበቅን ነው። ወንድሜ ሁሉን ወዳጅ ነበር። ለቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ቀና ነበር። እንዲህ አይነት ሰው ራሱን ያጠፋል ማለት አያሳምንም" በማለት አህቱ ሃርሞኒ ሃርሽ ለሚዲያዎች ተናግራለች። የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ)፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የካሊፎርኒያ ግዛት ምርመራ ቢሮ፣ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች የፍትህ ዘርፍ ክፍል ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በላኩት መመግለጫ ግለሰቦቹ ላይ የተከናወኑትን ምርመራዎች እየተገመገሙና እንደገናም ምርመራ ሊጀመር መሆኑን ነው። የመጀመሪያ ምርመራው የተከናወነው በሎስ አንጀለስና ሳንበርናርዲኖ ፖሊስ ቢሮዎች ሲሆን ለግምገማውም እንደሚተባበሩ አስታውቀዋል። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ የሁለቱ ግለሰቦች አሟሟት ላይም ምርመራ እንዲካሄድ ጫና አሳርፏል።
50127054
https://www.bbc.com/amharic/50127054
ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በዶይቼ ቬለ (የጀርመን ድምጽ ራዲዮ) ዘገባ ምክንያት በኤርትራ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀ።
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል "ያልተቋረጠ የመረረ ትችት" ባሉት የዶይቼ ቬለ ዘገባ ምክንያት በኤርትራ የጀርመን አምባሳደር ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በጀርመን መንግሥት ፈንድ የሚንቀሳቀሰው የዶይቼ ቬለ የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ አርታኢዎች የኤርትራን ብሔራዊ አገልግሎት በተመለከተ እንዲሁም በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሳሳተ መረጃን ያስተላልፋሉ ሲሉ ነቅፈዋል። የኤርትራን መንግሥት ያስቆጣው የዶይቼ ቬለ ዘገባ በትክክለ የቱ እንደሆነ ግልጽ ባይሆንም፤ በቅርቡ በድረ-ገጹ ላይ ይዞት የወጣው ጽሁፍ አንዱ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል። ይህ ከ10 ቀናት በፊት በአማርኛ ዴስክ ኃላፊ በሆነው ሉደር ሽዶመስኪይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈው የግል አስተያየት፡ ''ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የለውጥ አራማጅ ቢሆኑም ከኤርትራ ጋር በደረሱት ሰላም ምክንያት የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰጣቸው መወሰኑ ስህተት ነው'' የሚል ይዘት አለው። ሉደር በጽሁፉ የኤርትራውን ፕሬዝደንት "ብስጩና ፈላጭ ቆራጭ መሪ" ሲል የገለጻቸው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ". . . ስልጣን ላይ ለመቆየት ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ዜጎቹን በሰንሰለት ያስራል። . . . በዓለም ዓይን በግማሽ እድሜው በሚያንሰው መሪ መበለጥ የሚያስደስትው አይሆንም" በማለት ፕሬዝደንቱን ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር አነጻጽሮም አስነብቧል። በጉዳዩ ላይ የጀመርን መንግሥትም ሆነ ዶይቼ ቬለ ያሉት ነገር የለም። • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ጨምረውም፤ ቢቢሲን በተመለከተም ከዚህ ቀደም "ከአንድም ሁለቴ [በኤርትራ] የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር በጉዳዩ ላይ የመንግሥታቸው አቋም እና አስተያየት ምን እንደሆነ" መጠየቃቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። "በዚህም አስፈላጊ እርምጃዎች የማይወሰዱ ከሆነ ሌሎች አማራጮች/ዘዴዎች እንከተላለን" ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፈረዋል።
news-49889111
https://www.bbc.com/amharic/news-49889111
የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ለአራት ዓመት ከአትሌቲክስ ታገዱ
የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት ታገዱ።
በ2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ላይ ሳላዛር (መካከል) ሞ ፋራህ (በስተቀኝ ) ጋሌን ሩፕ (በስተግራ) የ61 ዓመቱ ሳላዛር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ፋራህን ማፍራት የቻለው የናይክ ኦሪጎን ፕሮጀክት ከ2011 እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ውሳኔው የተላለፈው በአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ለአራት ዓመት ያህል ምርመራ ሲደረግ ከቆየና ለሁለት ዓመት ያህል በፍርድ ቤት ክርክር ከተካሄደ በኋላ ነው። ምርመራው የተጀመረው ቢቢሲ በ2015 ፓናሮማ የተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ ጉዳዩን ካቀረበ በኋላ ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ይህ የቢቢሲ ፕሮግራም ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረገፅ ጋር በጋራ በመሆን በአሜሪካ ኦሪጎን ውስጥ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ስፍራ የሚሰጡ አበረታች መድሃኒቶችንና የሚካሄዱ ተገቢ ያልሆነ ተግባራትን አጋልጧል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ለስድስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናው፣ እንግሊዛዊው ፋራህ፣ ከ አሜሪካዊው ሳላዛር ጋር እንዲሰራ ይሁንታውን ሰጥቶት ነበር። በናይክ እየተከፈላቸው በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት ታግደዋል። ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ግን ገልጿል።
51186657
https://www.bbc.com/amharic/51186657
ርዕደ መሬት፡ እውን አዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር?
ሰኞ ጥር 11/2012 ንጋት አካባቢ መሬት ስትነዘር ሰምተናል ያሉ ሰዎች በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ያጋጠማቸውን ሲያጋሩ ነበር።
'አፍሪካ ኢንስቲቲዩት' የተባለ አንድ ገፅም ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ እንደነበር የሚጠቁም አንድ ድረ-ገፅ አያይዞ ትዊተር ላይ ፅፎ ነበር። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 እውን አዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ ሌሎች ሥፍራዎች የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ ነበር? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አታላይ አየለ [ፒኤችዲ] የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪ ናቸው። ተመራማሪው፤ በፉሪ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ያሉ ጣቢያዎችን ጨምሮ ከአምስት የተለያዩ ጣቢያዎች በተገኘ መረጃ መሠረት በምሥራቅ ኢትዮጵያ መኢሶ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አጣርተናል ይላሉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሰማቸው የመኢሶው ንዝረት ነው ሲሉ ያስረዳሉ። «መኢሶ አካባቢ በሪክተር ስኬል 5 የሚገመት የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጥሯል። ይህ የሆነው ዛሬ [ጥር 11/2012] 12 ሰዓት አካባቢ ነው። አዲስ አበባ ውስጥም ቢሆን ሰዎች ሊሰማቸው ይችላል። በተለይ ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች የበለጠ ሊሰማቸው ይችላል። በሪክተር ስኬል 5 ማለት እንግዲህ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል አይደለም፤ ነገር ግን ሰዎች ሊሰሙት ይችላሉ።» በተለይ አዋሽና አሰበ-ተፈሪ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጡ ጎልቶ የተሰማ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ደግሞ ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በመሆኗ መሰል ክስተቶች ይሰሟታል። ከዚህ በፊት መሰል የመሬት መንቀጥቀጦች በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ተከስተው ንዝረቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሲያስደነግጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ይላሉ ባለሙያው። «2009 አንኮበር አካባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። ባልሳሳት 4.7 ሪክተር ስኬል አካባቢ ነበር የተመዘገበው። ታኅሣሥ ውስጥ ነበር። የዛኔም አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ንዝረቱ ተሰምቶ ነበር።» አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምናልባት መሬት ላይ ያሉ ቤቶችን ያፈርስ ይሆናል እንጂ ብዙ ጉዳት አያደርስም ይላሉ። የደረሰ ጉዳት እንዳለ ገና አለማረጋገጣቸውንም ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስተናገደችው 1953 ላይ ሲሆን ካራቆሬ ተበሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በሪክተር ስኬል 6.5 ተመዝግቧል። በወቅቱ በደረሰ አደጋ 30 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቦ ነበር። ምንም እንኳ አንዳንድ አካባቢዎች በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ቢገኙም የመሬት መንቀጥቀጥ ኢትዮጵያን ይህን ያህል የሚያሰጋት አይደለም።
news-49541151
https://www.bbc.com/amharic/news-49541151
በቴክሳስ በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቴክሳስ ግዛት በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተደገሉ ታውቋል።
በግዛቲቱ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጎዜ በተከሰተው የጅምላ መሣሪያ ታጥቆ ያገኘው ሰው ላይ እየተኮሰ የነበረውን ታጣቂ በማስቆም ላይ ሳለ ተመትቶ መውደቁ ተነግሯል። ታጣቂው መኪናው ውስጥ ሳለ ነበር መንገደኞች እና ሞተር ብስክሌተኞች ላይ ይተኩስ የነበረው። ከዚያም አንድ መኪና ሰርቆ ጥቃቱን አጠናከረ። በዚህ መሃል አንድ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ተመትቶ ሊሞት ችሏል። በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ የተነገረለት ነጭ የጅምላ ጥቃት አድራሽ ለምን ጥቃቱን እንዳደረሰ እስካሁን አልታወቀም። ከአራት ሳምንታት በፊት እንዲሁ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ኤል ፓሶ በተሰኘች ከተማ አንድ ጅምላ ገዳይ የ22 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም። ጥቃት አድራሹ ምሽት 4፡00 ሰዓት ገደማ መሃል መንገድ መኪናው ውስጥ ሳለ ፖሊሶች ሲያስቆሙት ነው መተኮስ የጀመረው ተብሏል። በትላንትናው ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች ቆስለዋል፤ ከእነዚሀም ውስጥ ሶስቱ አባሎቼ ናቸው ብሏል ፖሊስ። ነገር ግን ሁሉም ተጎጂዎቹ በጥይት የተመቱ ሳይሆኑ ጥቃቱን ለማምለጥ ሲሞክሩ የተጎዱም አሉበት ሲል የከተማዋ ፖሊስ አክሏል። የኦዴሳ ከተማ ሆስፒታል ከተጎጂዎቹ መካከል የሁለት ዓመት ሕፃን እንደሚገኝ አሳውቆ 7 ሰዎች በሞት እና ሕይወት መካከል ናቸው ብሏል።
54341609
https://www.bbc.com/amharic/54341609
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በአስከሬን ላይ የሚደረገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ መቆሙ ተገለፀ
ኢትዮጵያ ከአስከሬን ላይ ናሙና በመውሰድ ታደርገውን የነበረውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማቆሟን አስታውቃለች።
ይህንን ያስታወቀችውም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ነው። የአለም ስጋት ሆኖ የቀጠለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት አገሪቷ የተለያዩ የመካላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን እየሰራች እንደነበር የጠቀሰው ደብዳቤው ከነዚህም መካከል ከአስከሬን የላብራቶሪ ናሙና መውሰድም ነበር። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ጋር በመሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ማስተባበሪያ ማዕከል በሟቋቋም የቫይረሱን ስርጭትና መጠን ለማወቅም ከተሰሩ ስራዎች መካከል ከአስከሬን የሚወሰድ የላብራቶሪ ናሙና መሆኑን አስታውሷል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ የቫይረሱ የማህበረሰብ ስርጭት ከ95 በመቶ በላይ በመሆኑና ከአስከሬን ይደረግ የነበረው የናሙና ምርመራም በህዝቡም ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሳበትም እንደነበር ደብዳቤው ጠቅሶ በነዚህም ምክንያቶች እንዲቆም ተወስኗል። በአሁኑ ወቅትም የብሄራዊ የኮቪድ-19 መከላከልና እና መቆጣጠር ግብረ ኃይል በወቅቱ ያለውን አለም አቀፋዊና ሃገራዊ ስርጭት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትም የመከላከሉና የምርመራው ስራ ይቀጥላል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም ሞት በኮሮናቫይረስ እንደሆነ ተደርጎም በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስቧል። ከሰባት ወራት በፊት የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ የተገኘባት ኢትዮጵያ እስከዛሬዋ እለት፣ መስከረም 19፣ 2013 ዓ.ም ባለው መረጃ በአገሪቷ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 73 ሺህ 944 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 177 ዜጎቿን በሞት ተነጥቃለች። በበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 30 ሺህ 753 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 260 ሺህ 929 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አከናውናለች።
news-56427912
https://www.bbc.com/amharic/news-56427912
በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ወልዳ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀችው
ፎዚያ ጀማል በ 2010 ዓ.ም ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ተመድባ ስትሄድ ገና አዲስ ሙሽራ ነበርች።
የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ፎዚያ በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 38 ኮርሶች 31 A+ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃለች በዩኒቨርስቲው የኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍል እንድትማር ስትመደብ ነፍሰጡር መሆኗን አወቀች። በዚህ ምክንያት ግን ምህርቷን ማቋረጥ አልፈለገችም። በእርግዝናዋ ወራት በዙሪያዋ ምን አማረሽ? ምን ይምጣልሽ? የሚል ወላጅ እና ባል ባይኖርም፤ እንደ ሌሎች የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በካፌም በቤተመጻህፍት በትምህርት ክፍልም እኩል እየተገኘች ትምህርቷን ተከታትላለች። ፎዚያ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቷን ስታጠናቅቅ የወሰደቻቸውን ኮርሶች በአጠቃላይ ኤ ያመጣች ስትሆን ሴት ልጅ ወልዳ ለመሳምም በቅታለች። ፎዚያ ከዚያ በኋላ በአንድ እጇ ልጇን አቅፋ በሌላ እጇ መጽሐፍ ዘርግታ ትምህርቷን በትጋተት ተከታትላለች። ትጋቷም ፍሬ አልባ አልነበረም። የሶስቱን ዓመት ትምህርት አጠናቅቃ ስትመረቅ ከወሰደቻቸው 38 ኮርሶች መካከል 31 A+ ሰባቱን ደግሞ A አምጥታለች። ፎዚያ ጀማል ከኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በ2012 ተመራዊ የነበረች ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በ2013 ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪዋን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቅቃ ተመርቃለች። የኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ከእርሷ ጋር አንድ ላይ 929 ተማሪዎችን አስመርቋል። ምዕራብ ሐረርጌ ቦኬ ወረዳ የተወለደችው ፎዚያ የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ትዳር መመስረቷን ለቢቢሲ ትናገራለች። በሶስት ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታዋ አንድ ዓመት ነፍሰጡር ሆና ሌላኛውን ዓመት ደግሞ ጨቅላ ልጇን እያሳደገች ስትማር የተለያዩ ፈተናዎች የነበሩ ቢሆንም ዓላማዋና ትኩረቷን በአንድ ጉዳይ ላይ በማድረግ በድል ማጠናቀቋን ትናገራለች። "ሥራዬ ነው ብለህ ራስህን አሳምነህ ከጀመርክ የማይቻል ነገር የለም። እኔም ነፍሰጡር መሆኔ በውጤቴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የለበትም በማለት በርትቼ ሳጠና ነበር፤ ነፍሰጡር ሆኖ በትምህርት ፈተና ውስጥ ማሳለፍ በዚያ ላይ ልጅን እያሳደጉ ፈታኝ ቢሆንም ያሰብኩትን አሳክቻለሁ። የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ሳለች እርግዝና ተጨማሪ ኃላፊነት ይዞባት ስላመጣ በእርግዝናና ልጅ ማሳደግ ነጥቧ እንዳይቀንስ ከበፊቱ በበለጠ ስታነብ እንደቆየች ታስታውሳለች። ከዚህ ስኬቷ ጀርባም የባለቤቷ ድጋፍ ብዙ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጻለች። ለዚህ ሁሉ ስኬቴ የባለቤቴ ሚና ትልቅ ነው የምትለው ፎዚያ "ባለቤቴ እውነቱን ለመናገር የተለየ ሰው ነው፤ እርሱ ለትምህርቴ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ልክ ለእርሱ እንደምማር ነው የሚወስደው፤ ከእኔ በላይ እርሱ ነው የሚጨነቀው። በሁሉም በኩል በጣም ያግዘኛል። እርሱ የስኬቴ ምስጢር ነው።" ፎዚያ ሶስት ዓመት ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በቆየችበት ወቅት ላስመዘገበችው ከፍተኛ ነጥብ ሁለት ዋንጫ እና አንድ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልማለች። እቅዴን ፈጣሪ ረድቶኝ ስለተሳካልኝ፣ ያሰብኩትን ስላሸነፍኩ በማለት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለች የወለደችውን ልጅ ሞኔት [ Mooneet] ብለው እንደሰየሟት ትናገራለች። ሞኔት የሚለው ወደ አማርኛ ሲመለስ አሸነፍን ማለት እንደሆነ ትናገራለች። ሴቶች ስኬታማ ለመሆን ቆራጥ መሆና ያስፈልገናል የምትለው ፎዚያ፣ ኋላ ቀር የሆኑትን አስተሳሰቦች በመተው የስኬት መንገዶችን ማየት አለብን በማለት ሴቶችን ትመክራለች። "ምንም አንችልም ብለን ራሳችንን ማሳመን የለብንም። አንችልም ብለን ራሳችንን ካሳመንን እውነትም አንችልም። እችላለሁ ብሎ ያመነ አእምሮ ይችላል። በሥራዬ ከግብ እደርሳለሁ ብላ የምትሰራ እደርሳለሁ ያለችው ቦታ ለመድረስ የሚከለክላት የለም " ትላለች። ፎዚያ በአሁኑ ጊዜ በኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል በመምህርነት ተቀጥራለች። ለወደፊት ደግሞ ትምህርቷን ማሳደግ እና ባገኘችውና እውቀት ኅብረተሰቡን የማገልገል ፍላጎት እነዳላት ትናገራለች።ፎዚያ ጀማል በ 2010 ዓ.ም ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ተመድባ ስትሄድ ገና አዲስ ሙሽራ ነበርች።
news-47743564
https://www.bbc.com/amharic/news-47743564
ለመጀመሪያ ጊዜ ከኤች አይቪ በሽተኛ ኩላሊት ተለገሰ
በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ኤች አይቪ ኤድስ በሽተኛ ወደ ሌላ የኩላሊት ልገሳ ተደረገ።
ኒና ማርቲኔዝ [መሀል] ቀዶ ጥገናው የተደረገው በአሜሪካ ሜሪላንድ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል ሲሆን ሁለቱም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። "በዓለማችን ኤች አይቪ ያለበት ሰው ኩላሊቱን ሲለግስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው" በማለት ዶ/ር ዶሪ ሴጄቭ ትናገራለች። ከዚህ በፊት በሚለግሰው ሰው ላይ ኤች አይቪ ከፍተኛ የኩላሊት በሽታ የመፍጠር ዕድል አለው ተብሎ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን አዲስ የመጡት መድኃኒቶች በኩላሊት ላይ ጉዳት እንደማያደርሱ ተረጋግጧል። ጆን ሆፕኪንስ የምትሠራው ዶ/ር ክርስቲን ዱራንድ ቀዶ ጥገናው "ኅብረተሰው ኤች አይቪን የሚያይበትን መንገድ ይፈትናል፤ ከዚም አልፎ መድኃኒቶች እንዲሻሻሉ ያደርጋል" ብለዋል። ታካሚዎቹ "በዚህ ልዩ ዕድል በጣም ደስተኛ ናቸው፤ አሁን የረጅም ጊዜ ውጤቱን ነው የምንጠባበቀው" በማለት ዶ/ር ዱራንድ ጨምረዋል። ቀዶ ጥገናው የተካሄደው ሰኞ ሲሆን ኩላሊት የለገሰችው የ35 ዓመቷ ኒና ማረቲኔዝ "በጣም ደህና ነኝ" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ኩላሊቷን ለመለገስ ያነሳሳት የ"ግሬይስ አናቶሚ" ተከታታይ ፊልም አንድ ክፍል እንደሆነ ተናግራ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን ቀዶ ጥገና ማድረጓ እንዳስደሰታትም ተናግራለች። "ዶክተሮቹ እኔን እየጠበቁ እንደነበር አውቃለው፤ ይህን የማድረግ ፍላጎት ያለው ማንም ሰው ቢሆን እንደሚቻል አሳይቻለው፤ ስለዚህ ቀጣዩን ሰው ለማየት ጓጉቻለው" ትላለች ኒና። ኩላሊት የተቀበለው ሰው እራሱን ለመግለፅ ያልፈለገ ቢሆንም ጤናው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሆነ ዶ/ር ዱራንድ ተናግረዋል። በዓለማችን ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከኤች አይቪ ጋር ይኖራሉ። • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች
news-41989509
https://www.bbc.com/amharic/news-41989509
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ
ኢትዮጵያ ከቻይና በመቀጠል ከሶሪያ እኩል የኢንተርኔት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ላይ ገደቦችን በመጣል በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ገልጿል።
ኢትዮቴሌኮም በበኩሉ ''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም'' ይላል። የቻይና እና የሩሲያ መንግሥታት የረቀቁ መንገዶችን በመጠቀም የኢንተርኔት ላይ ውይይቶችን እና ተጠቃሚዎችን በመግታት የጀመሩት ተግባር አሁን በመላው ዓለም ተንሰራፍቷል ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ይገልጻል። ኢትዮጵያ በፍሪደም ኦፍ ዘ ኔት (Freedom of the Net) ሪፖርት ''0=የኢንተርኔት ነጻነት ያለበት እንዲሁም 100=የኢንተርኔት ነጻነት የሌለበት'' በሚል መስፈርት ተመዝና 86 ነጥቦችን በማምጣት ከሶሪያ እኩል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ከቻይና ቀጥላ ተቀምጣለች። ሪፖርቱም ኢስቶኒያ እና አይስላንድ 6 ነጥብ በመያዝ በኢንተርኔት ነፃነት ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል። ሪፖርቱ የተከናወነው በ65 ሃገራት ሲሆን ሰሜን ኮሪያ እና ኤርትራ በጥናቱ ውስጥ አልተካተቱም። ''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም። ከዚህ በፊት የ ኦቨር ዘ ቶፕ (Over The Top) የሚባለውን ፌስቡክ እና የመሳሰሉ የማሕበራዊ ሚዲያዎች መጠቀም የሚያስችለውን አገልግሎት ብሔራዊ ፈተና ሲኖር ለተወሰነ ጊዜ እናግዳለን እንጂ በሃገራችን ኢንተርኔት ተዘግቶ አያውቅም'' በማለት የኢትዮ-ቴሌኮም የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አብዱራሂም ጨምረው እንደተናገሩት ፍሪደም ሃውስ የተሰኘው ድርጅት ከራሱ ፍላጎት ተነስቶ ያወጣው ሪፖርት ነው እንጂ እውነታውን የሚያሳይ አይደለም ብለዋል። ''ዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ህብረት (ITU) እና አይሲቲ አፍሪካ (ICT Africa) የመሳሰሉ ተቋማት ናቸው የኛን መሰረተ ልማት የሚያውቁት እና ሊመዝኑን የሚችሉት እንጂ ይህ ሪፖርት ተዓማኒነት የለውም'' ሲሉ ተናግረዋል። ፍሪደም ሃውስ ዓመታዊ ሪፖርቱን ''ማህበራዊ ሚዲያን በማዛባት ዲሞክራሲ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር'' በሚል ርዕስ ያወጣ ሲሆን በዋናነት ኢትዮጵያን በሚመለከት ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፡ ለአስር ወራት ያህል በስራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማኅበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ መደገፍን ጨምሮ ሌሎችንም መሰረታዊ የዜጎች መብቶች አፍኗል የሚለው ሪፖርቱ ራስን ሳንሱር የማድረግ እና ኃሳብን ከመግለፅ የመቆጠብ አዝማሚያዎች በአዋጁ ጊዜ ተጠናክረው ታይተዋል ሲል ይገልፃል፤ በርካቶች ኃሳባቸውን በኢንተርኔት መድረኮች ላይ በመግለፃቸው ታስረዋል፤ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ተከስሰው ተፈርዶባቸዋል በማለትም መንግስትን ይወነጅላል። ሪፖርቱ ጨምሮም በ2008 ዓ.ም የወጣው የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ የመንግስትን በዜጎች ግንኙነት ጣልቃ የመግባት እና መረጃ የመሰብሰብ ስልጣን ማስፋቱን የኢንተርኔት ነፃነትን ከሚያዳክሙ ምክንያቶች አንዱ ነው ይላል። በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ደካማ የቴሌኮም መሰረተልማት መኖሩ፣ የቴሌኮም አገልግሎት በመንግሥት ቁጥጥር ስር ብቻ መሆኑ እና የቴሌኮም ፖሊሲዎች ተጠቃሚዎችን የሚገደቡ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ሲል በዝርዝር ሪፖርቱ ያስቀምጣል። በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመረጃ ነጻነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራ ለነበረው አርቲክል 19 (ARTICLE 19) ተቀጣሪ የነበረው እና በኢትዮጵያ መንግሥት ከሃገር እንዲወጣ የተደረገው ፓትሪክ ሙታሂ በሪፖርቱ ላይ ይህን አስተያየት ሰጥቷል ''በኔ ግምገማ የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ያለውን ትክክለኛ ገጽታ ያሳያል።'' "ሰዎች ኢንተርኔትን እና የሞባይል ግንኙነትን ለመደራጀት፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ እና ለመቀስቀስ ይጠቀማሉ ይህም የኢትዮጵያን መንግሥት ስለሚያሳስበው የማይፈልጋቸውን ድረ-ገጾች፣ የኢንተርኔት እና የሞባይል አገልግሎቶችን ማቋረጥ የተለመደ ነገር አድርጎታል" በማለት ፓትሪክ ያብራራል። የሰሞኑ የኢትዮ-ቴሌኮም ምዝገባ ነፃነትን ይገድብ ይሆን? ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ? ፍሪደም ሃውስ እአአ1941 በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በሰብዓዊ መብቶች፣ በዲሞክራሲ እና በፖለቲካ ነጻነቶች ዙሪያ የመብት ስራዎችን እና ጥናቶችን ያከናውናል። እ.ኤ.አ በ2011 ከ1 በመቶ ትንሽ ብቻ ከፍ ብሎ ይገኝ የነበረው የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስርገት መጠን በ2016 ወደ 15 በመቶ ከፍ ቢልም እንዲሁም በተመሳሳዩ ጊዜ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭት ከ16 በመቶ ወደ 51 በመቶ ቢያድግም አገሪቷ አሁንም ከዓለማችን እጅግ በአነስተኛ ደረጃ በኢንተርኔት የተያያዙ አገራት መካከል መገኘቷ አልቀረም። ሪፖርቱ የተለያዩ ጥናቶችን በማጣቀስ ኢንተርኔት በጣም ውድ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ያወሳል። አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያዊያን በተንቀሳቃሽ ስልክም ሆነ በኮምፒውተር ላይ ኢንተርኔትን ለማግኘት በአማካይ በወር 85 የአሜሪካ ዶላር ያወጣሉ፤ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት አለባቸው በሚባሉት ኬንያና ኡጋንዳ ግን ይህ ወጭ በአማካይ ከ30 የአሜሪካ ዶላር የማይበልጥ ነው።
news-42700061
https://www.bbc.com/amharic/news-42700061
በካሊፎርኒያ 13 ልጆች በቤታቸው ውስጥ በሰንሰለት ታስረው ተገኙ
ሁለት ወላጆችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ 13 ልጆቻቸውን በሰንሰለት አስረው በማቆየታቸው በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የካሊፎርኒያ ፖሊስ አስታወቀ።
ሁለቱ ወላጆች፤ ልጆችን በማሰቀየት እና አደጋ ላይ መጣል የሚሉ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። የ57 ዓመቱ ዴቪድ ተርፒን እና የ49 ዓመቷ ባለቤቱ ሉዊዝ አን ልጆችን በማሰቀየት እና አደጋ ላይ መጣል የሚሉ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። ካሊፎርኒያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በሰንሰለት ታስረውና ተቆልፎባቸው የተገኙት ልጆች እድሜያቸው ከ 2-29 እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ጨምሮ እንዳስታወቅም ታስረው የተገኙት 13ቱ ሰዎች ወንድምና እህት ናቸው። የፖሊስ አዛዡ በሰጡት መግለጫ፤ ፖሊስ ከቦታው መድረስ የቻለው ከታሳሪዎቹ መካከል የ10 ዓመት እድሜ ያላት ህጻን አምልጣ ቤቱ ውስጥ ባገኘችው ተንቀሳቃሽ ስልክ ወደ ፖሊስ ከደወለች በኋላ ነው ብለዋል። የ10 ዓመቷ ህጻን ወደ ፖሊስ ደውላ ሌሎች 12 ወንድም እና እህቶቿ በወላጆቻቸው ታስረው እንደሚገኙ ተናግራለች። ፖሊስ በቦታው ሲደርስ በምግብ እጥረት የተጎሳቆሉ እና ንጸህና በጎደለው ጨለማ ክፍል ውስጥ የታሰሩ 12 ሰዎችን ማግኘቱን ተናግሯል። ወላጆቹ ልጆቻቸውን ለምን በዚህ አይነት ሁኔታ እንዳቆዩ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻሉም። ፖሊስ ከታሳሪዎቹ መካከል 7ቱ እድሜያቸው ከ18-29 የሚገመቱ አዋቂ መሆናቸው ድንጋጤን ፈጥሮብኛል ብሏል። 13ቱም ልጆች አሁን በአካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።
news-56569258
https://www.bbc.com/amharic/news-56569258
በምዕራብ ወለጋ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ።
ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን እንደፈጸመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ አመልክተዋል። ቡድኑ በጥቃቱ ዕለት ከምሽቱ ሦሰት ሰዓት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ "ጭፍጨፋ ፈፅሟል" ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከተገደሉት 28 ሰዎች መካከል 16ቱ ወንዶች ሲሆኑ 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት በተጨማሪ 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ጥቃቱን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም "አሰቃቂና ዘግናኝ" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ አመልክቷል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳም ከጥቃቱ በኋላ የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው በወሰደው እርምጃ የታጣቂው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና የጸጥታ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም። ጨምሮም ቡድኑን የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት "ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል" ብሏል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። መንግሥት "የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ በወሰደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ" ቡድኑ እየተዳከመ መሆኑን በመጥቀስ ነገር ግን "በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል" ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣውና መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በዚህ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ሲዘገብ ቆይቷል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችና፣ የጸጥታ አካላትና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ሲያደርግ ቡድኑ ግን ግድያዎቹን አለመፈጸሙን ሲያስተባብል ቆይቷል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከጥቂት ወራት በፊትም የቡድኑ መሪ የሆነው ኩምሳ ድሪባ በጸጥታ ኃይሎች መገደሉ የተነገረ ቢሆንም ከቀናት በፊት በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
news-55401206
https://www.bbc.com/amharic/news-55401206
ትግራይ ፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ ሰምሃል መለቀቋን እናቷ አዜብ መስፍን ገለጹ
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ ሰምሃል መለስ ትግራይ ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከቆየች በኋላ መለቀቋን እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ ገለጹ።
ወ/ሮ አዜብ እንዳሉት ሰምሃል ከእሁድ ጀምሮ አስከ ሰኞ ምሽት ድረስ ለ36 ሰዓታት ተይዛ መቆየቷን ገልጸው፤ ትናንት ምሽት እራሷ ደውላ መለቀቋን እንደገለጸችላቸው ለቢቢሲ ዛሬ [ማክሰኞ] ጠዋት ተናግረዋል። ወ/ሮ አዜብ ልጃቸው ሰምሃል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናገረው፣ ወደ መቀለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ገልጸዋል። አዲስ አበባ የሚገኙት ወ/ሮ አዜብ ጨምረውም ሰምሃል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍን ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር መሆኑን አመልክተዋል። ሰምሃል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል። ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" ያሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእስሯ ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሰምሃል በተጨማሪ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት ጀነራል ኃየሎም አርአያ ልጅ የሆነው ብርሐነመስቀል ኃየሎምም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ወ/ሮ አዜብ ከቀናት በፊት ልጃቸው ሰምሃል እየተፈለገች እንደሆነ በመስማታቸው አርብ ዕለት ወደ መቀለ ለመሄድ ፈልገው የነበረ ቢሆንም ፈቃድ ባለማግኘታቸው እንደቀሩና እሁድ ዕለት በቁጥጥር ሰር እንደዋለች መስማታቸውን ለቢቢሲ አብራርተዋል። ሰምሃል በየትኛው አካል እንደተያዘችና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከአንዳንድ አካላት ለማወቅ ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ ነገር ግን ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰምሃል መለስ በቁጥጥር ስር ስለዋለችበት ምክንያትና ለማወቅ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አወል ሱልጣን እና የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄይላን አብዲን ቢጠይቅም ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ሰምሃል መለስ የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና ከ20 ዓመታት በላይ አገሪቱን የመሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የወይዘሮ አዜብ መስፍን የበኩር ልጅ ስትሆን አስከ አባቷ ህልፈት ድረስ ስለእርሷ ብዙም የሚታወቅ ነገር አልነበረም። የ32 ዓመቷ ወጣት ሰምሃል የተወለደችው አባቷ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም የሚመራውን መንግሥት ለመጣል ህወሓትን በመምራት የሽምቅ ውጊያ በሚያደርጉበት ጊዜ ሱዳን ካርቱም ውስጥ ነበር። ሰምሃል ከአባቷ ህልፈት በኋላ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመዘከር በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችና በፖለቲካዊ መድረኮች ላይ አልፎ አልፎ በመቅረብ ሃሰብ ስትሰነዝር ከመታየት ውጪ በፖለቲካው መድረክ ጎልቶ የታየ ተሳትፎ አልነበራትም። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ መንግሥት በህወሓት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ አካሂዶ የህወሓት አመራሮችን ከክልሉ የስልጣን መንበር ላይ ማስወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ ለሦስት ሳምንታት ያህል ከተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ ኅዳር 19/2013 ዓ.ም የፌደራል መከላከያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ተቆጣጥሮ ይፈለጋሉ ያላቸውን ከፍተኛ የህወሓት አመራሮችን ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
news-55730083
https://www.bbc.com/amharic/news-55730083
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካመላ ሐሪስ ማን ናቸው? የትስ ነው የሚኖሩት?
ካመላ ዛሬ አዲስ ታሪክ ጽፋለች፡፡ የመጀመርያዋ የአሜሪካ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆናለች፡፡
ለመሆኑ ማን ናት? ከየት መጣች? የት ነበረች? ምን ትወዳለች? ስለሷ ልናውቃቸው የሚገቡ ቁልፍ ጉዳዮች ከዚህ እንደሚከተለው ተከትበዋል፡፡ በዕድሜ 55 ብትደፍንም ለጊዜው አንቱታውን ትተን እንቀጥል፡፡ ካመላ ሐሪስ የተወለደችው በካሊፎርኒያ ግዛት ኦክላንድ ከተማ ነው፡፡ እናቷ ሻየመላ ጎፓላን ሕንዳዊት ናት፡፡ አባቷ ዶናልድ ሐሪስ ደግሞ ጃማይካዊ ነበሩ፡፡ አባትና እናቷ ሁለቱም በስደት ነው ወደ አሜሪካ የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ በቅኝ ከገዛቻቸው አገራት ነው የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ ሄደው እንዲማሩ ተጠይቀው አሜሪካንን የመረጡ ናቸው፡፡ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በርክሌይ ካምፓስ ውስጥ ተማሪ ሆኑ፡፡ እሱ ኢኮኖሚክስ እሷ ሆም ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ የጥናት ቡድን ውስጥ ተያዩ፡፡ ያኔ አባቷ በካሊፎርኒያ በርክሌይ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ ነበር፡፡ በ1960ዎቹ መጀመርያ መሆኑ ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ብሪቲሾች እንዴት አገሩ ጃማይካ ገብተው በቅኝ ግዛት ሕዝቡን እንዳሰቃዩ ንግግር ያደርግ ነበር አባቷ፡፡ ተማሪ እያለ ነው ይሄ ታሪክ፡፡ ንግግሩን ሲጨርስ አንዲት በጣም ደቃቃ ቀጭን ሴት፣ ነጠላ ጫማ የተጫማች፣ የሕንዶችን ነጠላ ከደረቷ ያጣፋች፣ ሄዳ ተዋወቀችው፡፡ ከሕንድ አገር እንደመጣችና እዚያም እንግሊዞች አገሬውን ፍዳውን ያበሉት እንደነበር ነገረችው፡፡ ተቀራረቡ፣ ተዋደዱ፣ ተጋቡ፡፡ መጀመርያ ካመላን ከዚያም ማያን ወለዱ፡፡ ካመላ ማያ የምትባል ታናሽ እህት አለቻት፡፡ አባቷ ዶናልድ ሐሪስ ከእናቷ ሻይመላ ጋር በኋላ ላይ በ1970ዎቹ መጀመርያ ተለያይተዋል፡፡ ያን ጊዜ ካመላ ገና የ7 ዓመት ሕጻን ነበረች፡፡ ካመላና ማያን በማሳደጉ ረገድ የእናቷ ሚና ትልቅ ነበር፡፡ ሆኖም አባቷ ከፍቺ በኋላ ለቤተሰቡ ቅርብ ሆኖ ነበር የቆየው፡፡ እናቷ በኋላ ላይ እንደ አባቷ 3ኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ የሞቱት በ2009 ዓ.ም ሲሆን ለሞታቸው ምክንያት የደንዳኔ ካንሰር ነበር፡፡ አባቷ ዶናልድ አሁን የ82 ዓመት ዕውቅ የምጣኔ ሀብት "ኢምሬትስ ፕሮፌሰር" ሲሆኑ ከስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ጡረታ ወጥተው በራሳቸው የማማከር ሥራ ይሠራሉ፡፡ አባቷ በጃማይካ ቀልድ አያውቁም፡፡ ልጆቻቸው አገራቸውን እንዲወዱ፣ እንዳይረሱ ይፈልጋሉ፡፡ ሐሪስ በቅርቡ ጃማይካን ከእጸ ፋሪስ ጋር አገናኝታ በመቀለዷ ሽማግሌው አባቷ ቱግ ብለው ነበር፡፡ ካመላ ሐሪስ ባለትዳር ናት? የካመላ ሐሪስ ባል ዳግ ይባላል፡፡ ሁለት ለቁም ነገር የበቁ ወንድና ሴት ልጆች አሉት፡፡ ኮል እና ኢላ ይባላሉ፡፡ ከቀድሞ ባለቤቱ ከክሪስቲን ማኪን ነው የወለዳቸው፡፡ አሁን 26 እና 21 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ የአባታቸውን ሚስት ‹እንጀራ እናት› ብለው መጥራት አልፈለጉም፡፡ ካመላን ቅጽል ስም አወጡላት፡፡ ‹ሞማላ› እያሉ ነው የሚያቆላምጧት፡፡ እንደ እናትም ናት ለማለትም ጭምር ነው፡፡ ካመላ ሐሪስ ከእንጀራ ልጆቿ ኮል እና ኢላ ጋር በጣም ቅርብ ናት፡፡ ባሏ ዳግ በአሜሪካ ታሪክ ሁለተኛው "ካልአዊ አባወራ" (ሰከንድ ጀንትለማን) ይሆናል ማለት ነው፡፡ ካመላ ጥቁር ኢሲያዊት አሜሪካዊት ናት፡፡ የብዙ ደም ቅልቅል መሆኗ እንደማይረብሻት፣ ራሷንም አንዲት ጠንካራ ሴት አሜሪካዊት አድርጋ እንደምትቆጥር ተናግራለች፡፡ ዳግና ሐሪስ የተጋቡት በ2014 ሳንታ ባርባራ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነበር። ካመላ ኮሌጅ የተማረችው የብዙ ጥቁሮች ትምህርት ቤት በሆነው ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ሐሪስ ለዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቶች እጩ ለመሆን ሩጫ ጀምራ ኋላ ላይ በበቃኝ የወጣች ሴት ናት። በውድድሩ ወቅት አሁን የምርጫ ሸሪክ ካደረጓት ጆ ባይደን ጋር በተደጋጋሚ ተጋጭተዋል፣ ተከራክረዋል፣ አንድ ሁለት ተባብለዋል። በቀጥታ የክርክር ሥርጭት ወቅት ባይደንን አፋጣቸዋለች፡፡ የላይኛው ምክር ቤት አባል ሆና ካሊፎርኒያን ስትወክል በስብሰባዎች ላይ ትንፋሽ የሚያሳጥሩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ትታወቃለች፤ ሐሪስ፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት ዐቃቤ ሕግ ሆና ስትሰራ ስኬታማ አዳዲስ አሰራሮችን ዘርግታለች ተብላ ትሞካሻለች። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጆ ባይደን ሐሪስን የምርጫ ሸሪክ አድርገው ስለመምረጣቸው አስተያየት እንዲሰጡ በተጠየቁ ጊዜ፣ እንደመጣላቸው ስለሚናገሩ ይመስላል፣ "ባይደን አስቀያሚ ሴት ነው የመረጠው፤ ምን ነካው ባይደን? በምርጫው ተደንቂያለሁ" ብለው ነበር። ዛሬ ባይደንና ሐሪስ ትራምፕና ፔንስን አባረው ሥልጣኑን በይፋ ይረከባሉ፡፡ ሐሪስ በፊት የካሊፎርኒያ አቃቤ ሕግ ነበረች። በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ካሊፎርኒያን በመወከል የተሳተፈችበት ዘመን ስኬታማ ነበር፤ ጠንካራ ሴት መሆኗን ያስመሰከረችበት ነበር፡፡ አሁን ያን ምክር ቤት በሊቀመንበርነት ትዘውረዋለች። ሐሪስ በፊት በሳንፍራንሲስኮም የአንድ ቀጠና አቃቢ ሕግ ሆና ሠርታለች። ሃሪስ ለባይደን በምርጫ ውስቀሳ ወቅት 2 ሚሊዮን ዶላር በበይነ መረብ ገንዘብ ማሰባሰብ ችላ ነበር፤ በግዛቷ ካሊፎርኒያ። ከጆርጅ ፍሎይድ የግፍ ግድያ ጋር በተያያዘ ደግሞ ሐሪስ በትላልቅ ሰልፎች የሕዝብ ትኩረት ያገኙ ንግግሮችን አድርጋ ነበር። የቀድሞዋ የካሊፎርኒያ ዐቃቤ ሕግ ሐሪስ በፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ውስጥ ድምጽ ስታሰማ ነው የኖረችው። ገና የ7 ዓመት ሕጻን ሳለች እናትና አባቷ የጸረ ዘረኝነት ሰልፎች ላይ ይዘዋት እየሄዱ መፈክር እንድታሰማ ያደርጓት ነበር፡፡ ያ አድጎ ዛሬ ለጥቁሮች አለኝታ ሆናለች፡፡ በተለይም ሐሪስ በአሜሪካ ውስጥ የፖሊስ ክንድ በጥቁሮች ላይ መበርታቱን በመቃወም የፖሊስ ማሻሻያ እንዲደረግ ስትቀሰቅስ ትታወቃለች። ካመላ ሐሪስ ዛሬ ታሪክ የምትጽፈው አንድ ብቻ አይደለም፡፡ የመጀመርያዋ ሴት፣ የመጀመርያዋ ጥቁር ሴት፣ የመጀመርያዋ ጥቁር እና ሴት እና ደቡብ ኢሲያዊት-አሜሪካዊት ሴት እያለ ይቀጥላል ዝርዝሩ፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት ሥራው ምንድነው? በታሪክ እንደታየው የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራና ኃላፊነት ብዙ የሚባል አይደለም፡፡ ባርባራ ፔሪ የፕሬዝዳንታዊ ጥናት ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ፡፡ በአሜሪካ የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራ ምንድነው ሲባሉ በአጭሩ እንዲህ መልሰው ነበር፡- ‹‹የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራና ኃላፊነት የፕሬዝዳንቱን የልብ ትርታ ደረቱ ላይ ተለጥፎ እያዳመጡ መኖር ነው›› ባርባራ ማለት የፈለጉት ምንድነው? የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሚናና ጉልበት የሚገለጸው የፕሬዝዳንቱ ጤና ሲታወክ ወይም ደግሞ ሲሞት ብቻ ነው ማለታቸው ነው፡፡ በአሜሪካ ታሪክ ከ45 ፕሬዝዳንቶች ውስጥ ዘጠኙ የሥራ ዘመናቸውን ሳይጨርሱ ነጩን ቤተ መንግሥት ለቅቀዋል፡፡ ይህም ማለት ምክትሎቻቸው ትልቁን ሥልጣን ለመያዝና ለመሾፈር ዕድል አግኝተዋል ማለት ነው፡፡ ከዘጠኙ ታዲያ ስምንቱ በሞት ነው ከዋይት ሐውስ የወጡት፡፡ ባይደን 78 ዓመታቸው ነው፡፡ ሐሪስ በተጠንቀቅ መሆን አለባት ማለት ነው፡፡ አይበለውና አይቀሬው ሞት ቢመጣ የዓለም ትልቁ ሥልጣን ካመላ ሐሪስ እጅ ላይ ይወድቃል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ምክትላቸው እንዲሆኑ የሚመርጧቸው ሰዎች እነሱ የሌላቸውን የሚያሟሉ እንዲሆኑ ይሻሉ፡፡ ይሄን ነገር ጂሚ ካርተር ናቸው በ1970ዎቹ የጀመሩት ይባላል፡፡ ጂሚ የጆርጂያ ገዥ ነበሩ፡፡ ፖለቲካውን ብዙም አያውቁትም ነበር፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ ትርቃቸው ነበር፤ ለዓይንም ለልብም፡፡ ሲያሸንፉ ጊዜ ታዲያ ዎልተር ሞንዳሌ የሚባሉ ሴናተርን ምክትላቸው አደረጉ፡፡ ዋልተር የዲሲን ፖለቲካ ቀረጣጥፈው የበሉ ሰው ነበሩ፡፡ ምን ለማለት ነው፤ ፕሬዝዳንቶችና ምክትሎቻቸው በብዙ ነገር መለያየት የርዕዮተ ዓለምና አካባቢያዊ ሚዛንን ለማስጠበቅ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ ኦባማ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ብዙም የካፒቶል ሒልን ፖለቲካ አያውቁም ነበር፡፡ ጆ ባይደን የ35 ዓመት የፖለቲካ ልምድ የነበራቸው ሴናተር ነበሩ፡፡ ምክትላቸው አደረጓቸው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ይበልጥ ለመሳብ ኢቫንጀሊካል አጥባቂ ክርስቲያን ተከታይ የሆኑትን ማይክ ፔንስን አመጡ፡፡ ጆ ባይደን ደግሞ ጥቁሮችንና ሴቶችን ወደፊት ማምጣት ነበረባቸው፡፡ ደጋፊዎቻቸው ይህን እንዲያደርጉ ይጠብቁባቸዋል፡፡ በዚያ ላይ ከዕድሜያቸው ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ቅሬታ በወጣቷ ካመላ ሐሪስ ለማካካስ ሞክረዋል፡፡ ስለዚህ ሐሪስ ለጆ ባይደን የጾታ፣ የቀለምና የዕድሜ ሚዛን አስጠባቂ ናት ማለት እንችላለን፡፡ ሌላው ሐሪስን ከምክትል ፕሬዝዳንቶች ፍዝ ሚና የተለየ ሚና እንዲኖራቸው የሚያደርጋት በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ያለው የቁጥር መመጣጠን ነው፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንቶች 100 አባላት ባሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ሊቀመንበር ሆነው ስብሰባ ይመራሉ፡፡ ዘንድሮ ይህ ሚና መዶሻ መያዝ ብቻ አይሆንም፡፡ ወሳኙ ድምጽ የሚመጣው ከካመላ ሐሪስ ነው፡፡ ምክንያቱም በቁጥር ዲሞክራቶች 50፣ ሪፐብሊካኖችም 50 በመሆናቸው ነው፡፡ የመለያ የፍጹም ቅጣት ምቱን የሚመቱት ካሜላ ሐሪስ ናቸው፡፡ ካመላ ሐሪስ የት ነው የሚኖሩት? ጆ ባይደን ነጩ ቤተ መንግሥት ቢሮም መኝታም ይሆናቸዋል፡፡ ለመሆኑ ምክትላቸው ካመላ ሐሪስ የት ነው የሚኖሩት? ሐሪስና ባለቤታቸው ደግ ሌላ ቦታ ነው የሚኖሩት፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተሰራ እጅግ ግዙፍና ውብ ቤት ውስጥ ነው መኖርያቸው የሚሆነው፡፡ ቤቱ የሚገኘው በሰሜን ምዕራብ ዋሺንግተን ሲሆን የአሜሪካ የናቫል አብዘርቫቶሪ ግቢ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ ይሄ ግቢ ከዋይት ሐውስ ብዙም አይርቅም፡፡ የሐሪስ ቢሮ ደግሞ ዋይት ሐውስ ውስጥ ነው፡፡ ባለቤታቸው ሚስተር ዳግ የሚያስተምሩት በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ጠበቃም ናቸው፡፡ ስለዚህ ለባልና ሚስቱ አዲሱ መኖርያ ቤታቸው ለሥራም ቅርብ ሆነ ማለት አይደል? ባልና ሚስቱ ልጆቻቸውን ይዘው ወዲያ ወዲህ ማለት ሲፈልጉ ኤይርፎርስ-2 እና ቦይንግ 757 በተጠንቀቅ ሁልጊዜም ይጠብቃቸዋል፡፡ 24 ሰዓት ሐሪስንና ባለቤታቸውን የሚጠብቅ ደኅንነት ለሰከንድ ዐይኑን አይጨፍንም፡፡ ሐሪስ እንደ ትራምፕ ጎልፍ የሚወዱ አይደሉም፡፡ ምግብ ማብሰል ግን ነፍሳቸው ነው፡፡ ምናልባት የጥቁር ነገር ሆኖ ሊሆን ይችላል ነገር ቀለል ማድረግ ይወዳሉ ይባላል፡፡ ጂንስና ኮንቨርስ ሸራ ጫማን ከታኮ ጫማ በበለጠ ታዘወትራለች ሐሪስ፡፡ እስከዛሬ ሦስት መጽሐፎችን ለኅመት ያበቃች ሲሆን አንዱ የልጆች መጽሐፍ ነው፡፡ ‹እናቴ በዚያ ዘመን ስትወልደኝ እዚህ ትደርሳለች ብላ አስባ የምታውቅ አይመስለኝም› የምትለው ካመላ ሐሪስ ምናልባት የመጀመርያዋ የአሜሪካ ሴት ፕሬዝዳንት ሆና ሌላ ታሪክ ትጽፍ ይሆን? ይህ እንዲሆን ደግሞ 4 ወይም 8 ዓመት መጠበቅ ላይኖርባት ይችላል፡፡ አይበለውና! ቀጣይዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ማን ናቸው?
news-51060161
https://www.bbc.com/amharic/news-51060161
በአዲሱ ሕግ መሠረት ማን፣ ምን መታጠቅ ይችላል?
መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የሕዝብን መብትና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥርን በተመለከተ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈልጎኛል ብሏል።
ፎቶ፡ ፋይል። እአአ 2015 ላይ የቻይና መንግሥት በቁጥጥር ሥር አውሎ ያወደማቸው የጦር መሳሪያዎች። ረቂቅ አዋጁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ትናንት ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጸድቋል። "ተቆጣጣሪ ተቋም" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና የተሰጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሥሩ ብሔራዊ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሥራ ክፍል አደራጅቶ አዋጁን ያስፈጽማል። ለመሆኑ ይህ ሕግ ምን ይላል? ማን፣ ምን፣ እንዴት መታጠቅ ይችላል? የጦር መሳሪያ ፍቃድ እና ሁኔታ? ለግለሰብ የሚፈቀደው አንድ አነስተኛ ወይም አንድ ቀላል የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ለድርጅትም ቢሆን የሚፈቀደው የጦር መሳሪያ አይነት አነስተኛ ወይም ቀላል የጦር መሳሪያ ሲሆን፤ ዝርዝሩ እና የጥይት ብዛት በተቆጣጣሪው ተቋም በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተጠየቀበት የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም በሌላ ሰው ስም ፈቃድ ያልወጣበት እና የጦር መሳሪያው ወንጀል ያልተሰራበት መሆን አለበት። ፍቃድ የሚሰጥባቸው መስፈርቶች የተከለከሉ ተግባራት በዚህ አዋጅ መሰረት ከተፈቀደለት ሰው ውጪ ማንኛውም ሰው፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ እና መለዋወጫዎች ወይም አብረው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሳሪያዎችን፣ ወደ ሀገር ማስገባት እና ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር . . . ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ይገኙበታል። የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የማይቻልባቸው ሥፍራዎች መሳሪያ ታጥቀው ከላይ ወደ ተጠቀሱት ሥፍራዎች መግባት ካሰቡ በቅድሚያ የጦር መሳሪያውን ለተቋማቱ የጥበቃ ሰራተኞች ማስረከብ ይኖርብዎታል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ የማይሰጣቸው ተቋማት ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት ለጥበቃ ከሚያስፈልጋቸው የጦር መሳሪያ ውጪ ማንኛውም ዓይነት የጦር መሳሪያ ፍቃድ አይሰጣቸውም። በልማድ ለታጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለመስጠት በተለምዶ የጦር መሳሪያ የሚያዝባቸው አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ እና የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎች፤ የያዙት የጦር መሳሪያ በዚህ አዋጅ ያልተከለከለ አይነት እስከሆነ ድረስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በአካባቢያቸው ተገኝቶ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአካል ቀርበው ፈቃድ ሲጠይቁ ለአንድ ሰው አንድ የጦር መሳሪያ ፈቃድ በዚህ አዋጅ መሰረት ይሰጣል። በተገለፀው ጊዜ ገደብ ውስጥ ፈቃድ ያልወጣበት የጦር መሳሪያ ለተቆጣጣሪው ተቋም ገቢ መደረግ አለበት፣ በቁጥጥር በተገኘም ጊዜ ይወረሳል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለሚታደስበት ሥርዓት የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የፍቃዱ አገልግሎት ጊዜ ከማብቃቱ ከ60 ቀናት በፊት የእድሳት ጥያቄውን ለተቆጣጣሪው ተቋም ማቅረብ አለበት። ተቆጣጣሪው ተቋም ጥያቄው እንደቀረበለት በፍጥነት የፍቃድ መስጫ መስፈርቶቹ መሟላታቸውን ሲያረጋግጥ ፍቃዱን ያድሳል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለመሰረዝና መውረስ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ግዴታዎች የተቆጣጣሪ ተቋም ሥልጣንና ተግባር በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ ተቋሙ ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባራት መካከል፦ የወንጀል ተጠያቂነት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 481 የተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ የተመለከተውን ክልከላ እና ግዴታ የተላለፈ ከአንድ አመት እስከ ሦስት ዓመታት በሚደርስ ቀላል እስራት እና ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። • ካናዳ፣ አሜሪካ እና ዩኬ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አለን አሉ የተፈጸመው ወንጀል ብዛት ባለው የጦር መሳሪያ ሲሆን ቅጣቱ ከአምስት አመት እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከሀምሳ ሺህ እስከ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ ይቀጣል። በሕጋዊ መንገድ ያገኘውን የጦር መሳሪያ የሸጠ በማስያዣነት የተጠቀመ፣ ያከራየ ወይም በውሰት ለሦስተኛ ወገን ያስተላለፈ ማንኛውም ሰው ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል።
news-54223314
https://www.bbc.com/amharic/news-54223314
ኮሮናቫይረስ፡በእንግሊዝ የለይቶ ማቆያን መመሪያ የጣሱ ሰዎች 13 ሺህ ዶላር ይቀጣሉ ተባለ
ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የተነገራቸው እንግሊዛውያን መመሪያውን ካላከበሩ 13 ሺህ ዶላር እንደሚቀጡ መንግሥታቸው ከሰሞኑ አስታውቋል።
በአዲሱ መመሪያ መሰረት የኮሮናቫይረስ ተመርምረው ፖዘቲቭ መሆናቸው ከተረጋገጠ ወይንም በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት መኖራቸው የታወቀ ሰዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የሚያዝ መመሪያ ወጥቷል። በአገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደገና ማገርሸቱን ተከትሎም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠበቅ ያለ መመሪያ እንዲወጣ ያዘዙት። በትናንትናው ዕለት፣ መስከረም 9፣ 2013 ዓ.ም 4 ሺህ 422 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 27 ግለሰቦችም ህይወታቸው አልፏል። ከዚህም በተጨማሪ በስኮትላንድ 350 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ከግንቦት ወር በኋላም ከፍተኛ ነው ተብሏል። በዌልስ 212 ና በሰሜን አየርላንድ 222 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። መመሪያውን ለተላለፉ በመጀመሪያ 1 ሺህ 300 ዶላር የሚያስቀጣ ሲሆን በተደጋጋሚ መመሪያውን ለሚጥሱት እስከ 13 ሺህ ዶላር ያስቀጣል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሰቱ ከፍተኛም መሆኑ ከተረጋገጠ በመጀመሪያም ቢሆን መመሪያውን ለሚጥሱ 13 ሺህ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በእንግሊዝ እስካሁን ድረስ ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲያገሉ የምክር አገልግሎት ብቻ ነበር የሚሰጣቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱን መመሪያ ባወጁበት እለትም ቫይረሱን ለመታገል ሁሉም መመሪያውን ማክበር አለበት ብለዋል። "ሁሉም ቢሆን ይሄ አዲሱ መመሪያ ጠቃሚ እንደሆነ ሊረዳ ይገባል። መመሪያውን ሁሉም ሊያከብረው ይገባል። የብሄራዊ ጤና አገልግሎት በሚያዛችሁ መሰረት ቫይረሱ ተገኝቶባችሁም ከሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላችሁ ራሳችሁን ለይታችሁ ልታቆዩ ይገባል። ካለበለዚያ ግን እነዚህን መመሪያዎች ተላልፋችሁ ከተገኛችሁ ጠበቅ ያለ ቅጣት ይጠብቃችኋል" በማለት ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም ተጋላጭ ማህበረሰቦቹን ከቫይረሱ ለመታደግና ህይወት ማዳንም እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቢጤ አዘል መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል። እስካሁን ድረስ 19 ሺህ ሰዎች መመሪያውን የጣሱ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም የተጣለባቸውን ቅጣት እንዳልከፈሉም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች በአንድ ጊዜ የሚሰጥም 650 ዶላር ይኖራል ተብሏል።
50348475
https://www.bbc.com/amharic/50348475
" 'ፖስት ፒል' ብወስድም አረገዝኩ"
"እስከዛች እለት ድረስ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) ላይሠራ ይችላል የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ አልነበረኝም።"
ሬቸል (ስሟ ተቀይሯል)፤ አንድ ዓመት ከዩኒቨርስቲ እረፍት ወስዳ ካናዳ በነበረችበት ወቅት ነው የተደፈረችው። ጥቃቱ በደረሰባት በዛው እለት ምሽትም ነው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብል የተሰጣት። • ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት • ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው "ከሁለት ወራት በኋላ ማርገዜን ተረዳሁ፤ በጣም ነው የደነገጥኩት፤ በጭራሽ አረግዛለሁ የሚል ሃሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ አልነበረም።" የ34 ዓመቷ ሬቸል ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እርግዝናን ላይከላከል እንደሚችል ፍንጭ የሰጣትም አካል አልነበረም። "ውጤታማ ላይሆን ይችላል የሚለው እሳቤ ሲነሳ ራሱ ሰምቼ አላውቅም" ትላለች። መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያን ከሚወስዱት መካከል ከ0.6-2.6% የሚገመቱት ሴቶች ያረግዛሉ። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" • በፅንስ ማቋረጥ ታስራ የነበረችው ሞሮካዊቷ ጋዜጠኛ ምህረት ተደረገላት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) እንክብል ከተወሰደ በኋላ እርግዝና ሊያስከትል እንደሚችል መነጋገሪያ የሆነው አንዲት ጦማሪ እንክብሉን ብትወስድም እንዳረገዘች መፃፏን ተከትሎ ነው። ፅሁፏ ከፍተኛ የመወያያ ርዕስ የሆነ ሲሆን፤ እንክብሉ አንዳንድ ጊዜም ቢሆን ሊሠራ እንደማይችል በደንብ ሊታወቅ ይገባል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ጦማሪዋ በፅሁፏ ላይ እንዳሰፈረችውም፤ ከውፃት (ኦቩሌሽን) በኋላ አንዲት ሴት ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ፈፅማ እንክብሉን ብትወስድ ምንም ትርጉም እንደሌለው የተረዳችው በቅርቡ ነው። ይህንን መረጃ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ የሚያመርቱ ኩባንያዎች በሰፊው የማሳወቅ ሥራ ሊሠሩበት የሚገባ ነው ብላለች። ኮንዶም በመቀደዱ ምክንያት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ብወስድም ማርገዜ አልቀረም፤ እናም ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ምርመራዬን ጀመርኩ ብላለች። ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ የሚሠራው እንዴት ነው? ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ መድኃኒቶች በእንክብሉ መሥራት አለመሥራት ላይ ተፅእኖ እንደሚያደርሱ የሥነ ተዋልዶና የጤና ባለሙያዋ ዶክተር ካሮሊን ኩፐር ይናገራሉ። "እነዚህ መድኃኒቶች ከጉበት መድኃኒት ጋር ጣልቃ ይገባሉ" በማለት ዶክተሯ ገልፀው፤ እነዚህ መድኃኒቶች የኤችአይቪ፣ የሚጥል በሽታ እንዲሁም አንዳንድ ባህላዊ መድኃኒቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ሊሠራ የማይችልበት ሌላኛው ምክንያ፤ የሴቲቷ የሰውነት ክብደት እንደሆነ ዶ/ር ኩፐር ያስረዳሉ። የሰውነት ክብደታቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ ሴቶች ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ቢወስዱም ሊያረግዙ እንደሚችሉ ዶክተሯ ይናገራሉ። • ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል ግን ምን ያህል ሴቶች ስለዚህ ሁኔታ መረጃ አላቸው? የሌቭኔልም ሆነ ኤላዋን በራሪ ወረቀቶች የሚሰጡት መረጃ ውፃትን (ኦቩሌሽን) በማዘግየት እንክብሎቹ እንደሚሠሩ ቢሆንም የማያዩት ብዙዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም የመድኃኒቱ መሥራት አለመሥራት በወር አበባ ዑደት ዙሪያ ሊደናቀፍ እንደሚችልም ግልፅ ያለ መረጃ አይሰጥም። ታዲያ ለምንድን ነው ማንኛዋም ሴት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) ስትገዛ ይሄ ሁሉ መረጃ የማይሰጣት? "እንክብሎቹ አይሠሩም ብዬ አልሜ አላውቅም" ትላለች የ26 አመቷ ሃሪየት፤ ኮንዶም ቢቀደድባትም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ስለወሰደች አረግዛለሁ ብላ አልጠበቀችም። ያልጠበቀችው ሆነና አረገዘች። እሷ እንደምትለው በትክክል እንክብሎቹን ወስዳለች። ሃሪየት እንደተነገራትም እንክብሎቹ ረዘም ያለ ጊዜ ከተጠበቀ እንደማይሠሩ ነው። ነገር ግን እሷ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስለወሰደች አላስጨነቃትም ነበር። ከሳምንት በኋላ ግን ማርገዟን ተረዳች። ለሬቸል ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንደማይሠራ ማወቋ ያለችበትን ሁኔታ ባይቀይረውም፤ የአስራ አምስት አመት ልጅ እንዲኖራት አድርጓል። "እርግዝናዬ በጭራሽ ያልጠበቅኩት ነው። የሆነውን ነገር በፍፁም ባልቀይረውም ልጄን አልወልደውም ነበር" ትላለች። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዶ/ር ኩፐርን የወር አበባ ዑደት በድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ውጤት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ በፋርማሲስቶች ወይም በህክምና ባለሙያዎች ይነገራቸዋል ወይ? ብላ ለጠየቀቻት ጥያቄ "መንገር አለባቸው፤ ግዴታም ሊሆን ይገባል" ትላለች። ሌላኛው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ኮፐር ኢንትራዮትሪን ዲቫይስ (አይዩዲ) ነው። ያለ ጥንቃቄ ግብረ ሥጋ ግንኙነት በተፈፀመ በአምስት ቀናት ውስጥ በብልት ውስጥ ይገባል። ፖስት ፒል ውፃትን የሚያዘገዩ ሲሆን፤ ኮፐር አይዩዲ ደግሞ የተመረተ እንቁላል ማህፀን ውስጥ እንዳይቆይ ያደርገዋል፤ ውጤታማነቱም 99% ነው። ኤላዋንን ከሚጠቀሙ 100 ሴቶች መካከል ሁለቱ ያረግዛሉ፤ እንዲሁም ከሌቮኔል ተጠቃሚዎች መካከል በአማካይ 0.6-2.6 ፐርስንቱ የማርገዝ አጋጣሚዎች አሏቸው። ሬቸልም ሆነ ሃሪየት ኮፐር አይዩዲ እንደ አማራጭ እንዳልቀረበላቸው ይናገራሉ። • ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው የሥነ ተዋልዶ ጤና ባለሙያዋ ዶ/ር ጄይን ካቫንጋህ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሔ የሚሆነው ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያም ሆነ ስለ እርግዝና መከላከያ አወሳሰድ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ሊካተት ሲችል ነው ይላሉ። "እንዴት ነው ሁሉም ተማሪ ስለ እርግዝና መከላከያ የማይማረው? የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገው ሊያረግዙ የሚችሉበት አጋጣሚ ቢፈጠር ምን ያደርጋሉ? ማወቅ አለባቸው" ይላሉ። በተለያዩ ጊዜዎች ያነጋገረቻቸው ተማሪዎችም ብዙዎቹ ስለ ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንደማያውቁ ከውይይቱ መረዳት ችለዋል ባለሙያዋ። ስለ ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ሊያውቁ እንደሚገባ ሃሪየት ትናገራለች።
news-44312634
https://www.bbc.com/amharic/news-44312634
ሰባኪው የአንድ ቢሊዮን ብር አውሮፕላን ግዙልኝ አለ
በአሜሪካ እውቅ ከሆኑ የቲቪ ሰባኪዎች (ቴሌቫንጀሊስት) አንዱ የሆነው ነብይ ጀሴ ዱፕላንቲስ ተከታዮቹን የግል ጄት እንዲገዙለት በይፋ ጠየቀ። ምክንያቱም "ኢየሱስ አህያ ሊጋልብ አይችልም" ብሏል።
በሰሜን አሜሪካ የግል ጄት ያላቸው ሰባኪዎች ቁጥር በርካታ ነው አስገራሚ የሆነው ታዲያ ይህ ሰባኪ ሦስት የግል አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን ምዕመኑን መዋጮ እየጠየቀ ያለው ለ4ኛ አውሮፕላን (ጄት) ግዢ ነው። ሰባኪ ዱፕላንቲስ እንደሚለው ከሆነ ጌታ ግዛ ያለው ጄት ፋልኮን 7X የተባለውን ሲሆን ዋጋው ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህ ገንዘብ በብር ሲመነዘር 1.5 ቢሊዮን ብር ይጠጋል። ነብይ ዱፕላንቲስ ጨምሮ እንዳለው መጀመርያ ጌታ ይህን የግል ጄት ግዛ ሲለው "ትዕዛዙን ለመቀበል አቅማምቼ ነበር" ካለ በኋላ ጌታም ማቅማማቴን አይቶ "'አንተን ክፈል አላልኩህም፤ ይኖረኛል ብለህ እመን ነው ያልኩህ ሲል ጌታ ገሰጸኝ" ብሏል። ምንም እንኳ የግል አውሮፕላን ያላቸው ሰባኪዎች በአሜሪካን ምድር ማየት አዲስ ባይሆኑም ይህ የሰባኪ ዱፕላንቲስ ለ4ኛ ጊዜ "የጄት ግዙልኝ" ጥያቄ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንን በስፋት እያነጋገረ ነው። በተለይ የትዊተር ተጠቃሚዎች የሰባኪውን ድርጊት ማመን ተስኗቸዋል። አንዳንዶቹም የመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጾችን እየጠቀሱ እየሞገቱት ይገኛሉ። "ሐሳዊ ነብይ" ያሉትም አልጠፉም። "ምናለ ይህን የሚያህል ገንዘብ ለእርሱ መንደላቀቂያ ከሚሆን ለድሆች እርዳታ ቢውል" ያሉም አሉ። የ68 ዓመቱ እውቅ ሰባኪ ነብይ ዱፕላንቲስ በቪዲዮ ባስተላለፈው መልእክት እንዲህ ብሏል፦ "እንደምታውቁት ጄት ለኔ ብርቅ አይደለም። ከዚህ በፊት ሦስት የግል ጄቶች ነበሩኝ። ተጠቅሜባቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል አቃጥያቸዋለሁ።" ነብይ ዱፕላንቲስ እንደሚለው የጌታን ቃል ለዓለም ለማድረስ በተራ መኪና ወይም በባቡር ወይም በመርከብ የማይሆን ነገር ነው። ይህን ለማድረግ የቀረኝ ዕድሜ በቂ ካለመሆኑም በላይ አሰልቺም ነው። አንድ ጊዜ ነዳጅ ተሞልቶ ውቅያኖስ የሚያሻግርና ያለ ዕረፍት ረዥም ርቀት የሚጓዝ ዘመናዊ ጄት ያስፈልገኛል ብሏል። በ2015 ሰባኪ ዱፕላንቲስ ኬኔት ኮፕላንድ ከሚባል ሌላ ሰባኪ ጋር ሆኖ በቪዲዮ ባስተላለፈው አንድ መልዕክት እንደርሱ ያለ ትልቅ ሰባኪ ከሕዝብ ጋር በአውሮፕላን መሳፈር አሳፋሪ መሆኑን ለመግለጽ "በሕዝብ አውሮፕላን መጓዝ በትቦ ውስጥ ከአጋንንት ጋር እንደመሳፈር ያለ ነው" ብሎ ነበር።
news-42316149
https://www.bbc.com/amharic/news-42316149
ለማነፍነፍ የሰነፈችው ጥሩ ውሻ
በአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ ፈንጂ ለማነፍነፍ ከተመለመሉት ውሾች አንዷ የነበረችው ሉሉ ቦምብ የማነፍነፍ ምንም አይነት ፍላጎት ስለሌላት ከስልጠናው እንድትወጣ ተደርጓል።
ሲ አይ ኤ ሉሉን ያባረራት በአንድ ጊዜ ሳይሆን ለሳምንት ያህል በስልጠናው እንድትቆይ ካደረገ በኋላ ነው። ቦምብም ሆነ ሌላ አይነት ፈንጂ የማነፍነፍ ፍላጎት የሌላት ሉሉ እድሉን አግኝታው የነበረ ቢሆንም ለመቆየት ግን አላለላትም። ስለዚህም እንደ አውሮፓውያኑ ከየሲ አይ ኤ የስልጠና ክፍል ልትሰናበት ግድ ሆኗል። የሲ አይ ኤ ባለስልጣናትም ሉሉ ለምን እንደተባረረች በተደጋጋሚ በትዊተር ገጻቸው ላይ ሲፅፉ ነበር። የዚህ አይነቱን ስልጠና የሚወስዱ ውሾች በ10 ሳምንታት 19 ሺህ የፈንጂ አካባቢዎችን ማነፍነፍ ይጠበቅባቸዋል። በመጨረሻም ፈተና ይሰጣቸዋል። ፈተናውን ማለፍ የቻሉት ደግሞ በፈንጂ አሰሳ ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ድንገተኛ አደጋዎች ሲኖሩም እንደ ፖሊስ ያሉ የመንግስት ተቋማትን እንዲያግዙ ይደረጋል። ወደ ሌሎች ሀገሮች እንዲሄዱና በፈንጂ አሰሳ ላይ እንዲሳተፉም የሚደረግበት አሰራር አለ። አዳዲሶቹ ምሩቅ አነፍናፊ ውሾች በሳምንት አስከ ስልሳ ሰዓት ይሰራሉ። ስራ ላይ ባልሆኑበት ጊዜ እንኳን ልክ ስራ ላይ እንዳሉ ሁሉ የነቁ መሆናቸውን የሲአይ ኤ መረጃ ያሳያል። አብዛኛውን ጊዜ በሲ አይ ኤ የሚመረጡት ውሾች እንደ ላብራዶርና ጀርመን ሸፐርድ ያሉ ናቸው። ከእነዚህ ውሾች በተለየ መልኩ የሲ አይ ኤ ቆይታ ለሉሉ ፈታኝ ነበር። የሚሰለጥኑት ውሾች ስራውን ሊወዱት ግድ መሆኑን ሲ አይ ኤ ይናገራል። ሉሉ ግን ምንም እንኳን በምግብና በጨዋታ ሊያታልሏት ቢሞክሩ እንኳን ስራውን ልትወደው አልቻለችም። የሉሉ ከሲ አይ ኤ ስልጠና መሰናበት ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይአነጋጋሪ ሆኖ ነበር። አንዳንዶች "ፋታ ስጧት ትጫወትበት"ሲሉ ሌሎች ደግሞ ምናልባትም የሉሉ ፍላጎት "አርቲስት መሆን ዓለምን መዞር ሊሆን ስለሚችል ተዋት ህልሟን ታሳካበት"ሲሉ ተደምጠዋል።
news-46678595
https://www.bbc.com/amharic/news-46678595
ሀውስ ኦፍ ካርድ ላይ ፍራንክ አንደርውድን ሆኖ የሚተውነው ኬቨን ስፔሲ በፆታዊ ትንኮሳ ክስ ተመሰረተበት
ሀውስ ኦፍ ካርድስ የተሰኘው ተከታታይ ፊልም ላይ ፍራንክ አንደርውድ በሚል ገፀ ባህርይ የሚታወቀው ታዋቂው አሜሪካዊ ተዋናይ ኬቨን ስፔሲ ማሳቹሴትስ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ የ17 ዓመት ልጅ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ በማድረሱ ክስ ተመስርቶበታል።
ይህንን ፈፅሟል ተብሏል የተጠረጠረው ከሁለት ዓመታት በፊት ሲሆን ታህሳስ 29 ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ቢዘገብም ተዋናዩ በምላሹ ሰኞ ዕለት ምንም ስህተት እንዳልሰራ በመናገርም መልዕክቱን በተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) አስተላልፏል። •"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •"በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ "ምንም ባላጠፋሁት ጉዳይ ዋጋ ልከፍል አይገባም። ያለ ማስረጃ እንዴት ታምናላችሁ። እውነታውን ሳያገናዝቡ ለፍርድ መቸኮል አይገባም" ብሏል። ይህ 'ግልፅ ልሁን' የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቪዲዮ የፆታዊ ትንኮሳ ውንጀላ ከቀረበበት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየበት ነው። በቪዲዮው ላይ በሴረኛው ፍራንክ አንደርውድ የአነጋገር ዘዬን በመጠቀም " አንዳንዶች ሁሉንም ነገር ያምናሉ። እንድናዘዝም በጉጉት እየጠበቁ ነው" ብሏል። ትንኮሳውን ይፋ ያደረገችው ጥቃቱ የደረሰባት ወላጅ እናት የቀድሞ የዜና አቅራቢ ሄዘር ኡንሩህ ስትሆን ጊዜውም ባለፈው አመት ነው። በዛን ጊዜ አስራ ስምንት አመት ያልሞላውን ልጇን መጠጥ ከመግዛት በተጨማሪ እንደጎነታተለው በማሳወቅ ወንጅላዋለች። በኔትፍሊክስ በሚተላለፈው ተከታታይ ፊልም ከስድስተኛው ክፍል ቀድሞ ከመገደሉ በፊት ፍራንክ አንደርውድ የተሰኘው ገፀባህርይ በሴረኛነቱ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጠኛንና ፖለቲከኛን ገድሏል። ይህ ውንጀላ ከቀረበበት በኋላ አንቶኒ ራፕ የተሰኘው ተዋናይም በአውሮፓውያኑ 1986 ፆታዊ ትንኮሳን በማድረስ የወነጀለው ሲሆን ሌሎች ፆታዊ ትንኮሳዎችም ይፋ በመሆን ላይ ናቸው። ተዋናዩ ምንም እንደማያስታውስ ቢናገርም እንደ ሌሎች ውንጀላዎች ፈፅሞ አልካደም ነገር ግን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ውዝግቡ የሙያ ህይወቱን የጎዳው ሲሆን 'ሀውስ ኦፍ ካርድስ'ን ጨምሮ 'መኒ ኢን ዘ ወርልድ' የተሰኘው ፊልምም ያለ እሱ ተዋናይነት እንደገና እንዲቀረፅ ተደርጓል። እሱ የሚተውንበት ቢሊየነር ቦይስ ክለብ የተሰኘው ፊልም ነሀሴ ወር ላይ ሲኒማ ቤት በታየበት በመጀመሪያው ቀን 126 ዶላር ገቢ ብቻ በማስገባት የዝቅተኛ ገቢ ሬከርድ ሰብሯል።
56087297
https://www.bbc.com/amharic/56087297
"የተማረ ወንድ አይደፍርም" ያሉት ሚኒስትር ከፍተኛ ውግዘትን አስተናገዱ
"የተማረ ወንድ አይደፍርም" በማለት የተናገሩት የደቡብ አፍሪካ የትምህርት ሚኒስትር ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገዱ ነው ተባለ።
ሚኒስትሯ አንጂ ሞትሼክጋ ስለ ትምህርት ጠቃሚነት እያስረዱ በነበረበት ወቅት ነው ይህንን አስተያየት የሰጡት ተብሏል። በያዝነው ሳምንት ሰኞ እለት ሚኒስትሯ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደተናገሩት ግለሰቦች በትምህርታቸው የላቀ ደረጃ ላይ ከደረሱ መድፈርን ጨምሮ ሌሎች ነውረኛ ተግባራት ላይ የመሳተፍ እድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል። በርካቶች የሚኒስትሯ አስተያየት መሰረታዊ የሆነውን የፆታዎች የኃይል ሚዛን ልዩነትን ያላገናዘበ ነው ሲሉ ተችተዋቸዋል። በቦታው የነበሩት ተማሪዎች በሚኒስትሯ አስተያየት ባለመስማማት ሲያጉረመርሙ የተሰማ ሲሆን ሚኒስትሯም ለዚሁ ምላሽ በሚመስል መልኩ "የተማሩ ወንዶች በእንደዚህ አይነት ወንጀለኛ ድርጊቶች መሳተፋቸው በጣም አሳዛኝ ነው" ብለዋል። የተወሰነ ንግግራቸው ተቀንጭቦ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተጋራ ሲሆን በርካቶችንም አስቆጥቷል። የመድፈር ባህል በተንሰራባት ደቡብ አፍሪካ የተማሩ ወንዶች አይደፍሩም ምን ማለት ነው በሚልም ብዙዎች ተችተዋል። ሚኒስትሯ በበኩላቸው አስተያየታቸው ከአውድ ውጭ እንደተወሰደ ተናግረዋል። "መድፈር ከስልጣንና ኃይል ጋር የተገናኘ ነው። በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለውን የኃይል ሚዛን ልዩነት ለማስረዳት ወንዶችን ከህፃንነታቸው ጀምሮ እንዲያውቁ በማለት በትምህርተ ስርአቱ ቀርፀን እያስተማርን እንገኛለን። ወንዶች የኃይል ሚዛንን በተመለከተ፣ አባታዊ ስርአትን እንዲሁም የተሳሳተ የወንድነት ትርጉምን በተመለከተ ሊማሩ ይገባል። በተለይ ወሲባዊ ጥቃትን ለመታገል ወንዶች በፆታዎቹ መካከል ስላለው የኃይል ሚዛን ሊማሩ ይገባል" በማለት ከሚኒስትሯ የወጣው መግለጫ አስፍሯል። በአውሮፓውያኑ 2019 ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ወሲባዊ ጥቃቶች የአገሪቱ ብሔራዊ ቀውስ ነው በማለት አውጀው ነበር። በየአመቱም 40 ሺህ ወሲባዊ ጥቃቶች ሪፖርት የሚደረጉ ሲሆን ይህም በአገሪቷ ካለው ቁጥር አንፃር ኢምንት ነው ይላሉ።
44778468
https://www.bbc.com/amharic/44778468
የሰልፍ "ሱሰኛው" ስለሺ
ስለሺ ሐጎስ ለሰልፍ ባይታወር አይደለም። በተለይም ለተቃውሞ ሰልፍ። እንዲያውም ሱሰኛ ሳይሆን አይቀርም። ባለፉት ዐሥርታት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ በተደረጉ መንግሥትን የሚነቅፉና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን የሚያፋፍሙ ሰልፎች ላይ ሁሉ ተሳትፌያለሁ ይላል።
በሳቅ በተኳለ ንግግሩ እንደሚተርከው የቸርቸል ጎዳናን ታክኮ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ አደባባይ ቆሞ የቅዋሜ ድምፁን አስተጋብቷል፤ ከስድስት ኪሎ ተነስቶ አራት ኪሎ እስከሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ድረስ እጁን እያወናጨፈ ተጉዟል፤ ፍርሃት በደም ሥሩ ሲላወስ አስተውሎ ራሱን ታዝቧል፤ በዱላ ተቀጥቅጦ ሩሁን ስቷል፤ የሆስፒታል አልጋን ተለማምዷል፤ እስካሁን የዘለቀ ሕመምን ተቀብሏል። አሁን በሰላሳዎቹ የዕድሜ አፅቅ ውስጥ የሚገኘው ስለሺ፥ በጉርምስናው ወራት በትውልድ ቀዬው መቂ ከተማ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተከናወኑትን ሰልፎች ያስታውሳል። በተለይም በወርሃ ሚያዝያ በቅንጅት ለአንድነት እና ዲሞክራሲ ፓርቲ ደጋፊዎች የተከናወነው መስቀል አደባባይን እና ዙርያ ገባውን የሞላ ሰልፍ እጅጉን አስደምሞት ነበር። "ሚያዝያ ሠላሳ የነበረውን የቅንጅት ሰልፍ በቴሌቭዥን መታደም እጅግ የሚያስቀና ነገር ነበረው" ይላል ለቢቢሲ። • "ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምባገነን እንዳያደርጉት እሰጋለሁ" ጃዋር መሀመድ ሰልፉ፣ የድጋፍ ወይስ የተቃውሞ? ለስለሺ ከምርጫ 97 በኋላ ያሉት ተከታታይ ዓመታት የገዥው ፓርቲ ድምፅ ብቻ የተስተጋባባቸው፥ የገዥ ፓርቲ ድምፅ ብቻ የተፈቀደባቸው ሆነው ለመዝለቃቸው አንዱ ማሳያ ከአዲስ አበባ ትልልቅ አደባባዮች አንዱ የሆነው መስቀል አደባባይ ነው። በእነዚህ ዓመታት መስቀል አደባባይ ከሃይማኖታዊ በዓላት በዘለለ፤ ኢህአዴግ "ደግፉኝ እያለ ከየቀበሌው በሚቀስቅሳቸው ሰዎች አጥለቅልቆ" ራሱን የሚያሞካሽበት መድረክ ሆኖ ነበር ይላል። በመሆኑም ስለሺ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፥ በቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተ መዘክር፥ በዋናው አውደ ርዕይ ማዕከል እና የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜያት የምጣኔ ሃብት እርምጃ ምልክት ተደርጎ በሚቆጠረው ቀላል የከተማ ባቡር መንገድ እቅፍ ውስጥ ወደተዘረጋው መስቀል አደባባይ ከረዥም ጊዜ በኋላ ጎራ ያለው በቅርቡ ነበር። በሰኔ 16ቱ ሰልፍ። ሰልፉን በርካቶች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ለለውጥ እርምጃዎቻቸው ድጋፍን ለማሳየት እንደተከናወነ ሲገልፁ ማዳመጥ እንግዳ ባይሆንም፥ ለስለሺ ግን ይህ አገላለፅ የሰልፉን መንፈስ ሙሉ በሙሉ አይወክልለትም። ለስለሺ ሰልፉ የድጋፍነቱን ያህል የተቃውሞም ጭምር ነው። ለእርሱ መስቀል አደባባይ ላይ የተካሄደው ሰልፍም ይሁን አሁን በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚከናወኑ ሰልፎች አስኳላቸው ተቃውሞ ነው። "ሕዝቡ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር ላይ ያለውን ቅሬታን፥ ብሶት እና ተቃውሞ ለመግለፅ የሚከናወኑ ሰልፎች ናቸው" ይላል። "ይሄንን ለመለወጥ የተነሳውን አንድ ሰው እና አጋሮቹ ለማበረታታት በዚህም ተቃውሞውን ለማጠናከር የሚደረጉ ሰልፎች ናቸው። ዐብይን መደገፍ ኢህአዴግን መደገፍ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ተሳስተዋል።" ብዙ ከተባለለት ደማቅ ትዕይንት እና ከዚያም በኋላ አንኳሩ ዜና የነበረው የቦንብ ፍንዳታ የሚያስተምሩን አንኳር ነጥቦች አሉ ይላል ስለሺ። "የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ብዙ ጥያቄ አላቀረበም። መንግሥትን እጅህን ዘርጋልኝ አላለም፤ እጅህን ሰብስብልኝ ነው ሲል የነበረው። አንደኛ ይህንን ማስተዋል ችያለሁ" የሚለው ስለሺ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ የወሰዷቸው እርምጃዎች በአብዛኛው ይሄንን ያለቅጥ ተዘርግቶ የነበረ የመንግሥት እጅ መሰብሰብ ነበር" ይላል። "[ኮከብ ከሌለው] አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እስከ ኦነግ ባንዲራ" ድረስ የተለያዩ የአስተሳሰብ ጽንፎችን የሚወክሉ ትዕምርቶች በሰልፉ ላይ ቢስተዋሉም፥ እነዚህን የአስተሳሰብ መስመሮች ባንፀባረቁ ተሰላፊዎች መካከል ምንም ዓይነት ግጭትም ሆነ ውጥረት ያለመከሰቱ የሚነግረን ነገር አለ ይላል ስለሺ። "ተቃራኒ አስተሳሰቦቹን የሚያራምዱ ፖለቲከኞች ቁጭ ብለው መነጋገር የማይቻላቸው ቢመስልም፥ ደጋፊዎቻቸው ግን ተቃቅፈው ሁሉ መዘመር እንደተቻላቸው" ከጠቀሰ በኋላ "ይህም ብዙ አስተምሮኛል" ይላል። በስለሺ ዕይታ ይህ ወደ ዲሞክራሲ ለሚደረግ ጉዞ የተመቸ ሕዝብ እንዳለ የሚጠቁም ነው። ቅድመ ዐብይ ሰልፎች ስለሺ በትምህርት ምክንያት ወደ መዲናዋ ከዘለቀ እና እርሱንም ተከትሎ ኑሮውን በቋሚነት ከመሠረተ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሳተፍ የነበረውን ድባብ ሲያስታውስ ፈገግታ ያመልጠዋል። በሁለት ሺዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ነው። ጉምቱዋ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ ለእስር ተዳርገዋል፤ ይህ ያስቆጣቸው የአንድነት ፓርቲ አባላት ስሜታቸውን በአደባባይ ለመገልፅ ቆርጠዋል። በምርጫ 97 በኋላ ከተደረጉት ቀዳሚ የተቃውሞ ሰልፎች አንዱን ለማከናወንም ፈቃድ አግኝተዋል። ሦስት መቶ የማይሞሉ የፖርቲው አባላት ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት ተነስተው እስከ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ድረስ የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ ሲጓዙ ስለሺ ከመካከላቸው ነበር። "በ97 ዓ.ም የነበረው ግድያ እና ደም አእምሯችን ውስጥ ስለነበር ስጋት ሰንጎን ነበር" ይላል። "በማንኛውም ሰዐት ጥይት ሊተኮስ እንደሚችል እያሰብን ነበር የምንሄደው።" ሰልፈኞቹ ወደ ቤተ መንግሥት እየተቃረቡ ሲመጡ በርከትከት ብለው የቆሙ ወታደሮች ስሜታቸውን የበለጠ እንደረበሹት የሚናገረው ስለሺ፥ ይሄኔ ከሰልፈኞቹ አንደኛው ሰልፉን በጠንካራ መፈክሮች ከሚመራውን ሰው የድምፅ ማጉያ ነጥቆ "እኛ ሰላማዊ ነን" የሚል መፈክር እንዲያሰማ እንዳስገደዱት ያስታውሳል። ከዚያም በኋላ ተቃዋሚዎቹ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች ባዘጋጇቸው ሰልፎች ላይ የተሳተፈው ስለሺ፥ የአንድነት ለፍትህ እና ዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የነበረች "የሚሊዮኖች ድምፅ" የተሰኘች ጋዜጣን ማዘጋጅትም ጀምሮ ነበር። ፓርቲው የጠራውን ሰልፍ ለመዘገብ ከነ ፎቶ መቅረጫ በወጣበት አንድ ወቅት ለፖሊስ ዱላ መዳረጉን ይገልፃል። "ካሜራየን ደብቄ ዞር ስል፥ አንድ ዱላ መትቶ ጣለኝ" ከዚያም "በርካታ ፖሊሶች ቀጥቅጠው ግራ እጄ እንዲሰብር አደረጉ፤ በብረት ነው ያለው። ብረቱ አሁንም ድረስ አለ" ሲል ይናገራል ስለሺ። በድብደባው ምክንያት ስምንት ወር ይተኛ እንጂ እስካሁም በጣም የሚገርመው ግን በወቅቱ ከሠላሳ ለማይበልጡ ሰልፈኞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች መምጣታቸው መሆኑን ያስታውሳል። የዐብይ መቶ ቀናት በስለሺ ስለሺ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ወደ መሪነት መምጣት እና እርሳቸውም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰየሙ በኋላ የወሰዷቸውን እርምጃዎች "የአብዮት ትርፉቶች" ናቸው ሲል ይገልፃቸዋል። እናም "የኢትዮጵያ አብዮት ገና መጠናት አለበት።" ይሁንና ስለሺ የቅርብ ጊዜ የቅርብ አገራትን ተሞክሮ ማጤን ለንፅፅር ይጠቅማል ባይ ነው። "የሊቢያ አብዮት ጋዳፊን በመግደል ነው የተጠናቀቀው፤ የግብፅ አብዮት ሙባረክን በማሰር ነው የተጠናቀቀው።" ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከነባር የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ማንም ሳይሞት፥ ማንም ሳይታሰር "ኃሳባቸው ነው የሞተው" ይላል። ለስለሺ እንደሚለው አይበለውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በመቶኛ ቀናቸው ድንገት ሥልጣን ቢለቁ እንኳ የእስካሁኑ እርምጃዎቻቸው በቂ ስኬትን ይዟል። "ዐብይ ከዚህ በኋላ የሚመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ልኬታ አስቀምጧል።"
news-45742583
https://www.bbc.com/amharic/news-45742583
ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ጥቂት እንንገርዎ
ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን ኢንጅነር ስመኘው በቀለን ህልፈት ተከትሎ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን የርሳቸውን ቦታ ተክተው ላለፉት ሁለት ወራት በጊዜያዊነት ሲያገለግሉ ነበር። በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ የግድቡን የግንባታ ፕሮጀክት ለሚመሩ ግለሰቦች ኃላፊነት ሰጥተዋል። በመሆኑም ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ ኢንጅነር ኤፍሬም ወ/ኪዳንና አቶ ፈቃዱ ከበደ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ማን ናቸው? ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በምንህንድስና ሙያ በተለያዩ ቦታዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል። *በግቤ አንድ ፕሮጀክት ላይ በምህንድስ ሙያ ሲያገለግሉ፤ በዚያው ፕሮጀክት ላይ ከ1999 -2004 ድረስ ምክትል ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሰርተዋል። በኢትዮጵያ መብራት ኃይል ድርጅት የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍል ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉም ነበር። ኢንጂነር ክፍሌ ከ2006-2010 ድረስ በጣና በለስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል። በ2011 የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ በኋላ ከአንድ ዓመት በላይ የፕሮጀክቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍል ዋና ስራ አስኪያጅ ነበሩ። • ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የህዳሴው ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ ኢንጅነር ክፍሌ ደግሞ ከ1000 ኪሎሜትር በላይ የሚረዝመውን ኢትዮጵያና ኬንያን የሚያገናኘውን የመብራት ኃይል ዝርጋታ ፕሮጀክት ከ2013-2014 ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ ነበር። ከዚያ በኋላም እስከ 2016 የኢትዮጵያ የኃይል ማመንጫ ውስጥ የፕሮግራም ኃላፊ ( Generation program officer) ሆነዋል። የስራ አስፈፃሚው አማካሪ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ወደ ግል ስራ ተመልሰው እየሰሩ ሳለ ነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ የትምህርት ደረጃ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ወለጋ ተወልደው ያደጉ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በመንዲ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በቤተል ደምቢዶሎ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በ1984 በኤሌክትሪካል ምህንድስና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ከዚያም በተለያዩ ቦታዎች ሲያገለግሉ ቆይተው በ1999 ለስልጠና ወደ ጀርመን አገር አቅንተው ለ15 ወራት ተጨማሪ ስልጠና ተከታትለዋል። በ2015 ከእንግሊዝ ሳል ፎርድ ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክት ማኔጅመንት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል። * ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች እንደ አውሮፓውያኑ ናቸው።
news-54367341
https://www.bbc.com/amharic/news-54367341
አርሜንያ -አዘርባጃን ግጭት፡ ሩሲያ በናጎርኖ ካራባህ ጉዳይ የሰላም ውይይት ልታዘጋጅ ነው
ሩሲያ በናጎርኖ-ካራባህ ግዛት ይገባኛል ወደ ግጭት ያመሩት የቀድሞ የሶቪየት ሪፐብሊክ አካል በነበሩት አርሜንያና አዘርባጃን መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም የሰላም ውይይት ልታዘጋጅ መሆኑን አስታወቀች።
የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰረጌ ላቭሮቭ ለሁለቱ አገራት መንግሥታት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ መሥሪያ ቤታቸው እንደገለፀው ሚኒስትሩ፤ አገራቱ 'ለጦርነት መቋመጣቸውን' እንዲያቆሙ አሳስበዋል።. ረቡዕ ዕለት የሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ መሥሪያ ቤት እንደገለፀው፤ ሩሲያ የሰላም ውይይቱን ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኗን ለመግለፅ የሁለቱን አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጠርተው ነበር። የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲንም ግጭቱን አስመልክተው ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ሁለቱ መሪዎች የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያ ከአርሜንያ ጋር የጦር ሕብረት ያላት ሲሆን በአገሪቷም የጦር ሰፈር አላት። ይሁን እንጅ ከአዘርባጃን መንግሥት ጋርም የቅርብ ግንኙነት እንዳላት ይነገራል። አርሜንያ ራስገዝ የሆነችውን ናጎርኖ- ካራባክህን የምትደግፍ ቢሆንም ይፋዊ እውቅና ግን አላገኘችም። በሁለቱ አገራት መካከል እሁድ እለት በተቀሰቀሰው ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በዓመታት ውስጥ በግዛቷ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ከባድ ግጭት ነውም ተብሏል። የአዘርባጃን አካል እንደሆነች የምትታወቀው ናጎርኖ-ካራባህ የምትተዳደረው ግን በአርሜንያ ነው። አርሜንያና አዘርባጃን በግዛቷ ሳቢያ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1988-1994 ድረስ ተዋግተዋል። አሁንም ዓለም አቀፍ ኃይሎች በግጭቱ ጣልቃ ይገባሉ የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል። ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት መነሻው ግልፅ አይደለም። ረቡዕ ዕለት የአዘርባጃኑ ፕሬዚደንት ኢልሃም አሊየቭ የአርሜንያ ወታደሮች ግዛቷን ለቀው እስኪወጡ ድረስ እንደሚዋጉ ዝተዋል። " አንድ ቅድመ ሁኔታ ብቻ ነው ያለን፤ ይህም የአርሜንያ ወታደሮች ያለምንም ማቅማማት፣ ሙሉ ለሙሉ እና በአፋጣኝ መሬታችንን ለቀው መውጣት አለባቸው" ሲሉ ነበር ፕሬዚደንቱ የተናገሩት። አዘርባጃን በበኩሏ ሁለት የጠላት የጦር ታንኮች መውደማቸውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ያጋራች ሲሆን፤ የአርሜንያ ብርጌድ በቶናሸን መንደር ያለውን አካባቢ ጥለው መውጣታቸውን ገልፃለች። ረቡዕ ዕለት አዘርባጃን በማርታከርት ከተማ ላይ በፈፀመችው የአየር ድብደባ ሦስት ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን የአርመኒያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የመንግሥት የዜና ወኪሉ 'አርመንፕረስ' ደግሞ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ሰባት ሰላማዊ ሰዎች እና 80 ወታደሮች ተገድለዋል ብሏል። በሌላ በኩል የአርሜንያ መከላከያ ሚኒስቴር በቱርክ ኤፍ-16 ተመትቶ እንደተጣለ የተነገረው የአርመኒያ ኤስዩ-25 የጦር ጀትን ምስል አውጥቷል። የአዘርባጃን ታማኝ ወዳጅ የሆነችው ቱርክ ግን የቀረበባትን ክስ 'ርካሽ ፕሮፖጋንዳ' ስትል ውድቅ አድርገዋለች። ይሁን እንጅ አንድ ተዋጊ ባለፈው ሳምንት ከሰሜን ሶሪያ እንደተመለመለ እና ለውጊያው በቱርክ በኩል እንደተላከ ለቢቢሲ አረብኛ ተናግሯል። የቱርክ ፕሬዚደንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አማካሪ ኢልኑር ሴቪክ ግን ዘገባውን 'ሙሉ ለሙሉ መሰረተ ቢስ' ብለውታል። ግጭቱ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት -ኔቶ አባል አገራት በሆኑት ፈረንሳይና ቱርክ መካከል ውጥረትን ፈጥሯል። ፈረንሳይ ለበርካታ አርሜንያዊያን መኖሪያ ስትሆን ቱርክ ደግሞ በአዘርባጃን የሚገኙ ቱርካዊያንን ትደግፋለች። ረቡዕ ዕለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰተር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ፈረንሳይ "አርሜንያዊያንን ትደግፋለች" ሲሉ ከሰዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳነት ኢማኑኤል ማክሮንም ለዚህ የአፀፋ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከቱርክ የሚመጡ 'ጦርነት ቀስቃሽ' መልዕክቶችን ተችተዋል። ፕሬዚደንት ፑቲንና ማክሮን በስልክ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቀጣይ እርምጃዎች ላይ መነጋገራቸውንና የአውሮፓ የፀጥታና ትብብር ድርጅት-ሚንስክ ግሩፕ ግጭቱን ለመፍታት እንደሚሞክር የፑቲን መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚንስክ ግሩፕ በጎርጎሮሳዊያኑ 1992 የተመሰረተ ሲሆን የሚመራው በፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና አሜሪካ ነው።
49750897
https://www.bbc.com/amharic/49750897
በአሜሪካ የ'ወሊድ ቱሪዝም' በማጧጧፍ የተከሰሰችው ቻይናዊት
ቱጃር ቻይናውያን ልጆቻቸውን አሜሪካ እንዲወልዱ በማመቻቸት የተከሰሰችው ቻይናዊት ጥፋተኛ መሆኗን አመነች።
የሚወለዱት ልጆች የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ፤ እናቶቻቸው ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ ያመቻቸችው ቻይናዊት ዶንግዩአን ሊ፤ ክስ የተመሰረተባት አሜሪካ ውስጥ ነበር። 'የወሊድ ቱሪዝም' የሚል ስያሜ ባለው ሂደት፤ አንዲት ሴት ወደ አሜሪካ ሄዳ ለመውለድ ገንዘብ ትከፍላለች። ቻይናዊቷ ዶንግዩአን ያቋቋመችው ድርጅት በኃብት የናጠጡ ቻይናውያን ልጆቻቸው የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ ያመቻች ነበር። ዶንግዩአን፤ ሴቶቹ እርጉዝ መሆናቸው ሳይታወቅ የአሜሪካን ኢሚግሬሽን እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ ስልጠና ትሰጥ ነበር። ለአገልግሎቷ በጠቅላላው ከሦስት ሚሊየን ዶላር በላይ ሰብስባለች ተብሏል። • ፀረ-መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል? • በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች ጥቅምት ላይ በዶንግዩአን ጉዳይ ብይን የሚሰጥ ሲሆን፤ የ15 ዓመት እሥር መከናነቧ እንደማይቀር ተገምቷል። የ 'ወሊድ ቱሪዝም' ለምን? እንደ ጎርጎሮሳያውኑ ከ2013 እስከ 2015 ድረስ፤ ቻይናውያን እርጉዝ መሆናቸው ሳይታወቅ የአሜሪካን ኢሚግሬሽን ማለፍ የሚችሉበትን መንገድ ለማሰልጠን ከ40,000 እስከ 80,000 ዶላር ታስከፍል እንደነበረ ዶንግዩአን አምናለች። 'ዩ ዊን ዩኤስኤ ቫኬሽን ሰርቪስ' የተባለው ድርጅቷ የቻይና ባለሥልጣኖችን ጨምሮ ለብዙዎች አገልግሎቱን ሰጥቷል። የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘው ማስታወቂያ ወደ 500 የሚደርሱ ደንበኞቹ፤ "አሜሪካዊነት ከሁሉም አገሮች በበለጠ የሚያስደስት ዜግነት ነው" ማለታቸውን ይገልጻል። የዶንግዩአን፤ ደንበኞቿ መጀመሪያ ከቻይና ወደ ሀዋይ ከበረሩ በኋላ ወደ ሎስ አንጀለስ እንዲጓዙ ትመክር ነበር። የአሜሪካ ኢሚግሬሽንን በቀላሉ ለማለፍ መዳረሻን ሀዋይ ማድረግ የተሻለው አማራጭ ሲሆን፤ ደንበኞቿ ከሀዋይ ወደ ሎስ አንጀለስ ከበረሩ በኋላ አፓርትመንት ውስጥ ያርፋሉ። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች • በሻንጣ ውስጥ ተጉዞ ስፔን የደረሰው ልጅ አባት ከእስር ነፃ ሆነ ዶንግዩአን፤ ደንበኞቿ ለቻይና ኢሚግሬሽን ሠራተኞች፤ አሜሪካ ውስጥ ለሁለት ሳምንት ብቻ እንደሚቆዩ መንገር እንዳለባቸው ታሰለጥናቸው እንደነበርም አምናለች። ቻይናውያኑ ሴቶች ቢያንስ ለሦስት ወር አሜሪካ ውስጥ ይቆያሉ። ቻይናዊቷ ቪዛ በማጭበርበር የቀረበባትን ውንጀላ ከተቀበለች በኋላ፤ ወደ 850,000 ዶላር፣ 500,000 ዶላር የሚያወጣ ቤቷን እንዲሁም መርሴደስ ቤንዝ መኪኖቿን ለማስረከብ ተስማምታለች። የአሜሪካ ሕግ፤ አገሪቱን መጎብኘትና እዛው ሳሉ ልጅ መውለድን አይከለክልም። ሆኖም በሀሰተኛ መረጃ ቪዛ ማግኘት በሕግ ያስቀጣል። ዶንግዩአን፤ ቻይናውያን ሴቶች አሜሪካ ውስጥ ልጅ ቢወልዱ፤ ቤተሰቦቻቸው ለስደተኞች በወጣ ድንጋጌ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በመግለጽ ድርጅቷን ታስተዋውቅ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሌሎች አገራት ዜጋ ከሆኑ ቤተሰቦች አሜሪካ ውስጥ ለሚወለዱ ልጆች የአሜሪካ ዜግንት የሚሰጥበትን አሠራር የማገድ እቅድ እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።
52889061
https://www.bbc.com/amharic/52889061
ዙም መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን ከሥራ ማባረሪያም ሆኗል
ኮሮናቫይረስ ብዙዎች ቤታቸውን ቢሮቿው እንዲያደርጉ አስገድዷል። ስብሰባዎች በዙም መካሄድ ከጀመሩም ወራት ተቆጥረዋል። ዙም ስብሰባ ማከናወኛ ብቻ ሳይሆን ከሥራ ማባረሪያም ሆኗል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ‘ፓና’ የተባለ ድርጀት ነው። የድርጅቱ ኃላፊዎች ሁለት ስብሰባ እንደሚካሄድ አስታወቁ። የመጀመሪያው ስብሰባ 3፡00 ላይ ሁለተኛው ደግሞ 3፡45 ላይ።
የሦስት ሰዓቱ ስብሰባ ከተቋሙ ጋር ለሚቀጥሉ ሰዎች ነበር። ቀጣዩ ስብሰባ ደግሞ ለሚባረረሩ ተቀጣሪዎች። ሠራተኞቹ ለየትኛው ስብሰሰባ እንጠራ ይሆን? ብለው ተጨንቀው ነበር። ከነዚህ አንዷ የሽያጭ ኃላፊዋ ሩቲ ታውንሰንድ ናት። በጣም ከመጨነቋ የተነሳ የ3 ሰዓቱና የ3፡45ቱ ስብሰባ ትምታታባት። “ከሥራ የሚባረሩ ሰዎች አሉ የሚለው ዜና አስደንግጦኝ ስለነበር ስብሰባዎቹ ተምታቱብኝ። የሦስት ሰዓቱን ስብሰባ በዙም ከተቀላቀልኩ በኋላ ልባረር እንደሆነ ሲገባኝ ቪድዮውን አቋረጬ ወጣሁ።” • የፌስቡክ ሠራተኞች በመሥሪያ ቤታቸው ድርጊት ተበሳጩ • የጆርጅ ፍሎይድ የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ ዴንቨር የሚገኘው የጉዞ ድርጅቱ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ገቢው ስለቀነሰ ሠራተኞችን ለማሰናበት ተገዷል። ሌሎች ኪሳራ የገጠማቸው ድርጅቶችም ተመሳሳይ እርምጃ ከመውሰድ ውጪ አማራጭ አጥተዋል። ቀድሞ ቀጣሪና ተቀጣሪ ፊት ለፊት ተገናኝተው ያወሩ ነበር። አሁን ግን ሠራተኞች የሚባረሩት እንደ ዙም እና ማይክሮሶፍት ቲም ባሉ ቴክኖሎጂዎች ሆኗል። ክሪስ ማሎን መርሀ ግብሮች የሚያዘጋጀው የዩኬው ‘ስፓርክ’ የተባለ ድርጅት ውስጥ ይሠራ ነበር። የድርጅቱን የማይክሮሶፍት ቲም የቪድዮ ስብሰባ ከሰው ኃይል ክፍል ተቀጣሪዎች ጋር እንደሚያካሂድ ሲነገረው፤ ከሥራ ሊባረር እንደሆነ ጠርጥሮ ነበር። የፈራው አልቀረም ስብሰባው ላይ ከሥራህ ተሰናብተሀል ተባለ። “በስልክ ቢሆን የሚያባርርህን ሰው ፊት አታየውም። ለቪድዮ ስብሰባ ብለህ የክት ልብስህን አድርገህ በተቀመጥክበት መባረር ግን ምቾት ይነሳል። ከሚያባርረው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ብትሆን ከሰውነት እንቅስቃሴው ምን ለማለት እንደፈለገ ስለምትረዳ እንግዳ ስሜት አይሰማህም።” ክሪስ እንደሚለው፤ የአንድ ድርጅት ሠራተኞች ባጠቃላይ በቪድዮ በተሰበሰቡበት ከመባረር ይልቅ ቀጣሪ ለተቀጣሪው ለብቻው ደውሎ ቢያሰናብተው ይመረጣል። ሩቲ ሥራዋን ከማጣቷ በፊት በተሳተፈችበት የመጨረሻ ስብሰባ 15 ሰዎች ነበሩ። • በምዕራብ ኦሮሚያ ነጆ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ • “ኮሮናቫይረስን ለሦስት ሳምንታት በሦስት ሆስፒታሎች ታገልኩት” “እኔና አለቃዬ ብቻ ብንሆን ስሜቴን መረዳት ይችላል። የቡድን ስብሰባ ስለነበረ መጠየቅ የምፈልጋቸውን ጥያቄዎች ሳላነሳ ነው ስብሰባውን ያቋረጥኩት።” ጄኤምደብሊው የተባለ የሕግ አማካሪዎች ተቋም ውስጥ የምትሠራው ሣራ ኢቫንስ እንደምትለው፤ ሥራ ቦታ ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን ለተቀጣሪዎች ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ነው። “በዙም ትልቅ ስብሰባ ጠርቶ ለሁሉም ሠራተኞች ምን እንደተፈጠረ ማሳወቅ ያስፈልጋል” ስትል ታስረዳለች። ሠራተኞች ከተሰናበቱ በኋላ ምን እንደሚጠብቃቸው እንዲሁም ተቋሙ ስላለበት ሁኔታም ለማወቅ ግልጽነት የተሞላቸው ስብሰባዎች መካሄድ አለባቸው ትላለች። ሣራ እንደምትለው፤ ለአንድ ሰው ስልክ ደውሎ ተባረሀል ማለት ይሻላል? ወይስ በቪድዮ ስብሰባ ከሥራ መሰናበቱን ማሳወቅ? የሚሉት ጥያቄዎች በሕግ ማዕቀፍ ምላሽ ያላቸው አይደሉም። ተቀጣሪ እንዴት ይባረር የሚለው ጉዳይ የሥነ ምግባር ጥያቄ ነው። አሜሪካ ውስጥ በቡድን የቪድዮ ስብሰባዎች ላይ ተቀጣሪዎችን ማባረር ቢቻልም፤ በዩናይትድ ኪንግደም ግን ሕገ ወጥ ነው። ሩቲ የዩኬ ዜጋ ብትሆን፤ አለቃዬ ያባረረኝ ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ነው ብላ መክሰስ ትችል ነበር። ቪድዮ ስብሰባዎች ሲካሄዱ መቅረጽ ይቻላል ወይ? ሌላው ጥያቄ ነው። • ከስልክዎ ጋር ጨክነው ለመለያየት አምስት መንገዶች ኮርከር ቢኒንግ የተባለው የሕግ አማካሪዎች ድርጅት አጋር መስራች ፒተር ቢኒንግ እንደሚለው፤ ማንም ሰው የስብሰባ ቪድዮ ከመቅረጹ በፊት በይፋ ማስታወቅ አለበት። አንድ ሰው በቪድዮ የተባረረው ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መሆኑን ለማሳየት የቪድዮ ማስረጃ ለመጠቀም ቢፈልግም፤ ሕጋዊነቱ ላይ ጥያቄ ሊነሳ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ ባሙያው ያስረዳል። ቪድዮ የሰው ለሰው ግንኙነትን ለውጧል። ይህም በሥራ ቦታ ላይ ማጥላቱ አልቀረም። የሥነ ልቦና አማካሪዋ ፐርን ካንዶላ እንደሚሉት፤ አንድ ሰው ከሥራ ሲሰናበት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ግልጽ መረጃ ሊሰጠው ይገባል። “የአንድን ሰው አይን እያዩ ማባረር ምቾት ሊነሳ ይችላል። ንዴቱና ቁጣው ፊቱ ላይ ይነበባልና። ሆኖም ግን ግልጽ ሆኖ መነጋገር ያዋጣል።”
51964268
https://www.bbc.com/amharic/51964268
በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ከታየባቸው አራቱ ነፃ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ
በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩ ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ ነፃ መሆናቸው የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩት መካከል የሁለቱ ውጤት እንደታወቀ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። ይህ የተገለጸው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ዛሬ በባሀርዳር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሶስተ መቶ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም አምስት የለይቶ ማቆያዎች ብቻ እንደነበሩ የገለጹት ኃፊው በሁሉም ዞኖች አንድ አንድ የለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ መደረጉንም ገልጸዋል። በክልሉ በሚገኙ አራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በመተማ ድንበር እስካሁን 1900 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሙቀት ምርመራ ማድረጉን ቢሮው አስታውቋል። በክልሉ በበሽታው የተያዘ ሰው አለመኖሩን እንደ መልካም ዕድል መጠቀም ዝግጅቶችን አጠናክሮ ማካሄድ እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ ናቸው። ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመከታተል እና የግል ንጽህናውን አዘውትሮ በመጠበቅ የመከላከል ሥራውን ከእራስ መጀመር እንደሚገበባ አስረድተዋል። ከአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር በተጨማሪ የክልሉ መግቢያ በሆኑት በደጀን፣ ደብረ ብርሃን እና ባቲ የሙቀት መለካት ሥራ ከሰኞ ጀምሮ ተግበራዊ ይደረጋል ብለዋል። የቫይረሱን ምርመራ በክልሉ ለመጀመር የሚመለከታቸውን አካላት እየጠየቁ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ የሚሆን ግብዓት ከተገኘ ዝግጁ የሆነ ቤተ-ሙከራ መኖሩን ጠቁመዋል። ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በክልሉ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳደድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ጠቁመው፤ ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል። የክልሉን ከፍተኛ ሥራ ኃፊዎች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተዋቀሩበት ግብረ-ኃይል ወደ ሥራ ገብቷል። የክልሉ መንግሥትም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሚሠሩ ሥራዎች የሚውል 150 ሚሊዮን ብር መመደቡን ታውቋል።
news-44734884
https://www.bbc.com/amharic/news-44734884
በደቡብ አፍሪቃ አውራሪስ አዳኞቹ በአንበሳ ተበሉ
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ ዘልቀው በመግባት አውራሪስ በማደን ላይ የነበሩ ግለሰቦች በአንበሶች ተበልተዋል።
አንበሶቹ ቢያንስ ሁለት አዳኞችን 'ውጠው አላየሁም' ማለታቸው እየተዘገበ ሲሆን የማቆያው ሰዎች ግን አዳኞቹ ሶስት ሳይሆኑ አልቀሩም ሲሉ ይገምታሉ። የሁለቱ ሰዎች ቅሪት የተገኘ ሲሆን ለአደን ይረዳቸው ዘንድ ይዘውት የነበረ መሣሪያና መጥረቢያም ተገኝቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፍሪቃ ውስጥ የአውራሪስ አደን እየበረታ የመጣ ሲሆን ለዚህ ደሞ እንደምክንያት እየተጠቀሰ ያለው በውድ ዋጋ ለገበያ የሚቀርበው የአውራሪስ ቀንድ ነው። አውራሪስ በብዛት ከሚገኝባቸው የአፍሪቃ ሃገራት አልፎ ቻይና እና ቪየትናምን የመሳሰሉ ሃገራት በኢህ ጉዳይ ማጣፊያው አጥሯቸዋል። የእንስሳት ማቆያ ሥፍራው ባለቤት የሆኑ ግለሰብ በፌስቡክ ገፃቸው አዳኞቹ ወደ ቅጥር ግቢው የገቡት ድቅድቅ ጨለማን ተገን አድርገው እንደሆነ አሰውቀዋል። ግለሰቡ ጨምረው ሲገልፁ «አዳኞቹን አንክት አድርገው የበሏቸው አንበሶቹ በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ባናውቅም በርከት እንደሚሉ ግን እንገምታለን» ብለዋል። የሰዎቹ ቅሪት ከተገኘ በኋላ ሁኔታውን ማጣራት ይረዳ ዘንድ አንበሶቹ ራሳቸውን እንዲስቱ ተደርጓል። ፖሊስ ሌላ በአንበሳ የተበላ አዳኝ ይኖር እንደሆን ለማጣራት አካባቢውን ቢያስስም ፍንጭ ሊገኝ አልቻለም። በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ አዳኞች በዚህ ማቆያ ሥፋራ የሚገኙ ዘጠኝ አውራሪሶችን መግደላቸው ተመዝግቧል። ባለፉት አስርት ዓመታት ብቻ ደግሞ 7 ሺህ ያህል አውራሪሶች የአዳኞች ሲሳይ ሆነዋል።
news-55458662
https://www.bbc.com/amharic/news-55458662
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አራት የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በመተከል ዞን ከተፈጸመው የበርካታ ሰዎች ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አራት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበባቸው አቶ አድጎ አምሳያ፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፣ አቶ ግርማ መኒ እና አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው። አቶ አድጎ አምሳያ ቀደም ሲል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበርና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ የክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ናቸው። በተጨማሪም አቶ አረጋ ባልቢድ የመተከል ዞን አመራር የነበሩና አቶ ግርማ መኒ የክልሉ ምክር ቤት አባል ሲሆኑ አራቱ ሰዎች በክልሉ የመተከል ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ በአባልነታቸው ያላቸውን ያመከሰስ መብት እንዲነሳ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። የአራቱ የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በተነሳበት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ በመተከል ዞን የተፈጸመው ጥቃት አሳዛኝና ሊደገም የማይገባው መሆኑን መናገራቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ገልጿል። አራቱ ግለሰቦች ባለፈው ሳምንት ከተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት በኋላ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የክልሉ ምክር ቤት አባል በመሆናቸው የሚኖራቸው ያለመከሰስ መብት በቀዳሚነት መነሳት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው። ቀደም ሲል ከዚሁ መተከል ዞን ውስጥ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሰዎች መካከል በክልሉና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ይገኙበታል። በዚህም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ቶማስ ኩዊ አንዱ ናቸው። በተጨማሪም አቶ ባንዲንግ ማራ የመተከል ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ገመቹ አመንቲ የክልሉ የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ አድማሱ መልካ የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ይገኙበታል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለወራት የዘለቀ ተከታታይ ጥቃት በነዋሪዎች ላይ ሲፈጸምበት በቆየው የመተከል ዞን ውስጥ በሚገኘው ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት አሰሳ ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን በጭፍጨፋው ውስጥ በተለያየ መልኩ እጃቸው አለበት የተባሉ የመንግሥት ባለሰልጣናትም በቁጥጥር ሰር ውለዋል። ከጥቃቱ በኋላ የአካባቢውን ጸጥታ የሚቆጣጠር ግብረ ኃይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተቋቋመ ሲሆን ግብረ ኃይሉም ሥራውን በዚህ ሳምንት መጀመሩ ተገልጿል። ይህ ግብረ ኃይል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሰልጣናትና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችን ያቀፈ ሲሆን በመተከል ዞን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተነግሯ። ግብረ ኃይሉ በሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ የሚመራና በዞኑ በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈጸም ህይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በማደን ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር አውሎ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
news-44955171
https://www.bbc.com/amharic/news-44955171
ካለሁበት 41: አብዱልራሂም ከባሌ ገበሬዎችን እስከ ቻድ ሕዝቦች የመብት ጥያቄ ሲል ብረት አንስቷል
ስሜ አብዱልራሂም አብዱልዓዚዝ ይባላል። በባሌ ዞን ድሬ በምትባል ከተማ ውስጥ ነው ተወልጄ ያደኩት። በእርግጥ በልጅነቴ በሐረር ዘለግ ላለ ጊዜ ተቀምጫለሁ።
ከአገር ሽሽቼ የወጣሁት በንጉሡ ዘመን ነበር። ያኔ ባሌ ውስጥ የተጋጋለ ጦርነት ይካሄድ ነበር። በጦርነቱ ንብረት ወድሟል፣ ሰዎች ተገድለዋል፤ በርካቶች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። በዚያን ወቅት ታዲያ ገና የ12 ዓመት ልጅ ነበርኩ። ያም ኾኖ ዕድሜዬ ትግሉን ከመቀላቀል አልገደበኝም። በዚያን ወቅት የነበረውን ሥርዓት ለመጣል ነፍጥ አንስቼ ጫካ ገባሁ። ከዚያን ጊዜ በኋላ በሄድኩበት ሁሉ ትግል ይከተለኛል። ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከዐብይ አህመድ በፊትና በኋላ "ካለ ቪዛ ወደ 127 አገራት መጓዝ እችላለሁ" ያኔ ትግሉን ስቀላቀል የትግሉ መሪ ዝነኛው ጄነራል ዋቆ ጉቱ ነበሩ። በዚያ የተሟሟቀ ትግል ምክንያት በአገር ውስጥ ባሌ፣ ሐረር፣ ወለጋ እና አዲስ አበባ ተዟዙሪያለሁ። ከአገር ውጪ ደግሞ በሶማሊያ እና በሱዳን የትግል ስልጠናዎችን ወስጃለሁ። ቻድ-ሊቢያ-ኔዘርላንድ ከሱዳን በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዬ ቻድ ነበር። በቻድ በስደት ላይ በነበርኩበት ወቅት የሊቢያ መንግሥት ኡራ የሚባሉ የቻድ ሕዝቦችን ይበድል ስለነበረ ይህን በመቃወም አሁንም ተመልሼ ወደ ትግል ገባሁ። በትግል ላይ ሳለሁ በሊቢያ መንግሥት ተማርኬ ወደዚያው ተወሰድኩ። ሊቢያ ከአንድ ዓመት በላይ ጨለማ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ ታስሬ ቆይቼ ነበር። እጅግ መራራ ጊዜን ነበር ያሳለፈኩት። ከተፈታሁ በኋላ በብዙ ጥረት ወደ አውሮፓ አቀናሁ፤ ወደ ኔዘርላንድ። አሁን የምኖረው ናይሜጋን በምትባል የሆላንድ ከተማ ውስጥ ነው። እጅግ ውብ ከተማ ናት ታዲያ። የዚህ አገር ሰው ሲበዛ ሥራ ይወዳል። በዚህም ምክንያት ለራሳቸው እንኳ የሚሆን ጊዜ የላቸውም። በኔዘርላንድ ተወዳጅ ከሆኑ ምግቦች መካከል አንዱ የሆነው ''ኢስታንፖት'' በኔዘርላንድ ተወዳጅ ከሆኑ ምግቦች መካከል የኔ ምርጫ የሆነው ''ኢስታንፖት'' የሚባለው ምግብ ነው። ይህ ምግብ ከድንች እና ከካሮት የሚሠራ ሲሆን የኔዘርላንዶች ባህላዊ ምግብ ነው። ካለሁበት 38፡ ''ሳላስበው ወደ ትምህርት ዓለሙ የመቀላቀሉን ሕልሜን አሳካሁኝ'' እዚህ ''ዋል'' የሚባል ሥፍራ መጎብኘት ያስደስተኛል። ይህ የወደብ ሥፍራ ሲሆን ሰዎች ከመርከብ ላይ ሲወርዱ፣ እንዲሁም መርከቦች ባህር ላይ ሆነው ከርቀት በማየት ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች። ወደዚህ አገር በመምጣቴ የአእምሮ እረፍት ማግኘት ችያለሁ። ያም ኾኖ ግን ብቸኝነቱ ከባድ ነው። ሰዎች በአንድ አካባቢ ይኖራሉ እንጂ አይተዋወቁም። ይህ ሥፍራ ገጠራማውን የትውልድ መንደሬን ይስታውሰኛል። በምኖርበት ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ "ኦይ" የሚባል ልምላሜ ሥፍራ አለ። ይህ ሥፍራ ገጠራማውን የትውልድ መንደሬን ይመስለኛል። አካባቢው በተለያዩ ዓይነት ተክሎች የተሸፈነ ነው። ወደዚህ አገር ስመጣ ከብዶኝ የነበረው የአገሬውን ባሕል እና የአኗኗር ዘይቤ መላመዱ ነበር። በተለይ በሙቀት ወቅት እርቃናቸውን የሚሄዱ ሰዎችን ስመለከት በጣም እደነግጥ ነበር። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 42 : ''የጠበቀ ቤተሰባዊ ፍቅራቸውና ትስስራቸው ከኢትዮጵያውያን ጋር ያመሳስላቸዋል'' ካለሁበት 43፡" የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው"
news-47399590
https://www.bbc.com/amharic/news-47399590
ጎንደር፡ የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትን አደጋ ላይ የጣለው ምንድን ነው?
ጎንደር በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ፋሲለደስ እንደተቆረቆረች ይነገራል። ይሁን እንጂ ከአፄ ፋሲለደስ ንግሥና 300 ዓመታት ቀድማ በምንጮችና በተራሮች የተከበበች መንደር ነበረች ሲሉ የሚሞግቱም የታሪክ አዋቂዎች አሉ።
ጎንደር ለ200 ዓመታት የኢትዮጵያ መናገሻ ሆና አገልግላለች። ባሏት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶች፣ ታሪካዊ ቦታዎች እንዲሁም ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶች ትታወቃለች። የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈረው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ጎንደርን ከፋሲል ግንብ ነጥሎ ማየት ይከብዳል። ስለ ጎንደር የተዜሙ ሙዚቃዎች የሚነግሩንም ይህንኑ ነው። ዛሬ ዛሬ ግን የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ስም የሚነሳው በአስደናቂነቱ፣ በታሪካዊነቱና የኪነ ህንፃ ጥበቡ ብቻ ሳይሆን አደጋ የተጋረጠበት ቅርስ በመሆኑ ነው። በስፍራው ያገኘናቸው ጎብኚዎችም የፋሲል ግንብ ህልውና እንዳሳሰባቸው ገልፀውልናል። • የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር መቆየት ፋሲልን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ነው። "በጣም የሚገርም ጥበብ ነው ያየሁት። ታሪካዊ ቦታ ነው። ታሪካዊ በመሆኑ ደግሞ ለትውልድ የሚተላለፍ መሆን ነበረበት" ይላል። መቆየት ቤተ መንግሥቱን ተሰነጣጥቆና ተሰባብሮ ሲያየው ስሜቱ እንደተነካ ገልጿል። "ለምን ጥገና አይደረግለትም?" ሲል የሁሉም የሆነውን ጥያቄ ይጠይቃል። መንግሥትና የሚመለከተው የቅርስ ጥበቃ አካል ምን እየሠራ እንደሆነ ማወቅና መከታተል ያስፈልጋል ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሄደው ሌላው ጎብኝ ሳሙኤል በለጠም "ቤተ መንግሥቱን ሳየው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ" ይላል። ጥበብ የተሞላበትን ኪነ ህንፃ ሲያይ በኢትዮጵያዊነቱ ኩራት ተሰምቶታል። በሌላ በኩል ደግሞ ቅርሱ ጥበቃና እንክብካቤ መነፈጉ አሳፍሮታል። ሳሙኤል ይህን የተደበላለቀ ስሜት ውጦ ዝም አላለም። በጉዳዩ ላይ ከሥራ አስኪያጁ ጋር ተወያይተዋል። "ለምን ዝም እንዳሉ አልገባኝም፤ ለምን ከተማ ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል?" ሲል እንዲመለስለት የሚፈልገውን ጥያቄ ይሰነዝራል። ከዚህ ቀደም ላሊበላን መጎብኘታቸውን የሚናገሩት ምትኩ እንዳለ የአፄ ፋሲለደስን ግንብ ሲጎበኙ የመጀመሪያቸው ነው። በጉብኝታቸው ብዙ ጠብቀው ነበር። ይሁን እንጂ ያዩት ነገር አስደንግጧቸዋል። "ኢትዮጵያዊነትን እያጣን ነው" ሲሉ በአጭሩ ይገልፁታል። "ጥናት ተደርጎ በባለሙያ መጠገን አለበት፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት" ይላሉ። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? በጎንደር አስጎብኚዎች ማህበር አስጎብኚ የሆነችው ቁምነገር ቢምረው የፋሲል ግንብ ያን ያህል እየተጎበኘ አይደለም የሚል አቋም አላት። እሷ ዘወትር ስታየው የተለየ ስሜት እንደሚሰማትና እንደምትኮራ ትናገራለች። "ሳየው እኮራለሁ፤ ማንነቴን አገኘዋለሁ፤ ደስታ ይሰማኛል፤ በማያቸው ነገሮች እገረማለሁ፤ ትልቅ ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች እንደነበሩና፤ እኔም የዚያ ታሪክ አባል እንደሆንኩ ይሰማኛል። " ቢሆንም ግን እንደ ዓለም ቅርስነቱና ታሪካዊነቱ በመንግሥትም ሆነ በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም) ትኩረት ተሰጥቶት የሚያስፈልገው ጥገናም ሆነ እንክብካቤ እየተደረገለት አይደለም ትላለች። የአደጋው ምክንያት? ቁምነገር እንደምትለው፣ በፋሲል ግንብ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርካታ የሰርግ ሥነ ሥርዓቶች ይካሄዳሉ። ማህበረሰቡ ስለ ቅርስ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው ብዙዎች ፎቶ ለመነሳት ግንቦቹ ላይ ይወጣሉ። ሰርጉን ምክንያት በማድረግም ይጨፍራሉ። ይህ ቅርሱን አደጋ ላይ የጣለው አንድ ምክንያት እንደሆነ ታስረዳለች። ለቅርሱ ደህንነት ሲባል ማንኛውም የሰርግ እንቅስቃሴ መቆም አለበት ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች። • "ቤቶቹ በማንኛውም ሰዓት ሊደረመሱ ይችላሉ" የሥነ ሕንፃ ባለሙያ የሆኑት አቶ ማሞ ጌታሁን ተማሪ ሳሉ ጀምረው የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥትን (የፋሲል ግንብን) ለማየት ጉጉት እንደነበራቸው ያስታውሳሉ። ሥራ ሲይዙ ባህልና ቅርሶችን የሚከታተል መሥሪያ ቤት ተመድበው በቀጥታ ወደ ቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ሥራ ገቡ። ከ1980ዎቹ ጀምሮ የፕሮጀክት ጥናቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በአፄ ፋሲል፣ በእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥት፣ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን፣ በአፄ ፋሲል መዋኛና ሌሎች በርካታ ቅርሶች ላይ ከሙሉ የጥገና ሥራ እስከ መለስተኛ እንክብካቤ ድረስ ሰርተዋል። አቶ ጌታሁን ቅርሱ የሚገኝበትን ሁኔታ ለማየት ጥናት መሥራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ፋሲልን በተደጋጋሚ ጎብኝተውታል፤ የወዳጅ ያህል ያውቁታል። በዚህ ልምዳቸው የከተማ መስፋፋትና ያለ በቂ ጥናት የሚሰሩ ጥገናዎች በቅርሱ ላይ ችግር ሲያስከትሉ ተመልክተዋል። ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው ትኩረት ማነስ፣ የበጀት እጥረት፣ የእንክብካቤና ጥገና ጊዜ መዘግየትንም እንደ ምክንያት ይጠቅሳሉ። የፋሲለደስ ግንብ የአሁን ይዞታ የሥነ ህንፃ ባለሙያው እንደሚሉት፣ በቅርሱ ጣራያ ላይ ከሚታዩ ችግሮች በተጨማሪ ግድግዳዎች ተሰነጣጥቀዋል፤ በቅርፁ የመንሸራተትና የመዝመም እክሎችም ገጥመውታል። በአእዋፋትና በእፅዋት እንዲሁም በሌላ ንክኪ መብዛት የተነሳ ተሸርሽሯል፤ ካቦቹም ወዳድቀዋል። የጎንደር ዓለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር አስተዳደሪ አቶ ጌታሁን ሥዩም በበኩላቸው "የፍቅር ቤተ መንግሥት ከተዘጋ ከ10 ዓመት በላይ ሆኖታል፤ የዮሐንስ ቤተ መንግሥትም እንዲሁ ተዘግቶ ነው ያለው፤ የታላቁ እያሱ ቤተ መንግሥትም ከፈረሰ በኋላ ጥገና አልተደረገለትም" ብለዋል። የዳዊት ቤተ መንግሥትና የአፄ በካፋ ቤተ መንግሥትም እንዲሁ አደጋ ላይ እንደሚገኙ ሌሎቹም በርካታ ስንጥቆች እንዳሉባቸው ገልፀዋል። በአንድና በሁለት ሴንቲ ሜትር ይለካ የነበረው ስንጥቅ አሁን ወደ 5 ሴንቲ ሜትር ሰፍቷል። በምስጥና በፈንገስ ምክንያት የእንጨት አካሎቻቸው እየተበሉና እየበሰበሱ ይገኛሉ። አስፈላጊው ጥገና ካልተደረገ የመውደቅ ወይም የመደርመስ አደጋ ማጋጠሙ ጥርጥር የለውም። የመኪና ንዝረትና ግጭትም ቅርሶቹን ይፈታተኗቸዋል። መፍትሔው ምንድን ነው? ጎብኚዎች፣ አስጎብኚዎች እንዲሁም ባለሙያዎች ያስቀመጧቸው የመፍትሔ ሀሳቦች ተመሳሳይ ናቸው። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ቅርሱን የማዳንና የማቆየት ሥራ ሊሠሩ እንደሚገባ ይናገራሉ። ቅድሚያ የሚሰጠውን መለየት፣ ለቅርሱ ኃላፊነት ወስዶ የሚሠራን ሰው መመደብ፣ መገምገምና ክትክክል ማድረግ ይገባል። በቂ በጀት መመደብም ከመንግሥት ይጠበቃል ይላሉ። የቅርሶቹ የጉዳት መጠን በጥናት ታውቆ በቅርሱ አካባቢ የከባድ መኪኖችን እንቅስቃሴ መቆጣጠርም ያሰመሩበት ጉዳይ ነው። ምን እየተሠራ ነው? ለቅርሱ ጥበቃ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ የሚናገሩት የጎንደር ዓለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ጌታሁን ሥዩም ናቸው። በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚቻሉ የጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል ይላሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው ሀገራዊ ተቃውሞ ምክንያት የቱሪስት መቀዛቀዝ የታየ ቢሆንም አሁን ላይ በተሻለ ሁኔታ ጎብኚዎች ይመጣሉ። ይሁን እንጂ የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜ አናሳ ነው። "የግማሽ ቀን ጉዞ የሚያደርጉ ጎብኚዎች በዝተዋል፤ ይህም ከመሰረተ ልማት ጋር የተገናኘ ነው" ይላሉ። • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በየዓመቱ ከ1 ሚሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ይመድባል። ከሌሎች ድጋፍ አድራጊዎች ጋር በጋራ በመሆንም ቅርሱን ከአደጋ ለመጠበቅ እየተሠራ እንደሆነ አቶ ጌታሁን ገልፀዋል። ቤተ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን በውስጡ ያሉት ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምን ያህል ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው? ንጽህናቸውስ ይጠበቃል? የሚሉ ጥያቄዎችም ይነሳሉ። አቶ ጌታሁን፣ እነዚህና ሌሎችም በርካታ መዋቅራዊ ችግሮች ካልተፈቱ ቅርሱ "አደጋ ላይ ነው" የሚለው ቃል አይገልፀውም ይላሉ። የአፄ ፋሲለደስ ቤተመንግሥት የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት በ1979 ዓ. ም. በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን ያቀፈ ነው። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶች ከ100 በላይ ክፍሎች አሏቸው። ባለ ሦስትና ባለ አራት ፎቅ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ 7 ሄክታር (70 ሺህ ስኩየር ሜትር) ይሸፍናሉ። ግንቡ የተሠራው ከ300-400 ዓመታት በላይ በኖረ የድንጋይ ካብ ሲሆን በዋናነት ድንጋይ፣ ኖራና እንጨት ጥቅም ላይ ውለዋል። በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች መሠራቱም ይነገርለታል። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶችን ልዩ የሚያደርጋቸው እያንዳንዱ ነገሥታት የራሳቸውን አሻራና ታሪክ ለትውልድ ትተው ማለፋቸው ነው። ቤተ መንግሥቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ 1. የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት፡- ይህ ቀደምቱ ነው። ንጉሡ ቤተ መንግሥቱን ለማሳነፅ 10 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል። 2. የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት፡- አፄ ፋሲለደስ ለ36 ዓመታት ከነገሱ በኋላ ልጃቸው እሳቸውን ተክተው ወደ ስልጣን መጥተው ከ1667-1682 ዓ. ም. ሲነግሡ የተሠራ ነው። 3. የታላቁ አዲያም ሰገድ እያሱ ቤተመንግስት፦ የነገሡት ከ1682-1706 ዓ. ም. ነበር። ንጉሡ ጥሩ ፈረሰኛ ነበሩና በኮርቻ ቅርፅ የተሠራ ውብ ቤተ መንግሥት እንደተሰራ ታሪክ ያወሳራል። 4. የአፄ ዳዊት ቤተመንግስት፦ ለአምስት ዓመታት (ከ1716-1721 ዓ. ም.) ሲነግሡ ያሳነፁት ህንፃ ነው። ትልቅ የሙዚቃ ግንብ ያለው ሲሆን፣ ግንባር ቀደሙ የኪነ ጥበብ ማሳያ ህንፃ እንደሆነ ይነገራል። ጥቁር አንበሳ የሚባሉት አንበሶች መኖሪያ ይገኝ የነበረውም በዚህ ነበር። 5. የንጉሥ መሲሰገድ በካፋ ቤተ መንግሥት፦ ለዘጠኝ ዓመታት (ከ1721-1730) የነገሡ ሲሆን፣ የሳቸው ፍላጎት የነበረው ሕዝቡን ግብር የሚያበሉበት ትልቅ ሕንፃ መሥራት ነበር። ስለዚህም ከ250 በላይ ሰዎች መያዝ የሚችልና ፈረሶች የሚቆሙበት ቦታ ያለው ትልቅ የግብር አዳራሽ አሳነጹ። 6. የእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥት፦ ከ1730-1755 ዓ. ም. የነገሡ ሲሆን፣ በጣና ገዳማት ላይም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
news-41919875
https://www.bbc.com/amharic/news-41919875
የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን
ሶስትና አራት አስርት ዓመታትን ወደ ኋላ ብንሄድ የኢትዮጵያን የስነ-ፅሁፍ ስራዎች በሩሲያ ወይም በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ፀሀፊያን የትርጉም ስራዎች የተሞላ ነበር።
አያልነህ ሙላቱ ከቀድሞው መሪ መንግስቱ ኃይለማርያም በማስተርጎም ስራ ላይ ከነዚህም ውስጥ የፊዮዶር ዶስቶቭስኪ 'ክራይም ኤንድ ፐኒሽመንት' የሚለው ፅሁፍ ወንጀልና ቅጣት በሚል ርዕስ በሩሲያ አምባሳደር በነበሩት ካሳ ገብረ-ህይወት ተተርጉሟል። የዚሁ ደራሲ ስራ የሆነው 'ኖትስ ፍሮም አንደርግራውንድ' የስርቻው ስር መጣጥፍ በሚል የማክሲም ጎርኬይ እናት እንዲሁም የሊዮ ቶልስቶይ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው። በፅሁፋቸውም ስለ ሩሲያ አብዮት፤ ስለ ጭቆናና መደብ ትግል፤ ወይም ታዋቂ ስለሆነው ሬድ ስኩዌር (አደባባይ)ም ይሁን ስለ አጠቃላይ ባህሉ ጠቅሰዋል። በአድዋ ጦርነትም ይሁን ለሁለተኛ ጊዜ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ድጋፍ ወደሰጠቻት የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ብዙ ተማሪዎች በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ ሄደዋል። በተለይም ዓለም አቀፍ ሶሻሊዝም በተስፋፋበት ወቅት የሶቭየት ህብረትና የኢትዮጵያ ግንኙነት ጠንካራ ነበር። የሶሻሊዝምን ርዕዮተ-ዓለም የሚያንፀባርቁት የካርል ማርክስ፣ የቭላድሚር ሌኒን ሀውልቶች፤ የኮሚዩኒስት ማኒፌስቶ ትርጉም በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው። በዚያን ወቅት የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ሄደው ከተማሩት ውስጥ ታዋቂው ፀሐፊ-ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ይገኙበታል። አያልነህ የትያትር ድርሰትን ለመማር ወደ ሞስኮ ያቀኑት በንጉሱ ዘመን በ1962 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ የትምህርት ዕድል የነበረ ቢሆንም ከደራሲያን ማህበር መንግስቱ ለማ "ገንዘብን ለማካበት ከሆነ በካፒታሊዝም ወደ ምትመራዋ አሜሪካ ብሄድ ጥሩ እንደሆነ ነገር ግን ስነ-ፅሁፍን ለመማር ከሆነ ወደ ሶቭየት ህብረት ብሄድ ጥሩ እንደሆነ መከሩኝ" በማለት ይናገራሉ። ቦታው ላይ ሲደርሱ የአሌክሳንደር ፑሽኪን አያት ኢትዮጵያዊ/ኤርትራዊ ከመሆን ጋር ተያይዞ በክብር እንደተቀበሏቸው ያስታውሳሉ። ፀሀፊና ገጣሚ መሆናቸውም ከእሱ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ በመያያዙ ሞስኮ በሚገኝ ሬድዮ በሳምንት ሁለት ጊዜ "የደራሲው ደብተር" በሚል ርዕስ በአማርኛ የሬድዮ ፕሮግራም ያቀርቡ ነበር። ፑሽኪን ስለ አያቱ "ዘ ኒግሮ ኦፍ ፒተር ዘ ግሬት" በሚለውም ፅሁፉ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ በሶሻሊዝም፣ኮሚዪኒዝምና ማኦይዝም ርዕዮተ-ዓለም በተዋጠበት ወቅት የሶሻሊዝም ሀገራት የኑሮ ሁኔታ ምን እንደሆነ መሬት ላይ ያሳያቸው ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። "የሶቭየት ህብረት ሶሻሊዝም ሰዎችን የማያበላልጥ፤ የሰዎችንም ክብርም ከፍ የሚያደርግ ስርአት ነው" በማለት ይናገራሉ። በቦታው ሲደርሱ በጣም ያስደነቃቸውም የማህበራዊ አኗኗራቸው ነው። እንደ ኢትዮጵያ አይነት ከፍተኛ የማህበራዊ ኑሮ ትስስር ካለበት ቦታ ቢመጡም የሩሲያ ከማስደነቅም በላይ ነበር የሆነባቸው። "የግል ንብረት የሚባል የለም" የሚሉት አያልነህ በመጀመሪያ በመጡበትም ወቅት ሸሚዛቸውን ያለሳቸው ፈቃድ ለብሶ ያገኙትን ተማሪ ተናደው ሊጣሉት ባሉት ወቅት "ለምን እንደተናደድኩ አልገባውም፤ የኔ ልብስ እኮ ስላልታጠበ ነው፤ ሲታጠብ ትለብሳለህ" ብሏቸዋል። የካፒታሊዝም ዋና ፅንሰ-ሀሳብ የሆነውን "የሀብት ክምችትን" በመቃወም "ለነገ የሚያስቀሩት ነገር የለም" ይላሉ። ማንኛውም የሰው ልጅ መሰረታዊው ነገር ሊሸፈን ይገባል በሚለው መርሀቸው መሰረት ምግብ ርካሽ ከመሆኑ በተጨማሪ ህክምናና ትምህርት በነፃ እንደነበር ይናገራሉ። ኑሮ በሞስኮ ቀላል አልነበረም ምክንያቱም እንደ አቶ አያልነህ ሀይማኖት አጥባቂና ከፊውዳሊዝም ስርዓት የመጣ ሰው መደብ የሌለበትና እምነት እንደ ማርክስ አባባል ኦፒየም (ማደንዘዣ) የሚታይበት ሁኔታ ቀላል አልነበረም። በወቅቱም የሩሲያ አብዮት አመላካች የሆነችውን የቀይ ኮከብ አርማን "ኮከቧ ወደ እግዚአብሄር እያመላከተች ነው" በማለታቸው ብዙዎችን እንዳስደነገጠም አይዘነጉትም። ምንም ባይደርስባቸውም እምነትን እንዲህ ባደባባይ ላይ መናገር ፍፁም ክልክል እንደነበር ይናገራሉ። በወቅቱም ብዙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ስለነበሩ ማህበር የነበራቸው ሲሆን የአውሮፓ ተማሪዎች ማህበር አባል ነበሩ። "የሶሻሊዝሙ ዕምብርት ላይ ስለነበርን ማዕከልም ነበርን" ይላሉ። ሞስኮ ውስጥ እንጀራም ይሁን የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባይኖርም አብዛኛውን ጊዜ ከማርክስ ሀውልት አጠገብ ያለው ሬድ ስኩዌር የተባለ አደባባይ እንዲሁም ፑሽኪን አደባባይ እንደሚሄዱም ይናገራሉ። ስለ ደግነታቸው አውርተው የማይጠግቡት አያልነህ ልጃቸው ሩሲያ ከተወለደ በኋላ ይንከባከቡላቸው የነበሩት "ባቡሽካ" (የሩሲያ አያቶችንም) በእጅጉ ያስታውሳሉ። አሁንም የእርጅና ጊዜያቸውን እዛው ቢያሳልፉ ደስ እንደሚላቸው ይገልፃሉ። ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ከአቶ አያልነህ በ20 ዓመታት ልዩነት የሄዱት የስነ-ጥበብ መምህርና ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ልምድ ከዚህ በተቃራኒው ነው። የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ዋዜማ ላይ የሄዱት በቀለ መኮንን ታላቅ እየተባለ ሲሞካሽ የነበረው ሶሻሊዝም በከፍተኛ ደረጃ በሚተችበት፤ "የግራ ፖለቲካ ጣኦቶቻቸውን መደርመስ የጀመረበት ጊዜ ነበር" በማለትም ይገልፃሉ። ራሱን ሶሻሊስት ብሎ የሚጠራው የደርግ መንግስት "ብዙ ሰዎችን በማፈስ፣ በማሰር፣ በማንገላታት ላይ ስለነበር ወደ ሩሲያ መሄዱም አማራጭ ከማጣት ጋር ወይም ሽሽት ነው" ይላሉ። መጀመሪያ ሞስኮ የገቡበትን ቀን የማይረሱት በቀለ "አጥንት ድረስ የሚሰማው ብርድ ሲሰማኝ፤ ብረት የማሸት ነው የመሰለኝ" ይላሉ። በጊዜው ሶሻሊስት ተብላ ብዙ ጥፋት ካለባት አገር ወደ ሌላ ሶሻሊስት ሀገር መሄድ የነበረውን ስሜት ሲገልፁ "ሁሉን ነገር በጥርጣሬና በጥላቻ ነበር የምመለከተው፤ ሩስኪ በምማርበት ወቅት እንኳን የነበረኝን የእንግለዚዝኛ ቋንቋ ለማስጠፋትና ለማደናበር ይመስለኝ ነበር" ይላሉ። "ህዝቡ በፍርሀት ከተሸበበት እየወጣ በነበረበት ሁኔታ ላይ ነው የደረስኩት" የሚሉት በቀለ ሶሻሊዝም የተተረጎመበት መንገድም ትክክል ነው ብለው እንደማያስቡም ይናገራሉ። "ቤተ-ክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ነፃ ህክምናም ሆነ ነፃ ትምህርት አያገኙም፤ ስለዚህ ሰዎች ተደብቀው ይሄዱ ነበር" ይላሉ። መሰረታዊ ነገሮች የተሟሉበት ሁኔታ እንዲሁም ምግብ እንደ ሰብዓዊ መብት ታይቶ የሚራብ ሰው ባይኖርም ስርዓቱን መቃወም አይቻልም ነበር በማለት በቀለ ያወሳሉ። "የተቃወሙ ብዙዎች ወደ ሳይቤሪያ ይጋዛሉ፤ ነፃነት አልነበረም" ይላሉ። የነበረውን ስርኣት ከጆርጅ ኦርዌል "አኒማል ፋርም" ከተሰኘ ድርሰት ጋር የሚያመሳስሉት በቀለ በወቅቱ ይሰበክ የነበረውን የመደብ እኩልነትም ጥያቄ ውስጥ ይከቱታል። "ባቡር ውስጥ ስንገባ ሰዎች ይገላመጣሉ፤ ስታሊን በዘረጋው የጠበቀ ስለላ መሰረት ሚስቶች ባሎቻቸውን የሚሰልሉበት መረብም ነበር። ብዙዎችም ወደ ሳይቤሪያም ተግዘዋል" ይላሉ። የጅምላ አስተሳሰብ የሰፈነበት ስርዓት ነው ቢሉም የሥነ-ፅሁፍ ባህላቸው በጣም የመጠቀና የማንበብ ባህላቸው አስደናቂ እንደነበር ግን ሳያወሱ አያልፉም። የሩስያ የአብዮት ፖስተሮች የቦሪስ የልሰንን መሪነትን ተከትሎ የሶሻሊዘም ዓለም አቀፍነት ተደምስሶ በጥቁር ህዝብ ላይ ያለው ዘረኝነት ጎልቶ ቢወጣም በዛን ጊዜ ግን በአደባባይ ዘረኝነት እንዳልነበር ይናገራሉ። "ጥቁር ሰው አይተው የማያውቁ ወይም አንዳንዶች በግዴለሽነት ቢያደርጉትም ብዙዎች ከሩሲያ ወዳጅ ስለመጣን ማስቀየም ይፈሩ ነበር" ይላሉ። ምንም እንኳን በ6 አመት ቆይታቸው ሞስኮን ብዙ ባይወዱዋትም የሌኒን ግራድ፤ ዊንተር ፓላስ የመሳሰሉ አካባቢዎች ትዝታ አሁንም እንዳለ ነው።
news-55909547
https://www.bbc.com/amharic/news-55909547
የሚየንማር ወታደራዊ መሪዎች "አገሪቷን ለማረጋጋት" በሚል ፌስቡክን አገዱ
ከቀናት በፊት የሚየንማርን መንግሥት በኃይል የገረሰሰው ወታደራዊ ኃይል የማህበራዊ ሚዲያውን ፌስቡክ አግዶታል።
ወታደራዊ መሪዎቹ ፌስቡክን ለማገድ ምክንያት ነው ያሉት "አገሪቷ እንድትረጋጋ" ለማድረግ ነው ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የተነሳውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በርካታ የአገሪቷ ዜጎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉት በፌስቡክ ነው። ፌስቡክ ለተቃውሞው አጋርም ሆኗል እየተባለ ነው። ከዚህ ሰላማዊ አመፅ ጋር ተያያይዞ የአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ከመዲናዋ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቶች ወደ ውጭ አንወጣም በማለት ተቃውሟቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በያንጎን ከተማ እንዲሁ ነዋሪዎች ከበሮ በመደብደብ የሰላማዊ አመፁን እንዳጠናከሩ እየተዘገበ ነው። የፌስቡክ ሚና ምንድን ነው? የአገሪቱ ኮሚዩኒኬሽንና መረጃ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ፌስቡክ ለቀናት ያህል ዝግ እንደሚሆን ነው። ነገር ግን ሚኒስቴሩ ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላ ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዳንዶች ፌስቡክን እየተጠቀሙ እንደነበር ነው። በያንጎን የጉዞና የአስጎብኝ ድርጅት ያለው አንቶኒ አንግ ለቢቢሲ እንደተናገረው በዋይፋይ ፌስቡክን መጠቀም እንደሚችልና በዳታ ብቻ እንደታገደ ተናግሯል። በርካቶችም ፌስቡክን መጠቀም ያስችላቸው ዘንድ አማራጭ ቪኢኤን እየጫኑ እንደሆነም አስረድቷል። ነገር ግን ይህንን ከተናገረ ከሰዓታት በኋላ ሙሉ በሙሉ ፌስ ቡክ ተዘግቷል። በርካቶችም ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚጥስ ነው በማለት እየተቹት ነው። ከሚየንማር 54 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ግማሹ ፌስቡክን የሚጠቀሙ ሲሆን በተለይ በዚህ ወቅትም የአገሪቱ በርካታ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና አቀንቃኞች መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቃወም የፌስቡክ ገፆችን በመፍጠር ድምፃቸውን እያሰሙ ነበር። ፌስቡክ መታገዱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "ባለስልጣናቱ እግዱን እንዲያነሱና የሚየንማር ዜጎች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከወዳጅ፣ ዘመድና ጓደኞቻቸው ጋር በነፃነት መረጃ እንዲለዋወጡና እንዲገናኙ ማድረግ አለባቸው" በማለት ኩባንያው ጠይቋል። ቴሌኖር ሚየንማር የተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በበኩሉ ፌስቡክን እንዲያግድ የተሰጠውን የመንግሥት ትዕዛዝ ተግባራዊ ቢያደርግም ይህ ሁኔታ የሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ነው በማለት በመግለጫው አውጥቷል።
news-56023791
https://www.bbc.com/amharic/news-56023791
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ ተነገረ
የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚወስዱ ገለጹ።
በአካባቢው የትምህርት መሠረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሳምንታት ተፈታኞች በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚጓጓዙና ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማ መቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች እንደሆኑ ተገልጿል። በኦንላይን (በበይነ መረብ) ይሰጣል ተብሎ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29፣ 2013 ዓ. ም ጀምሮ በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫል ብሏል። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በበይነ መረብ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ መግለፃቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ፈተናው በወረቀት እንዲሰጥ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ታብሌቶች ወደ ሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ ጠይቋል። ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል። በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል። ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ እና 12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ መሆናችውን መናገራቸው ይታወሳል። በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናም እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ገልጸው ነበር። ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ግን በተለያዩ ደረጃዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት ይጀምራል ተብሎ ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በትግራይ ውስጥ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
news-52179743
https://www.bbc.com/amharic/news-52179743
ኮሮናቫይረስ፡ ተስፋ ቢኖርም ይህ ሳምንት ለአሜሪካ አደገኛው ይሆናል ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ባጠቃቸው ቦታዎች ላይ ለውጦች መታየታቸውን ተከትሎ በሽታውን ለማስቆም ተስፋ እንዳለ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።
በበሽታው የተያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የሚገኘው በአሜሪካ ትናንት እሁድ በአሜሪካ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ዋነኛ ማዕከል በሆነችው የኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱም ተነግሯል። ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ ይህ የቁጥር መቀነስ "ጥሩ ምልክት" እንደሆነ ቢናገሩም፤ ወረርሽኙ በአሜሪካ ከፍተኛው ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ተጨማሪ ሞት ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። "በመጪዎቹ ቀናት አሜሪካ የዚህን ወረርሽኝ ከፍተኛው ጉዳት ሊያጋጥማት ይችላል" ሲሉ በጽህፈት ቤታቸው በየዕለቱ በኮሮናቫይረስ ላይ በሚሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። • በኮሮና ዘመን የትኞቹ ፊልሞች ቀን ወጣላቸው? የአፍና ፊት መሸፈኛ ጭንብልና የመተንፈሻ መሳሪያዎችን ጨምሮ የህክምና ባለሙያዎችና መገልገያዎች በበሽታው ክፉኛ ወደ ተጠቁትና ከፍተኛ ድጋፍን ወደሚፈልጉት ግዛቶች እንደሚላኩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የፕሬዝዳንቱ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል የሆኑት ዴብራ ቢርክስ እንዳሉት በወረርሽኙ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በቅርብ ቀናት ውስጥ እየቀነሰ ባለባቸው ጣሊያንና ስፔን ውስጥ የሚታየው "ወደፊት በሚኖረው ሁኔታ ላይ ተስፋን የሚሰጥ ነው" ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ዶክተር ቢርክስ "ከበርካታ ሳምንታት በፊት ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው የበሽታው መስፋፋት በሚቀጥለው ሳምንት ሊረጋጋ እንደሚችል ተስፋ" መኖሩን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወረርሽኝ "በጣም መጥፎ ነው" ያሉት የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ የጤና አማካሪ ዶክትር አንተኒ ፋውቺ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች የፕሬዝዳንቱና የዶክተሯ የታያቸውን ተስፋ ጋር አይስማሙም። ነገር ግን ዶክትር አንተኒ ፋውቺ እንዳስጠነቀቁት "ይህ ሳምንት በአብዛኞቹ አሜሪካዊያን ህይወት ውስጥ ከባዱና አሳዛኙ ሳምንት ይሆናል።" "ይህ ሳምንት በታሪካችን ከባድ ጉዳት እንደደረሱበት የፐርል ሃርበርና የመስከረም 11ዱ ጥቃቶች ያህል ይሆናል" በማለት ለፎክስ ኒውስ የተናገሩት ደግሞ ዋነኛው ሐኪም ጄሮም አዳምስ ናቸው። አሜሪካ እስካሁን ድረስ ከ337 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውንና 9,619 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርት አድርጋለች። ይህም በዓለም ላይ ከፍተኛ በኮቪድ-19 የተያዙና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ነው።
55825417
https://www.bbc.com/amharic/55825417
ጀርመን አዛውንት ዜጎቼን አስትራዜኔካ የኮቪድ ክትባትን አልከትብም አለች
የጀርመን የክትባት ኮሚቴ አስትራዜኔካ ክትባት መሰጠት ያለበት ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በታች ለሆኑት ብቻ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።
ኮሚቴው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአዛውንቶች ላይ ክትባቱ ያስገኘው ውጤትን በተመለከተ በቂና የማያወላዳ ሳይንሳዊ ማስረጃ ባለመገኘቱ ነው። የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ዛሬ አርብ አስትራዜኔካ ክትባት ዕድሜያቸው ለገፉ ሰዎች ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ታላቋ ብሪታኒያ ይህን ክትባት በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ዜጎቿ እየሰጠች ትገኛለች። የጤና ባለሙያዎችም ደኀንነቱ የሚያሰጋ አይደለም፤ ከፍ ያለ መከላከል አቅምም አለው ሲሉ ይናገራሉ። ጀርመን ግን ይህን አሳማኝ ሆኖ አላገኘችውም። የአውሮጳ ኅብረትና አስትራዜኔካ ኩባንያ ከሰሞኑ በምርት አቅርቦት ማነስ ምክንያት ሲነታረኩ ነው የከረሙት። ይህ የጀርመን ዜና የመጣውም ይህ አለመግባባት ባልተቋጨበት ወቅት ነው። አስትራዜኔካ እንደሚለው በአውሮጳ ያሉ መድኃኒቱን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ችግሮች ካልተቀረፉ ክትባቱን ለአውሮጳ በተባለው ጊዜ ለማድረስ እንደሚቸገር ይናገራል። ነገር ግን የአውሮጳ ኅብረት አስትራዜኔካ ውል ገብቷል፤ ውሉን ማክበር አለበት፤ በታላቋ ብሪታኒያ ያለውን ክምችት ለአውሮጳ ኅብረት ሊሰጥ ይገባል ይላል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ወደ ሕግ እንደሚሄድም ኅብረቱ አስታውቋል። አስትራዜኒካ ብቻም ሳይሆን ፋይዘር እና ባዮንቴክም በተመሳሳይ ለ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አባል አገራት ክትባት በወቅቱ ማድረስ እንደማይችል አስታውቋል። የጀርመን መንግሥትን በክትባቶች ዙርያ የሚያማክረው የባለሙያዎች ኮሚቴ እንደወሰነው አስትራዜኔካ በአዛውንቶች ዘንድ የሚያመጣው የጎንዮሽ ጉዳትን በተመለከተ አስተማማኝ ሳይንሳዊ መረጃዎች እስኪገኙ ድረስ ጀርመን ክትባቱን መስጠት ያለባት ከ18 እስከ 64 ዓመት ለሆናቸው ዜጎች ብቻ ነው። ነገር ግን የታላቋ ብሪታኒያ የክትባት ዘመቻ መሪ ዶ/ር ሜሪ ራምሴይ በዚህ አይስማሙም። እሳቸው እንደሚሉት አስትራዜኔካም ሆነ ፋይዘር ዕድሜያቸው ለገፉ ሰዎች መስጠቱ ጉዳት አላሳየም። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጀርመን ኮሚቴ ያስተላለፈው ውሳኔ እንደማይረብሻቸውና አስትራዜኒካን ለሁሉም ዜጎች በስፋት ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
news-53159019
https://www.bbc.com/amharic/news-53159019
"ለፖሊስ በመደወሌ የጎረቤቴ ልጅ ህይወት ተቀጠፈ"
በቴክሳስ ግዛት ፎርት ወርዝ ከተማ ነዋሪ የሆው ጄምስ ስሚዝ በተቻለ መጠን ከፖሊሶች ጋር ምንም ግንኙነት እንዳይኖረውም ብዙ ጥሯል።
አንዳንድ ጊዜ ግን ያው አስገዳጅ ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም እና በአንድ ምሽትም ግዴታ ፖሊስ ጋር የሚያስደውለው አጋጣሚ ተፈጠረ። በጣም መሽቷል ግን ጎረቤቱ ግን በሯ እንደተከፈተ ነው። ምን ሁና ይሆን? በሚል ፖሊስ ጋር ደወለ። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተኩስ ሰማ፤ ቀጥሎም የጎረቤቱ የ28 ዓመት ሴት ልጅ አስከሬን በቃሬዛ ሲወጣ አየ። በጣም ተረበሸ። ተናደደ፣ ደከመው፣ አመመው፤ ምን እንደሚያስብ ሁሉ ግራ ገባው። ከዚያ በኋላ ማንኛውም ጥቁር ሰው በፖሊስ ሲገደል አታቲና ጄፈርሰንን የተገደለችበትን መጥፎ ጊዜ ያስታውሰዋል። "ከፀፀት ጋር አብሬ ነው የምኖረው፤ በሚቀጥሉት ዓመታትም መቼም ቢሆን ሊቀለኝ የማይችለውን ሸክም ተሸክሜ ነው የምኖረው፤ እንደ ሰማይ ያህልም ከብዶኛል" በማለትም የሚናገረው ጄምስ ፖሊስ ጋር የደወለበትንም ምሽት ይረግማል። ጥቅምት 12 ቀን፣ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል ነበር። የጎረቤቱ በር እንደተከፈተና መብራትም እየበራ ነው ብለው የቀሰቀሱት የእህቱና የወንድሙ ልጆች ናቸው። ጎረቤቱና የቤቱ ባለቤት ዮላንዳ ካር የልብ ህመምተኛ ስትሆን፤ በቅርብ ጊዜም ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል በተደጋጋሚ ከመግባቷ አንፃር አንድ ነገር ሆና ይሆን በሚልም ተጨነቀ። ከግቢው ወጥቶ መንገዱ ላይ ሆኖ ሲያይ በግቢዋ ውስጥ የአትክልት መኮትኮቻ ቁሳቁሶቹ በቦታቸው ናቸው፤ ሶኬቶቹም አለመነቀላቸው ግራ አጋብቶት ፖሊስ ደኅንነቷን እንዲያረጋግጥ በሚል ስልክ ደወለ። ያሰበው ፖሊስ መጥቶ በሩን አንኳኩቶ ቤተሰቡ ደህና መሆናቸውን ይጠይቃል በሚልም ግምት ነበር። ጄምስ ያላወቀው ግን ጎረቤቱ ዮላንዳ በዚያ ምሽት ሆስፒታል ነበረች። እናም ልጇ አታቲያናና የልጅ ልጇ ቪዲዮ እየተጫወቱ እየጠበቋት ነበር። በፖሊስ የተገደለችው አታቲያና ጄፈርሰን ፖሊስ ሲደርስም ጄምስ በቤቱ ትዩዩ ቆሞ ነበር። አሮን ዲን የተባለው አንደኛው ፖሊስ ሽጉጡን አውጥቶ ወደ በሩ ተጠጋ፣ በመቀጠልም ቤቱን በመዞር በአትክልት ስፍራው በኩል በጓሮ በር ወደ መስኮቱ ተጠጋ። ከጥቂት ሰኮንዶች በኋላ የተኩስ ድምፅ ተሰማ። "ተኩሱ እንደተሰማም ' እንዳታስመልጣቸው ስትል ድምጿን ሰማሁት" ብሏል ጄምስ። በመቀጠልም ምን እየተከናወነ እንደሆነም አልገባውም፤ ነገር ግን በርካታ ፖሊሶች መጥተው ጎዳናውን ሞሉት፤ በአካባቢውም ውር ውር ማለት ጀመሩ። ተኩስ ከሰማ ከስድስት ሰዓታት በኋላ ነው ምን እንደተፈጠረ ያወቀው። የጎረቤቱ ልጅ አታቲያና ጄፈርሰን እንደተገደለችም ተረዳ። አስከሬኗን በቃሬዛ ይዘውት ወጡ። የጄምስ ቤተሰብና የዮላንዳ ጉርብትና በቅርብ ነው የጀመረው። ዮላንዳ ቤቱን የገዛችው ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን፤ በቤቷም በጣም ነበር የምትኮራው፤ ያለቻትን አጠራቅማ የገዛችው ቤት። የእሷንና የጄምስን ቤትም የሚለየው የአትክልት ቦታና መንገድ ነው። ጄምስ በሰፈሩ ለረዥም ዘመናት ኖሯል። ልጆቹን እዚህ ነው ያሳደገው፤ የልጅ ልጆቹም እዚሁ ሰፈር ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አምስት የቤተሰቡ አባላትም እንዲሁ በዚያው አካባቢ ነው የሚኖሩት። ዮላንዳ ለዚህ ሰፈር አዲስ ብትሆንም ከጄምስ ጋር እየተቀራረቡ ነበር። ጄምስ ዮላንዳን ጠንካራ ሠራተኛ እንደሆነች ይናገራል "በህይወቷ ውስጥ ብዙ ፈተና ቢያጋጥማትም ያንን ተወጥታዋለች። ለዚያም ነው ቤት መግዛቷን እንደ ትልቅ ድል የምታየው" ብሏል። ልጇም አታቲያናም የእናቷን መታመም ተከትሎ ነው ልታስታምማት የመጣችው። እናቷን እንዲሁም የስምንት ዓመት የወንድሟን ልጅ ከመንከባከብ በተጨማሪ ለህክምና ትምህርት ቤትም የሚሆን ገንዘብ እየቆጠበች ነበር። ከመገደሏ ጥቂት ቀናት በፊት አካባቢያቸው ባለው መንገድ ላይ የመኪና አደጋ ተከስቶ ነበር። አታቲያናም በሩጫ ልትረዳቸው ከቤት ወጣች፤ እናም አምቡላንሱ እስኪመጣ ድረስ አብራቸው ቆየች በማለትም ቀናነቷን ያስታውሳል። "ዶክተር የመሆን ህልም ነበራት፤ ያንን እውን ሳታደርግ ተቀጨች" ይላል። ጄምስ አንዳንድ ጊዜ አትክልታቸውን ይኮተኩትላቸዋል፤ አታቲያናም የሚጠጣ ውሃ አምጥታ ይጫዋወቱ ነበር። የተገደለችበት ዕለት የወንድሟን ልጅ አትክልቶቹን እንዴት መንከባከብ እንዳለበት እያሳየችው ነበር። ከፖሊስ የተገኘው ቪዲዮ እንደሚያሳየው አሮን ዲን የተባለው ፖሊስ በጓሮ በኩል በሚገኘው መስኮት በኩል ሲሄድ የሚታይ ሲሆን፤ አታቲያናም በመስኮት በኩል ውልብ ስትል ትታያለች። "እጅ ወደ ላይ፣ እጅሽን አሳይ" በማለት ንግግሩን ሳይጨርስ በመስኮት በኩል ተኮሰ። ፖሊስ ነኝም አላለም። መሞቷንም ተከትሎ አሮን ዲን ከሥራ ከመባረሩ በፊት በራሱ ለቀቀ። ታህሳስ ወር ላይም በግድያም ወንጀል በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፤ ለአጭር ጊዜም በእስር ላይ ነበር። ነገር ግን የፍርድ ሂደቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲዘገይ ተደርጓል። የፎርት ወርዝ ፖሊስ ኃላፊ ኤድ ክራውስ "አታቲያና ጄፈርሰን ህይወቷን ያጣችበት መንገድ ምንም ትርጉም አይሰጥምም" ብለዋል። ኃላፊው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ዕለት ስሜታዊ ሆነው የታዩ ሲሆን የአታቲያና አሟሟትም በፖሊስና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ድልድይ አፍርሶታል ብለዋል። ለጄምስ ግን ኃላፈው ያሉትም ትርጉም ሊሰጠው አልቻለም፤ በሕግ አስከባሪዎች ላይ የነበረውን ጥቂት እምነቱንም አጥቶታል። "ከፖሊስ ጋር ጥሩ ግንኙነት የለንም፤ ምክንያቱም አናምናቸውም። በጭራሽ የማንገናኝም ከሆነ በህይወት የመቆየት እድላችን ከፍተኛ ነው" ይላል ጄምስ። ጄምስ ከዚህ ክስተት በኋላ ተአምር ቢፈጠር ፖሊስ ጋር እንደማይደውል ያውቀዋል። በቅርቡ እህቱ በሰፈራቸው ውስጥ የተኩስ ድምፅ ሰምታ ፖሊስ ጋር ደውል ብትለውም እምቢ ብሏል። "ጥቁር ካልሆንክ ነገሩን አትረዳውም" የሚለው ጄምስ በቅርቡም ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ሲያቅፉ፣ ሲንበረከኩ ቢያይም ቲያትር እንደሆነ ነው የተረዳው። ለአስርት ዓመታትም እንዲሁ ፖሊሶች ሲያስመስሉ መቆየታቸውንም ይናገራል። በተለይም የጎረቤቱን ልጅ ከገደላት ፖሊስ ጋር ተያይዞ ያለው የፍርድ ሂደትም በርካታ ጥያቄዎችን ያጭሩበታል። የአይን እማኝ ቢሆንም ሊያናግረው የመጣ ሰው የለም። አሟሟቷ ለሚዲያ ይፋ ባይሆን ኖሮ ምርመራ እንደማይጀመርም ተረድቷል። ያለው የፍርድ ሂደትም በከፍተኛ ሁኔታ ያናድደዋል። ወረርሽኙን እንደ ምክንያት በመጠቀም የፍርድ ሂደቱ ለሚቀጥለው ዓመት የተራዘመ ሲሆን በወንጀል የተጠረጠረው ሰው ጥቁር ቢሆን ኖሮ፤ ክስ እንደሚመሰረትበት እንዲሁም የፍርድ ሂደቱም እንደሚፋጠን ምንም ጥርጣሬ የለውም። "ትንፋሻችንን እንደያዝን ነው፤ መተንፈስ አልቻልንም" ይላል። አታቲያና ጄፈርሰንን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ አሮን ዲን በዓመታት ውስጥ በርካታ ፖሊሶች ብዙ ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም ማቁሰላቸውን የተለያዩ ተቋማትና ተመራማሪዎች በአብዛኛው ከሚዲያ ከሚገኙ ሪፖርቶች መረጃ ሰብስበዋል። ከእነዚህም ውስጥ 'ማፒንግ ፖሊስ ቫዮለንስ' በተባለው ድርጅት በባለፈው ዓመት ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 24 በመቶ ጥቁሮች ሲሆኑ፤ የጥቁሮች የሕዝብ ቁጥርም አስራ ሦስት በመቶ ብቻ ነው። ሌሎች መረጃዎችም እንደሚያሳዩት ከሌሎች ዘሮች በበለጠ ጥቁሮች በፖሊስ ሊተኮስባቸው እንዲሁም ሊገደሉ ይችላሉ። ግድያ የፈፀሙ ፖሊሶ መከሰስም የተለመደ አይደለም። ድርጅቱ በጎርጎሳውያኑ 2013- 2019 ባለው ጊዜ 7 ሺህ 500 የሚሆኑ ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸዋል ወይም ተድለዋል ይላል። ከእነዚህም ውስጥ 71ዱ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን 23ቱ ብቻ ናቸው የተፈረደባቸው። ጄምስም ስለ ጎረቤቱ ግድያ ለማውራት በቴሌቪዥን በቀረበበት ወቅት ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ የሕዝብ ቁጥር ባለባት ፎርት ወርዝ ባለፈው ዓመት ብቻ ሰባት ሰዎች በፖሊስ መገደላቸውን ተረድቷል። የጆርጅ ፍሎይድ ግድያንም ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ አንዳንድ አሰቃቂ ታሪኮች ለሕዝብ ይፋ ሆነዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት ክርስቶፈር ሎው የተባለው አጎቷ እንዴት በሁለት ፖሊስ ኃላፊዎች እንደተገደለ ቲፋኒ በንተን የተባለች ጥቁር ፖሊስ ተናግራለች። ከፖሊስ የተገኘው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ክርስቶፈርን እየጎተቱ ይወስዱታል። ለማየት በሚረብሸው ቪዲዮ ላይ ክርስቶፈር ለመራመድም ሆነ ለመቆም ሲታገል ይታያል። "አሞኛል፤ መተንፈስ አልቻልኩም፤ እየሞትኩ ነው" ቢላቸውም ፖሊሶቹ ሐዘኔታ አልነበራቸውም። አንደኛው ፖሊስም "ምራቅህ ቢነካኝ ከጭቃው ጋር ነው የማደባይህ" ሲልም ይሰማል። ከአስራ ሦስት ደቂቃ በኋላም ክርስቶፈር መኪናው ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። ቲፋኒ አጎቷ አሞኛል እያለ ሲማፀን ፖሊሶቹ አምቡላንስ ቢጠሩ ሞቱን ማስቀረት ይቻል እንደነበርም ታምናለች። ከግድያውም ጋር ተያይዞ አምስት ፖሊሶች ቢባረሩም ሁለቱ ከዓመት በኋላ ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል። አታቲያና ከሞተች ከሁለት ሳምንታት በኋላ አባቷ ማርክስ ጄፈርሰን በልብ ድካም ሞተ። የአታቲያና አጎት ሐዘን ወንድሙን ሐዘን እንደገደለው ያምናል። እናቷም ዮላንዳ ካር ታማ ሆስፒታል ስለነበረች ልጇን መቅበር አልቻለችም። ከሆስፒታልም ከወጣች በኋላ የልጇን ምስል ያለበት ቲሸርት ለብሳ፣ ልቧም በሐዘን ተሰብሮ ጄምስ አግኝቷት ነበር። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ የፎርት ወርዝ ከንቲባ ቤትሲ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ የጆርጅን ስም በመጥቀስ ሐዘናቸውን የገለፁ ሲሆን የአታቲያናን ስም ሳይጠቅሱ በማለፋቸው ጄምስን በጣም ነው ያሳዘነው። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ ተቃውሞ ቢቀጣጠልም ለምን የአታቲያና ሞትስ ተቃውሞን እንዳላነሳሳ ይጠይቃል። "ዝም ባልን ቁጥር መረሳቷ አይቀርም፤ እንድትረሳ አልፈልግም" ይላል። የአታቲያናንም ህይወት ለመዘከር እህቶቿና ወንድሞቿ በስሟ አንድ ፋውንዴሽን አቋቁመዋል። ፋውንዴሽኑ ትምህርት ላይ የሚያተኩር ሲሆን የተገደለችበት ቤትም እንደ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። የፖስታ ቤት ሠራተኛ የሆነው ጄምስ ቤቱ በልጆቹ የዲግሪና የማስተርስ ምርቃት ፎቶዎች ያሸበረቀ ነው። በርካታ መልካም ነገሮችን ያየበት ቤቱ እንዲሁም ሰፈሩ ነው። ዮላንዳም ብትሆን ከነርስነቷ ከምታገኘው ደመወዝ ልጆቿን አስተምራለች። የተደላደለ ህይወትም ለመኖር አቅዳም ነበር፤ ሳይሆን ቀርቶ ልጇን አጣች። ለዮላንዳ ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ ለኖረው ጄምስም ሰፈሩ ሞትን ያስታውሰዋል። የአታትያና ሞት ከጭንቅላቱ ሊጠፋ አልቻለም። የተኩሱ ድምፅ በጭንቅላቱ ውስጥ ይሰማዋል። ባልሰራው ወንጀል ለሃያ ሶስት አመታት የታሰረው ሮበርት ጆንስ በአሜሪካ ውስጥ በጥቁሮች ላይ የሚፈጸም ኢ-ፍትሃዊነት አዲስ ነገር አይደለም። ሮበርት ጆንስ በጎርጎሳውያኑ 1992 በኒው ኦርሊያንስ ውስጥ እንግሊዛዊ ቱሪስቶችን ገድለሃል በሚል ወንጀል ተከሰሰ። ከአራት ዓመታት በኋላ የፍርድ ሂደቱ የተካሄደ ሲሆን በዚህም ወቅት ሌላ ግለሰብ በወንጀሉ ቢፈረድበትም ሮበርት ጆንስም በተመሳሳይ ወንጀል እንዲሁ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። ንፁህ ቢሆንም ለሃያ ሦስት ዓመታት ያህል በእስር ቆይቷል። የፈረዱበት ዳኛ በቅርቡም የቆዳው ቀለም የህይወቱን መጥፎ እጣ ፈንታ ወስኖለታል ሲሉ ተሰምተዋል።
news-52106876
https://www.bbc.com/amharic/news-52106876
ኮሮና ቫይረስ፡ "ከቫይረሱ በላይ የሚያስጨንቀን ረሃብ ነው?" የናይጄሪያዋ ጉሊት ቸርቻሪ
የኮሮና ቫይረስ መዛመትን በመፍራት ብዙ አገራት የከተሞቻቸውን እንቅስቃሴ የመገደብ እርምጃን እየወሰዱ ሲሆን ናይጄሪያም ዋና ዋና ከተሞቿ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ ወስናለች።
ሃያ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ናይጄሪያውያን እንቅስቃሴያቸው ተገድቧል። በተለይም በተጨናነቁ መንደሮች ለሚኖሩት ሁኔታው ዱብ እዳ ነው የሆነባቸው፤ የማይወጡት አዘቅት፤ እንደ ሰማይ ከባድ ሆኖባቸዋል። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ንዱካ ኦሪጅንሞ ከናይጄሪያዋ ንግድ ማዕከል ሌጎስ የተወሰኑትን አናግሯል። "ይሄን የምትሉትን ለእጅ መታጠቢያ የሆነውን ውሃ ከየት ነው የምናገኘው" በማለት የ36 ዓመቷ ዴቢ ኦጉንሶላ ትጠይቃለች። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች የንግድ ማዕከል የሆነችውን ሌጎስ፣ አጎራባቿን ኦጉን እንዲሁም ዋና መዲናዋን አቡጃን ለሁለት ሳምንታት ያህል የመዝጋት ውሳኔ የተላለፈው በትናንትናው ዕለት ሲሆን፤ የአገሪቱም ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የቫይረሱን መዛመት ለመከላከል ብቸኛው አማራጭ ይሄ ነው ካሉ በኋላ "ይህ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው" ብለዋል። ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱ ይህንን ይበሉ እንጂ እንደ ዴቢ አጉንሶላ ላሉ ሰዎች ቤት ውስጥ መቀመጥ ፈታኝ ነው። እሷም ሆነ ቤተሰቦቿ በአንድ ቤት ውስጥ ሆነው ተጨናንቀው ነው የሚኖሩት፤ በተለምዶም ቤቶቻቸው ካላቸው መጠጋጋት የተነሳ 'ፊት ለፊት' የሚል ቅፅል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል። የቢቢሲ ጋዜጠኛም በቦታው በተገችበት ወቅት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን በቤቱ ውስጥ ጭላንጭል ብርሃን ይገባል። በአካባቢው የሚኖሩ 20 ቤተሰቦችም የሚጋሩት ሁለት መፀዳጃ ቤትና መታጠቢያ ቤት አላቸው። "የምንፈራው ረሃብን ነው፤ ቫይረሱን አይደለም" ዴቢ በምትኖርበት አላፔሬ የውሃ መስመርም ሆነ ውሃ ባለመኖሩ በአቅራቢያዋ ካለ አምሳ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የተሰበረ የህዝብ ቧምቧ ሄዳ ትቀዳለች። "ከኔ በላይ የምጨነቀው ለልጆቼ ነው" ትላለች። ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየጣለ ቢሆንም አራቱም ልጆቿ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። "ወጥቼ አትክልትና ፍራፍሬ መንገድ ላይ ካልሸጥኩ ልጆቼ ምን ይበላሉ? እንዴትስ ይተርፋሉ" ትላለች ጉሊት በመቸርቸር የምትተዳደረው ዴቢ። እጇን የምትታጠብ ልጅ ባለቤቷ በደቡብ ናይጄሪያ በምትገኘው ዋሪ የነዳጅ ማውጫ ውስጥ ተቀጥሮ ነው የሚሰራው፤ ቤቱም የሚመጣው በየወሩ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወር ላታየው ትችላለች፤ ናይጄሪያ በተለያዩ አካባቢ የሚገኙትን ሪቨርስ፣ ዴልታ፣ ካኖ፣ ባዬልሳ ድንበር ከተሞች መዝጋቷ፤ ከአንድ ግዛት ወደ አንድ ግዛት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዲገደብ አድርጎታል። የከተሞች መዘጋት ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ባለቤቷን የምታይበትን ጊዜ ሩቅ ያደርገዋል። "የሚያስጨንቀኝ ረሃብ ነው፤ ቫይረሱ አይደለም። ቫይረሱ ህፃናትን እንደማይገድል ሰምቻለሁ" ትላለች ኦጉንሶላ ። ምንም እንኳን ቫይረሱ ክፉኛ የሚያጠቃውም ሆነ የሚገድለው በዕድሜ ከፍ ያሉትን እንዲሁም ተደራራቢ የጤና እክል ያላቸውን ቢሆንም ዴቢ እንደምትለው ሳይሆን ህፃናትም በቫይረሱ እየሞቱ ነው፤ ቫይረሱንም ከሰው ወደ ሰው ያስተላልፋሉ። •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው ቤሳ ቤስቲን በሌለበት ሁኔታ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የዴቢ ብቻ አይደለም፤ የጎረቤቶቿ እንዲሁም ድንበር፣ ወንዝ፣ ባህልን ተሻግሮ በድህነት የሚኖሩባት የዓለም ሁኔታ ነው። የዴቢ ጎረቤት ተለቅ ያለ በረንዳ ያላቸው ሲሆን ሁለት በእድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ቁጭ ብለው ያወራሉ። በእድሜ ተለቅ ያሉ ቤተሰቦች እንደ ልጆች ጠባቂ ሆነው ከልጆቻቸው እንዲሁም ከዘመዶች ጋር መኖር የከተሜው እውነታ ነው። በዚህም ሁኔታ ቫይረሱ ቢዛመት በእድሜ ለገፉት ከፍተኛ ስጋት ነው። "አሁንም ቢሆን ሰብሰብ ብለው ቤት ይቀመጣሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ ቢያዝ በአካባቢው ያሉ ሰዎች የመያዛቸው እንዲሁም የመዛመቱ ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ነው" ይላሉ የጤና ባለሙያው ዶ/ር ኦየዋሌ ኦዱባንጆ። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው በጣልያንም የአኗኗር ሁኔታቸው ለቫይረሱ መዛመት ምክንያት ነው። አያቶች፣ አጎት፣ አክስት፣ አባት፣ እናት፣ ልጆች፤ የተለያየ ትውልድ ተሰባስበው ይኖሩባት የነበረችው ጣልያን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ህይወት አጥታለች። ናይጄሪያም የሌሎች አገሮችን ፈር በመከተል እንቅስቃሴዎች የተገደቡ ሲሆን፤ የግሉም ይሁን የመንግሥት ሰራተኞች ከቤት እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል። መብራት በሚቆራረጥበት እንዲሁም ደካማ ኢንተርኔት ባለበት ሁኔታ ከቤት ሆኖ ሥራ ይሰራል ማለት አስቸጋሪ ነው። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ከተሞች መዘጋታቸውን ባወጁ ማግስት በትልልቅ መደብሮች ላይ ምግብ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቁሶችን ለመሸመት ተሰልፈውም ታይተዋል። ነገር ግን ይሄ የብዙ ናይጄሪውያን እውነታ አይደለም። ከእጅ ወደ አፍ ለሆነው ናይጄሪያዊ፣ ቤሳ ቤስቲን ለሌለው ናይጄሪያዊ የነገን ምግብ ማከማቸት አይደለም ዛሬን በልቶ ማደር ቅንጦት ነው። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች ብዙ ናይጄሪያውን የዚህ ወር ደመወዝ እየጠበቁ ከመሆናቸውም አንፃር የኑሮ ሁኔታቸውን አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶታል። ይህንን ሸክም ለማቃለል በሚል ፕሬዚዳነት ሙሃማዱ ቡሃሪ የደሃ ደሃ ተብለው ለተለዩ ሰራተኞች 420 ብር ቅድሚያ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ቢወስኑም ኢ-መደበኛ በሆነ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሚሊዮኖች ናይጄሪያውያን ከአርዳታው ውጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል በማለትም እየተተቹ ነው። "የሚሸምተውም ሆነ የሚያከማቸው ገንዘብ ያለው ነው። ገንዘብ ከሌለ ምን ማድረግ ይቻላል?" ይላል ከአንደኛው ትልቅ መደብር ውጭ የቆመ የታክሲ አሽከርካሪ። ሌላኛው ፍራቻ ደግሞ በከተሞች ያሉ ችግሮች ከተባባሱና ከፍተኛ የምግብ እጥረት የሚያጋጥም ከሆነ ብዙዎች ምግብ ለማግኘት ገጠር ወደሚገኙ ዘመዶቻቸው ለመሰደድ ይገደዳሉ። ይህም ሁኔታ በመጀመሪያ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የእድሜ ባለፀጎች ለቫይረሱ ያጋልጣል፤ በተለይም የጤና አገልግሎት ደካማ በሆነባቸው በነዚህ ስፍራዎች መሆኑ ደግሞ ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ያደርገዋል። በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ጣልያናዊ ሲገኝ የናይጄሪያ ባለስልጣናት ግለሰቡን ለይቶ ማቆያ ውስጥ በማስገባት፤ ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እንዲሁም ንክኪ ያላቸውን ክትትል በማድረግ ከዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ምስጋና ተችሯቸው ነበር። ነገር ግን አሁን ቫይረሱ እንዳይዛመት ያደረገችው ጥረት እንዲሁም ወረርሸኙን ለመቆጣጠር ያላት የጤና ሥርዓት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። "ይህንን ጊዜ እናልፈዋለን" አገሪቷ ያሏት መመርመሪያዎች ጥቂት ቢሆኑም ምልክቱ ያልታየባቸው የመንግሥት ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች መመርመራቸው የፍትሃዊነት ጥያቄን አጭሯል። ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ስልጣን ሲረከቡ ለህክምና የሚደረጉ ማንኛውም የውጭ ጉዞዎችን እንደሚያስቀሩ ቃል ቢገቡም እሳቸውም ሆነ ሌሎች ባለስልጣናት ለህክምና የሚያደርጉትን የውጭ ጉዞ አላቆሙም ነበር። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ግን ይህ የሚሆን አይደለም። ሌጎስም ሆነ ሌሎች ከተሞች ስብሰባዎችንም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ቢያግዱም፤ ፓስተሮችን ጨምሮ ብዙዎች አካላዊ ርቀት መጠበቅ የሚለውን እየጣሱት ይገኛሉ። አላፔሬ በሚገኘውና በተጨናነቀው የአውቶብስ መናኸሪያ ጉሊት ቸርቻሪዎች፣ እንዲሁም ጌጣጌጥና ልብሶችን መንገድ ላይ የሚሸጡ ግለሰቦች መሸጫ ቦታ ይፈልጋሉ። ከቫይረሱ በላይ የእለት ጉርሳቸው ያስጨንቃቸዋል። "ሁሉም ሞት ሞት ነው" ትላለች በሁለት አውቶብሶች እየተመላለሰች በትሪዋ ላይ አሳ እየሸጠች የነበረች ሴት። "ቤቴ ብቀመጥ በረሃብ እሞታለሁ፤ እዚህ መጥቼ የዕለት ጉርሴን ለማግኘት ብሞክር በቫይረሱ እንደምሞት እየነገራችሁኝ ነው" "በህይወታችን ብዙ ፈተና አይተናል፤ ያላየነው ነገር የለም። አሁንም አለን፤ ነገን እናያለን፤ ይህንንም ጊዜ እናልፈዋለን"ብላለች።
news-53698695
https://www.bbc.com/amharic/news-53698695
ኮሮናቫይረስ ፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት ፖለቲካዊ ጦርነት ያጋጥም ይሆን?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዓለም ስጋት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የማንነካ ነን የሚሉ ታላላቅ አገራትን እያብረከረካቸው ይገኛል። የሰው ልጅ ደረስኩበት የሚለውን የሳይንስ ልህቀት ፈትኗል፤ እየፈተነም ይገኛል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እስካልተገታ ድረስ የዓለም ሕዝብ ወደቀደመው ህይወት መመለስ አይችልም። እናም ቀጣዩ እሽቅድምድም የኮቪድ-19 ክትባትን ማግኘት ሆኗል። በርካታ ኃያላን አገራት አሜሪካ፣ ቻይና ሩሲያና ዩናይትድ ኪንግደም ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ክትባቱ በማዞር ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸውን እየፈተኑ ይገኛሉ። በርካታ ሳይንቲስቶቻቸውን በማሰማራትና የምርምር ማዕከላትም ላይ በርካታ መዋዕለ ንዋይም እያፈሰሱ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በዚህ ሰዓት በሙከራ ላይ ካሉ ክትባቶች መካከል የትኛው ቀድሞ ይደርሳል የሚለውን መገመት ቢከብድም፤ የበለፀጉት አገራት በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች እያወጡ ከላብራቶሪዎች እነዚህን ክትባቶች እየገዙ ይገኛሉ። በዚያም መንገድ አቅርቦታቸውንም እየጨመሩ ነው። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንግደም የክትባት ሙከራውን ከሚያቀርቡት አስትራዜንካ፣ ፋይዘርና ባዮንቴክና ቫልኔቫ ከተባሉት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ፈርማለች። እነዚህ ስምምነቶች ሁለት አገራትን ያካተቱ ሳይሆኑ በኩባንያዎችና በአገራት ወይም በግለሰቦች መካከል የሚፈፀሙ ክስተቶች በመሆናቸውም "የክትባት ብሔርተኝነትም" እየተባለ ነው። ለክትባቶች የሚደረገውን እሽቅድድም በተመለከተ ቢቢሲ ካውንስል ኦን ፎሬይን ሪሌሽንስ (የውጭ ግንኙነት ጉባኤ) ጥናት ማዕከል ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሪቻርድ ኤን ሃስን አናግሯል። ግለሰቡ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮም በፖሊሲ አውጪ ዳይሬክተር እንዲሁም የአፍጋኒስታን እጣፈንታ ፕሮግራምና አየርላንድንም በተመለከተ ልዩ መልዕክተኛና አስተባባሪ ሆነው ሰርተዋል። በባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እነዚህ ኃያላን አገራት የተለያዩ የክትባት ሙከራዎች ዕውቅና ከማግኘታቸው በፊት እየሸመቱ ይገኛሉ። እሽቅድምድም ይመስላል። ይህንንም በማስመልከት እርስዎም "የክትባት ብሔርተኝነት" እየታየ፣ እየጎላ ነው በሚል ፅፈዋል። እንዲሁም ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል አስፍረዋል። እንዴት እንዲህ ሊሉ ቻሉ? በርካታ አገራት የኮቪድ 19 ክትባትን የግላቸው ለማድረግ እየተሽቀዳደሙ ነው። አገራቱ ማንም እንዳይቀድማቸው በገፍ እየሸመቱም ይገኛሉ። ይሄ መቅረት የሚችል ብሔርተኝነት ነው። መንግሥታት ከሁሉ በፊት የራሳቸውን አገራት በማስቀደምም ላይ ይገኛሉ፤ ምክንያቱ ግልፅ ነው። እነዚህ መሪዎች ለዜጎቻቸው የኮሮናቫይረስን ወረርሸኝን በመግታትና ክትባቱንም አቅርቡ በሚል ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል። ችግሩ ግን እነዚህ አገራት ብቻ በበላይነት ክትባቶቹን ከያዟቸው ቢሊዮኖችን ያገላል፤ አይደርሳቸውም። በተለይም ተጋላጭ ለሆኑት ማኅበረሰብ አለመድረሱ ቀውስን የሚፈጥር ነው። ከዚህም በተጨማሪ ክትባት ብሔርተኝነትን ሙጭጭ ብለው ለያዙት ለእነዚህ አገራት መንግሥታትም ውጤቱ አሉታዊ ነው። በእነዚህ አገራት በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራቸው በሽታው በዚያው አይገታም። ዓለም ካለችበት የግሎባላይዜሽን ሥርዓት በሽታው ይዛመታል፤ ወደ ሌሎች አገራትም መሰራጨቱ ስለማይቀር ነው። በአሁኑ ወቅት ከክትባቶቹ ጀርባ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ የሆነ የብልጦች አካሄድ ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ላይ ናቸው። በሆነ መንገድ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት ላይ መደረስ ካልተቻለ ቀውስ ይፈጠራል። በአገራቱ ያለውን የፖለቲካ ጫና በተወሰነ መልኩ እረዳዋለሁ። ለአንድ መንግሥት ሌሎች አገራትን መርዳት አለብን እንዲሁም በተመሳሳይም ራሳችን መርዳት አለብን የሚለውን አብሮ ማስኬድ ፈታኝ ነው። የኮሮናቫይረስ ክትባት ፖለቲካዊ ጦርነት ላይ ነን ወይስ ሊገጥመን ይችላል? ጦርነት ባልለውም ለክትባት የሚደረግ ውድድርና እሽቅድምድም እለዋለሁ። ሁሉም ቀዳሚ መሆን ይፈልጋል። አንዳንዶች ለንግድና ትርፍን ለማጋበስ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ፖለቲካዊ ምክንያቶችን ከጀርባው ሰንቀዋል። ዋናው ችግሩ ከዚህ በበለጠ በርካቶች በቫይረሱ የሚያዙ ከሆነ መላው የዓለም ሕዝብም ተጋላጭ ነው። የዚህም በሽታ ዋነኛ አስተማሪነቱ ይሄ ነው። አንድ አገር ከሁሉ ቀድማ የኮሮናቫይረስ ክትባቱን ብታመርትም በሌሎች አገራት ላይ ጥገኛ መሆኗ አይቀርም። ምክንያቱም ምርቱን ለማምረት የተለያዩ ግብዓቶችን ከተለያዩ አገራት መፈለግ አይቀርም። የየትኛውንም አገር ድጋፍ ሳያስፈልገኝ መቶ በመቶ ራሴን የቻልኩኝ አገር ነኝ ማለት የሚችል ያለ አይመስለኝም። በክትባቱም እንደዚሁ ነው፤ ከሌሎች አገሮች ለክትባቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ሳልጠቀም መቶ በመቶ በራሴ ብቻ የኮሮናቫይረስ ክትባትን መስራት እችላለሁ የሚል የለም። ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? አገራቱ ስምምነትስ ላይ እንዴት ሊደርሱ ይችላሉ? ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ልክ እንደ ኢንሹራንስ ፖሊስ ስምምነት ላይ ለመድረስ ይሞክራል። ይሄ ስምምነትም ዋነኛው ነገር ምንድን ነው አንድ አገር የኮሮናቫይረስ ክትባትን ባያመርት የተለያዩ አገራት ከክትባቱ የሚጠቀሙበትን መንገድ መቀየስና ማከፋፈል ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት ያሻዋል። ክትባቱ ከተገኘ በኋላ መንግሥታት ለመከፋፈል መንገድ ለማበጀት ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸው። ለምሳሌ አንድ መንግሥት ግማሹን ክትባት ለራሱ ሕዝብ ካዋለ ግማሹን ለተቀረው ዓለም የሚሰጥበት መንገድን ማሰብ አለበት። በዚህም መንገድ ሁሉም ተጠቃሚነቱ ይረጋገጣል። እንደነዚህ አይነት ስምምነቶች ላይ መደረስ ከተቻለ የተለያዩ አገራት ክትባቱን ባያመርቱም እንኳን ለሕዝባቸው ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው። እንደነዚህ አይነት ስምምነቶች ላይ የሚደረስ ይመስልዎታል? አይሆንም፤ የሚደረስ አይመስለኝም። በርግጠኝነት አሜሪካ፣ ቻይና የመሳሰሉት አገራት ክትባቱን በመጀመሪያ የሚያገኙት እነሱ እንደሆኑ ልበ ሙሉ ናቸው። እናም ከዚህ ክትባት ቅድሚያ መጠቀም ይፈልጋሉ፤ ይሄንንም ለዓለም ሕዝብ አሳልፈው መስጠት አይፈልጉም። ቅድሚያ ለሕዝባቸው እንደሚሉም እርግጠኛ ነኝ። በአሁኑ ሰዓት ብሔራዊ ስሜት በከፍተኛ ሁኔታ የጎለበተበት ወቅት ነው። ቅድሚያ ለእኔ! ለብቻዬ የሚሉ ሁኔታዎችም ይሰማሉ። መንግሥታት ከሌሎች አገራት ጋር የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለመከፋፈል ስምምነት ላይ ቢደርሱ በአገራቸው ፖለቲካዊ ክፍተት ይፈጠራል፤ እንዲሁም ጨና ይፈጠርብናል ብለው ያምናሉ፤ ሊሆንም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ክትባትንም ለማግኘት የመጀመሪያ መሆን በራሱ ድል የማድረግ ስሜት አለው፤ ጠንካራ ምልክትም ነው፤ በተለይ የፖለቲካ ኃይልንን ለመቆጣጠር። ክትባቱን በመጀመሪያ ማግኘት የራሱ ጥቅሞች አሉት። ነገር ግን አሁን ያለውን አካሄድ ስንመለከተው በርካታ ክትባቶች ይፈጠራሉ እነዚህ ክትባቶች ደግሞ መፍትሄ አይሆኑም። ሁሉም ክትባቶች የራሳቸው ውስንነት አላቸው። ምን ያህል ሰዎችን መርዳት ይችላሉ እንዲሁም ከጎንዮሽ ጉዳቶችና ሌሎችም ነገሮች ተያይዞ ማለት ነው። ይህን ውይይታችንን የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ሰዎች ክትባቱ ሲገኝ የወርቅ ሜዳልያ እንደተገኘ ያህል ሊቆጥሩት እንደሚችሉ ሳስብ ነው። ብዙዎች የክትባቱ መገኘት የኮቪድ-19 መፍትሄ ነው፤ አበቃ አከተመለትም ሊሉ ይችላሉ። ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም። የክትባቶችን ታሪክ ብናይ ለበሽታዎች ክትባት ሲገኙ የተወሰነውን ሰው ነው መርዳት የሚችሉት ሁሉንም አይደለም። ለተወሰነ ጊዜም የሆነውን ማኅበረሰብ ክፍል ይረዳሉ። ያልተፈለገ የጎንዮሽ ጉዳትም ያስከትላሉ ብዙዎች አንወስድም ብለው ያቆሙታል። የእኔ ግምት አንድም ይሁን ሌሎች ክትባቶች ቢገኙም የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት አሁን የምናደርጋቸውን ጥንቃቄዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ጭምብል ማድረግ እንዲሁም እጅን በተደጋጋሚ መታጠብና በፀረ ተህዋሲያን ማፅዳቱን የምንቀጥልበት ይሆናል። በርካቶች ክትባቱ ሲገኝ የሚኖረውን ሚና ያገዝፉታል ወይም ያዳንቁታል። ክትባቱ ሁላችንንም አያድነንም። ክርክሩ በመርህ ደረጃ ልክ ነው። እውነታውን ካየነው በአሁኑ ሰዓት አገራት ክትባቶችን የራሳቸው ለማድረግ ነው እንጂ ለሌሎች ሲያስቡ አይታይም። በአገራቱ መካከል ስምምነቶች መደረስ ካልቻሉስ ዋናው አደጋ የሚሆነው ምንድን ነው? ዋናው አደጋማ የሰብዓዊ ቀውስ ይፈጠራል። በርካታ አገራት የምጣኔ ሃብትም ሆነ ለጤና ሥርዓቱ ምላሽ መስጠት አይችሉም። ክትባቶቹንም በብልህነት ካልተጋራናቸው ቫይረሱ ዓለማችንን ሊያጥለቀልቃት የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። በርካቶችም ተጋላጭ ይሆናሉ።
news-55905192
https://www.bbc.com/amharic/news-55905192
በሚየንማር ሳን ሱቺ ይለቀቁ የሚሉ ጥያቄዎች መበርታታቸው ተሰማ
በትናንትናው ዕለት በቀድሞዋ በርማ በአሁኗ ሚየንማር ጦሩ በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ የአገሪቷ መሪ ኦንግ ሳን ሱ ቺ ይለቀቁ የሚሉ ጥያቄዎች በርትተዋል።
የኖቤል ተሸላሚዋና በምርጫ ስልጣን የተቆናጠጡት ኦንግ ሳን ሱ ቺ በወታደሮች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ አልታዩም ተብሏል። ከሳቸው በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርላማ አባላትም በመዲናዋ በሚገኘው መኖሪያ ስፍራቸው በወታደሮች ተከበው ነው የሚገኙት። ምንም እንኳን ይኸንን ያህል ጠንከር ያለ ተቃውሞ በአደባባዮች ባይሰማም የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ መትተዋል ፤አንዳንድ እምቢተኝነትም እየተስተዋለ ነው። በቅርቡ በምርጫ ማሸነፋቸው የታወጀውን ኦንግ ሳን ሱ ቺን ፓርቲ ምርጫውን አጭበርብሯል በማለት ጦሩ የሚወነጅል ሲሆን በትናንትናው ዕለት ስልጣን በእጁ ካስገባም በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ፓርቲያቸው ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ (ኤን ኤል ዲ) ኦንግ ሳን ሱቺ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄውን በዛሬው እለት አቅርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በዚህ አመት በህዳር ወር የተደረገውና 80 በመቶ አሸናፊነቱን ያገኘው ኤንልዲ ፓርቲ ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበል ለጦሩ ጥያቄ አቅርቧል። ምንያማር የሲቪል አስተዳደር በአውሮፓውያኑ 2011 ስልጣን እስኪይዝ ድረስ በጥምር ወታደራዊ ኃይል ትመራ ነበር። ምንያማር በመፈንቅለ መንግሥቱ ማግስት አገሪቷ በመፈንቅለ መንግሥቱ ማግስት ፀጥ ረጭ ያለች ሲሆን፤ ጎዳናዎቿም ነዋሪዎች አይታዩባቸውም። ወታደሮች በመኪና ተጭነው በተለያዩ ከተሞች በመዞር እየቃኙ ሲሆን የምሽት የሰዓት እላፊ አዋጅም ተጥሏል። በትናንትናው ዕለት ተቋርጦ የነበረው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሷል። በዋነኛዋ ከተማ ያንጎን ጎዳናዎች ላይ አንዳንዶች ለአመታት የተዋጉለት ዲሞክራሲ መና ቀረ ማለታቸው ተሰምቷል። የኦንግ ሱን ሱቺ መለቀቅ እየጠየቀ ያለው ፓርቲዋ ብቻ ሳይሆን በመንግሥት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ካልተለቀቀች ከነገ ጀምሮ ስራ አንገባም ማለታቸው ተሰምቷል። አንዳንዶችም ተቃውሟቸውን ለማሳየት ለየት ያለ ልብስ ለብው መጥተዋል። አንድ ዶክተር ከስራው መልቀቁ ተነግሯል።
46161572
https://www.bbc.com/amharic/46161572
"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ
ከሰሞኑ ከ7 ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራርና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራችና መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ያለፈውን የፖለቲካ ትግላቸውንና የወደፊት ውጥናቸውን በተመለከተ ከቢሲሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ቢቢሲ - አሁን ጊዜው ወደሀገር ቤት የምመለስበት ነው ብለው የወሰኑበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው?
ወ/ት ብርቱካን-የወሰንኩበት ቀንና ሁኔታ እንደዚህ ነው ብዬ መናገር ባልችልም በሀገራችን ያለው የለውጥ ሂደት ከመነሻው ጀምሮ በዚህ የለውጥ ሂደት ሕይወቱን ሰጥቶ እንደነበረ ሰው በደስታም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በመስጋትም የምከታተለው ነገር ነበር። በጣም ጥሩ የሚባሉ ነገሮች ተከናውነዋል፤ አንደኛ ለውጡ ከውስጡ ጭቆናን ሲፈጥር በነበረው አገዛዝ አካል መሪነት የሚከናወን መሆኑ ሀገራችን ልትገባበት ከነበረው ቀውስ ያዳናት ይመስለኛል። ያው የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ፣ለሚዲያ የተሻለ ነገር ሲፈጠር ጎን ለጎን ደግሞ የሚያሳስቡኝ ነገሮች ይታዩኝ ነበር ፤ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ እንዲሁም ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ በኩል የታዩ ችግሮችን እንደ ሀገር ካላስወገድንና የዲሞክራሲ ለውጡን ወደ ተሻለ ሂደት ካልለወጥነው፤ በፊት ከነበርንበትም ወደበለጠ ችግር ውስጥ ልንገባ እንደምንችል ተመልክቻለሁ ። እናም ሁላችንም የምንችለውን ነገር አድርገን የዴሞክራሲ ለውጡ ሊመለስ ወደማይችልበት ሁኔታ ካላሳደግነው ችግር ውስጥ እንደምንወድቅ በምረዳበት ጊዜ የራሴን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ ብዬ ወስኜ ነው እንግዲህ የመጣሁት። • "በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት እንታገላለን" እስክንድር ነጋ • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ • ጀግኒት ከትናንት እስከ ዛሬ ቢቢሲ- ምን ዓይነት አስተዋጽኦ? ወ/ት ብርቱካን-እስካሁን ያደረግኩት የትግል ሂደት የዴሞክራሲ ስርዓት ከማምጣት ጋር፣ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማትን ከመገንባት ጋር የተያያዘ ነው ። በፖለቲካ ትግል የተሳተፍኩትም እነዚህ ተቋማት፣ ለምሳሌ እኔ ራሴ ስሰራበት የነበረው ፍርድ ቤት፣ የዜጎችን መብት ለመጠበቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ያለበት ነገር ግን በአብዛኛው አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያደርግ የነበረው የፖሊስ ኃይል፣ የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤት፣ የምርጫ አካላትና የመሳሰሉትን ተቋማት በገለልተኝነትና በጠንካራ ሁኔታ ተቋቁመው እንዲታዩ ስለምፈልግ ነው፤ አሁን ይህን እውን ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ ነው ያለው። የግድ በፖለቲካ በመቀናቀን መሆን የለበትም የሚል አረዳድ አለኝ፤ ምክንያቱም ሥልጣኑን ይዘው እየመሩ ያሉ ወገኖች ያንን ለማድረግ ፈቃደኝነት ስላሳዩ ማለት ነው። የኔም አሰተዋጽኦ በዚሁ ላይ የሚያተኩር ይሆናል፤ በየትኛው ተቋም ላይ እሳተፋለሁ የሚለውን ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሳውቅ እነግራችኋለሁ። ቢቢሲ-መቼም ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ነገር እየተባለ እንደሆነ እርሶም ሳይሰሙ አይቀሩም፤ ሰዎች ፍላጎታቸውን እየገለጹ ነው ወይስ በእርግጥም የተሰማ ነገር አለ? ወ/ት ብርቱካን-ወሬው ከየት እንደመጣ ይሄ ነው ማለት አልችልም፤ በብዙ ሰዎች እንደሚነሳ አውቃለሁ። ከመንግሥትም ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ከሙያዬና ከልምዴ አንጻር የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማትን አይተን ልታግዢ ትችያለሽ? የሚል ጥያቄ ቀርቦልኛል፤ እኔም አስቤያለሁ፤ ግን ጨርሰን ይህን አደርጋለሁ የሚለው ላይ ገና ስላልደረስኩኝ ምንም ማለት አልችልም። ሰዎች ምኞታቸውንም ሊሆን ይችላል የገለጹት፤ በበጎ መልኩ ነው የማየው። ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሜሪካ እያሉ 'በኢትዮጵያ የሴቶች ትግል ውስጥ ደማቅ ቀለም የጻፈች ጀግና ሴትን እንዳመሰግን ፍቀዱልኝ" ሲሉ ምን ተሰማዎት? ወ/ት ብርቱካን-እኔ ራሴን የተለየ አድናቆት እንደሚቸረው፣ ወይም የተለየ ጥንካሬ እንዳሳየ ሰው አልቆጥርም፤ ሀገሬ ላይ የተሻለ ነገር ማየትን እፈልጋለሁ፤ ሕይወቴን የህዝብ ተጠያቂነት ያለበት ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለማምጣት፣ ለዜጎችም የተሻለ ሕይወትን ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ በመሳተፍ ማሳለፍ እፈልጋለሁ። ግን ሀገራችን የነበረችበት ሁኔታ መጥፎ ሆኖ ያ ጥረቴ በአብዛኛው በውጣ ውረድ ፣ ስቃይን በሚያመጡ እስራትና መንገላታት የታጀበ ነው፤ ውጭ በነበርኩበትም ጊዜ በብዙ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ስቃይ ሲፈጸም ሁልጊዜ የሚሰማኝ ህመም ነበር፤ እና በእርሳቸው ደረጃ የኔን አስተዋጾ በዚያ መልኩ ሲያቀርቡት ደስ ብሎኛል። ለሀገራችን በአጠቃላይ የሚሰጠው ተስፋ ደግሞ ይበልጥ አስደስቶኛል፤ ብቻ የተደበላለቀ ስሜት ነው፤ ግን የዚያ የስቃይና የእንግልት ዘመን ምዕራፍ መዝጊያ መሆኑን እንዲሰማኝ አድርገዋል። ቢቢሲ-ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩበት ምክንያት ያው ያኔም ስለ ጨቋኝነቱ የሚናገሩለትና ወህኒ ያወረዶት የኢሕአዴግ መንግሥት ነበር፤ አሁንም የተመለሱበትን ሀገር የሚመራው ኢሕአዴግ ነው። በሁለቱ መካከል መሰረታዊ የሆነ ለውጥ አለ ብለው ያምናሉ? ወ/ት ብርቱካን-በውስጥ ያሉ ለውጦች ወደ አደባባይ እየወጡ የሚታይ እውነት ነው? ወይስ ከውጭ የሚደረግ የመቀባባት ሂደት ነው? ለሚለውን ጥያቄያችን በሂደት መልስ እያገኘንለት መጥተናል። ማንም ሊክዳቸው የማይችላቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ተወስደዋል፤ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፣ በሚዲያ ላይ የነበረው ተጽዕኖ ተነስቷል፤ ንግግሮችም ቢሆኑ በቀላሉ የሚታለፉ አይደሉም፤ ምክንያቱም ንግግርና ያንን ለማሳካት የሚታየው ቁርጠኝነት ነው ወደተግባር የሚወስዱት፤ ግን ያ ተግባር አሁን የበላይነቱን በተቆጣጠረውና ለውጡን በሚደግፉ በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ሰዎች ላይ ብቻ የሚመረኮዝ ከሆነ አሁንም በስጋት ነው የምንኖረው፤ ለዚያ ነው ተቋማዊ መሰረት በጣም አስፈላጊ ነው የምለው። ቢቢሲ- በቀጣዩ ዓመት ጠቅላላ ምርጫ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፤ ኢትዮጵያውያን በዚህ ምርጫ ከእርስዎ ምን ይጠብቁ? ወ/ት ብርቱካን-አንድ ነገር በእርግጠኝነት መጠበቅ ይችላሉ ፤ በምርጫው አልወዳደርም። እውነት ለመናገር የፖለቲካ ፉክክርን በጣም ከሚመኙት ሰዎች መካከል አይደለሁም፤ ከፉክክር በላይ መተጋገዝን፣ መተሳሰብን፣ የቡድን ሥራን ነው ግብ ማድረግ የምፈልገው ። መጀመሪያውኑም የገባሁበት መንግሥት ጨቋኝ ስለነበረ፣ የምፈልጋቸውን የህግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ መብት መከበርና የዴሞክራሲ አስተዳደር የምንላቸውን ነገሮች ለማምጣት የግድ የፖለቲካ ትግል አስፈላጊ ስለነበረ ነው፤ አሁን ግን የፖለቲካ ውድድር ውስጥ ለመግባት ምንም ፍላጎት የለኝም፤ ህዝቡን ለማገልገል እድል አለ ብዬ አምናለሁኝ፤ ምርጫውን ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም። ቢቢሲ- በእስካሁኑ የፖለቲካ ተሳትፎዎ ይህን ባለደረግኩኝ ብለው የሚጸጸቱበት ነገር አለ? ወ/ት ብርቱካን-በፍጹም የለም ካልኩኝ ሰው አይደለሁኝም ማለት ነው፤ ወደ ኋላ ስትመለከቺው ልታሻሽይው የምትችይው ፣የተሻለ ምርጫ ልትወስጂበት የምትችይው ነገር ሁልጊዜም ይኖራል፤ ግን ባለኝ መረዳት የሞራል መርሆዎቼን ጠብቄ ባለሁበት ጊዜ ትክክለኛ ነው የምለውን ውሳኔ ወስኛለሁ። በዚህ ደግሞ ሁልጊዜም ትልቅ የህሊና ነጻነት ይሰማኛል፤ በሄድኩበትና በመረጥኩት መንገድ አንድም ቀን ጸጸት ተሰምቶኝ አያውቅም ፤ድጋሚም ህይወቴን ብኖረው በዛው መንገድ እኖረዋለሁ።
news-43382436
https://www.bbc.com/amharic/news-43382436
ጠ/ሚ ሜይ ሞስኮ በሰላዩ መመረዝ ጉዳይ አስተያየት መስጠት አለባት ብለዋል
የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ እና ልጁን ለመመረዝ ጥቅም ላይ የዋለው ኬሚካል ነርቭን የሚያሽመደምድና በሩስያ ወታደራዊ ኃይል የተሠራ ነው በማለት ቴሬዛ ሜይ ለእንግሊዝ ሕዝብ ተወካዮች ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጋር ካደረጉት ስብሰባ በኃላ ሕዝብ ተወካዮችን አነጋግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ በሳልዝበሪ የተደረገው ጥቃት የሩስያ እጅ የሚኖርበት ዕድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሩስያውን አምባሰደር በመጥራት ሁኔታውን እንዲያስረዱ ጠይቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ እስከ ማክሰኞ ባለው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልተሰጠ ሞስኮ ሕጋዊ ያልሆነ ኃይል ተጠቅማለች ብላ ዩናይትድ ኪንግደም እንድትደመድም ትገደዳለችም ብለዋል። ጥቃቱን ለማድረስ የተጠቀሙበት ኬሚካል 'ኖቪቾክ' በመባል የሚታወቀው መርዝ መሆኑ እንደተደረሰበትም ጠቅላይ ሚንስትሯ ተናግረዋል። ቴሬዛ ''ይህ ሩስያ በቀጥታ በሃገራችን ላይ የወሰደችው እርምጃ እንደሆነ ወይም ደግሞ የሩስያ መንግሥት አደገኛና ነርቭ ጎጂ የሆነው መርዝ ቁጥጥሩን አጥቶ በሌላ ሰው እጅ እንደገባ ያሳያል'' ብለዋል። የእንግሊዙ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለሩስያ አምባሳደር እንደተናገሩት ሞስኮ ኖቪቾክ የተሰኘውን ነርቭ ጎጂ ኬሚካል ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ለዓለም አቀፉ የኬሚካል መሣሪያዎች እገዳ ድርጅት ማስረከብ አለባት። የ66 ዓመቱ የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ እና ልጁ ቴሬዛ አክለውም ዩናይትድ ኪንግደም ወደፊት ከባድ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት እንደሚያስፈልጋትና ከሩስያ ምንም ምላሽ ካልመጣ በረቡዕ ዕለት እርምጃዎቹን እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። ባላፈው ሳምንት እሁድ ጡረተኛው የሩስያ ወታደር የ66 ዓመቱ ሰርጌ ስክሪፓል እና የ33 ዓመት ልጁ ዩሊ ስክሪፓል በሳልዝበሪ የገበያ ማዕከል በአግዳሚ ወንበር ላይ ነበር እራሳቸውን ስተው የተገኙት። እስካሁን ጤናቸው አስጊ ደረጃ ላይ ቢደርስም ግን በሕይወት እንዳሉ ተነግሯል። ሰርጌ በአውሮፓውያኑ 2004 ለኤምአይሲክስ ምስጢር አቀብለሃል ተብሎ በሩስያ መንግሥት ከተከሰሰ በኋላ በ2010 የሰላዮች ልውውጥ ሲደረግ በዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ተስጥቶት ነበር። ኖቮቾክ ምንድን ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ የሕዝብ ተወካዮችን ሲያነጋግሩ ''እንደዚህ ዓይነት ነርቭ ጎጂን መርዝ ተጠቅሞ ለመግደል የተደረገው ሙከራ በስክሪፓል ቤተሰብ ላይ ብቻ የተደረግ ጥቃት አይደለም'' ብለዋል። አክለውም "ይህ ዩናይትድ ኪንግደም ላይ የተሰነዘረ ጥንቃቄ የጎደለው ድርጊት የብዙ ንጹሃን ግለሰቦችን ሕይወት አደጋ ላይ የጣለ ነው'' ብለዋል። ጣታቸውን ወደ ሩስያ ለመቀሰር ውሳኔ የወሰዱት ''ሩስያ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የመንግሥት እጅ ያለበት ግድያዎች በማካሄዷ እና ሃገር ሸሽተው የወጡ ሰዎች ለእንደዚህ ዓይነት ግድያዎች ዒላማ የተጋለጡ በመሆናቸው ነው'' ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። የሌበር ፓርቲ መሪ የሆነው ጄሬሚ ኮርብን ነገሮች የተወሳሰቡ ሳይመጡ ከሩስያ ጋር ጠጣር ንግግር እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል። መርማሪዎች በሳልዝበሪ አካባቢ የነበረን መኪና አስነሱ ሰርከስ መሰል ሁኔታ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ጉዳይ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር እንደምትስማማ ተናግረዋል። ቴሬዛ ሜይ ሰኞ ዕለት ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋግረው ነበር። የኔቶ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ጄንስ ስቶለተንበርግ የነርቭ ጎጂው ኬሚካል አጠቃቀም ''አስቀያሚ እና ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት ማሪያ ዛካሮቫ ቴሬዛ ሜይ ''በእንግሊዝ ፓርላማ ያደረጉት መግለጫ የሰርከስ ትርዒት ነበር'' ብለዋል። የቢቢሲ ፖለቲካ አርታዒ ሎራ ኩዎንዝበርግ በቦሪስ ጆንሰንና በሩስያው አምባሳደር አሌክሳንደር ያኮቬንኮ መካከል የተደረገው ንግግር የተረጋጋና ቀጥተኛ ነበር ብላለች። ሁለቱ እጅ እንዳልተጨባበጡና ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዝን ሕዝብ 'ቁጣ' እንዳንፀባረቁ አርታኢዋ ፅፋለች።
news-55489740
https://www.bbc.com/amharic/news-55489740
የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 ምርጥ ፊልሞች የትኞቹ ናቸው?
የቢቢሲ የፊልም ሀያሲዎች ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ በተጠናቀቀው 2020 ጎልተው ወጥተዋል ያሏቸውን ምርጥ ፊልሞች ይፋ አድርገዋል። ለመሆኑ እነዚህ ፊልሞች የትኞቹ ናቸው? ማንግሩቭ (Mangrove)
የዚህ ፊልም ዳይክተር ስቲቭ ማክዊን በርካታ ጥቁር እንግሊዛያውያን እና የካረቢያን ማህበረሰቦች ከ1960ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ያሳለፏቸውን መከራዎች በማሳየት ይታወቃል። ማንግሩቭ ደግሞ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በ1960ዎቹ አካባቢ አንድ የምግብ ቤት ባለቤት ላይ ፖሊስ ስለሚያደርሰው መከራ ያሳያል። ዋናውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትጫወት ሌቲሺያ ራይት በወቅቱ የነበረውን የጥቁሮች እንቅስቃሴ ትመራለች። በፊልሙ ላይ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የሚወስደው እርምጃ በወቅቱ ምን ያክል ጭካኔ የተለመደ እንደነበር ማሳያ ነው ይላሉ ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። ዎልፍዎከርስ (Wolfwalkers) ይህ የአኒሜሽን ፊልም በርካቶችን ማስደነቅ ችሏል። የዋና ገጸ ባህሪ ሮቢን ድምጽ በሻን ቤን የተሰራ ሲሆን በ1600 አካባቢ በአየርላንድ ውስጥ የነበረች አዳኝ ሴት ልጅ ላይ ያተኮረ ነው። የሮቢን አባት ከጫካ ውስጥ ተኩላዎችን ሲያጠፋ በፊልሙ ላይ ሮቢን አንድ ተኩላ ወደ ሰውነት መቀየር እንደሚችል ታስተውላለች። አባቷ ለማጥፋት የሚተጋውን ተኩላ ለማዳንና ጫካውን ባለበት ለማቆየት የምታደርገው ፍልሚያ አስገርሞናል ብለዋል ባለሙያዎቹ። አም ቲንኪንግ ኦፍ ኤንዲንግ ቲንግስ (I’m Thinking of Ending Things) ይህ የቻርሊ ኮፍማን አስፈሪ ድራማ በዓመቱ ካየናቸው ፊልሞች ሁሉ ይለያል። ዋናውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትጫወተው ጄሲ ባክሊ በፊልሙ ላይ የፍቅር ጓደኛዋን ቤተሰቦች ለመተዋወቅ በበረዶ የተሞላ አካባቢ በመኪና ትሄዳለች። ቤተሰቦቹ ጋር ከተዋወቀች በኋላ ለመረዳት የሚከብዱ ነገሮችን ማስተዋል ትጀምራለች። ቤተሰቦቹ ልብሳቸው አይቀየርም፣ እድሜያቸው ደግሞ ቶሎ ቶሎ ይቀያየራል። እሷም ብትሆን ስሟን ማስታወስ ያቅታታል። ይህ ፊልም በጣም ግራ የሚያጋባ፣ የሚያስፈራና በሌላ በኩል ደግሞ የሚያጓጓ ነው። አኖማይት (Ammonite) ታዋቂዋ ተዋናይ ኬት ዊንሰልት በዚህ ፊልም ላይ እጅግ ድንቅ የተባለ የትወና ችሎታዋን ማሳየት የቻለችበት ነው። በፊልሙ ላይ ኬት ዊንስሌት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የፓሊዮንቶሎጂ ዘርፍን የቀየረ የቅሪተ አካል ያገኘችው ሜሪ አኒንግን ወክላ ነው የምትጫወተው። የፊልሙ ጸሀፊና ዳይሬክተር ፍራንሲስ ሊ ሜሪ በእድሜዋ አጋማሽ አካባቢ ስላጋጠማት የፍቅር ሕይወት፣ ስራ እና የጾታ ተጽዕኖ ለማሳየት ሞክሯል። ሮክስ (Rocks) የዚህ ፊልም ዳይሬክተር ሳራህ ጋቨርን ናት፤ ጸሀፊ ደግሞ ቴሬሳ ኢኮኮ እና ክሌር ዊልሰን። አንዲት ታዳጊ እና ታናሽ ወንድሟ እናታቸው በድንገት ከቤት ከጠፋች በኋላ ስለሚያሳልፉት ሕይወት ይተርካል። ታዳጊዋን ሆና የምትተውነው በኪ ባክሬይ በፊልሙ ላይ በርካታ ስህተቶችን ብትሰራም ጥሩ ጓደኞች ግን አሏት። ልብን በሀሴት የሚሞላና ተስፋ የሚሰጥ ፊልም ነው ብለውታል ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። ማ ሬይኒስ ብላክ ቦተም (Ma Rainey's Black Bottom) በቅርቡ በሞት የተለየን ታዋቂው የብላክ ፓንተር ተዋናይ ቻድዊክ ቦዝማን የሚተውንበት ይህ ፊልም በ1924 በቆዳ ቀለሙ ምክንያት በሚደርስበት ጥቃት የተጎዳ ሙዚቀኛ ሆኖ ነው የሚተውነው። ገጸ ባህሪው ሊቪ የሚሰኝ ሲሆን በልጅነቱ በደረሰበት የዘር ጥቃት የአዋቂነት ሕይወቱ ሲቃወስ ያሳያል። አምቆት የቆየው ቁጣው የሆነ ሰአት ላይ ሲፈነዳም ይታያል። ሊቪ ተጫዋች፣ ዳንስ የሚወድ፣ ሳቂታ ወጣት ነው። ቻድዊክ ደግሞ ገጸ ባህሪውን በደንብ ተላብሶ ተጫውቶታል። ዳ 5 ብለድስ (Da 5 Bloods) ስፓይክ ሊ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል ይሄኛው በጣም ምርጥ ከሚባሉት ነው ብለዋል ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። አራት ጥቁር አሜሪካውያን በወጣትነታቸው ለጦርነት ወደሄዱባት ቬትናም ይመለሳሉ። ዋናው አላማቸው ደግሞ በጦርነቱ ሕይወቱን ያጣውን ጓደኛቸውን አስክሬን ይዞ ለመመለስና የደበቁትን ወርቅ ለማምጣት ነው። በዚህ ፊልም ላይ የአራቱን ጓደኛማቾች አስገራሚ የሕይወት ጉዞ እና በአሜሪካ ያለውን ዘረኝነት ይታያል። ዘ ሃንት (The Hunt) ይህ ፊልም ገና ለተመልካች ይፋ ሳይደረግ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። በፊልሙ ላይ ሀብታም አሜሪካውያን ግራ ዘመም ደሀ አሜሪካውያንን አግተው ወስደው እንደ እንስሳ እያሳደዱ ሲያድኗቸው ይታያል። በአሜሪካ ባጋጠሙ ሁለት ጥቃቶች ምክንያት ፊልሙ ሁለት ጊዜ የሚለቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ተገድዷል። በመጨረሻ ፊልሙ ይፋ ሲደረግ በርካቶችን ያስደሰተ ፊልም መሆን ችሏል። ፊልሙን እየተመለከቱ ማን ቀጥሎ ይሞት ይሆን፣ማን ከማን ጋር አብሯል፣ መጨረሻው ምን ይሆን የሚሉ ጥያቄዎችን አለመጠየቅ በጣም ከባድ ነው።
49575650
https://www.bbc.com/amharic/49575650
የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ
በኬንያ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ዝርዝር ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ ከሚባለው የማዉ ጫካ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ60ሺ በላይ ዜጎችን መንግስት ማባረር ጀምሯል።
የኬንያ ዋነኛ የውሃ ምንጭ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ጫካ የዝናብ ውሃን ለረጅም ጊዜ ይዞ የሚያቆይ ሲሆን በደረቅ ወራት ደግሞ ውሃውን ወደ ሃገሪቱ ብዙ ወንዞች መልሶ ይለቀዋል። ባለስልጣናት እንደሚሉት ሰዎቹ በሕገ-ወጥ መንገድ የሰፈሩ ሲሆን የእርሻ ቦታ ለማዘጋጀት በማሰብ ጫካውን እየመነጠሩት ነው። • 'በእርግማን' የተፈጠረው የኮንሶው 'ኒው ዮርክ' • በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል? ከሰኞ ጀምሮ አንዳንድ ፍቃደኛ ቤተሰቦች ጫካ ውስጥ የሰሩትን ቤትና ያዘጋጇቸውን የእርሻ ቦታዎች በገዛ ፍቃዳቸው ለቅቀው መሄድ የጀመሩ ሲሆን መንግሥት በኃይል ንብረታችን ከሚያወድም በሰላም ለመልቀቅ መርጠናል ብለዋል። በአካባቢው የሚገኙ 31 ትምህርት ቤቶችም በዚሁ ምክንያት ከሰኞ ጀምሮ ዝግ ሆነዋል። በዚህም ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ቀርተዋል። የኬንያ የደን አገልግሎት መስሪያ ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ጠባቂዎቹን ከፖሊስ ጎን ሆነው ነዋሪዎቹን ከማዉ ጫካ የማስወጣት ስራውን እንዲያግዙ በማለት አሰማርቷቸዋል። ነዋሪዎቹን የማስወጣት ስራውን እጅግ አስፈላጊ ያደረገው አካባቢው ትልቅ ውሃ የመቋጠር አቅም ስላለውና የዝናብ ዑደትን በእጅጉ ስለሚወስን ነው ብለዋል የሃገሪቱ የአካባቢ ሚኒስትር ካሪያኮ ቶቢኮ። ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ጎብኚዎችን የሚስበውና ብዙ የዱር እንስሳት ወደ ታንዛንያ ሲሄዱ አቋርጠውት የሚያልፉት የማራ ወንዝ ቋሚ የውሃ ምንጭ ነው። ነገር ግን ይህ የመንግሥት እርምጃ ከአንዳንድ የግዛት አስተዳዳሪዎች ወቀሳን አስከትሏል። መንግሥት ጉዳዩን በድርድርና በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲገባው በኃይል እርምጃ መውሰዱ ተገቢ አይደለም ብለዋል። • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? ጫካው የሚገኝበት ክልል አስተዳዳሪ የሆኑት ኪፕቹምባ ሙርኮመን በበኩላቸው ነዋሪዎቹ ከጫካው ወጥተው እንዳይሄዱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በቅርብ የሚገኝ አዋሳኝ ክልል አስተዳዳሪ ሌዳማ ኦሌ ኪና ደግሞ በእሱ በኩል ያሉት የማሳይ ማህበረሰብ ነዋሪዎች በሰላም መውጣታቸውን በመግለጽ የማዉ ጫካን የመታደግ ስራው በመጨረሻም ተጀመረ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። እንደ ዓለማቀፉ የዱር እንስሳት ጥናት ፈንድ መረጃ መሰረት ከሆነ ኬንያ ነጻነቷን ካገኘችበት እ.አ.አ. 1963 ጀምሮ የማዉ ጫካ 37 % የሚሆነውን ሽፋኑን በሰዎች ምክንያት አጥቷል።
news-55444874
https://www.bbc.com/amharic/news-55444874
1ሺ ሄክታር የሚሰፋው የማይክል ጃክሰን የመኖርያ ግቢ በ22 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ
'ዘ ኔቨርላንድ' በሚል ስሙ የሚታወቀው የሟቹ ማይክል ጃክሰን መኖርያ ቤት መሸጡን ለጉዳዩ ቅርብ ነን የሚሉ ሰዎች ተናገሩ።
ይህ እጅግ ግዙፍ መኖርያ የሚገኘው ከሎስ ኦሊቮስ ከተማ ቀረብ ባለ ጫካ በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ነው። ንብረቱን የገዙት ቢሊየነር ቤቱ ያወጣል ተብሎ ከተጠበቀው አንድ አራተኛውን ብቻ ከፍለው ነው የራሳቸው ያደረጉት። ይህ የማይክል ጃክሰን የቀድሞ መኖርያ ግቢ እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ተገምቶ ነበር። ቤቱን የገዙት ቢሊየነር ሮን በርከል የሚባሉ ሰው ናቸው ተብሏል። ዜናውን የዘገበው ዎል ስትሪት ጆርናል ሲሆን በዚህ ግዢኛ ሽያጭ በቀጥታ የተሳተፉ ሦስት ሰዎችን በምንጭነት ጠቅሷል። ይህ የማይክል ጃክሰን ግቢ ስፋቱ 2ሺ 700 ኤከር ወይም 1ሺ 100 ሄክታር የሚሸፍን እጅግ ግዙፍ መኖርያ ግቢ ነው። በካሊፎርኒያ ግዛት ከሳንታ ባራባራ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የሚገኘው ይህ እጅግ ግዙፍ መኖርያ ግቢ የማይክል ጃክሰንን ሞት ተከትሎ ሊሸጥ ዋጋ ሲወጣለት ለዓመታት ሲንከባለል ቆይቷል። በ2015 የቤቱ ግምት 100 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን በ31 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ ነው የሚሉ ዜናዎች መውጣት ጀምረው ነበር። ማይክል ጃክሰን ቤቱን መጀመርያ ሲገዛው በ19 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ነበር። የቤቱን ስምም በልጆች ዝነኛ የተረት ተረት ታሪክ ፒተር ፓን ውስጥ ባለው ደሴት ስም ሰይሞት ነበር። በተረቱ ዓለም ውስጥ ይህ ደሴት ልጆች የማያድጉበት ዓለምን የሚወክል ነው። ማይክል ይህንን ቤት የገዛው እንደነሱ አቆጣጠር በ1987 ነበር። በዚያ ጊዜ ትሪለር የተሰኘውን ሙዚቃ ያወጣበት እና በዝና ማማ ላይ የወጣበት ዘመን ነበር። ይህንን ቤቱን ወደኋላ ላይ የመዝናኛ ስፍራ አድርጎት ቆይቷል። ግቢው ከስፋቱ የተነሳ እጅግ ግዙፍ የእንሰሳት መጠበቂያ (zoo)፣ የአእዋፋት መናኸሪያ፣ የዲዝኒላንድ ሁሉም ዓይነት መጫወቻና መዝናኛዎች፣ በርካታ ሲኒማ ቤቶች፣ ሰው ሰራሽ ሐይቆች፣ መለስተኛ ባቡር መጓጓዣዎችና በናቱ ስም የተሰየመ የባቡር ጣቢያ ያሉት ምናልባትም አንድ አነስተኛ የገጠር ቀበሌን የሚያህል ስፋት ያለው ነው። በዚህ ስፍራ ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸው እንዲዝናኑበት በማሰብ አካባቢውን በከፊል የመዝናኛ ማዕከል አድርጎትም ነበር ማይክል ጃክሰን። በኔቨርላንድ መኖርያ ቤቱ ተከፍተው የማያውቁ፣ አንድም ቀን አንድም ሰው አድሮባቸው የማያውቁ በርካታ ክፍሎች ያሉ ሲሆን በግቢው ውስጥ የመኖርያ ቤት ሕንጻዎች ቁጥር ግን 22 እንደሆነ ይታወቃል። በጊዜው ከ120 በላይ የቤት ሰራተኞች የነበሩት ማይክል ለደመወዝ ብቻ በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ዶላር ያላነሳ የወጣ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ማይክል በዚህ ስፍራ ይኖር የነበረው በርካታ ሕጻናት ጋር ሲሆን ፖሊስ ይህንን ግቢ ድንገት በመውረር ማይክል ይታማበት የነበረውን ከልጆች ጋር ጾታዊ ፍላጎት አለው በሚል ክስ መስርቶበት ነበር። ፖሊስ ማይክልን በዚህ ግቢ ውስጥ ሕጻናትን ያባልጋል፣ ምናባዊ ዓለም ሊፈጥር ፈልጓል በሚል ከሶት ነበር። ማይክል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ክዶ ተከራክሯል። በ2005 ማይክል የ13 ዓመት ልጅን አባልገሀል በሚል ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት ነጻ አድርጎት ነበር። ከዚህ በኋላ ይህንን ኔቨርላንድ ግቢ ጠልቼዋለሁ አልመስም ብሎ ስፍራውን ትቶት ኖሯል። እንዳለውም ማይክል ጃክሰን ወደ ኔቨርላንድ የተጠንጣለለ ቤቱ ሳይመለስ ነው የኖረው። ከአራት ዓመታት በኋላ በ2009 ማይክል ጃክሰን ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሌላ መኖርያ ቤቱ ውስጥ ከልብ ጋር በተያያዘ በሽታ፣ ከመጠን ያለፈ ብዙ መድኃኒት በመውሰዱ ለሞት መዳረጉ አይዘነጋም። ሞቱን ተከትሎ በርካታ የምርመራ ዘጋቢ ፊልሞች በዚህ ኔቨርላንድ መኖርያ ቤቱ ዙርያ ተሰርተዋል። ማይክል ጃክሰን በዚህ ግዙፍ ቤቱ ውስጥ ያልተገቡ ምናባዊ የሚመስሉ ድርጊቶችን ይፈጽም እንደነበረ የሚገምቱ ፊልም ሰሪዎች ጥርጣሪያቸውን የሚያንጸባርቁ መረጃዎችን አሰራጭተዋል። ኔቨርላንድ ግቢ የማይክል ጃክሰንን ሞት ተከትሎ ስሙን ወደ ሲካሞር ቫሊ በመቀየር እድሳት ተደርጎለት ነበር። አሁን ይህንን ታሪካዊና ግዙፍ ንብረት የግሉ ያደረጉት ቢሊየነሩ ሚስተር በርክል አካባቢውን ምን ሊሰሩበት እንደሆነ ይፋ አላደረጉም። ሆኖም ግን ይህንን ቤት ለመግዛት ሐሳቡ እንዳልነበራቸውና በዚያ ስፍራ በሄሊኮፕተር ሲንሸራሸሩ ከሰማይ ላይ ካዩት በኋላ ፍላጎት እንዳደረባቸው አብራርተዋል። የ68 ዓመቱ በርክል የዩዋኪፓ ኩባንያ መሥራችና ባለቤት ሲሆኑ ፎርብስ በያዝነው ወርና ዓመት ጠቅላላ ሀብታቸውን 1 ቢሊዮን ተኩል ገምቶታል።
news-52881187
https://www.bbc.com/amharic/news-52881187
“ኮሮናቫይረስን ለሦስት ሳምንታት በሦስት ሆስፒታሎች ታገልኩት”
ሦስት ልጆች በዊልቸር ያለ አባታቸውን እየቦረቁ ሲቀበሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ በሺህዎች ታይቷል።
ጃክ ማክሊሀህ ልጆቹ የጃክ ማክሊሀህ ናቸው። ቪድዮው የተቀረጸው በሦስት የተለያዩ ሆስፒታሎች ለሦስት ሳምንት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ወደ ቤቱ ሲገባ ነው። ድሩሞር በተባለች ከተማ ይኖራል። የአይቲ ባለሙያ ነው። ህክምናውን ሲያጠናቅቅ፤ በክሪያጋቮን፣ በማተር ሆስፒታል እና በናይቲንጌል ሆስፒታል ኦፍ ቤልፋስት እንክብካቤ ያደረጉለትን የህክምና ባለሙያዎችን በአጠቃላይ አመስግኗል። ምስጋናውን በማኅበራዊ ሚዲያም አጋርቷል። ሆስፒታል የገባው በእናቶች ቀን ነበር። አገግሞ ከወጣ በኋላም ድካም እንደሚሰማው ይናገራል። “ትንሽ በእግሬ ስንቀሳቀስ ይደክመኛል፤ ሆስፒታል ሳለሁ ከስቻለሁ፤ ሰውነቴን ዳግመኛ መገንባት አለብኝ” ይላል። ህመሙ የጀመረው ሚያዝያ ላይ ነው። አስር ቀን ራሱን አግልሎ ቤቱ ባለው ቢሮ ተቀመጦ ነበር። ከሚስቱ፣ ከሦስት ልጆቹና ከአማቹ ጋር አይገናኝም ነበር። በሽታው ተባብሶ ለመተንፈስ ሲቸገር ሆስፒታል ተወሰደና በጽኑ ህሙማን ማቆያ ገባ። ወቅቱን እንዲህ ያስታውሳል. . . “ለባለቤቴ ደወልኩላትና ጠዋት ህሊናዬን ስቼ ልታገኚኝ ትችያለሽ አልኳት። ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ ክፍል እየተወሰድኩ ነው፤ ቬንትሌተርም ተደርጎልኛል ብዬም ነገርኳት። ከዚያ ከሁለት ሳምንት በኋላ ራሴን ሌላ ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁት።” ከሆስፒታሉ የወጣው በሦስተኛ ሳምንቱ ቢሆንም የተፈጠረውን ነገር በቅጡ አያስታውስም። ባለቤቱ ያኔ የየዕለት ውሎ ማስታወሻ ትይዝ ነበር። የጤና ሁኔታውን፣ የጻፈችለትን ደብዳቤ፣ አስቸጋሪ የነበረውን ወቅት እና ተስፋ የጣለችበትን ጊዜም በጽሁፍ መዝግባለች። ለፋሲካ ቤቱ ቢመለስም ሙሉ በሙሉ አላገገመም ነበር። ዶ/ር ማይክል መኪያና እንደሚሉት፤ ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። “በቫይረስ ሳቢያ የተከሰተ በሽታ የያዛቸው ሰዎች ቬንትሌተር የሚያስፈልጋቸው ለሁለት ወይም ቢበዛ ለአራት ቀን ነበር። አሁን ግን ከ14 እስከ 20 ቀን ሲያስፈልጋቸው እናያለን” ይላሉ። ጃክ በቤቱ መናፈሻ ከባለቤቱ ጋር የውሎ መዝገቧን ያገላብጣል። ወደ ቤት ከተመለሰ በኋላም ለማገገም ቀላል እንዳልነበረ ይናገራል። “እናቴ ከዓመታት በፊት ታማ የገዛሁላትን ዊልቸር ነው የተጠቀምኩት። መጸዳጃ ቤት፣ ማዕድ ቤትም ለመሄድ እሱን እጠቀም ነበር። ሁሉም ቅርብ ቢሆኑም የምንቀሳቀሰው በዊልቸር ድጋፍ ነበር” ሲል ጃክ ያለፈበትን ያስታውሳል። ዶክተሩ እንደሚሉት ከሆነ፤ የትኛው ሰው ከበሽታው በቶሎ እንደሚያገገም ማወቅ አዳጋች ነው። ጃክ የአሁኑን የበጋ ወቅት ያለፈውን ጊዜ በማስታወስ ማሳለፍ ይፈልጋል። ምን እንደገጠመው እና ገጠመኙ ሕይወቱን እንዴት እንደቀየረውም ያሰላስላል። “በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሆኜ፤ ቤቴ መመለስ አለብኝ ብዬ ሳስብ አስታውሳለሁ” ይላል። ምኞቱ ሰምሮ ቤቱ በመመለሱ ደስተኛ ነው። “ከቤተሰቤና ከልጆቼ ጋር መሆን እጅግ አስደሳች ነው። ምንም እንኳን ከቤት ባንወጣም አብረን መሆናችን ያስደስታል። በሕይወት የሚያስፈልገው ነገር ምን እንደሆነም አሳይቶናል።”
news-52564126
https://www.bbc.com/amharic/news-52564126
አል ሲሲን ተችቶ ለእስር የተዳረገው የፊልም ባለሙያ 'ሳኒታይዘር ጠጥቶ ህይወቱ አለፈ'
በሙዚቃ ቪዲዮ የግብጹን ፕሬዝደንት የተቸው የፊልም ባለሙያው ሻዲይ ሐባሽ በተመረዘ አልኮል ህይወቱ አለፈ ሲሉ የግብጽ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የ24 ዓመቱ የፊልም ባለሙያ ካይሮ በሚገኘው እርስ ቤት፤ ከቀናት በፊት ውሃ መስሎት ሳኒታይዘር በመጠጣቱ ነው ህይወቱ ያለፈው ሲል አቃቤ ሕግ ተናግረዋል። አቃቤ ሕጉ ጨምረውም የኮቪድ-19 ወረርሽኘን ለመከላከል ሳኒታይዘር በእስር ለሚገኙ ታራሚዎች ተከፋፍሏል ብለዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ለሻዲይ ሐባሽ ሞት ምክያቱ በቂ የህክምና ክትትል ማጣት ነው ሲሉ ይኮንናሉ። ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ላለፉት ሁለት ዓመት በእስር ላይ የቆየ ሲሆን፤ "ሐሰተኛ ዜናዎችን ማሰራጨት" እና "የሕገ-ወጥ ድርጅት አባል መሆን" የሚሉ ክሶች ተመስርተውበት ነበር። ሻዲይ ሐባሽ ለአስር የተዳረገው ከአገር ውጪ በስደት የሚገኘውን የራሚይ ኢሳም 'ባላህ' የተሰኘ ሙዚቃ ዳይሬክት [ካዘጋጀ] ካደረገ በኋላ ነበር። 'ባላህ' የሚለው ቃል በግብጽ ዝነኛ ፊልም ላይ ውሸታም ገጸ ባህሪን ወክሎ የሚተውንን ሰው ይወክላል። የፕሬዝደንት አል-ሲሲ ተቺዎችም ፕሬዝደንቱን 'ባላህ' ሲሉ ይጠሯቸዋል። የዘፈኑን ግጥም የጻፈው ጋላል ኤል-ቤሃይሪ ከሁለት ዓመት በፊት የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ሻዲይ ሐባሽ ለሁለት ዓመታት በእስር ላይ ሲቆይ ለፍርድ አለመቀርቡ የፈጠረበትን ተስፋ ቢስነት በአንድ ደብዳቤ ላይ ገልጾ ነበር። ሻዲይ ሐባሽ "መቼ እና እንዴት እንደምወጣ ሳላውቅ በብቸኝነት ወደ አንደ ክፍል ከተወረወርኩ ሁለት ዓመታት አለፉ" ያለ ሲሆን ጨምሮም፤ "እስር አይደለም የሚገድለው፤ ብቸኝነት ነው" ብሎ ነበር። ጠበቃ አህመድ አል-ካህዋጋ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ ኮቪድ-19 ወደ እስር ቤት እንዳይዛመት በማሰብ የግብጽ መንግሥት በማረሚያ ቤት ያሉ ሰዎች መጠየቅን መከልከሉን ተከትሎ በቅርቡ ሻዲይ ሐባሽን የጎበኘ ሰው የለም። ጠበቃው እንዳሉት ሻዲይ ሐባሽ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ወደ ማረሚያ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ዓርብ ምሽት ህይወቱ አልፏል። ማክሰኞ ዕለት አቃቢ ሕጉ በበኩላቸው ሐበሻ ወደ ሆስፒታል ባመራበት ወቅት ከመሞቱ አንድ ቀን በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው እጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር መጠጣቱን ተናግሯል ብሏል። ሻዲይ ሐባሽ ሳኒታይዘሩን የጠጣው ከውሃ ጋር ተመሳስሎበት መሆኑን እና ከፍተኛ የሆድ ህመም ሲሰማው እንደነበረ ለሃኪሞች መናገሩን አቃቤ ሕጉ ጨምረው ተናግረዋል። ይህን የሻዲይ ሐባሽን ሞት ምክንያት የሚጠራጠሩ በርካቶች ናቸው። መንግሥት ለወጣቱ ፊልም ባለሙያ ሞት እንደምክንያት ያቀረበው ብዙ አጠራጣሪ ነገሮች አሉበት ይላሉ። ከፍተኛ ህመም ላይ ከነበረ ለምን በቂ ህክምና አልተደረገለትም፣ ሕግን በተጻረረ መልኩ ለምን ክስ ሳይመሰረትበት ለሁለት ዓመታት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደረገ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
news-50937648
https://www.bbc.com/amharic/news-50937648
'ልጃችንን እንደ ክርስቲያንም እንደ ሙስሊምም ነው የምናሳድጋት'
የእስልምና እምነት ተከታዩች በሚበዙባት ቡርኪናፋሶ በቅርብ ዓመታት ወዲህ በአክራሪ ጂሃዲስቶች ጥቃት ሰለባ መሆን ጀምራለች። በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ እንኳን 30 ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ ሴቶች ነበሩ።
ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ጀርባ በሀገሪቱ ያለው ምስል ለየት ያለ ነው። በቡርኪናፋሶ 23 በመቶ የሚሆኑት ክርስቲያኖች ከሙስሊሞች ጋር ትዳር መስርተው መኖር የተለመደና በብዛት የሚታይ ነው። እስቲ በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ የሚገኝ አንድ ቤተሰብን እንመልከት። • በቡርኪናፋሶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ሞቱ • በቡርኪና ፋሶ መስጅድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ የአምስት ዓመቷ አይሪስ ኦስኒያ ኡታራ ከአባቷ በወረሰችው የካቶሊክ እምነት እና በእናቷ የሙስሊም አስተምሮ መሰረት ነው የምታድገው። የፈረንጆቹን ገና ከአባቷ ጋር በደማቅ ሁኔታ የምታከብር ሲሆን በእስልምናው ደግሞ ኢድን ታከብራለች። ''አይሪስ ሁሌም ቢሆን ወደ መስጂድ ስሄድ አብራኝ እንድትሄድ አደርጋለሁ፤ እሁድ እሁድ ደግሞ ከአባቷ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ ትምህርት ትከታተላለች'' በማለት ስልጃቸው አስተዳደግ እናትየው ትናገራለች። የአይሪስ እናት አፎሳቱ በቀን አምስት ጊዜ በቤት ውስጥ የምትሰግድ ሲሆን አርብ ሲደርስ ደግሞ ልጇን ይዛ ወደ መስጂድ ትሄዳለች። አይሪስም ብትሆን የመጀመሪያውን ጸሎት ለማድረስ ከእናቷ ጋር በጠዋት ትነሳለች። '' እስልምና ሁሌም ቢሆን መቻቻልና ሌሎችን መቀበል ላይ የተመሰረት ነው፤ የሌሎችን ችግር መረዳት ነው እስልምና'' ትላለች አፎሳቱ። በእነ አይሪስ ቤት እስልምና ማስተማሪያ መጽሀፍት ቁርአን እንዲሁም የክርስትናው መጽሀፍ ቅዱስ ጎን ለጎን ተቀምጠው ይታያሉ። የአይሪስ አባት ዴኒስ እና እናቷ አፎሳቱ በቡርኪናፋሶ ቶዉሲያና ከተማ ከተዋወቁበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ዓመታት አብረው ኖረዋል። በሚቀጥለው ዓመት ትዳር የመመስረት እቅድ ያላቸው ሲሆን ሰርጋቸው በሁለቱም እምነቶች ስነስርአት መሰረት እንዲካሄድ ይፈልጋሉ። • ቻይና ሙስሊም ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው እየነጠለች ነው • ኬንያ ውስጥ ታየ የተባለው "ኢየሱስ" ማን ነው? ዴኒስ ለጊዜውም ቢሆን ሀይማኖቱን ወደ እስልምና ለመቀየር ያስባል። በቡርኪና ፋሶ ክርስቲያን ወንዶች የሚስቶቻቸው ቤተሰቦችን ለማስደሰት ወደ እስልምና መቀየር የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ከሰርጉ በኋላ ወደ ቀድሞ ሀይማኖታቸው ይመለሳሉ። '' ለመጋባት መወሰናችንን ይፋ ስናደርግ ብዙ ተቃውሞ አጋጥሞናል'' ይላል ዴኒስ። '' መጀመሪያ አካባቢ ትንሽ የተወሳሰበ ነበር። አባቴ ምንም ችግር የለውም ሲለኝ እናቴ ግን አልተስማማችም። ባልና ሚስት የተለያየ ሀይማኖት የሚከተሉ ከሆነ ሁሌም እናቶች ደስ አይላቸውም።'' አሁንም ቢሆን የአፎሳቱን እናት ለማሳመን በጥረት ላይ ይገኛሉ ጥንዶቹ። በቡርኪና ፋሶ በርካታ ቤተሰቦች ከክርስቲያን እና ሙስሊሞች የተውጣጡ ናቸው። አንዱ በአንዱ ቤተ እምነት ውስጥም መግባት ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ የሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት ተደርጋ ትቆጠራለች። አፎሳቱ በምትኖርበት አካባቢ ብዙ ክርስቲያን ጓደኞች ያሏት ሲሆን በአላት ሲደርሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው በመሄድ አብራቸው ታከብራለች። ከዴኒስ ቤተሰቦችም ጋር ቢሆን ጥሩ ግንኙነት መመስረት ችላለች። '' ክሪስማስም (የገና በዓል) ሆነ ኢድ አል አድሃ ሁሉንም በአላት አከብራለሁ። እድለኛ ነኝ ብዬ ነው የማስበው'' ትላለች አፎሳቱ። • ለልመና ታግቶ የነበረው ታዳጊ ከዓመታት በኋላ ተገኘ ዴኒስ በበኩሉ '' ሀይማኖቴ ሌሎችን እንድወድና በማንነታቸው እንድቀበላቸው አስተምሮኛል። ለሁሉም ነገር ፈራጁ ፈጣሪ ነው፤ እኛ አይደለንም'' ብሏል። ዴኒስና አፎሳቱ ልጃቸው አይሪስ እድሜዋ ከፍ ሲል የፈለገችውን ሀይማኖት እንድትከተል እንደሚያስመርጧት ይናገራሉ። ለአሁኑ ግን በመስጂድም ሆነ በቤተ በቤተክርስቲያን መመላለሷን ትቀጥላለች። የትኛውንም ሀይማኖት ብትመርጥ ለእኛ ግድ አይሰጠንም የሚሉት እናትና አባት ''ፍቅር ከሀይማኖት በላይ ነው'' መልእክታቸው ነው።
53104052
https://www.bbc.com/amharic/53104052
ፌስቡክ የዶናልድ ትራምፕን የምረጡኝ ቅስቀሳ አገደ
ፌስቡክ አንድ የዶናልድ ትራምፕን የድጋሚ ምረጡኝ ማስታወቂያ ቅስቀሳ መልእክት ከገጹ ላይ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱም ደግሞ መልእክቱ የፌስቡክን ደንብና ሁኔታዎች ስለሚጥስ ነው ብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ለቅስቀሳ የተጠቀሙበት ምልክት የናዚ ጀርመን አርማ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህን ደግሞ ፌስቡክ ሊታገሰው የሚችለው አልሆነም፡፡ የተገለበጠ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያለውና መደቡ ቀይ የሆነው ይህ ምልክት በናዚ እንደ አርማ ካገለገለው ምልክት ጋር ተቀራራቢነት ያለው ነው፡፡ የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባላት በበኩላቸው ምልክቱን የተጠቀምነው በአሜሪካ ግራ ዘመም እንቅስቃሴን እያፋፋመ ያለውን አንቲፋ የተባለውን ቡድን ለመተቸት ነበር ሲሉ ፕሬዝዳንቱን ተከላክለዋል፡፡ ፌስቡክ ግን ምንም ይሁን ምን ማስታወቂያው ጥላቻን የሚሰብክ በመሆኑ አስወግደነዋል ብሏል፡፡ ይህ የፌስቡክ እርምጃ በግዙፍ የማኅበራዊ ሚዲያ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና በዋይት ሃውስ መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደ አዲስ ምዕራፍ ይወስደዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ባለፈው ወር ትዊተር ኩባንያ በተመሳሳይ ዶናልድ ትራምፕ የሚኒያፖሊሱን ክስተት ተከትሎ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ያሰፈሩት ጽሑፍ ነውጥን ያበረታታል በሚል አንስቶባቸው ነበር፡፡ ይህን የትዊተር እርምጃን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ ቁጣቸውን ገልጸው ፕሬዝዳንታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ‹ተጠያቂነትን የሚጨምር የሕግ ማጥበቂያ ሸምቀቆ› ማሰራቸው አይዘነጋም፡፡ ፌስቡክ በወቅቱ ትዊተር የወሰደውን ርምጃ በፕሬዝዳንቱ ላይ መውሰድ ነበረበት በሚል ከፍተኛ ውግዘት አስተናግዶ ነበር፡፡ አሁን ፌስቡክ የፕሬዝዳንቱን የምረጡኝ ቅስቀሳ መልእክት ማንሳቱ ዶናልድ ትራምፕን ክፉኛ እንደሚያስቆጣ ይጠበቃል፡፡ ትራምፕ ከትዊተር ይልቅ ፌስቡክን ለምርጫ ቅስቀሳ እጅግ አድርገው ይፈልጉታል፡፡ ትልቁ የፕሬዝዳንቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ በጀት የሚፈሰውም ወደ ፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ዙርያ ትራምፕ ‹‹ዘራፊዎችን ዘረፋ ሲጀምሩ፣ ተኩሱም ይቀጥላል›› የሚል መልእክት በትዊተርና ፌስቡክ አስፍረው ነበር፣ ያኔ፡፡ ትዊተር በወቅቱ በመልእክቱ ላይ እርምጃ ሲወስድ ፌስቡክ ቸል በማለቱ የፌስቡክ ኩባንያ ሰራተኞች ‹‹በድርጅታችን አፍረናል›› ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
48933118
https://www.bbc.com/amharic/48933118
የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው
አሸናፊ አህመድና ግርማይ ሞተር በመንዳት የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ለማሻሻል ይታትራሉ። አሸናፊ እንደሚለው ባለፉት አስር ዓመታት በሞተሩ በእያንዳንዱ የከተማ ጥግ እየተንቀሳቀሰ ሰዎች ያዘዙትን ያመላልስ ነበር።
"ገንዘብም ሆነ እቃ አድርስ ያሉኝን በታማኝነት አደርስ ነበር" ያለው አሸናፊ የሁለት ልጆች አባት ነው። አሸናፊም ይሁን ግርማይ ሕይወታቸው ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው ሞተር መንዳት ላይ ነበር። አሁን ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ፈቃድ የሌለው ሞተር ከተማ ውስጥ ማሽከርከር ስለከለከለ፤ ሥራ አቁመው ቀን የሚያመጣውን ይጠብቃሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ሰላም ስጋት ናቸው ያላቸውን ሞተር ብስክሌቶች ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ እንዳይንቀሳቀሱ ያገደው ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ. ም. ነበር። • የሞተር ብስክሌቶች እና ሕገወጥነት በአዲስ አበባ በ15 ቀን ውስጥ አስፈላጊውን ምዝገባና ተያያዥ ጉዳዮች በትራንስፖርት ቢሮ እንዲፈፅሙና ሕጋዊ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቆ ነበር። እነ አሸናፊን የከተማ አስተዳደሩ ተደራጅታችሁ ሥሩ ብሏል ምን እያሰባችሁ ነው? ተብለው ሲጠየቁ አማራጮችን ለመፈለግ ጊዜው አጭር መሆኑን ግርማይ ይናገራል። የእለት ጉሮሯቸውን ከሚደፍኑበትን ሥራ ማፈናቀል ተገቢ አለመሆኑን በመቃወም ሞተር አሽከርካሪዎች ተሰብስበው ሰልፍ ማድረጋቸውንም ያስታውሳል። ሰልፉን ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ. ም. ቢያደርጉም ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው እንዳዘነ የሚናገረው ግርማይ፤ "ነገሩ ተስፋ ያለው አይመስልም" ይላል። አሸናፊም ጉዳዩን ወደሚመለከተው አካል ለመውሰድ ፍላጎት የለውም። • “የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ አሸናፊ፤ ሞተር ከማሽከርከር ውጪ ሥራ ለመቀየር ባያስብም፤ "ባሉት ስራ አጦች ላይ ሌላ ሥራ አጥ ሆኜ ተደምሬያለሁ" ይላል በቁጭት። ሞተር በማሽከርከር በሚያገኙት ገቢ ቤት ተከራይተው ሦስትና አራት ልጅ የሚያሳድጉ፣ ወላጆቻቸውን የሚጦሩም አሉ የሚለው አሸናፊ፤ በእርግጥ አዲስ አበባ ውስጥ ወንጀል ስለተበራከተ መንግሥት ወንጀልን ለመከላከል እርምጃ ቢወስድም በርካቶችን ሥራ አጥ ማድረግ ደግሞ ተገቢ አይደለም ይላል። በከተማዋ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወንጀል ለመፈጸም ቢውሉም፤ ሞተር ላይ ብቻ እርምጃ መወሰዱ አስገርሞታል። አሸናፊ፤ ደንቡ ሰኔ 30 ይተገበራል ቢባልም፤ ከሰኔ 15 ጀምሮ ሥራ እንዳስቆማቸው ይጠቅሳል። ግርማይ በበኩሉ ከሰኔ 28 ጀምሮ ሥራ እንዳስቆሟቸው ይጠቅሳል። የ"ዘ ሞል ዴሊቨሪ" አገልግሎት ባለቤት አምባዬ ሚካኤል ተስፋዬም በመንግሥት እርምጃ ሥራቸው መጎዳቱን ይናገራል። "ሞተሮቻችን ቆመዋል" የሚለው አምባዬ፤ ሥራ ሙሉ በሙሉ ማቆማቸውን ይገልጻል። • ሲፒጄ ለኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች መስጋቱን ገለጸ የጥርስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ሰብለ ማሞ ድርጅታቸው በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚያመርታቸውንና ለተለያዩ የጥርስ ክሊኒኮች የሚያቀርቧቸውን ትዕዛዞች በሞተር ያመላልሱ እንደነበር ይናገራሉ። አሁን ግን ማቅረብ ባለመቻላቸው ደንበኞቻቸው እየተማረሩ መሆኑን ይገልጻሉ። አምባዬ፤ ደንቡ ይፋ እንደተደረገ የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎችን ለማነጋገር መሞከራቸውን አስታውሶ፤ ደንቡን ያወጡትን አካላት ቢያነጋግሩም ምዝገባ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት መሆኑን ይጠቅሳል። የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን መስፈርት ሙሉ በሙሉ ማሟላታቸውን አምባዬ ገልጾ "ሞተሩ ላይ ጂፒኤስ ማስገጠም፣ ሞተረኛውን የደንብ ልብስ ማልበስ የሚሉትን አሟልተን ብናቀርብም በምንፈልገው ፍጥነት ጉዳያችን እየተስተናገደ አይደለም" ይላል። ማንን ማነጋገር እንዳለባቸው፣ ወይም የሚመለከተው ኃላፊ ማን እንደሆነ ግልፅ ያለ ነገር እንደሌለ የሚናገረው አምባዬ፤ በዚህም የተነሳ የተለያዩ ቢሮዎች ለመሄድና ደጅ ለመጥናት መገደዳቸውን ያክላል። የዘ ሞል ዴሊቨሪ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተመስገን ገብረሕይወት፤ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በርካታ አማራጮችን መኖር አለባቸው ይላሉ። "በአሁኑ ሰአት ሞተር ብስክሌቶች ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ርካሽ አገልግሎት እየሰጡ ነው" በማለትም ስለ አገልግሎቱ ሀሳባቸውን አካፍለውናል። • በኻሾግጂ ግድያ የአሜሪካ ዝምታ 'መፍትሄ አይሆንም'፡ የተባበሩት መንግሥታት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ ሞተር በመጠቀም በተደራጀ መንገድ ቅሚያ፣ ስርቆትና አልፎ አልፎ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረው ነበር። ሰሌዳቸው የአዲስ አበባ ያልሆኑ ሞተር ብስክሌቶች ዋነኛ የችግሩ ምንጭ መሆናቸውን በማመልከት ነው የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ሞተሮች እንዳይንቀሳቀሱ መታገዳቸውን ያስታወቁት።
news-56282077
https://www.bbc.com/amharic/news-56282077
አማራ ክልል፡ "የትግራይ ክልል ጥያቄ ካለው ለፌደራል መንግሥት ማቅረብ ይችላል"
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የወልቃይትና የራያ አካባቢዎችን በተመለከተ ያሚያቀርበው ጥያቄ ካለ በሕጋዊ መንገድ ማቅረብ ይችላል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ።
አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል የመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያነሳው ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ክስ እና ውሃ የማይቋጥር ነው" ብለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ካሳ በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች መያዛቸውን ገልጸው፤ አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በአማራ ክልል በኩል በወልቃይትና በራያ አካባቢዎች ቀደም ሲል አንስቶ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ሲነሱ የቆዩ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ግዛቸው፣ ለዚህ የሕዝብ ነው ላሉት ጥያቄ "በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን" ይናገራሉ። በጥቅምት ወር መጨረሻ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ተሰማርቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በቅራቅር እና በሶሮቃ በኩል የከፈቱትን ጥቃት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ "በተደራጀ መልኩ" መመከት ችለዋል ሲሉ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታውሰዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይል ከትግራይ ክልል እንዲወጡ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠይቋል። ኃላፊው የክልሉ መንግሥት እነዚህን የራያና የወልቃይት አካባቢዎች በጊዜያዊነት እያስተዳደረ መሆኑን ገልፀው ሕግ የማስከበሩ ሥራ መቀጠሉን፣ የዕለት እርዳታ ማቅረብ እና የመንግሥት ተቋማትን መልሶ ማደራጀትና ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። እንደ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጻ ከሆነ በአካባቢው አሁንም የሕግ ማስከበር ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው የመንግሥት ተቋማት ወደ ሥራ እንዲገቡም ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። ኃላፊው አካባቢዎቹን በኃይል መያዝ ሕገ-መንግሥቱን አይጻረርም? ተብለው ተጠይቀው በየትኛውም ዓለም አቀፍ ሕግ ቢለካ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ተግባር አይደለም ሲሉ መልሰዋል። ይህንንም ሲያስረዱ "ከመጀመሪያው በሕገ-መንግሥት ወይንም በአዋጅ የተወሰዱ ቦታዎች አይደሉም" በማለት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል "ጥያቄ ካለው በሕጋዊ መልክ ማቅረብ ይችላል" ብለዋል። ጨምረውም የአማራ ክልል አካባቢውን በጊዜያዊነት እያስተዳደረው መሆኑን ገልፀው የፌደራል መንግሥቱ በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጠው ጥያቄያችን ይቀጥላል ብለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች መያዛቸውን ገልጸው፤ "አስተዳደሩ ህወሓት ያስተዳድረው ከነበረው ግዛት በሴንቲሜትር የቀነሰ ክልልን አያስተዳድርም" ብለዋል። አቶ ገብረ መስቀል እንዳሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተገለጸውን የትግራይ ክልልን እንደሚያስተዳድር ገልጸው፤ "እነዚህን ቦታዎች ከሕግ ውጪ የያዙ ኃይሎች የአገሪቱን ሕገ መንግሥት እየተጻረሩ ነው" ብለዋል። እንደ አማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ደግሞ "በሕግ ማስከበሩ ሂደት" ውስጥ እነዚህ የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎችን "እግረ መንገዱን መልስ ሰጥቷል" ብለዋል። "በጉልበት ተወስዷል፤ በጉልበት ተመልሷል፤ በኃይል ተነጥቀናል በኃይል አስመልሰናል" ባሉት በዚህ እርምጃ "የተጠቀሱት አካባቢዎች የአማራ እንጂ የትግራይ አይደሉም፤ በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ ኃይልም ሆነ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጣልቃ ሊገባብን አይገባም" ብለዋል። አጠቃላዩ ምዕራባዊ የትግራይ ክፍል እንዲሁም በደቡብ አላማጣ፣ ኮረምና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ስር መሆናቸውን ያመለከቱት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ይህም ለፌደራል መንግሥቱ ሪፖርት ተደርጎ ኃይሎቹ ከአካባቢዎቹ እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ገልጸዋል። "ግፊት የምናደርገው የተሰማራው ኃይል እንዲወጣ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎቹ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲቆሙና ፈጻሚዎቹ በሕግ እንዲጠየቁ ነው" ሲሉ አቶ ገብረ መስቀል ተናግረዋል። አቶ ግዛቸው "የትግራይ ክልል ቦታዎቹ የእኔ ናቸው፣ ይገባኛል የሚል ከሆነ አሰራሩን ተከትሎ በሕጋዊ መንገድ ይጠየቅ" በማለት የአማራ ክልልም "ሕጋዊ አካሄዱን ይቀጥላል" ብለዋል። ወልቃይት፣ ጠለምት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ፣ ኮረም አካባቢዎች በአማራ ክልል መንግሥት ስር መሆናቸውን ኃላፊው አረጋግጠው፤ "በእነዚህ አካባቢዎች ያለው ሕዝብ ነጻነቱን በኃይል አውጇል" ብለዋል። በተጠቀሱት አካባቢዎች ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ በደል ተፈጽሟል እንዲፈናቀሉም ተደርጓል በሚል ለቀረበው ክስም አቶ ግዛቸው ሲመልሱ "የትግራይ ተወላጆችም ከአማራ ሕዝብ ጋር አብረው የኖሩ አብረውም የሚኖሩ ናቸው። አንድም የትግራይ ተወላጅ እንዲገፋ አልተደረገም" በማለት በአካባቢው ባሉ የሥራ እድሎች ማንንም ሳይለዩ ቅጥር መፈፀማቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን ግጭት ሲከሰት መፈናቀል የማይቀር ነው ያሉት ኃላፊው፤ ከአካባቢው ተፈናቅለው የነበሩት ነዋሪዎች እንዲመለሱ የክልሉ መስተዳደር አስፈላጊውን ሥራ እያከናወነ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል እነዚህን የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች "በህወሓት የአስተዳዳር ዘመን በኃይል የተወሰዱ ናቸው ይመለስልኝ ሲል ለዓመታት ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን" አቶ ግዛቸው ገልጸዋል። ጨምረውም በወቅቱም በአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ላይ መፈናቀልና ከዚያም ያባሱ በደሎች ተፈጽመዋል በማለት "አሁን ሕዝቡ ከዚህ አፈና ነጻ ወጥቷል" ብለዋል። በመሆኑም ጥያቄውን ሕጋዊ ለማድረግ ከፌደራል መንግሥት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክልሉ በሕዝቡ ጥያቄ ላይ እንደማይደራደር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ለሦስት ሳምንታት በተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ የፌደራሉ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ሲቆጣጠር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተካሄደው "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" መጠናቀቁን አውጀው ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላም ባለፉት ሦስት ወራት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ከክልሉ የሚወጡ ሪፖርቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት የገለጹ ነው። በጦርነቱ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ በትክክል የታወቀ ነገር ባይኖርም በሺዎች የሚቆተሩ ሊሆኑ እንደሚችል ይገመታል። ከዚህ ባሻገር ግጭቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የተነገረ ሲሆን፤ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ መንግሥትና ረድኤት ድርጅቶች ጥረት እያደረጉ ነው።
41818229
https://www.bbc.com/amharic/41818229
የናይጀሪያ ህፃናት የኩፍኝ ወረርሽኝ አደጋ ላይ ናቸው
ኩፍኝ በከፍተኛ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን፤ በቀላሉም በክትባት በሽታውን መከላከል ይቻላል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ካልተከተቡት 20 ሚሊዮን ህፃናት መካከል 3 ሚሊዮኑ ናይጀሪያ ውስጥ እንደሚገኙ አዲስ የወጣ ሪፖርት ያሳያል። ሁለቱ አፍሪካውያን ሀገሮች ኢትዮጵያና ኮንጎም ከሌሎች በተለየ መልኩ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ያልተከተቡ ህፃናት ልጆች ያሉባቸው ሀገራት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጨምሮ ያስረዳል። ይህ ሪፖርት የወጣው ዝናብ በማይዘንብበት በበጋ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞች ስጋት በሆኑበት ወቅት ነው። በናይጀሪያ ከኅዳር እስከ መጋቢት ባለው ወቅት የከፋ የኩፍኝ ወረረሽኝ የሚከሰትበት ጊዜ ነው። በባለፈው ዓመት ከጥር እስከ መስከረም ባለው ወቅት በሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ አካባቢ 3 ሺህ ያህል የሚሆኑ በኩፍኝ የተጠረጠሩ ህሙማን እንዳሉ ሪፖርት ተደርጓል። በዚሁ አካባቢ አሁንም ባሉት ግጭቶች የተነሳ የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፤ ሰባት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችም የጤና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። ይህ ሪፖርት እንደ ዓለም ጤና ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው በጥምረት ያወጡት ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም ከፍተኛ የሆነ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ጠቁሞ። በሽታው ውስብስብ ለሆኑት የሳንባ ምች፣ ዓይነ-ስውርነት እንዲሁም ለሞት እንደሚዳርግ ይገልፃል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ለግጭት በተጋለጡ አካባቢዎች ላይ በቆየ የሁለት ሳምንት የክትባት ዘመቻ፤ ዕድሜያቸው ከአስር ወራት እስከ አስር ዓመት የሆኑ አራት ሚሊዮን ልጆች ተከትበዋል።
41671070
https://www.bbc.com/amharic/41671070
"ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው"
ጎንደር ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ምሬቶች የሾፈሯቸው ናቸው የተባሉ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ካስተናገደች ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ቢያልፍም፤ ነዋሪዎቿ የሻቱትን ለውጥ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።
በከተማዋ አሁንም የብሔር ተኮር ውጥረት ምልክቶች የሚስተዋሉ ሲሆን፤ በመዝናኛ ስፍራዎች ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው የሚታመኑ ዘፈኖችን ማድመጥ እንግዳ አይደለም። ከዚህም ባሻገር ስፖርታዊ ትዕይንቶችን እና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት የሚፈጥሯቸውን አጋጣሚዎች ቅሬታዎቻቸውን ለማንፀባረቅ እንደሚጠቀሙባቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ወጣቶች ይገልፃሉ። የመልዕክቶቹ ፖለቲካዊ አንድምታ ብዙም የተደበቀ እንዳልሆነ የሚያወሳው የከተማዋ ነዋሪ ወንድወሰን አለባቸው*፤ ከሳምንታት በፊት የተከበረው የመስቀል በዓል ላይ ይታዩ ከነበሩ አልባሳት ላይ ከታተሙ ጥቅሶች መካከል "የፈራ ይመለስ" እና "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም" የመሳሰሉትን እንደሚያስታውስ ይናገራል። የፀጥታ ኃይሎች አልባሳትን ለማስወለቅ ሲጥሩ መመልከቱንም ጨምሮ ይገልጻል። "ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው" ይላል ወንድወሰን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። በ2008 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎንደር ተቃውሞ መቀስቀስ ሲጀምር ከሰሜናዊው አዋሳኝ የትግራይ ክልል ጋር የድንበር ጥያቄ በማንሳት እንደነበር ይታወሳል። በሐምሌ ወር መባቻ አዋሳኙ የወልቃይት አካባቢ በአማራ ክልል ስር እንዲጠቃለል ጥያቄ ለማቅረብ የተዋቀረውን ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ስር ለማዋል ሙከራ ተደርጎ በከሸፈበት ወቅት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከአስር በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተዘግቦ የነበር ሲሆን፤ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ክስ ተመስርቶባቸው እስር ላይ ይገኛሉ። ኮሎኔሉን ከመያዝ ለመታደግ ሲጥር በተኩስ ልውውጡ ወቅት ሕይወቱን ያጣ ጠባቂያቸውን በማስታወስ ወደ መቃብር ስፍራው ሲያቀኑ ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ የገቡና እንዲመለሱ የተደረጉ ሰዎችን እንደሚያውቅ ሌላኛው የከተማዋ ኗሪ አንዋር አብዱልቃድር ይናገራል። ባህረ ሰላም ሆቴል ያልተወራረደ ሒሳብ ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ያለመረጋጋት ጥቃት ከደረሰባቸው የንግድ ተቋማት መካከል ባሕረ ሰላም ሆቴል አሁንም እንደተሰባበረ ተዘግቶ ይገኛል። ሆቴሉ የጥቃት ሰለባ የሆነው የኮሚቴው አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የመጡ የደህንነት አባላት ስላረፉበት መሆኑን የስፍራው ኗሪዎች ይናገራሉ። በሆቴሉ አካባቢ በአነስተኛ የችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማራች ወጣት የሆቴሉ ባለቤቶች ከጥቃቱ በኋላ ተመልሰው መምጣታቸውን እንደማታውቅ ትናገራለች። ተቃውሞው በከረረበት ወቅት ከጥቃት ለመሸሽ በርካታ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሐብትና ንብረታቸውን ጥለው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸው የተዘገበ ሲሆን ከመካከላቸው ጥቂቶቹ ብቻ መመለሳቸውን እንደሚያውቅ አንዋር ይናገራል። በበርበሬ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራችው ሰናይት መኮንን* እንደምትለው በጎንደር እና በትግራይ ክልል መካከል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ መዳከሙ ሥራዋን ክፉኛ ከማወኩም ባሻገር "ግርግሩ ብዙ ገንዘብ አሳጥቶኛል" ትላለች። ሰናይት በርበሬን ከምዕራብ ጎጃም ከገዛች በኋላ የተለያዩ እሴቶችን ጨምራ በሽሬ እና ሑመራ ለሚገኙ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ትልክ እንደነበር ትገልፃለች። "ሁሌም በንፁህ መተማመን ነበር የምንሰራው። ስልክ ደውለው የሚፈልጉትን ያህል መጠን ይነግሩኛል፤ አስጭኜ እልክላቸዋለሁ። እርሱን ሸጠው በሳምንትም በወርም ገንዘቡን ይልኩልኛል" ስትል ለቢቢሲ ታስረዳለች። በዚህም መሰረት ያለመረጋጋቱ ሲከሰት 280 ሺህ ብር የሚገመት በርበሬ ለደንበኞቿ ልካ እንደነበርና ከአንድ ዓመት የሚልቅ ጊዜ ቢያልፍም ገንዘቡን ማግኘት መቸገሯን ትናገራች። "እነርሱም ወደዚህ አይመጡ፤ እኔም ወደዚያ አልሄድ፤ በስልክ ብቻ እየወተወተኩ ነው" ትላለች። ደንበኞቿ በጎንደርና በአካባቢው ሌሎች ከተሞችም ጭምር ልዩ ልዩ የንግድ ሥራዎችን ያከናውኑ የነበረ ሲሆን፤ ያለመረጋጋቱን ተከትሎ ሥራቸውን እንደቀደመው ማከናወን ባለመቻላቸው ለኪሳራ ተዳርገው ገንዘቧን ሊልኩላት እንዳልቻሉ ገልፀውላታል። በዚህ መልኩ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብን ያጡ በተለይ በሕንፃ ሥራዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ የሙያ አጋሮቿን እንደምታውቅ የምታስረዳው ሰናይት "እንግዲህ ከእነርሱም ወገን እንዲሁ ገንዘብም ዕቃም የቀረበት ይኖር ይሆናል" ትላለች። "ከዚህ በኋላማ መተማመኑ ጨርሶ ጠፍቷል" የምትለው ሰናይት የወትሮ የንግድ አሰራሯ እንዳከተመለት ትናገራለች። በመምህርነት ሙያ ለተሰማራው ሞገስ አብርሃ* የመተማመን መሸርሸር እጅጉን የሚያሳስብ ጠባሳ ነው። "ፖለቲካው በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ሰርጎ ጥርጣሬን የዘራ ይመስለኛል" ይላል የትግራይ ተወላጁ ሞገስ። ከተማዋ በተቃውሞና በግጭት በምትናጥበት ወቅት በቤተሰባዊ ጉዳይ ትግራይ ውስጥ የነበረው ሞገስ፤ ወደጎንደር እንዳይመለስ ከዘመዶቹ ግፊት እንደነበረበት ያስታውሳል። "ስጋታቸው ገብቶኛል፤ ነገር ግን ትዳርና ልጆች ካፈራሁበት ቦታ እንዲሁ ብድግ ብዬ አዲስ ህይወት ልመሰርት አልችልም" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ያለመረጋጋቱን መስከን ተከትሎ ወደሥራው ከተመለሰ በኋላ የገጠመው የተለየ ነገር እንደሌለ የሚናገረው ሞገስ ሄደው የቀሩ የሥራ ባልደረቦች እንዳሉት ይጠቅሳል። "የትግራይ ክልል ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ አድርጌያለሁ ቢልም [በግለሰብ] ከጥቂት ሺህ ብር በላይ የሰጠ አይመስለኝም።" ከአንድ ዓመት በኋላ የጎንደር ከተማው የባህል፣ ቱሪዝም እና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አስቻለው ወርቁ ወደ ከተማዋ ዘላቂ ሰላምን እንዲሁም ተጠቃሚነትን እንዲመለስ ለማድረግ ብዙ ሥራዎች ተከናውነዋል ይላሉ። ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ለመፍጠርና ለከተማዋ እና ለአካባቢው ምጣኔ ሃብት የጎላ ሚና የሚጫወተውብን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግመኛ ለማነቃቃት መሰራቱን ይገልፃሉ። "በ2009 የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር በጣም ቀንሶ የነበረ ሲሆን፤ ይህንን በማካካስ በዘርፉ ላይ የተሰማሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች የማይጎዱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሞክረናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከ45 ሺህ በላይ የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች ለመዝናናት፣ ለስብሰባ፣ ስፖርታዊ ትዕይንቶችን ለመታደም እንዲሁም በክብረ በዓላት ላይ ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ አቅንተዋል። "በያዝነው ዓመት ግን ከውጭ አገር የሚመጡ ጎብኝዎች ቁጥር ከፍ ያለ ሆኗል" የሚሉት አቶ አስቻለው ከተማዋ በነሐሴና መስከረም ወራት ብቻ ከ3000 በላይ የውጭ አገር ጎብኝዎችን ማስተናገዷን ይገልፃሉ። ቁጥሩ ከዚህ እየተሻሻለ እንደሚሄድም ይጠብቃሉ። በዚህ አባባል የሆቴል ባለቤትና አስተዳዳሪው አቶ ስዩም ይግዛውም ይስማማሉ። "በአሁኑ ሰዓት ካሉን ክፍሎች መካከል ሰባ አምስት በመቶው ያህል ተይዘዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጎብኝዎች ቁጥር እና ተያይዞ ያለው ኢንዱስትሪ በወቅት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚያስረዱት አቶ ስዩም፤ በሥራ ላይ ከቆዩባቸው ስድስት ዓመታት መካከል ያለፈውን ዓመት እጅግ ዝቅ ባለ የሥራ እንቅስቃሴ በተለየ እንደሚያስታውሱት ያወሳሉ። ለዚህም የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ጉልህ ሚና እንዳለው ይገምታሉ። በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርካታ ስፍራዎች ተቃውሞዎች እና ግጭቶች መቀጣጠላቸውን ተከትሎ፤ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ የጎብኝዎች ቁጥር ለማሽቆልቆሉ በምክንያትነት ይወሳል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመደንገጉ የተለያዩ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ ስፍራው እንዳይሄዱ መምከራቸው አልቀረም። ከዚህም ባሻገር ባለፈው ዓመት አጋማሽ በተከታታይ ያጋጠሙት የእጅ ቦንብ ፍንዳታዎች፤ የተለያዩ ሃገራት ወደ ጎንደር ለማቅናት ላሰቡ ዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ እንዲያወጡ አስገድዷቸዋል። "የጉዞ ማስጠንቀቂያዎቹ ሥራችንን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድተውታል፤ ከየሃገራቸው ለጎብኚዎች ጉዞዎችን የሚያሰናዱ አካላት ስለአካባቢው ያለውን ሁኔታ ከኤምባሲያቸው ማጥናታቸው አይቀርም" ይላሉ አቶ ስዩም። አዋጁ ያለመረጋጋቱን ቢያሰክነውም ለጥያቄዎች መልስ በመስጠት ረገድ ግን መንግሥት በቂ እርምጃዎችን እንዳልወሰደ ተንታኞች ሲያስረዱ ይደመጣሉ። ወንድወሰን ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ "ምንም የተቀየረ ነገር የለም" ባይ ነው። የከተማዋ ነዋሪ አንዋር እንደሚለው፤ ተቃውሞዎቹ ኅብረተሰቡ ያለውን ስሜት እንዲያሳይ እድል ፈጥረውለታል፤ ይሁን እንጅ "ጥያቄያችን ሳይመለስ ችግሩ ተቀርፏል ማለት ራስን ማታለል ነው።" *ስም የተቀየረ
news-54022841
https://www.bbc.com/amharic/news-54022841
"ልደቱ እዚሁ ጣቢያ ነው መታሰር ያለብኝ ብሎ ለምኖ ነው [ቢሾፍቱ] የቀረው"፡ የኢዴፓ ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ
የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ የተፈጠረውን ሁከት በማነሳሳት፣ መምራትና በገንዘብ መደገፍ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው "ህገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ" ሞክረዋል በሚል አዲስ ውንጀላ እንደቀረባባቸው ጠበቃቸው አቶ አብዱልጀባር ሁሴን ገመዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብታቸውን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በትናንትናው ዕለት ውሳኔ ለማስተላለፍ በዋለው ችሎት ላይ ነው አቃቤ ህግና ፖሊስ አዲስ ክስ ያቀረቡባቸው። የቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የፖሊስን ጥያቄ የህግ አግባብነት እንደሌለው ጠቅሶ ሳይቀበለው የቀረው ነሐሴ 25፣ 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነበር። ፖሊስ አልለቅም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው እንደገና ማመልከቻ ያስገቡ የሚል ጥያቄም አንስቷል። ፍርድ ቤቱም የፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ዘግቶ አቶ ልደቱ በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። በትናንትናው ዕለት በዋለውም ችሎት የዋስትና ጥያቄ መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግና ፖሊስ በግድያ ከመጠርጠር በተጨማሪ "ህገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል የመናድ" ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበዋል። ለዚህም መሰረት የሆነው የሽግግር መንግሥትን ምስረታን ለመንግሥት እንደ አማራጭነት ያቀረቡት ሰነድ ሲሆን ይህም ጠበቃው እንደሚሉት ጥር ወር ገደማ የተፃፈ ሲሆን ሁከቱ ግን ከአርቲስቱ ሞት በኋላ የተከሰተ ነው። በተጨማሪም አቶ ልደቱ እየፃፉት ነው የተባለውና ቤታቸው ውስጥ የተገኘው የመፅሃፍ ረቂቅ በአባሪነት የቀረበ ሲሆን በይዘቱ "ለውጡን የሚተችና ህገ መንግሥቱን ለመናድ ዝግጅት" የሚሉ አዳዲስ ውንጀላዎች ቀርበውባቸዋል ብለዋል። "እነዚህ ምክንያቶች አቃቤ ህግ ዋስትና ለማስከልከል ያቀረባቸው ናቸው። የምርመራ መዝገቡን መሰረት ያደረጉ አይደሉም" የሚል ክርክር ማቅረባቸውንም ያስረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ አቶ ልደቱ ገና በረቂቅ እንዳለና ለህዝብ ይፋ ያልሆነ ያልታተመ መፅሃፍ እንደሆነም ነግረዋቸዋል። "ይሄ እንግዲህ በሃሳብ ደረጃ ያለ ስለሆነ፤ ማንኛውም ግለሰብ በሃሳቡ አይቀጣም። ሃሳብ ወንጀል አይደለም። እንዳያስብ ሁሉ ሊከለከል ነው ማለት ነው የሚል ነገር ነው አቶ ልደቱም ያነሱት" ብለዋል ጠበቃቸው በበኩላቸው ዋስትና በኢትዮጵያ ህገ መንግሥትም ሆነ ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መስረት መብት እንደሆነ ጠቅሰው ዋስትና የሚከለከልበት በአንዳንድ አጋጣሚ እንደሆነ ጠቅሰው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል ግድያ የሌለበትና ከአስራ አምስት አመት በላይም ሊያስቀጣ ስለማይችል የዋስትና መብታቸው እንዲከበር መከራከሪያ ሃሳብ እንዳቀረቡም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ በጥዋት ቀጠሮው አቃቤ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረቡትን ውንጀላ የሚያስረዳ የምርመራ መዝገብ ማምጣት የሚለውን ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠትም ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ትናንት ከሰዓት በዋለው ችሎትም አቃቤ ህግና ፖሊሶች የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ማምጣት አንችልም በሚልም ብዙ እንዳንገራገሩ የገለፁት ጠበቃው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ለዞን አቃቤ ህግ ተልኳል በማለት ምክንያት ሰጥተዋል። ግራ ቀኙን ያየው ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ማምጣት አለባችሁ የሚል ውሳኔን አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ፣ ፖሊስ የምርመራ መዝገብና ማስረጃውን እንዲያቀርብ በማዘዝ ለዛሬ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን የምርመራ መዝገቡ ክስ ለመመስረት በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚለውንም ሁኔታ የሚወስን እንደሆነ ጠበቃቸው ጠቁመዋል። በዛሬው ዕለት አካልን ነፃ የማውጣት ክስን ለመመስረት ከደንበኛቸው ጋር መነጋገራቸውንም በተጨማሪ አስረድተዋል። ዋስትናን በሚመለከት ደግሞ በዛሬው እለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔን እንደሚሰጥ ተናግረዋል። "የዋስትና መብት ይከበር በሚል እኛ የምንከራከረው የነፃነትን መብት ለማስጠበቅ ነው" የሚሉት ጠበቃው አቶ ልደቱ፣ ከዚያም ባለፈ በህይወት የመቆየት ሁኔታቸውን ሊፈታተን የሚችል የሃኪም ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል። ከዚህ ቀደም የልብ ቀዶ ህክምና አድርገው አርቲፊሻል ነገር ልባቸው ላይ እንዳለ ሐምሌ 30፣ 2012 ዓ.ም አሜሪካን ሃገር የምርመራ ቀጠሮ ቢኖራቸውም እሱንም መሄድ እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ በቀጠሮዎቹ ሲጠቀስ እንደነበርም አቶ አብዱልጀባር ያስረዳሉ ። ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛቸው የአስም ህመምተኛ ሲሆኑ ከልብ ህመማቸው ጋር ተያይዞ ለኮቪድ-19 ተጋላጭነታቸው በጣም ከፍተኛ እንደሚያደርገውና በአዲስ አበባ የሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል የተያያዘው የሃኪም ማስረጃንም ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። "በሕይወት የመኖር መብትና በነፃነት መካከል የመብት መበላለጥ ባይኖርም ሰው በህይወት ሲኖር ነው የነፃነት መብቱ የሚጠይቀው የእርሳቸው ትንሽ አስከፊ የሚያደርገው በህመም ላይ መሆናቸው ነው" ብለዋል አቶ አብዱልጀባር። አቶ ልደቱ በመጀመሪያ የተጠረጠሩበት ወንጀል በቢሾፍቱ ከተማ ሁከት በማስነሳት መምራትና በገንዘብ መደገፍ የሚል ነበር። በጊዜ ቀጠሮ በቆዩባቸው ወቅት ቤታቸው ሲበረበር በተገኙት ፅሁፎችና ሰነዶች የምርመራ ሂደቱ መልኩን ቀይሮ ወደ ሌላ ሁኔታ እያጋደለ የመጣበት ሁኔታ እንደነበር ይጠቅሳሉ። "ህገ መንግሥታዊውን ስርዓት በኃይል የመናድ፣" አንቀፅ 238ን በመጥቀስ አቶ ልደቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ለዚች አገር የሽግግር መንግሥት ነው የሚበጃትና ሌሎች አማራጮችን ሲናገሩ ከነበሩት አንዳንድ ነገሮች ተገኝተዋል በሚል መልኩንም የቀየረው ቀድሞም እንደነበር ነው ጠበቃቸው ገልጸዋል። በ25/12/12 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ሲዘጋ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቄያለሁ ብሎ እንደነበርና ሁለተኛ ደግሞ የምርመራ መዝገቡ ውስጥ ከዚህ በፊት መርማሪ ፖሊሶች ሶስት ምስክር ተሰምተው ነበር። በኋላ ላይ ግን ፍርድ ቤት ሲያጣራ ግን በቢሾፍቱ አቶ ልደቱ ብጥብጥ አስነስተዋል፣ መርተዋል፣ ገንዘብ ደግፈዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ ሶስት ምስክር የተባሉት የአቶ ልደቱ ቤት ሲበረበር በምርመራ እንዲገኙ በታዛቢነት የቆሙ ግለሰቦች መሆናቸውን ደርሶበታል ይላሉ። በአጠቃላይ "እሳቸውን አስሮ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን እንዲያውም ወንጀል የማፈላለግ ሁኔታ ነው ሲደረግ የነበረው" ይላሉ። ፓርቲያቸው ምን ይላል? የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ፤ "አሁን ባለው ሂደት መፍትሔ ማግኘት እንደማይቻል ተማምነን አካልን ነጻ የማውጣት ክስ ለመመስረት ወስነናል" ብለዋል። ፖሊስ አቶ ልደቱ ከቢሾፍቱ ወደ አዳማ ማረሚያ ቤት መሄድ አለባቸው ብሎ እንደነበረ ገልጸውም፤ "ልደቱ እዚሁ ጣቢያ ነው መታሰር ያለብኝ ብሎ ለምኖ ነው [ቢሾፍቱ] የቀረው" ሲሉ አስረድተዋል። አቶ አዳነ የዛሬው ፍርድ ቤት ውሎ የተቋጨው "በአሳዛኝ ሁኔታ" ነው ብለው፤ "አስፈጻሚው ከሕግ አውጪው በላይ ጡንቻ አለው ብለን ስለምናምን ሰኞ አዲስ አበባ ላይ አካልን ነጻ የማውጣት ክስ እንመሰርታለን" ሲሉ ውሳኔያቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
55183182
https://www.bbc.com/amharic/55183182
ናሳ ከጨረቃ ላይ የአፈር ናሙና ለሚያመጣለት ኩባንያ 1 ዶላር ብቻ ሊከፍል ነው
ናሳ የአፈርና የዓለት ናሙና ከጨረቃ ላይ ለሚያመጣልኝ ኩባንያ ጠቀም ያለ ገንዘብ እከፍላለሁ ባለው መሰረት በርካታ ግዙፍ ኩባንያዎች ተወዳድረው ነበር።
ጨረታውን ያሸነፈው ኩባንያ ተለይቷል። ይህን ግዙፍና ውስብስብ ሥራ ሲያጠናቅቅ የሚከፈለው ግን አንድ ዶላር ብቻ ነው። በዚህ በርካቶች በተሳተፉበት ውድድር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ያሸነፈው "ሉናር አውትፖስት" የተባለ ኩባንያ ነው። ይህ ኩባንያ ለአሜሪካው የሕዋ ኤጀንሲ ሥራውን ለመሥራት በ1 ዶላር ዋጋ ነው ስምምነት የተፈራረመው። ናሳ ከዚህ ስምምነት ጋር ሌሎች አራት ተመሳሳይ ኮንትራቶችን ያስፈረመ ሲሆን አራቱም እጅግ ዝቅ ባለ ዋጋ የተሰጡ ኮንትራቶች ናቸው ተብሏል። ዓላማውም በዝቅተኛ ዋጋ ጨረቃ ላይ ያሉ ነገሮችን ናሙና ማስቀለቀም ነው ተብሏል። ከአራቱ ጨረታዎች አንዱን ያሸነፈው ሌላኛው ኩባንያ መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው "ማስተን ስፔስ ሲስተም" ሲሆን ሦስተኛው ኩባንያ ደግሞ ቶክዮ የሚገኘው "አይስፔስ" ነው። ናሳ ለነዚህ ኩባንያዎች አገልግሎት ለእያንዳዳቸው አንድ አንድ ዶላር ይከፍላቸዋል። ሥራቸው የሚሆነው ጨረቃ ሄደው ከ50 እስከ 500 ግራም የሚመዝኑ ሪጎሊስ ወይም የጨረቃ አፈር (ዐለቶችን) ጭኖ ማምጣት ነው። የጨረቃ ዐለቶች በቢሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያላቸው ናቸው። "እነዚህ ኩባንያዎች የጨረቃ አፈር ናሙና ለቅሞ ማምጣት ብቻ ሳይሆን ያን ስለማድረጋቸው በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው" ብለዋል የናሳ ቃል አቀባይ። ይህ ሥራ የሚከናወነው በ2023 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነው። መቀመጫውን ኮሎራዶ ያደረገው ሉናር አውትፖስት የሮቦት ድርጅት ሲሆን ከደቡባዊ የጨረቃ ዋልታ አፈር ሰብስቦ ለማምጣት የአንድ ዶላር ኮንትራት ማሸነፉ እጅጉኑ አስደስቶታል። ይህ ድርጅት በዚህ ሥራ ለመሰማራት ዋና ዓላማው ገንዘብ አይደለም። ኩባንያዎቹ ይህንን ሥራ ካሳኩ በኋላ በርከት ያሉ ሳይንሳዊ ትርፎችን ያገኛሉ። አንዱ ተስፋቸው ከጨረቃ ወለል የሚገኙ ማዕድናትን እንዲያወጡ ዕድል ስለሚሰጣቸው ነው። ይህ ነው በ1 ዶላር ክፍያ እንዲህ ዓይነት ውስብስብ ኮንትራት ውስጥ ለመግባት የሚያበረታታቸው። ኩባንያው አሁን "ብሉ ኦሪጅን" ከተባለ ሌላ ግዙፍ ኩባንያ ጋር እየተነጋገረ ነው። ንግግሩ ያተኮረው ወደ ጨረቃ የሚያሳፍር የሕዋ ታክሲ ለመኮናተር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው። "ብሉ ኦሪጅን" የምድራችን የናጠጠው ቁጥር አንድ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ኩባንያ ነው። ዋና ሥራው ሰዎችን ህዋ አሳፍሮ መመለስ ነው። ከናሳ ጋር ርካሽ የሥራ ውል ካደረጉት ድርጅቶች መካከል የጃፓኑ "አይስፔስ" ይገኝበታል። አይስፔስ በሰሜን ምሥራቅ ዋልታ በ2020 ዓ ም ለሚሰበስበው የጨረቃ ዐለት 5ሺ ዶላር ቁርጥ ክፍያ ያገኛል። የሐዋ ጉዳዮች ተንታኝ ሲኒየድ ኦ ሱሊቫን እንደሚሉት ለዚህ የሥራ ሥምምነት 1 ዶላር ቀላል ገንዘብ አይደለም። ምክንያቱም ይላሉ ተንታኙ፤ ኩባንያዎቹ በዚህ የሥራ ውል ስምምነት የሚገቡት ገንዘቡን ብለው አይደለም። ወደፊት የሚፈጥርላቸውን ዕድል ታሳቢ በማድረግ ነው። ይህ ኮንትራት ገዢና ሻጭ ከመሬት ውጭ ባለ ነገር ላይ እየተፈራረሙ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። የሚደንቀው አንድ ዶላር መከፈሉ ብቻ አይደለም። ኩባንያው ከጨረቃ የአፈር ናሙና ለማምጣት 1 ዶላሩ የሚከፈለው በሦስት ዙር መሆኑ ነው። መጀመርያ ውሉን ሲያስር የአንድ ዶላር 10 በመቶ ይከፈለዋል፤ ይሄ ተከፍሎታል። ቀጥሎ ደግሞ መንኩራኩር ተሳፍሮ ሲሄድ ነው። ሦስተኛውና ትልቁ ክፍያ ናሙናዎቹን ከጨረቃ ጭኖ አምጥቶ ሲያስረክብ ነው። ያን ጊዜ የአንድ ዶላር 80 ከመቶ ይከፈለዋል። "አዎ ይህ ቀልድ ሊመስል ይችላል፤ 1 ዶላር የሚከፈለው በአንድ ጊዜ አይደለም። በ3 ዙር ነው። መጀመርያ $0.10, ከዚያ ደግሞ $0.10, በመጨረሻም $0.80 ክፍያ ይፈጸማል ብለዋል" ቃል አቀባዩ ሳይረስ። ይህ ስምምነት የተፈረመው ቻይና የጨረቃ ናሙና ለማምጣት መንኩራኩር በላከች ማግስት ነው። የቻይናው ቼንጅ5 የጨረቃ መንኩራኩር አሁን በዚህ ሰዓት ናሙናዎቹን ጭኖ ወደመሬት በመምጣት ላይ ይገኛል።
news-51179301
https://www.bbc.com/amharic/news-51179301
በየመኑ ጥቃት የሟቾች ቁጠር 111 ደረሰ
በየመን አንድ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት የሟቾች ቁጥር በትንሹ 111 መድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ሚሳኤሉ የተተኮሰው በወታደራዊ ማሰልጠኛው ውስጥ በሚገኝ መስጂድ ውስጥ ወታደሮች የምሽት ጸሎታቸውን በማድረስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል። መንግስት ጥቃቱን የፈጸሙት የሁቲ አማጺያን ናቸው ቢልም ቡድኑ ግን ለጥቃቱ ወዲያው ሀላፊነት ከመውሰድ ተቆጥቧል። በየመን የዛሬ አምስት ዓመት የእርስ በርስ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ይሄኛው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ ከሚባሉት መካከል እንደሆነም ተገልጿል። • ቦንብ የሚዘንብባትን የሶሪያ ከተማ አልለቅም ያለው የነፍስ አድን ሰራተኛ • በርካቶች መርሳት ያልቻሉት ጦርነት ሲታወስ በሳኡዲ የሚደገፈው መንግስት ታማኝ ወታደሮች እና የሁቲ አማጺያን መካከል የሚደረገው ጦርነት ሀገሪቱን ከማፈራረስ አልፎ እስካሁን ለ 100 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። በየመን ከ 11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የሚቸገሩ ሲሆን 240 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ለከባድ ረሀብ የቀረበ በሚባል ደረጃ ህይወታቸውን ይመራሉ ብሏል የዓለም የምግብ ፕሮግራም። በአማጺያን ቁጥጥር ስር ከምትገኘው ሳናአ በምስራቅ በኩል 170 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው አል ኤስቲቅባል የተባለው ወታደራዊ ካምፕ ላይ በደረሰው ይህ ጥቃት 80 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል። ነገር ግን በሚሳኤል የተደረገው ጥቃት ከፍተኛ ስለነበረ ጉዳት አጋጥሟቸው የነበሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በዚህም የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 111 እንደደረሰ ተገልጿል። 'ኤኤፍፒ' የተባለው የዜና ወኪል ደግሞ ከወታደሮችና የህክምና ባለሙያዎች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የሟቾች ቁጥር ከ 116 በላይ ይደርሳል። • በብሩንዲ ከአራት ሺህ በላይ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ • እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ተቀስቅሶ እናየው ይሆን? እነሆ ምላሹ የየመኑ ፕሬዝዳንት አብደራቡህ ማንሱር ሃዲ ከጥቃቱ በኋላ '' የከሀዲዎችና የሽብረተኞች ተግባር ነው'' ብለዋል ጥቃቱን። አክለውም ''የሁቲ አማጺያን ለሰላም ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ማሳያ ነው'' ብለዋል። የሳኡዲ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ጥቃቱን ''አማጺዎቹ ሁቲዎች ክብር ላለው የእምነት ቦታ እና ለየመን ዜጎች ህይወት ምንም ክብር እንደማይሰጡ ማሳያ ነው'' ብሎ ገልጾታል።
news-56563214
https://www.bbc.com/amharic/news-56563214
ናይኪ የሰው ደም ጠብታ ያረፈበት "የሰይጣን ጫማ" ላይ ክስ መሰረተ
ናይክ ብሩክሊን የጥበብ ሥራዎችን ሰብሳቢ የሆነው ኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) ያመረተው ጫማ ላይ ክስ መሰረተ።
በዚህ አወዛጋቢ ጫማ ሶል ላይ እውነተኛ የሰው ደም ጠብታ ያረፈበት ሲሆን "የሰይጣን ጫማ" በመባል ይታወቃል። 1,018 ዶላር ዋጋ የተተመነለት ይህ ጫማ የተገለበጠ መስቀል፣ አምስት ጫፍ ያለው ኮከብ እንዲሁም ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 18 የሚል የሰፈረበት ሲሆን የተሰራው ናይኪ ኤይር ማክስ 97ን በማስመሰል ነው። ኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) 666ን ጫማን ሰኞ ዕለት ከራፐር ሊል ናስ ኤክስ ጋር በመሆን ለገበያ ያቀረበው ሲሆን በደቂቃ ውስጥ ተሸጦ ማለቁ ተነግሯል። ናይክ የንግድ ምልክት ጥሰት በማለት ክስ መስርቷል። በኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) ለገበያ የቀረበው ይህ ጥቁሩና ቀይ ጫማ አርብ ዕለት ከራፐር ሊል ናስ ኤክስ ከለቀቀው "ኮል ሚ ባይ ዩር ኔም" ከሚሰኘው የሙዘቃ ሥራ ጋር ተገጣጥሟል። በሙዚቃ ቪዲዮው ላይ ራፐሩ ከመንግሥተ ሰማያት ወደ ሲኦል ይህንን ጫማ ተጫምቶ ተንሸራትቶ ሲወርድ ይታያል። በሙዚቃ ቪዲዮ ላይ የቀረበው ምሰላ እና ጫማው ላይ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ከቁጥር 18 "ሰይጣንን ከሰማይ እንደመብረቅ ሲወድቅ አየሁ" የሚለውን ጥቅስ ለማስታወስ ነው። እያንዳንዱ ጫማ የናይኪን ሶል የያዘ ሲሆን 60 ኪዮቢክ ሴንቲሜትር ቀይ ቀለም እና ከጥበብ ሥራዎችን ከሚሰበስበው ድርጅት አባላት የተወሰደ ጠብታ የሰው ደም አለበት። የስፖርት ጫማ አምራቹ ናይኪ ኒውዮርክ ለሚገኝ ፍርድ ቤት ባስገባው ክስ ላይ ይህንን ተመሳስሎ የተሰራ 'የሰይጣን ጫማ' እንዲመረት አልፈቀድኩም ብሏል። ናይኪ ለችሎቱ ኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) ጫማውን መሸጥ እንዲታገድ እንዲሁም ዝነኛ የሆነውን የንግድ ምልክታቸውን እንዳይጠቀም እንዲከለከል ጠይቋል። ግዙፉ ጫማ አምራቹ በክሱ ላይ"ኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) እና ፈቃድ ያላገኘው የሴጣን ጫማው ግርታን፣ ናይኪን ከኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) ጋር የተሳሳተ ዝምድና እንዲፈጠር ያደርጋሉ" ብሏል ። የኤምኤስሲኤችኤፍ (MSCHF) ሰይጣን ጫማ ለገበያ ከቀረበ በኋላ ናይኪ ምርቱን አጽድቆ ለገበያ ያቀረበው የመሰላቸው ደንበኞች የናይኪን ምርት ላለመግዛት ዘመቻ መክፈታቸውን በመጥቀስ ግርታ መኖሩን ማሳያ መሆኑን አመልክቷል። ወግ አጥባቂ የሆኑ አሜሪካውያን ራፐሩን እና ጫማውን በመቃወም በትዊተር ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።
news-56937339
https://www.bbc.com/amharic/news-56937339
የትንሳዔ ገበያ፡ በወሊሶ አካባቢ 115 ሺህ ብር የተገዛው በሬ
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው ለትንሳኤ በዓል በየአካባቢው ለአውደ ዓመት የሚቀርቡ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ሞቅ ባሉ የግብይት ስፍራዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ።
በዚህም ሁሉም እንደ አቅሙ እና ፍላጎቱ ይሸምታል። በዓልን በዓል ከሚያስመስሉ ነገሮች መካከል ደግሞ አንዱ የገበያው ድባብ ነው። ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቄጤማ፣ ቅቤ፣ ፍየል፣ በግ፣ በሬው ገበያውን በስፋት ይቆጣጠሩታል። ሸማችና ሻጭ በዋጋ ክርክር ይወዛገባሉ። የከተሞች ዋና መንገዶች በእርድ እንስሳት፤ በሰው ትርምስ ይሞላሉ። በዚህ ሁሉ መካከል አንዱ ሸማች ሌላኛውን የገበያውን ውሎ ይጠይቃል። መቼም ቢሆን "ርካሽ ነው" የሚል ወሬ ከገበያተኛ አይሰማም። እኛም ከሰሞኑ አንድ በሬ በ115 ሺህ ብር ስለመሸጡ ሰምተናል። 115 ሺህ ብር አውጥተው ይሄን ግዙፍ ሰንጋ የገዙት ሰው ደግሞ አቶ አሸብር ናቸው። አቶ አሸብር ጎሳ ባልቻ የከብት ነጋዴ ናቸው። ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወሊሶ አካባቢ በሚገኝ የከብት ገበያ ከቀናት በፊት በሬውን በ115ሺህ ብር መግዛታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አሸብር 115 ሺህ ብር ስለወጣበት በሬ ምን አሉ? "በሬው ትልቅ ነው። ሁለት ዓመት አካባቢ ነው የተቀለበው። በሬውን የገዛሁት ከገበሬ ነው። ሻጩ ሦስት ዓመት ሲቀልበው እንደነበር ነግሮኛል" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እሳቸው የተፍኪ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በሬውን የገዙት ደግሞ ኢሉ ወረዳ ተጂ ውስጥ ነው። "እኔ የከብት ነጋዴ ነኝ። ለሥጋ ቤት ወይም በበዓሉ ሰሞን ዝግጅት ላላቸው ወይም ሆቴል ለሚያስመርቁ ሰዎች ለመሸጥ ነው ያሰብኩት። ያው እንደ ገበያው ሁኔታ ሆኖ እስከ 3ሺህም 2ሺህም አትርፌ እሸጣለሁ። እንደ ገበያው ነው።" ብለዋል። ለዚህ ከብት 115ሺህ ብር አውጥተው የገዙት በገበያው ሁኔታ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አሸብር፤ "ፋጉሎ እኮ እስከ 3ሺህ ብር እያወጡ ነው የሚገዛው። ይሄ በሬ ሁለት እና በሦስት ዓመት ሲቀለብ ስንት ኩንታል ጨርሷል የሚለውን ማሰብ ነው።" ሲሉ ዋጋው ያን ያህል እንዳልተጋነነ በስሌት አስረድተዋል። እንዲህ በውድ ዋጋ የተሸጠ በሬ ከዚህ በፊት ያውቁ ይሆን? እኔ እስከማውቀው በትልቅ ብር የተሸጠው በሬ ይሄ ነው። ትልቁ ይሄ ነው። ከዚህ በታች ያለው 85ሺህ፣ 75ሺህ፣ 65ሺህ የሚሸጥ አለ። በግ ራሱ 12ሺህ ብር ተሽጧል። ዳዎ ወረዳ ቡሳ ከተማ አንድ በግ 12 ሺህ ብር ተሽጧል። በሌሎች አካባቢስ ከፍተኛው የከብት ዋጋ ስንት ይሆን? መልካም በዓል!
news-55036276
https://www.bbc.com/amharic/news-55036276
የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት፡ ሁለት አፍሪካዊያን ለዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ታጩ
የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እና ኬንያዊቷ ፔረስ ጀፕቺርቺር ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።
የዓለም አትሌቲክስ ማክሰኞ እለት በአስሩ ዝርዝር ውስጥ ገብተው ከነበሩ አትሌቶች አምስት ለመጨረሻው ዙር መመረጣቸውን አስታውቋል። ሌሎች ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አስሩ ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ አትሌቶች ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ፣ ኬንያዊያኖቹ ዶ ፌዝ ኪፕየጎን እና ሔለን ኦቢሪ ናቸው። ለ ሌሎቹ በአምስቱ ዝርዝር ውስጥ መካተት ያልቻሉት አትሌቶች ደግሞ የኔዘርላንዷ ፌምኬ ቦል እና እንግሊዟ ላውራ ሙር ናቸው። የዘንድሮው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በቨርቹዋል [ኢንተርኔት] በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 የሚካሄድ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት 5ቱ እጩዎች ለተሰንበት ግደይ በ5000 ሜትር በ14፡06፡62 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች። ቫሌንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰከንዶች ነበር። በሞናኮ በተካሄደው በዋንዳ ዲያመንድ ሊግም 5000 ሜትር ሩጫ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች። ሲፋን ሐሰን 18,930 ሜትር በአንድ ሰዓት ጊዜ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ይዛለች። በ10 ሺህ ሜትር በ29፡36፡67 በማጠናቀቅም የአውሮፓ ክብረወሰን ያስመዘገበች ሲሆን በታሪክ አራተኛዋ ፈጣኗ ሯጭ ተብላለች። የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ናት። በሴቶች ውድድር 1፡ 05፡34 እና 1፡ 05፡ 16 ሰዓት በመግባት የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ሁለት ጊዜ ሰብራለች። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በተደረጉ አራት የርዝመት ዝላይ ውድድሮች አሸንፋለች። በቤት ውስጥ በተካሄደ የርዝመት ዝላይ ውድድር 15.43 ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች። በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች አሸንፋለች። በዓለም መሪነት 100 ሜትር በ10.85 ሰከንድ ሮጣለች። ከእነዚህ እጩዎች አሸናፊውን ለመለየት ሦስት የድምፅ አሰጣጥ መንገዶች አሉ። የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት እና የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፃቸውን በኢሜይል የሚሰጡ ሲሆን አድናቂዎቻቸው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ድምፅ ይሰጣሉ። ከአጠቃላይ ድምፁ የምክር ቤቱ ድምፅ 50 በመቶ ይይዛል። የአትሌቲክስ ቤተሰቦችና የሕዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ይይዛሉ።
news-55631981
https://www.bbc.com/amharic/news-55631981
ዐቃቤ ሕግ በእነአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ታዘዘ
የአቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ተከሳሾች ጉዳይ ዛሬ [ማክሰኞ] የተመለከተው ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጎ ዐቃቤ ሕግ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ አዘዘ።
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ ሃምዛ አዳነ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጓል። ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ክሳቸውን ለማየት ሥልጣን እንደሌለውና ወንጀሉ ተፈፀመ የተባለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሆኑ እንዲሁም ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ጋር ያላትን ልዩ ጥቅም በመጥቀስ ክሳቸው ወደ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሄዶ መታየት አንዳለበት መከላከያ አቅርበው ነበር። ከዚህም በተጨማሪም የአስተዳዳር አዋጅና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እንዲሁም የቴሌኮም ማጭበርበርን አስመልክቶ ተከሳሾች መከላከያ አቅርበው ነበር። ክሳቸው ሕገ መንግሥቱ የሚሰጠውን እኩልነት በጣሰ መልኩ ነው የቀረበው በሚል በመከላከያ ላይ ያካተቱ ሲሆን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለዚህም ክስ መልስ ሰጥቶ ነበር። በፍርድ ቤቱ ውሎ እነአቶ ጃዋር መሐመድም ያቀረቡት እነዚህ የክስ መከላከያዎች በችሎቱ በሙሉ ድምጽ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክሶቹ ላይ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዐቃቤ ሕግም ክሶቹን አስተካክሎ እንዲያቀርብ የአንድ ወር ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው ግን ተቃውመውታል። የሕግ የበላይነት ማስከበር፣ ለተከሳሾች ፍትሕ መስጠት፣ ተጎጂዎች ካሳ እንዲያገኙ ከታሰበም ጉዳዩ በፍጥነት እንዲታይ የተናገሩት ጠበቆች የተሰጠው ቀጠሮ እንዲያጥር ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከተከሳሾች ውስጥ "መንግሥት ያሰረን ወንጀል ሰርተን ሳይሆን ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ነው" ያሉት አቶ ሐምዛ አዳነ የቀጠሮው ጊዜ እንዲያጥር ጠይቀዋል። ፍርድቤቱም የሁለቱን ወገን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለጥር 14/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ችሎት ላይ ምን ተባለ? አለብን ካሉት የደኅንነት ስጋት በመነሳት ባሉበት ቦታ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው የጠየቁና ባለፉት ሦስት ቀጠሮዎች ያልተገኙት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ በዛሬው ችሎት ላይ ተገኝተዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ እንዳሳዘናቸው አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሐመድ ተናግረዋል። "እኛ አንቀርብም ያልን በማስመሰል 'በግድ ፍርድ ቤት ይቅረቡ' ተብሎ ትዕዛዝ መውጣቱ በጣም አሳዝኖናል፤ በዚህም መሰረት ለደኅንነታችን እየሰጋን ነው የምንመጣው" በማለት ወደ ፍርድ ቤት የመጡበትን ሁኔታ ገልጸዋል። አቶ በቀለ ገርባ ከደኅንነታቸው በተጨማሪ የሚደርስባቸው ጥቃት አገሪቷን ችግር ውስጥ እንደሚከታት በመናገር፣ ለሚያጋጥመው ችግር መንግሥትና ችሎቱ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድም፣ አገሪቷ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ በመግለጽ "አንዳች ነገር ቢደርስብን፣ በዚህ ምክንያት አገሪቷ ላይ ችግር ቢመጣ፣ ሸኔ ሻዕብያ እያሉ ምክንያት መስጠት አያዋጣም። የምትጠየቁት እናንተ የሕግ ባለመያዎችና መንግሥት ነው" ብለዋል። ዳኞቹ በበኩላቸው ትዕዛዝ በሚሰጡበት ወቅት ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል እምነት ኖሯቸው መሆኑን በመጥቀስ "የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አታከብሩም የሚል እምነት የለንም። በግድ መቅረብ አለባቸው የሚለውን ትዕዛዝ የሰጠነው እንደ አማራጭ ነው" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እነአቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን ክስ በስፋት ማየታቸውን በመናገር፣ የደኅንነታችሁን ሁኔታ እንከታተላለን። ወደዚህ የምትመጡበትንም ሁኔታ እንከታተላለን ብለዋል። በሌላ በኩል የመንግሥት ሚዲያዎችና አንዳንድ የግል ሚዲያዎች ዘገባቸው ወገንተኝነት እንዳለበት ቅሬታ ያቀረቡት ደግሞ አቶ ደጀኔ ጣፋ ሲሆኑ፣ የመገናኛ ብዙሃኑ የፍርድ ቤት ውሎን በአግባቡ አንዲያቀርቡ "ይህንን ፍርድ ቤቱ እንዲያሳስብልን" በማለት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሚዲያዎቹ ችሎቱ ላይ የተባለውንና የችሎቱን ውሎ ብቻ እንዲዘግቡ አሳስቧል። የአቶ ጃዋርና የ24 ሰዎች የክስ መዝገብ በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሰዎች የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የቴሌኮም ወንጀልን ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የአስተዳደርና የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅንና የአገሪቱን ወንጀል ሕግ የተለያዩ አንቀጾችን በመተላለፍ ነው የተከሰሱት። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሎና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነአቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ከዚያም በኋላ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ክስ መክፈቱ ይታወሳል። ይኹን እንጂ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ለደኅንነታችን እንሰጋለን ብለው ሲናገሩ ነበር። ስለዚህም ይህን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሚገኙበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።
news-47729876
https://www.bbc.com/amharic/news-47729876
የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ?
የወንዶች የእርግዝና መከላከያ የመጀመሪያ የሙከራ ሂደቱን ማለፉን ባለሙያዎች ተናገሩ። በየቀኑ የሚወሰደው የመከላከያ አይነት ወንዶች የዘር ፈሳሽ እንዳያመነጩ የሚያደርግ ነው።
ይህም አሁን ላይ ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉት ኮንዶምና ቫዝክቶሚ በተጨማሪ ሌላ አማራጭ ነው ተብሏል። ነገር ግን ሃኪሞች እንደሚሉት ምርቱን በተሟላ ሁኔታ አጠናቅቆ ለገበያ ለማቅረብ ምናልባትም አስርት ዓመታትን ሊጠይቅ ይችላል። ለምን እስካሁን አልነበረም? የሴቶች የእርግዝና መከላከያ የተጀመረው ከ50 ዓመታት በፊት በሀገረ እንግሊዝ ነበር። ምነው ታዲያ የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ ለመስራት ለምን ይህን ያህል ጊዜ ወሰደ? የሚለው ዋናው ጥያቄ ነው። አንዳንዶቹ ይህ ያልሆነው ምናልባትም ወንዶች ስለማይፈልጉ ነው የሚሉ ቢኖሩም በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ የተጠየቁ ወንዶች ቢኖር ኖሮ መከላከያውን እንጠቀም ነበር ብለዋል። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ሌላኛው ነገር ደግሞ ሴቶች ራሳቸው ወንድ የእርግዝና መከላከያ ወስጃለሁ ቢላቸው ያምኑ ይሆን? ወይ የሚለውም ነው። ሩስኪን ዪኒቨርሲቲ በ2011 እንግሊዝ ውስጥ ባደረገው ጥናት መሰረት ከ134 ሴቶች 70 የሚሆኑት ወንድ የፍቅር ጓደኞቻቸው የእርግዝና መከላከያ መውሰዳቸውን ይዘነጋሉ ብለው ይሰጋሉ። የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ በወሲባዊ ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳይኖረው መጠንቀቅ ያስፈልግ ስለነበር ነው ጉዳዩ ጊዜ የወሰደው የሚል አስተያየት የሰነዘሩም አሉ። የወንድ የዘር ፈሳሽ ማመንጨትን በተመለከተ መካን ያልሆነ ወንድ በሆርሞኖች አማካኝነት እየታገዘ በተከታታይ የዘር ፈሳሽ ያመነጫል። የእርግዝና መከላከያ ይህን ሂደት ሊያዛባ ይችላል ውይ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ግን አሁን በኤልኤ ባዮሜድ እና በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው ጥናት ውጤታማ ነው። በ40 ወንዶች ላይ የመጀመሪያ ሙከራ ተደርጎ ያለችግር ውጤታማ መሆኑን ኒውኦርሊንስ ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ተገልጿል። • «የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ከሙከራው በኋላ የተወሰኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ተገኝተዋል። የእርግዝና መከላከያን ከወሰዱት ወንዶች መካከል አምስቱ የወሲብ አቅማቸው ቀንሷል፤ ሁለቱ ደግሞ የብልት መቆም ችግር አጋጥሟቸዋል። በአጠቃላይ ግን የወሲብ ተነሳሽነት ላይ ችግር አልተገኘም። የጥናቱ መሪ ክሪስቲና ዋንግና ጓደኞቿ "ሙከራችን የሚያሳየው ሁለቱን ሆርሞኖች አንድ ሥራ ላይ እንዲተባበሩ ማድረግን ነው። የዘር ፈሳሽን ማመንጨት ይቀንሳል፤ በአንጻሩ ለወሲብ ያለው ተነሳሽነት እንዳለ ይቀጥላል" ብለዋል። የስሜት መዘበራረቅን በተመለከተ ሌሎች ሳይንቲስቶች በየወሩ የሚወሰድ የእርግዝና መከላከያ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ። ነገር ግን የመጀመሪያውን ዙር ካጠናቀቁ በኋላ ሁለተኛውን ሙከራ አቁመዋል። ምክንያታቸው ደግሞ የስሜት መዘበራረቅና ድብርትን ያመጣል የሚል ነው። በጥናታቸውም የዘር ፈሳሽን እንቅስቃሴ የሚገድብ ምናልባትም ከወንድ ብልት እንዳይወጣም ሊያደርግ ይችላል ብለዋል። እናም ቫዛልጀል (vasalgel) የተሰኘ በሁለቱ የወንድ የዘር ፍሬዎች የሚወጋና የዘር ፈሳሽን ከግራና ቀኝ ፍሬዎች ወደ ብልት የሚወስድ ህክምና ተጀምሯል። ነገር ግን እስካሁን ትግበራው በእንስሳት ላይ ብቻ የተገደበ ቢሆንም ውጤታማ በመሆኑ ተመራማሪዎች ሰው ላይ ለመጀመር ተዘጋጅተዋል። የገበያ ሁኔታን በተመለከተ ፕሮፌሰር ሪቻርድ አንደርሰን ይህን ምርምር በእንግሊዝ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ ናቸው።እሳቸው እንደሚሉት ፋርማሲዎች ይህን የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ለመሸጥ ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው ምክንያታቸው ደግሞ ወንዶችና ሴት ጓደኞቻቸው በዚህ ጉዳይ ላይ እምነት የላቸውም ሚል ነው። "ያለውን የገበያ ሁኔታ በደንብ ለማሳመን የተደረገ ጥረት ያለ አይመስለኝም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ተመራማሪዎቹ በእርዳታና በምርምር በጀት ላይ የተንጠለጠለ ሥራ ነው የሚሰሩት። ምክንያቱም በዘርፉ ያለው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ ነው። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና በሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የአንድሮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት አለን ፒሴይ "እስካሁን የወንዶች የእርግዝና መከላከያ በደንብ አልተሰራበትም ስለዚህ አዳዲስ ሥራዎችን መስራት ይኖርብናል" ብለዋል። ቁልፉ ጥያቄ ፋርማሲዎች በበቂ ሁኔታ ያከፋፍሉታል ወይ? የሚለው ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እሳቸው እንደሚሉት እስካሁን ፋርማሲዎች ለዚህ ጉዳይ ፍላጎት አያሳዩም ፤ ትኩረታቸውም ለቢዝነሳቸው ነው።
news-54179744
https://www.bbc.com/amharic/news-54179744
መዓዛ መንግሥቴ፡ 'ቡከር' በተባለው ዓለም አቀፍ ሽልማት የታጩት አፍሪካዊ ሴት ደራሲዎች
'ቡከር ፕራይዝ' በቀድሞ ስሙ 'ቡከር ሚክኮኔል ፕራይዝ' እና 'ዘ ማን ቡከር ፕራይዝ' በመባል ይታወቃል።
ዓለም አቀፍ የሽልማት ድርጅቱ በየዓመቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ እና በዩናይትድ ኪንግደም ወይም በአየርላንድ የታተሙ ወጥ የልብ-ወለድ መፅሐፍትን አወዳድሮ ይሸልማል። የሽልማት ድርጅቱ የተቋቋመው በጎርጎሮሳዊያኑ 1969 ሲሆን የመጀመሪያውን ሽልማት የሰጠውም በዚያው ዓመት ነበር። ላለፉት ከ50 ዓመታት በላይም ይህንን ሲያደርግ ነው የቆየው። በዘንድሮው ዓመትም ሁለት ሴት አፍሪካዊያን ደራሲዎች ለሽልማቱ ታጭተዋል። በትውልድ ኢትዮጵያዊ- አሜሪካዊት መዓዛ መንግሥቴ አንዷ ናት። 'ዘ ሻዶው ኪንግ' [The Shadow king] በሚል ርዕስ የታተመው መፅሐፏ ነው ለሽልማቱ የታጨው። መጽሐፉ መቼቱን ያደረገው የሁለተኛው አለም ጦርነት ጅማሮ የሚባለውና ፋሽስት ጣልያን ኢትዯጵያን በወረረችበት ወቅት ነው። መፅሀፉ በጦርነቱ ውስጥ ሴት የነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ ተጋድሎ ቢያደርጉም ምን ያህል ከታሪክ መዝገብ እንደተፋቁ የሚዘክርና የነበራቸውንም ግዙፍ ሚና ያወጣ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ መዓዛ በጎርጎሮሳዊያኑ 2010 የወጣው 'ቢኒዝ ዘ ላየንስ ጌዝ' [Beneath the Lion's Gaze] በተሰኘው መጽሐፏ ጨምሮ በሌሎች ሥራዎቿ ትታወቃለች። በወቅቱም የጋርዲያን የአፍሪካ ምርጥ 10 መፅሐፍት ተርታ ተመድቧል። መዓዛ እጩ መሆኗን በሰማች ወቅት በትዊተር ገጿ ላይ "ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም። ኦ ፈጣሪየ!" ስትል ነበር ደስታዋን የገለፀችው። ለሽልማቱ ከታጩት 6 መጽሐፍት መካከል ለሽልማቱ የታጨው ሁለተኛው መጽሐፍ በዚምባብዌያዊቷ ደራሲ ጺጺ ዳንጋሬምባ ድርሰት ነው። መጽሐፏ ' ዚስ ሞርነብር ቦዲ' 'This Mournable Body' ይሰኛል። ከዚህ ቀደም ያወጣችውና ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈላት 'ነርቨስ ኮንዲሽንስ' ተከታይ ነው። ዚምባብዌ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣቷን ተከትሎ የመጣውን የድህረ-ቅኝ ግዛት ጭቆና፣ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት አገሪቱን ማሽመድመድና ካፒታሊዝም ጥምረት ምን ያህል መርዛማ እንደሆነም ያስቃኛል። መፅሀፉ 'ሾና' ቤተሰቦች ላይ የሚያጠነጥን ነው። የሾና ህዝብ በደቡባዊ የአፍሪካ አካባቢዎች ይኖራሉ። አሁን ላይ 10 ሚሊየን ገደማ ሾናዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተብሎ ይገመታል። አብዛኞቹ የሚኖሩት በዚምባብዌ ነው። ጺጺ ለሽልማቱ በመታጨቷ ደስታ እንደተሰማት በትዊተር ገጿ ላይ አጋርታለች። ደራሲ ፣ የተውኔት ፀሐፊ እና ፊልም ሰሪዋ ጺጺ፤ ይህን መጽሐፏን ከሁለት ዓመታት በፊት ቢቢሲ ዓለምን ከለወጡ 100 መጽሐፍት አንዱ አድርጎ መርጦት ነበር። ባለፈው ዓመት እንግሊዛዊ ናይጀሪያዊቷ ደራሲ ቤርናዲኔ ኢቫሪስቶል ሽልማቱን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ነበረች። ከዚህ ቀደም ናዲን ጎርዲመር፣ ጀም ኮትዜ እና ቤን ኦኪሪን ጨምሮ ሌሎችም የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል። ለዚህ ዓመቱ ሽልማት እጩ የሆኑት ሌሎቹ መፅሐፍት፦ •በዲያኔ ኩክ የተፃፈው 'ዘ ኒው ወይልደርነስ' [The New Wilderness] •በአቭኒ ዶሽ የተፃፈው 'በርንት ሹገር' [Burnt Sugar] •በብራንደን ቴይለር 'ሪል ላይፍ' [Real Life] •በዳግላስ ስቱዋርት የተፃፈው 'ሹጌ ቤን' [Shuggie Bain] አሸናፊዎቹ 64 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል። በእንግሊዝኛ የተፃፈ እና በዩናይትድ ኪንግደም የታተመ ማንኛውም መፅሐፍ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል።
news-51479249
https://www.bbc.com/amharic/news-51479249
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበተነ
ባለፈው ወር ላይ ለቀናት ሲካሄድ በነበረው ውይይት ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሦስቱ አገራት ስብሰባ ያለስምምነት ተጠናቀቀ።
የሦስቱ አገራት የውሃ ሚንስትሮች በግድቡ ዙሪያ በካርቱም ሱዳን ታህሳስ 11 በተገናኙበት ወቅት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የካቲት 4 እና 5 2012 ዋሽንግተን ረቂቅ ሰነድ ለማዘጋጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት "በዚህኛውም ዙር ሳይቋጭ" ተጠናቋል። የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በታዛቢነት ይሳተፉበታል የተባለውን ይህን ድርድር ያለውጤት እንዲያበቃ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ አምባሳደር ፍጹም ያሉት ነገር የለም። ውይይቱ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረ ነው። ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም በግብጽ በኩል ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው ብለዋል። በሱዳን በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የቆየው የህዳሴ ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ ወደ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ መሄዱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ። እኚህ ምንጫችን ሱዳን የአቋም ለውጥ አድርጋ ከግብጽ ጋር መወገኗን እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለግብጽ መወገናቸውን በመጠቆም አሁን ላይ ጉዳዩ "4 ለ 1" ሆኗል በማለት ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በግድቡ ዙሪያ እጃቸውን እንዲያስገቡ መፈቀዱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ እንድትከፍል እያደረጋት እንደሆነ እኚህ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ ተገለፀ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከሁለት ቀናት በፊት ተደራዳሪ ቡድኑ ''በብዙ ጉዳዮች ላይ የመከረ ቢሆንም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ ማዘጋጀት አለመቻሉ ታይቷል'' ብለው ነበር። ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት የሰነዱ አብዛኛው ክፍል የቀረበው በአሜሪካ በመሆኑ፤ ትኩረቱም ስለ ግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ በመሆን ፈንታ፤ "ማን ምን ያህል የውሃ ድርሻ ይኑረው? የሚለው ላይ የሚያተኩር በመሆኑ" ከስምምነት መድረስ እንዳልተቻለ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት እኚህ ባለሙያ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም በግድቡ ጉዳይ የኢትዮጵያ የህግ አርቃቂ ቡድን አሁንም አሜሪካ እንደሚገኝ በማስታወስ፤ በውሃ ክፍፍል ላይ ለመነጋገር እንደ አገር ዝግጁ አይደለንም፤ የድርድሩ አላማም ይህ አይደለም ብለውናል። እሳቸው እንደሚሉት ከግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ በድርቅ፣ በረዥም ጊዜ ድርቅ እና በተከታታይ ድርቅ በሚሉት ሰነዱ ላይ በሰፈሩት ቃላቶች ትርጓሜ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ስብሰባ መከልከል በጅማ ስለዚህም የኢትዮጵያ የህግ አርቃቂች በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ሰነዱ ላይ የሰፈሩ በርካታ ነጥቦችን በጥያቄ ምልክት ውስጥ ለማስቀመጥ ተገድደዋል። "ትልቁ ነገር ሰነዱ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሊያተኩር አይገባም ነበር። ወደ አሜሪካ የሄደው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ቡድንም በዚህ ላይ [የውሃ ድርሻ ክፍፍል] ለመነጋገር ስልጣን አልተሰጠውም። ስለ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ብቻ ሳይሆን ከአስሩም የተፋሰሱ አገራት ጋር ነው መነጋገር ያለባት" ይላሉ። ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍን ፈርማ ያፀደቀች አገር መሆኗን እና ይህ ስምምነት ሳይጣስ ሁሉም የተፋሰሱ አገራት ባሉበት መነጋገር እንደሚገባት ያስታውሳሉ። ታዛቢ ወደ አደራዳሪ ሶስቱ አገራት በሚያደርጉት ድርድር ላይ የሶስተኛ አካል ጣልቃ መግባት ይኖርበታል ብላ ሃሳብ ያቀረበችው ግብጽ መሆኗ ይታወቃል። ፕሬዝደንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ታሸማግለን ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውም የሚታወስ ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል ገልጻ ነበር። ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጠችው በሶስቱ አገራት የተደረሱ ''አበረታች'' ስምምነቶችን ያፈርሳል እንዲሁም ሶስቱ አገራት እአአ 2015 ላይ የፈረሙት የመርህ ስምምነትንም ይጥሳል የሚል ነበር። • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? የኋላ ኋላ ግን ዓለም ባንክ እና አሜሪካ በሶስቱ አገራት መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የታዛቢነት ሚና ኖሯቸው ይሳተፋሉ ሲባል ቆየ። የኢትዮጵያ መንግሥትም አሜሪካና አለም ባንክ በድርድሩ ታዛቢዎች እንጂ አደራዳሪ አይደሉም ብሎ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ላይ አደራዳሪነታቸው አጠያያቂ አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጥር 25 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ የአሜሪካ መንግሥት እና ዓለም ባንክ 'ለማደራደር' ጥያቄ አቅርበው 'ሲያደራድሩ' ቆይተዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ "ለአሜሪካ እና ዓለም ባንክ ምስጋና ማቅረብ የሚያስፈልገው፤ በሚያውቁን እና አቅም ባላቸው ፊት ስንነጋገር መስማማት ጀምረናል" ሲሉም ተደምጠዋል። እኚህ የቢቢሲ ምንጭ እንደሚሉትም የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ በታዛቢነት ተቀመጡ፣ ካይሮ ላይ በታዛቢነት ቀጥለው ሱዳን ካርቱም ላይ ግን አደራዳሪ ሆኑ። ከዚያም ተመልሰው አዲስ አበባ ላይ አደራዳሪ መሆናቸውን ቀጠሉ። "አሁን እኮ ዋሽንግተን ላይ የሕግ እና የቴክኒክ ቡድኑ ተገኝቶ፤ ሰነድ ቀርቦ ግልፅ ድርድር ነው እየተካሄደ ያለው" በማለት ያስረግጣሉ። እነዚህ አካላት ከታዛቢነት ራሳቸውን ወደ አደራዳሪነት ከማሸጋገራቸውም በላይ ኢትዮጵያ ላይ "ከፍተኛ ጫና ማሳደርና ማስፈራራትም ደረጃ ደርሰዋል" ይላሉ ባለሙያው። እርሳቸው እንደሚሉት አሜሪካና አለም ባንክ በኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች በኩል የሚነሱ ሃሳቦችን ለመቀበል በፍጽም ፍላጎት አያሳዩም። ይልቁንም እየተቀበሉ ያለው የግብፅና የሱዳንን ሃሳብ ብቻ ነው። በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለራሷ ጥቅም ስትል ከኢትዮጵያ ጎን ቆማ የነበረችው ሱዳን አቋሟን ቀይራ ከግብፅ ጎን መሰለፏንም ያረጋግጣሉ። እሳቸው እንደሚያብራሩት በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የምትፈልገው ሱዳን ይህን ፍላጎቷን ይዛ ስትመጣ አሜሪካ በበኩሏ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለች። • ‘በአስራ አራት ዓመቴ ስደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ነበር' ምናልባትም የሚሉት እኚህ ምንጭ ከትናንት በስቲያ እንደተሰማው የቀድሞውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ መሰጠት ሱዳን ያሟላችው አንድ ቅድመ ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ከግብፅ ጎን መቆም ሁለተኛው ቅድመ ሁኔታ ሲሆን ይህንንም ሱዳን እየፈፀመች ነው። "ሶስተኛ ወገን ማስገባት ካስከፈለው ከባድ ዋጋ አንዱ ይሄ ነው" በማለት ድርድሩ ለኢትዮጵያ አጣብቂኝ መንገድ ላይ እንዳለ ይገልፃሉ። አሜሪካ ለግብጽ ለምን ወገነች? ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሰላም ለብልጽግና [ፒስ ቱ ፕሮስፔሪቲ] የተሰኘውን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅዳቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ የትራምፕ እቅድ እየሩሳሌም ያልተከፋፈለች የእስራኤል መዲና ትሆናለች ከማለቱም ባሻገር ፍሌስጤማውያን እና የተቀረው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሕገ-ወጥ የሚለውን የእስራኤልን የዌስት ባንክ ሰፈራ እውቅና ይሰጣል። ይህ የትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ በፍልስጤማውያን ወዲያው ውድቅ የተደረገ ሲሆን እንደ ኢራቅ እና ሶሪያ ያሉ የሰላም እቅዱን በይፋ ከተቃወሙት አገራት መካከል ይገኙበታል። • ''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቀላል የማይባሉ የአረቡ ዓለም አገራትም የትራምፕን የሰላም እቅድ በጥርጣሬ ዕይን መመልከታቸው አልቀረም። ታዲያ በአረቡ ዓለም ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነችው ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ግብጽ፤ የትራምፕ ዕቅድ በአረቡ አገራት ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍተኛ የሆነ የራሷን አስተዋጽኦ ልታበረክት ትችላለች። እኚህ የቢቢሲ ምንጭ እንደሚሉት፤ የፕሬዝደንት ትራምፕ እቅድ እንዲሰምር ግብጽ የበኩሏን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ልታበረክት ትችላለች። ሱዳን እና እስራኤል ለእስራኤል እውቅና ከማይሰጡ የአረብ ሊግ አባል አገራት መካከል ሱዳን አንዷ እና ተጠቃሽ ነች። ሁለቱ አገራት ይህ ነው የሚባል ፖለቲካዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ግነኙነት የላቸውም። እአአ 1967 የአረብ አገራት ያካሄዱት ታሪካዊ ስብሰባ ይታወሳል። በሱዳን ካርቱም በተካሄደው በዚህ ስብሰባ የአረብ አገራቱ 'ሶስቱ እምቢታዎች' ["Three No's"] ተብሎ የሚታወቀውን በእስራኤል ላይ ያላቸውን አቋም አንጸባርቀው ነበር። ለእስራኤል እውቅና አለመስጠት፣ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት አለመድረስ እና ከእስራኤል ጋር አለመደራደር። ዛሬም ድረስ በርካታ የአረብ ሊግ አባል አገራት ለእስራኤል እውቅና አልሰጡም። ከእነዚህም መካከል ሱዳን አንዷ ነች። ከአንድ ሳምንት በፊት ግን ታሪካዊ በተባለ ሁኔታ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር መንግሥት ካውንስል ሰብሳቢ አብድል ፈታህ አል-ቡረሃን በኡጋንዳ ኢንቲቤ ተገናኝተው ነበር። • "የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕ/ት ኢሳያስ ሁለቱ መሪዎች ለሰዓታት ከተነጋገሩ በኋላ ግንኙነት ለመጀመር መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ኔታኒያሁ ከውይይቱ በኋላ ሱዳን አዲስ እና አዎንታዊ ወደሆነ አቅጣጫ እያመራች ነው ማለታቸውን የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የእስራኤል ወዳጅ የሆኑት ትራምፕ፤ የኔታኒያሁ አገር በመካከለኛው ምስራቅ እና በአረብ ሊግ አባል አገራት ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራት ይሻሉ። ሱዳን ይህንን የአሜሪካንን ፍላጎትን ማሳካት የምትችል ከሆነ በግድቡ ድርድር ዙሪያ ያላት ፍላጎት ሊጠበቅላት እንደሚችል ይታመናል። ለቢቢሲ ምልከታቸውን የሰጡት ባለሙያ እንደሚሉት ደግሞ፤ በግድቡ ድርድር ዙሪያ ሱዳን ከግብጽ ጋር አብራ የምትቆም ከሆነ፤ ተጥሎባት የሚገኘውን ማዕቀብ ሊነሳላት እንደሚችል ይጠቁማሉ። የሱዳን ከግብጽ ጎን መቆም ማለት፤ የትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ እንዲተገበር፣ የአረብ ሊግ አባላት በእስራኤል ላይ ያላቸውን አቋም ማለሳለስ ማለት ሊሆን ይችላል ይላሉ። አሜሪካ ዋና ዓላማዋ ሶሰቱን አገራት ማስማማትም ሳይሆን የራሷን እና የእስራኤልን ፍላጎት ማሳካት ዋነኛ ግቧ መሆኑን ይጠቁማሉ። በዚህ ከባድ ድርድር ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል መታለፍ የሌለበት መስመር የቱ ነው? ለባለሙያው ያቀረብነው ጥያቄ ነበር። "እየተሄደበት ያለው መንገድ በሙሉ አደገኛ ነው" በማለት ድሮም ስለ ውሃ ክፍፍል ኢትዮጵያ ለብቻዋ ከግብፅና ሱዳን ጋር ድርድር አላደርግም ያለችው ለሁለት ጫና ያሳድሩብኛል በሚል ፍራቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። "አሁን ግን ብሶ አራት ለአንድ ሆኗል" በማለት ግብፅ፣ ሱዳን፣ አሜሪካና አለም ባንክ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ ደግሞ በሌላ ወገን አጣብቂኝ ውስጥ መውደቋን ያስረዳሉ። በጫና ውስጥ የሚደረግ ስምምነት አለም አቀፍ ተቀባይነት እንደማይኖረው፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስምምነት ላይ መድረስ ቢቻል እንኳ በኢትዮጵያ በኩል በቀጣይ የሚመጡ መንግሥታትና ትውልድ የሚቀበሉት ነገር ስለማይሆን ነገሩ ወደ ፊት አገራቱን የባሰ ግጭት ውስጥ የሚከት ሊሆን እንደሚችልም ምልከታቸውን ያስቀምጣሉ ባለሙያው። • የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ በኩል አሁን መወሰድ ያለበት እርምጃ ምን መሆን አለበት? ለሚለው ጥያቄያችን "አሁን ያለውን ሂደት መቆም ያለበት ይመስለኛል። ወደ ኋላ ተመልሶ ተመካክሮና ነገሮችን አጢኖ ሁሉንም ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ነገር ላይ መስራት [የተሻለ] ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ነገሮች በ2015 አገራቱ በተፈረሙት 'ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንስፕልስ' ስምምነት መሰረት መቀጠል አለባቸው ይላሉ። ስምምነቱ አገራቱ መመሪያ አዘጋጅተው በግድቡ ውሃ አያያዝና አለቃቅ ላይ ከስምምነት መድረስ እንደሚያዋጣ ያትታል። ከዚያ አንፃር አሁን እየተደረገ ያለው ድርድር ትኩረቱን ስቶ ከግድቡ ውሃ አያያዝና አለቃቀቅ ወደ የውሃ ድርሻ ክፍፍል የሄደ እንደሆነ ያስረግጣሉ ባለሙያው። የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በግድቡ ዙሪያ ለመራደር በካርቱም ሱዳን ታህሳስ 11 በተከናኙበት ወቅት የኢትዮጵያ መሪዎች ምን ይላሉ? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙበት ወቅት ሶስቱ አገራት የመጨረሻ የተባለለትን ስምምነት ለመፈረም ከተዘጋጁ በኋላ፤ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት ዝርዝር ዕይታ እና ውይይት ስለሚያስፈልገው እንዳይፈረም የሚል አቅጣጫ በመስጠታቸው ፊርማው እንዲዘገይ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ ፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በስልክ ተገናኝተው ረዘም ላለ ጊዜ መነጋገራቸውን ተናግረዋል። • ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእርሳቸው በፊት አገሪቱን ይመሩ የነበሩ መሪዎች ጋርም ተመሳሳይ አቋም እንደነበራቸው በማስታወስ፤ የድርድሩ ውጤት ኢትዮጵያን የሚጎዳ እንዳይሆን እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያን ወክለው የሚደራደሩት የውሃ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለም ከሁለት ቀናት በፊት "የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፍላጎት ባማከለ መልኩ ጠንክረን እንሰራለን" ብለዋል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋም፤ ኢትዮጵያ "በአባይ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት አትፈጽምም!" ብለዋል። የግብጹ አህራም ኦንላይን በበኩሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እንዳይፈረም አድርጌያለሁ ያሉትን ስምምነት ግብጽ መፈረሟን በወቅቱ ዘግቦ ነበር። አህራም የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ፊርማቸውን ከማኖራቸው በፊት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ውይይት ማድረግን መርጠዋል ያለ ሲሆን፤ ሱዳንም በተመሳሳይ መልኩ ስምምነቱን እንዳልፈረመች ዘግቧል። "በግድቡ አሞላል እና ውሃ አለቃቀቅ ላይ በካርቱም እና በካይሮ መካከል ጉልህ ልዩነት የለም" ሲል አህራም ጨምሮ ዘግቧል።
41411130
https://www.bbc.com/amharic/41411130
ቀጣዩ ኢትዮጵያዊ የማራቶን ባለተስፋ ጉዬ አዶላ ማነው?
በቅርቡ በርሊን ማራቶን በተደረገው ውድድር ላይ የጉዬ አዶላ ስም አልተጠቀሰም። ቀጣዩን የዓለም አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ሬከርድ የሚሰብረው ማን ይሆን የሚለው መላ ምት ውስጥ ታላላቆቹ ሯጮች እነ ቀነኒሳ በቀለ፣ ዊልሰን ኪፕሳንግና ኢሉድ ኪፕቾጌ ነበሩ ግምት የተሰጣቸው።
ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸንፎ በገባበት ወቅት ጉዬ እንኳን የማሸነፍ ግምት ሊሰጠው ይቅርና የማራቶን ውድድር ላይ ተወዳድሮ አያውቅም። ውድድሩ ሲያልቅ ግን ብዙዎች ስሙን አንስተውታል። ቀነኒሳ በቀለና ዊልሰን ኪፕሳንግ ሩጫውን መጨረስ ቢሳናቸውም፤ ጉዬ አዶላ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ እልህ በሚያስጨርስ ሁኔታ ተወዳድሮ በጥቂት ሰከንዶች ተበልጦ ሁለተኛ ወጥቷል። ያስመዘገበውም ሰዓት በዓለም የማራቶን ሩጫ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት እንዲሁም ለኢትዮጵያም ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። ጉዮ ማነው? ብዙ ያልተባለለት የ26 አመት እድሜ ያለው ጉዬ አዶላ ድንገት ከየት ተገኘ? በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቢሉ በምትባል አካባቢ የተወለደው ጉዬ፤ እንደ ቀደሙት አትሌቶች ሩጫን የጀመረው በህፃንነቱ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ነው። ዕድሜው 17 ሲሞላ ለቀጣይ ስልጠናዎች አዲስ አበባን መዳረሻው አደረገ። የአምቦ አትሌቲክስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ተፈሪ መኮንን በሩጫ ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ አበክሮ የሚናገረው ጉዬ፤ የሩጫ ህይወቱ ግን ማንሰራራት የጀመረው በኦሮሚያ የውሃ ሥራዎች ክለብ ቆይታው ነበር። ጉዬ ከውድድሩ በኋላ ሜዳልያውን አጥልቆ የመጀመሪያው ትልቅ ውድድር የነበረው ከሦስት ዓመታት በፊት ማራኬሽ ከተማ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። ይህም ለቀጣይ ውድድሮቹ ፈር የቀደደለት ሲሆን፤ በዚያው ዓመትም በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በ10 ኪ.ሜ ብዙ ውድድሮችን አድርጓል። ነገር ግን ብዙ የሚያስደስት ውጤት ማምጣት አልቻለም። "የጤና እክል ደርሶብኝ ስለነበር ምግብ መመገብ ከብዶኝ ነበር" በማለት የሚናገረው ጉዬ፤ "ሰው ካልበላ ደግሞ መሮጥ ከባድ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ቀላል የማይባሉ የእግር ጉዳቶች ደርሰውብኝ ነበር" ይላል። ብዙዎች አትሌቶች ከድህነት በመውጣት የተሻለ ህይወትን ለማግኘት ሩጫን እንደ መውጫ መንገድ ያዩታል። የጉዬም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። "ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ምን አይነት ህይወት እንደሚመሩ ከዚያው የመጡ ያውቁታል። ከደሃ ቤተሰብ ነው የመጣሁት፤ ሩጫ ከጀመርኩ በኋላ ግን የቤተሰቦቼ ህይወት ላይ መሻሻል አለ" በማለት ይናገራል። ከእሱ በፊት የመጡ የሩጫ ጀግኖች የሚላቸውን የእነ ቀነኒሳ በቀለ እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባን ስኬት ማየቱ ትምህርቱን ዘጠነኛ ክፍል ላይ አቋርጦ ለሩጫ ሙሉ ትኩረቱን እንዲሰጥ አደረገው። የእሁድ ዕለቱ ድልም በሩጫ ዘመኑ ሁለተኛ የሚባለውን የ24 ሺህ ዶላር ሽልማትን አስገኝቶለታል። ከሦስት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የሚባለውን ብር ያገኘው ህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሆን፤ ከማሸነፉ በተጨማሪ አዲስ ክብረ-ወሰንም አስመዝግቧል። በወቅቱ የተከፈለውም 35 ሺህ ዶላር ነበር። ከበርሊን ውድድር በኋላ ጣልያናዊው ማኔጀሩ ዝናውም ሆነ የሚያገኘው ብር ይቀየራል በማለትም አስተያየቱን ይሰጣል። "በዚህ ውድድር ላይ ያሸንፋል ተብሎ ስላልተጠበቀ፤ በአዘጋጆቹ የተሰጠው ክፍያ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።" በማለት የሚናገረው ጂያኒ ዲማዶና "ከዚህ በኋላ ግን ጠቀም ያለ ክፍያ ይሰጡታል" ይላል። ተጨማሪ የማራቶን ተስፋዎች ጉዬ የእራሱ ቤት የለውም፤ አላገባም። ነገር ግን በበርሊን ላይ ካሸነፈ በኋላ ብሩህ ተስፋ እንደሚታየው ተናግሯል። ጂያኒ ዲማዶናም የአሁኑን የጉዬን ድል እንደ ትልቅ ስኬት በማየት፤ ቀጣዩ ዝግጅታቸው በሚያዝያ ወር ላይ ለሚካሄደው ትልቁ የለንደን ማራቶን መሆኑን ይናገራል። ጉዬ አዶላ ከዚህ ቀደም ለምን በማራቶን ሩጫ አላሸነፈም? ምንም እንኳን በአሰልጣኞቹ አስተያየት ማራቶን ላይ እንዲሳተፍ ምክር ቢሰጠውም ጉዬ እንደሚለው ለማራቶን ሩጫ ምንም ፍላጎት አልነበረውም። በእድሜው ትንሽ መሆኑና እንዲህ አይነቱን ረዥም ርቀት ለመሮጥ ከባድ ነው በሚልም ይመልስላቸው ነበር። አሁን ግን ያለምንም ጥርጣሬ የማራቶን ሯጭ ነው። በበርሊን ያሸነፈበት ሰዓት ከአለም ሬከርድ በ49 ሰከንዶች ብቻ መለየቱ፤ በኢትዮጵያ ደረጃም ምርጥ የሚባል ሰዓት ማስመዝገብ አስችሎታል። ጂያኒ ዲማዶና እንደሚለው በስልጠናው ወቅት ጥሩ ሰዓትን ቢያስመዘግብም ይህ ግን "ታላቁ ህልማችን" ነው። "ባስመዘገብነው ሰዓት በጣም ነው የተደነቅነው። እየጠበቅን የነበረው 2፡05 ወይም ደግሞ 2፡06 ነበር። በጭራሽ 2፡03፡46 ግን አልነበረም" ይላል። የጉዬ ረዳት አሰልጣኝ የሆነው ከሊል አማን በበኩሉ፤ ጉዬ ለረዥም ርቀት ሩጫ ለየት ያለ ተሰጥኦ እንዳለው ይመሰክራል። "አሯሯጡ፤ እግሩን የሚያነሳበት መንገድ ጉልበቱን በብቃት እንደሚጠቀም የሚያሳይ ነው። ለዛም ነው የማይደክመው።" በማለት ሙያዊ አስተያየቱን ይሰጣል። ጉዬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሩጫ የህይወቱን 'ሀ' ብሎ የጀመረው ከሦስት ዓመታት በፊት ዴንማርክ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ሲሆን፤ በወቅቱም የነሐስ ሜዳሊያ ለማግኘት ችሏል።
news-54145139
https://www.bbc.com/amharic/news-54145139
ትግራይ፡ በክልላዊው ምርጫ ተቃዋሚዎች አንድ ወንበር ብቻ አገኙ
ባለፈው ሳምንት ትግራይ ክልል ከተካሄደው ምርጫ ተርፈው ከነበሩትና በተመጣጣኝ ውክልና እንደሚከፋፈሉ ከተገለፀው 38 የምክር ቤት መቀመጫዎች ህወሓት 37.35ቱን ማግኘቱ ተገለጸ።
በዚህም መሰረት የክልሉ ምክር ቤት ካለው 190 መቀመጫዎች ውስጥ 189ኙን በማግኘት ከአንድ መቀመጫ በስተቀር ሁሉንም መውሰዱን ምርጫ ኮሚሽነሩ መምህር ኪዳነማርያም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። በምርጫው ከተሰጠው አጠቃላይ 10 ሚሊዮን 840 ሺህ 159 ድምጽም ህወሓት 10 ሚሊዮን 655 ሺህ 840 የመራጮች ድምጽ በማግኘት፣ አጠቃላዩን በሚባል ደረጃ የምክር ቤቱን ወንበር ተቆጣጥሮታል። በክፍፍሉ ቀመር መሰረት 0.65 ድምጽ ያገኘው ባይቶና የተባለው ፓርቲ ቀሪዋን ብቸኛ አንድ ወንበር እንደሚወስድም ተገልጿል። በተመጣጣኝ ውክልና እንደሚከፋፈሉ ከተገለጹት 38ቱ የምክር ቤቱ መቀመጫዎች ከተሰጡት የመራጮች ድምጽ አንጻር የአንዱ ወንበር ውክልና 285,267.3 የነበረ ሲሆን ከህወሓት ውጪ ይህን ያህል ድምጽ ያገኘ ፓርቲ የለም። በምርጫው ከተሳተፉት አምስት ፓርቲዎች መካከል ክልሉን በብቸኝነት ላለፉት 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያስተዳደረው ህወሓት 10,655,840 ድምጽ፣ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆነው የቀረቡት አዳዲሶቹ ፓርቲዎች ባይቶና 93,495 ድምጽ፣ የትግራይ ነጻነት ድርጅት 58,779 ድምጽ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ 27, 987 ድምጽ እና ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ደግሞ 3,088 ድምጽ አግኝተዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም በተካሄደው የትግራይ ክልል ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት 2,789,254 መራጮች ውስጥ 2,757,495 ሕዝብ በምርጫው ላይ ተሳትፏል ተብሏል። ይህም 98.8% እንደሆነ ተመልክቷል። በተጨማሪም ድምጽ ከሰጡ መራጮች መካከልም 31,759 ድምጽ ለየትኛውም ተወዳዳሪ ሳይሆኑ የባከኑ እንደሆነ መመዝገቡን ኮሚሽኑ አሳውቋል። በመላው አገሪቱ በነሐሴ ወር ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ተወሰነ ቢሆንም፤ የትግራይ ክልል ግን በተናጠል ምረጫውን ለማካሄድ በመወሰኑ ሲያወዛግብ ቆይቶ ነበር። በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው ሕገ ወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ ከምርጫው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው መግለጹ ይታወሳል።
news-54569299
https://www.bbc.com/amharic/news-54569299
ትራምፕ ዳግም ምርጫውን ሊያሸንፉ የሚችሉባቸው ምክንያቶች
ከምርጫ በፊት የሚከናወኑ አስተያየት መሰብሰቢያዎች የትራምፕ ተቀናቃኝ ጆ ባይደን ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ናቸው።
ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ከምርጫ በፊት የምርጫ ውጤቶችን የሚተነብዩ ተቋማት ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ምርጫን የማሸነፍ እድል ከ83.5 % እስከ 87% ያደርሱታል። ጥቅምት 24 በሚካሄደው ምርጫ ባይደን የማሸነፋቸው ነገር የማይቀር ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። የቢቢሲ የሰሜን አሜሪካ ፖለቲካ ተንታኙ አንቶኒ ዙራከር ግን ታሪክ እራሱን ከደገመ እውነታው ሌላ ሊሆን ይችላል ይላል። ትራምፕ ሳይጠበቁ ምርጫውን ሊያሸንፉ ይችላሉ። የዛሬ አራት ዓመት የሆነውም ይህ ነው ይላል አንቶኒ። . በመጀመሪያው የዶናልድ ትራምፕ እና የጆ ባይደን ክርክር ማን የበላይ ሆነ? . አንድ ወር ያህል በቀረው የአሜሪካ ምርጫ ማን ያሸንፋል? ባይደን ወይስ ትራምፕ? . ዶናልድ ትራምፕ ቻይና በጆ ባይደን ላይ ምርምራ ትጀመር ሲሉ ጠየቁ ልክ የዛሬ 4 ዓመት ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ሳምንታት ብቻ በቀሩበት ወቅት የወቅቱ የትራምፕ ተቀናቃኝ ሂላሪ ክሊንተን ትራምፕን እንደሚረቱ ቅድመ ግምቶች ነበሩ። የኋላ ኋላ ነገሮች ተቀያይረው ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈዋል። ትራምፕ ቃለ መሃላ ፈጽመው አሜሪካንን ለተጨማሪ 4 ዓመታት እንዲመሩ ህዝቡ ከፈቀደ ለዚህ ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው። በምርጫ ዋዜማ ያልተጠበቀው ሲከሰት የዛሬ አራት ዓመት ለምርጫው 11 ቀናት ብቻ ሲቀሩ ሂላሪ ክሊንተን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሉ የግል ኢሜል ሰርቨርን በመጠም የሥራ ኢሜይል ልውውጥ ስለማድረጋቸው ዳግም ምርመራ በኤፍቢአይ ይጀምራል ተባለ። የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚይ በሂላሪ ላይ ምርመራ መከፈቱ ለትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ኃይል ሆኖ ነበር። የዘንድሮ ምርጫ ከመከናወኑ በፊትም ተመሳሳይ የፖለቲካ ውጥንቅጥ ለትራምፕ የድል በር ሊከፍት ይችላል። እስካሁን ግን የተከሰቱት ነገሮች ትራምፕን ነጥብ የሚያስጥሉ እንጂ ወደ ዋይት ሃውስ የሚያስገቡ ሆነው አልተገኙም። ለምሳሌ ኒው ዮርክ ታይምስ ትራምፕ የከፈሉትን የገቢ ግብር መጠን ይፋ ማድረጉ እና በኮቪድ 19 የተሳለቁት ፕሬዝደንት በኮቪድ 19 ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው ለምርጫ ቅስቀሳቸው ውድቀት ነው። ሃንተር ባይደን እና ጆ ባይደን እአአ 2014-2019 የጆባይደን ልጅ ሃንተር ባይደን በዩክሬን የሚገኝ አንድ ነዳጅ አውጪ ኩባንያ ቦርድ አባል ሆኖ ሰርቷል። በወቅቱ ባይደን ደግሞ በፕሬዝደንት ኦባማ አስተዳደር ውስጥ ምክትል ፕሬዝደንት ነበሩ። አባት እና ልጅ አንድ ወቀሳ ይቀርብባቸዋል። ሃንተር በቦርድ አባልነት የሚያገለግልበት ኩባንያ በዩክሬን መንግሥት የጸረ-ሙስና ምርመራ እንዳይደረግበት ባይደን ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ጫና አሳድረዋል የሚል። ባይደን ምክትል ፕሬዝደንት ሳሉ ይህን ስለመፈጸማቸው ቢረጋገጥ ታሪክ ቀያሪ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። የቅድመ ምርጫ ግምቶች ስህተት ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ከዴሞክራቱ ጆ ባይደን ጋር አንገት ለአንገት የተናነቁት ፕሬዝደንት ትራምፕ ቁርጣቸውን የሚያውቁት ጥቅምት 24/2013 ነው። ይሁን እንጂ የአሜሪካ የምርጫ ትንቅንቅ የምርጫ ዕለት ብቻ የሚታይ አይደለም። የቅድመ ምርጫ ምርጫም አለው። ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅቶች የትኛውን ዕጩ ነው የምትመርጡት እያሉ ከአሜሪካውያን የሚሰበስቡትን ድምፅ ይፋ የሚያደርጉበት ነው ቅድመ ምርጫ ማለት። መግቢያችን ላይ እንደጠቀስነው በዚህ ቅድመ ምርጫ ጆ ባይደን የማሸነፍ ሰፈ እድል ተሰጥቷቸዋል። 2016 የነበሩት ቅድመ ምርጫ ውጤቶች ግን የምርጫ ውጤት ተገላቢጦሽ ሆነው ነበር የተገኙት። የቅድመ ምርጫ ውጤቶች ሂላሪ እንደሚያሸንፉ ቢያመላክቱም የመጨረሻው ውጤት ግን ድሉን ለትራምፕ አሳልፎ ሰጥቷል። ቅድመ ምርጫ ውጤቶች ረብ የለሽ እና አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ ይላል የፖለቲካ ተንታኙ አንቶኒ ዙራከር። በ2016 የሆነውም ይሄው ነው። ምርጫውን ማን ሊያሸንፍ ይችላል ሲባል 'ማን ወጥቶ ድምጹን ሊሰጥ ይችላል?' የሚለውን መገመት ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ፈታኝ ነው ይላል። በኮሮናቫይረስ ስጋት ዘንድሮ መራጮች ድምጽ የሚሰጡት በፖስታ ቤት አማካኝነት ነው። ድምጽ ሰጪዎች የምርጫ ቅጾችን እና የፖስታ አድራሻ በትክክል መሙላት ካልቻሉ ድምጻቸው አይቆጠርም። ማርሽ ቀያሪ ፕሬዝደንታዊ የፊት ለፊት ክርክሮች ትራምፕ እና ባይደን ከሳምንታት በፊት ፊት ለፊት በተገናኙ ጊዜ ነጥብ የጣሉት ፕሬዝደንት ትራምፕ ነበሩ። ቁጡነታቸው፣ ባይደንን እና ጋዜጠኛውን በተደጋጋሚ ማቋረጣቸው በበካታ ድምጽ ሰጪዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም። ትራምፕ ይህን ለመቀየር አንድ እድል አላቸው። በቀጣይ በሚኖራቸው ክርክር ላይ እርግት ብለው የተሻለ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ከሆነ የምርጫውን ውጤቱን አቅጣጫ የማስቀየር እድል ይኖራቸዋል ይላል አንቶኒ። ወሳኝ ግዛቶች ላይ ድምጽ ማግኘት በዚህ ምርጫ ላይ የበላይነትን በመያዝ ለማሸነፍ ቁልፍ በሚባሉት ግዛቶች ላይ በልጦ መግኘት ያስፈልጋል። ትራምፕ እንደ ሚቺጋ እና ዊስኮንሲን ያሉ ቁልፍ ግዛቶች ላይ ማሸነፍ የሚችሉ አይምሰሉም። ይሁን እንጂ እንደ ፔንስያለቫኒያ እና ፍሎሪዳ ያሉ ግዛቶች ላይ የሚያሸንፉ ከሆነ ቀጣይ አራት ዓመታትን በዋይት ሃውስ መሰንበታቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ።